ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ!

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ በፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉን አቀፍ ጭፍጨፋ (ዘር ማጥፋት) እየተካሄደበት ይገኛል።
የህልውና አደጋ የተደቀነበት የአማራ ህዝብ ተፈጥሯዊ የሆነውን እራስን መከላከል እና የመኖር መብቱን ለማስከበር ተደረጅቶ
የአገዛዙን አከርካሪ በመስበር ትግሉን እያቀጣጠለውና አላማውን ለማሳካት በመገስገስ ላይ ይገኛል።
የጎጃም ዕዝ ከምስረታው ጀምሮ እስካሁን እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፤ እያስመዘገበም
ይገኛል። የጎጃም ፋኖ ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየማረከ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ድረስ ታጥቋል። የክላሽንኮቭ
እጥረት የነበረበት ፋኖ አሁን ላይ የስናይፐር፣ የመትረየስ፣ የድሽቃ ፣ ሞርታር፣ እና ዙ-23 ባለቤት ሆኗል።
ይህ የሆነው ደግሞ የዘወትር የሎጅስቲክ አቅራቢያችን ከሆነው የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሃይል መሆኑ ታውቆ ያደረ ሀቅ ነው።
አማራ እንዲጠፋ የታቀደበት፣ በድኑ እንኳ እንዲሰደድ የተሴረበት ህዝብ በመሆኑ ለትግሉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቁርጠኝነት
ተነስቷል።
የፋሽስት አገዛዙ በአማራው አንገት ላይ ያስገባውን የወፍጮ ድንጋይ በአማራ ብርቅየ የቁርጥ ቀን ልጆቹ ብርቱ ትግል
እያወላለቀ ይገኛል። “በፍርድ ከሄደችው በቅሎየ ያለፍርድ የሄደችው ጭብጦየ” እንዲል ብሂሉ፤ የአማራ ህዝብ ለርትዕና ፍትህ
የሚታገል፤ የመለኮትን አኗኗር የሚተረጉም፤ የጥበብ ባህርና የትንቢት ጥልቀት የተነተነ፤ እይታው በንስር አምሳል የተሰየመ፤
ቤት ከመስራት በላይ ሀገረ መንግስት መገንባት የሚቀለው ህዝብ ነው።
ከልቡ ለሚወደው ህዝብ ነፍሱ ጠርታው እናትና አባቱን፣ ልጅንና ሚስቱን ትቶ እንደ መክሊቱ ወደ ትግል ያልገባ ፋኖ የለም።
ለአማራ ህዝብ ነፃነት ነፍሱን አስይዞ በሂወት የመኖር መብቱን በክንዱ ለማስከበር ውቅያኖስ የማይሰነጥቅ፣ በረሃ የማያቋርጥ፣
ተራራ የማይቧጥጥ ፋኖ የለም።
ንስሃውን ከሚሰማው፣ ምህላውንና ዱዓውን ከሚቀበለው አምላክ ፊት እንደሚቀርብ የዕጣን መስዋዕት የአማራ ህዝብ
ጭፍጨፋ ልቡን የማያነደው የአማራ ፋኖ የለም። በአሁኑ ሰዓት እንዲጠፋ ለተፈረደበትና ለህልውና ለሚታገለው የአማራ
ህዝብ ትግል ጎን መቆምና ለአማራ ህዝብ መታገል በሃይማኖት እንደ ቅድስናም እንደ ምሁርነትም የሞራል ልዕልናም ተደርጎ
ይቆጠራል ብለን እናምናለን።
ትግሉ የህልውና ትግል በመሆኑ የአሁኑ የአማራ ህዝብ ትግል መሳሳትን የሚፈቅድ አይደለም። ዕዙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ
ከተወያዬ በኋላ ባለ 4 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
1ኛ. በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ሲስተዋል የነበረው ከፋሽስት አገዛዙ ጋር “የድርድርም ሆነ
“የንግግር ‘ የሚመስሉ ሀሳብና አስተያየቶች በበርካታ የዕዙ አባላትና ደጋፊዋች እንዲሁም ማህበረሰባችን ዘንድ ብዥታን
ስለፈጠረ “የድርድር ወይም የንግግር” ጉዳዩ ዕዙን የማይመለከት መሆኑን በግልፅ ማሳወቅ እንፈልልጋለን።
የአማራ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፃታ ሳይመርጥ ለህልውና ትግሉ ነፍጥ አንግቦ እየተዋጋ ይገኛል። በዚህ የህልውና የትግል
ወቅት አገዛዙ ባሰማራው ሰራዊት በከባድ መሳሪያ ህፃናትና አዛውንቶች ተጨፍጭፈዋል፤ መስጊድና ቤተክርስትያን
ተቃጥለዋል። የህዝባችን ንብረት ወድሟል ተዘርፏል። እንዲሁም አሰቃቂ ድርጊቶች በህዝባችን ላይ ተፈጽሟል።
እንደ ጎጃም ዕዝ የአማራ ህዝብ ማሸነፍ ብቻ ነው ምርጫው ብለን እናምናለን። ነገር ግን የፋሽስት አገዛዙ መሸነፉን አረጋግጦ
ድርድር የሚፈልግ ከሆነም እንኳ የትግሉ ባለቤት ከሆነው ከመላው የአማራ ህዝብ (ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋና ከክልሉ*
ውጭ ካለው ህዝባችን) እንዲሁም ከትግል አጋር ኢትዮጵያውያን ጋር ተመካክረን በግልፅ የምናሳውቀው እንጂ የጓዳ ቤት
ድርድር የማይኖር ብቻ ሳይሆን የማይታሰብ መሆኑን በአፅኖት እየገለጽን ትግሉ እንደ ጎጃም ሳይሆን እንደ አማራ መሆኑን
ሁሉም እንዲረዳው እንፈልጋለን።
2ኛ. ቤተ እምነቶቻችንን ከሚያረክስ፣ ቤተክርስትያንን ከሚያቃጥል፣ መስጊዶቻችንን ከሚያወድም፤ ቄሶችን፣ ሸኮችን፣
ድያቆንና ደረሳዋችን፤ ህፃናትና እናቶችን ከሚደፍር፣ አዛውንቶችን ከሚያርድ የጠላት ሃይል ጋር የተሰለፋችሁ የፀጥታም ሆነ
የፖለቲካ አመራሮች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ማሳወቃችን ይታወቃል። ይህን ማስጠንቀቂያ ተላልፋችሁ በተገኛችሁት
የአማራ ጡት ነካሾችና የእፍኝት ልጆች ላይ ማንኛውንም የማያዳግም እርምጃ ከዛሬ ጀምሮ እየወሰድን እና በቀጣይነትም
የምንወስድ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል።
3ኛ. ለተለያዩ አካባቢዎች ምሳሌ የሆነውን “የጎጃም እዝ ፋኖ” ለማፍረስ እና የራስን ሃይል ለማደራጀት በአማራ ህዝባዊ
ሃይልም ሆነ በአማራ ህዝባዊ ግንባር ስም የምትንቀሳቀሱ ግለሰቦች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ለትግሉ ፈር ቀዳጅ
ስለነበራችሁና ለከፈላችሁት ዋጋ ስለምናከብራችሁ በባለፈው መግለጫችን ለምንጠይቃችሁ ጥያቄ ምላሽ እንድትሰጡን እና
በአሰላለፋ አንድ ሆናችሁ በእዙ መዋቅር በመግባት እንድታታግሉን ስንል ጥሪ ማድረጋችን ይታወቃል።
ነገር ግን ጥሪዎችን ተቀብሎ የተደረጉ ውይይቶች ደካማ መሆናቸውና እንደተቋም በቂ ውይይት ባለመደረጉ ለመጨረሻ ጊዜ
በቅርብ ቀን ጥሪያችንን አክብራችሁ ተገኝታችሁ ጥያቄዎቻችንን እንድትመልሱልን እያሳሰብን ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ
በጎጃም እዝ የትእዛዝ ሰንሰለት ውስጥ ማንኛውም አካል እንደልቡ ልዩነቶችን እያሰፋ አደረጃጀት መያዝም ሆነ መንቀሳቀስ
የማይቻል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
4ኛ. ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ የመኪኖችን እንቅስቃሴ በመጠቀም የጨፍጫፊው ሃይል ደህንነቶችንና ኦፒዎችን እያሰማራ
በድሮንና በሜካናይዝድ ከሞርተር እስከ ቢኤም በከባድ መሳሪያ ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ይገኛል።
በተጨማሪም በሚዲያ ቀርቦ በአደባባይ ሸቀጣሸቀጦች ስንዴን ጨምሮ መድሃኒቶች ወደ አማራ “ክልል” እንዳይገባ ትእዛዝ
ተሰጥቷል። በተቃራኒው ከከሰል እስከ ማርና ቂቤ፣ ከስንዴ እስከ ጤፍ ድረስ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እየገዛ ሲሆን አላማውም
ጦርነትን በማራዘም የአማራን ህዝብ በርሃብ አለንጋ እንዲገረፍና በኢኮኖሚው እንዲዳከም በመዋቅራዊ መንገድ ታቅዶበት
እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።
ስለሆነም የፋሽስቱ ዙፋን ጠባቂ የሆነው ሀይል ከክልሉ እስኪወጣ ድረስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደማይደረግ በአፅኖት
መግለፅ እንፈልጋለን።
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ ሆናችሁ እንዳትገኙ እያሳሰብን ይህን
መመሪያ ተላልፎ በተገኘ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰደው እርምጃ ሃላፊነቱን እራሱ አሽከርካሪው ወይም የተሽከርካሪው ባለቤት
ይወስዳል።
ከእውነት ጋር የቆመ ህዝብ ያሸንፋል!!
ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!!
ድል ለፋኖ!!
የጎጃም ዕዝ ፋኖ!
ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *