የማይጠይቅ ትውልድ ዛሬም እንደ ትላንቱ (ክፍል 1) | ታኅሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም.

አቻሜለህ ታምሩ የማይጠይቅ ትውልድ ዛሬም እንደትላንቱ በሚል የውይይት መድረክ ላይ ስለ እስክንድር ተጠይቆ ከተናገረው የተወሰደ እስክንድር የአማራ ትግል ውስጥ ውጤታማ ሊሆንበት ይችላል ብዬ የማስበው ቦታ አሁን ለሻለቃ ዳዊት የሰጠውን ቦታ እሱ እዚህ ሀገር ሆኖ ቢያስተባብር እና ዲፕሎማሲውን ቢሰራ ጥሩ ድጋፍ ያደርግ ነበር ባይ ነኝ። ስለዚህ አሁን ላይ እስክንድር ያለቦታው ነው የተገኘው እስክንድር ለአማራ የያዘው አላማ…

Read More

ለድሮን አብራሪዎች እና ለድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመን ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችው፣ የሰው ልጅ ክብሩ የተረጋገጠባትን አገር ከውጭ ነጣቂ ጠብቆ በነፃነት ለማቆየት በነበራት ቁርጠኝነት ነው። ኢትዮጵያ በነጻነቷ የኖረቸው ሥልጣንና ጥቅም፥ የግል ድሎትና ምቾት፥ ተራ ዝናና ጊዜአዊ ክብርን እንደ ርኩሰትና ውርደት የሚቆጥሩ፣ በምትኩ ለአገር፥ ለሕዝብ፥ ለታሪክ፥ ላለፈው ትውልድ አደራና ለመጭው ትውልድ ቀጣይነት ዋስትና እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ዜጎች ሁሌም ስላሏት ነበር። ይህ ማለት…

Read More

የአማራን ሕዝብ የህልውና ትግል ውጤታማነት ለማስጠበቅና ዘለቄታዊነቱን ለማረጋገጥ ጥቂት ጥንቃቄዎች

ታህሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ምከኢያሱ ዘአዲስ አበባ የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል በድል ላይ ድል እያስመዘገበ ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ የሚገኝ እንደመሆኑ ውጤታማነቱን ለማስጠበቅና የህልውና ትግሉ ግቡን እስኪመታ ድረስ ለማዝለቅ፣ ትግሉ የሚገኝበትን ደረጃና ሂደት በመገምገምና ትግሉ ያስገኘውን በጎ ዕድል በመተንተን፣ የታዩ ድክመቶችንና ስጋቶችን ከግምት በማስገባት ሊወሰዱ የሚገባቸውን ቀጣይ እርምጃዎች በሚከተሉት ነጥቦች ለመጠቆም ተሞክሯል፡፡ ትግሉ የሚገኝበት አዎንታዊ…

Read More

ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ!

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ በፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉን አቀፍ ጭፍጨፋ (ዘር ማጥፋት) እየተካሄደበት ይገኛል።የህልውና አደጋ የተደቀነበት የአማራ ህዝብ ተፈጥሯዊ የሆነውን እራስን መከላከል እና የመኖር መብቱን ለማስከበር ተደረጅቶየአገዛዙን አከርካሪ በመስበር ትግሉን እያቀጣጠለውና አላማውን ለማሳካት በመገስገስ ላይ ይገኛል።የጎጃም ዕዝ ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፤ እያስመዘገበምይገኛል። የጎጃም ፋኖ ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየማረከ ከነፍስ ወከፍ እስከ…

Read More

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት መግለጫ

ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ. ም.አዲስ አባባኢትዮጵያየአማራን ህዝብ ገድዬ፣ አፈናቅዬ፣ አሥር ቤት እና በድሮን ጨፍጭፌ እጨርሰዋለሁ ብሎ የተነሳው የአብይ አህመድ የፖለቲካዊ ኦሮሙማ ሀይል በሁሉም መንገድ አማራን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት፣ ይህም ካልተሳካ ቁጥሩን ለመቀነስ በእጁ ያለውን መሳሪያ ሁሉ እየተጠቀመ ነው።ከኢትዮጵያ ህዝብ ለልማት የሚሰበሰበውን የገበሬ የመሬት ግብር፥ የንግድና ኢንዱስትሪ ታክስ ብር፣ በእርዳታ የሚመጣውን ዶላር፣ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጭምር…

Read More

ክፍል ሁለት የአማራ “ፋኖ አንድነት ምክር ቤት” መቼ ተቋቋመ?

የዛሬ 12 ወር ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎ እና ከሸዋ የመጡ የፋኖ መሪዎች ተሰብስበው ህዳር 12 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት በርማጭሆ፣ ሱዳን ድንበር ላይ ኮረደም በርሀ ውስጥ “የፋኖ አንድነት ምክር ቤት” በአንድ እዝ ተዋቅሮ ተመሰረተ።የኢትዮጵያ ፓለቲካ ከተግባሩ ይልቅ ወሬው እየቀደመ ጠላት እያዘጋጀ ስላስቸገረ ይህንን ስብሰባ ከማጯጯህ ሚስጥራዊ ማድረጉ ግድ ነበር። ይሁንና ፋኖን በቅርብ ሲያግዝ በነበረው በማገር ሚዲያ…

Read More

የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምሥረታን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ መግለጫ

ክፍል 1ስለ ፋኖ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ እውነታመግቢያፋኖ በዩቲዩብና በአንዳንድ ሚዲያዎች እንደሚነገረው ‘አንድ ያልሆነ፣ አንድ አመራርና ቅንጅት የሌለው፣ ”በጥይት ቅንድብ የሚላጭ” ነገር ግን ብዙ የሚያስብ ሰው የሌለበት፣ ማኒፌስቶ ያልጻፈና ወዴት መድረስ እንዳለበት በቅጡ የማያውቅ ተደርጎ ሲሳል እናያለን። እነዚህ እውነት ናቸውን? ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የራሱን ድህረ ገጽና ዩቲዩብ አቋቁማል።…

Read More