ክፍል አንድ
ራሴላስ ወልደ ማርያም
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሊወርዱ ሰባት ወር ሲቀራቸው በሀምሌ 2010 ዓመተ ምህረት አቶ ዳንኤል ክብረት አንድ በውሾች ገጸ ባህሪ መስለው ያሳተመት መጽሀፍ አለ። ይህንን መጽሐፍ በቻግኒ ዩቲዩብ የተተረከውን አደመጥኩት። መጽሐፏ የፓለቲካ ስላቅ (Political satire) እንደሚባለው ነው።
አቶ ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስቴርና አማካሪ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ዘላለማዊውን የክርስቶስን መንግስት በመስበክና በደራሲነት ይታወቁ ነበር። ለምድራዊ ሀያላን ግልጋሎት መስጠት ከመጀሩ ቦሀላ ግን ለክርስቶስም ለድርሰቱም ገዜ አላገኙም። ራአዳቫን ካራዲዝች (Radovan Karadzic) የሰርበያ ዜጋ ዛጋ ከባዝንያ ጦርነት ክፍት የተዋጣለት ገጣሚ ነበር። ባሀላ በቦዝንያ ጦርነት ተካፋይ እና በዘር ማጥፋት ተከሶ ሆኖ ከገጣሚዎች አለም ተለየ። የኔም ስጋት “የአዲስ አበባ ውሾች” ብለው አቶ ዳንኣል ያሳተሙት መጽሐፍ የመጨረሻቸው ይመስለኛል።
የዚህ ጽሁፍ አላማ አቶ ዳንኤል ሳይሆኑ ይህ መጽሀፋቸው ነው። የስነ ጽሁፍ ችሎታው እንደ ፓለቲካቸው አወዛጋቢ አይደለም። አማርኛን አሳክቶ የመጠቀም፣ የማያልቅ የአዛውንቶች ተረት በመጽሀፋቸው ውስጥ ነስንሰውና አዋህደው ማቅረብ ይችላሉ። ለኔ የአቶ ዳንኤል ክብረትን የስነ ጽሁፍ ችሎታሰውን ያሳዩበት መጽሐፍ ካለ “የአዲስ አበባ ውሾች” ብለው ያሳተሙት ነው።
የመጽሐፏ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፣
“አዲስ አበባ፣ በደሳለኝ ሆቴል ጎን ታጥፎ ወደ ጎዳና በሚወስደው ስላች አስፓልት አንድ ወገቡ ላይ ልብስ የለበሰ ውሻ ልቡ እስኪጠፋ ይሮጣል። ከኋላው ደግሞ መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ፓሊሶች ድንጋይ አየወረወሩ ያባርሩታል። እነርሱ ከጓላ ሲወረውሩበት በባለሥልጣናቱ ቤት በር ላይ ለጥበቃ የተቀመጡት ሌሎች ወታደሮች ይቀባበሉበታል። እርሱ ደግሞ ልቡ ከእግሩ እየፈጠነ ይፈተለካል። ወደ የት እንደሚሄድ አያውቅም፣ በየት በኩል እንደሚሮጥ አያውቅም። ብቻ ይሮጣል።እንግዲህ በጎዳና ላይ በእግሩ ሲዳክር ለመጀመሪያ ግዜው ነው። መኪና ተመድቦለት፣ ወንበር ተደልድሎለት ከተማዋን በክብር ሲዞርባት እንዳልነበር ዛሬ ከተማዋ ራሷ ትዞርበት ጀመር።
ወደ አትላስ ሆቴል የሚወስደውን አስፓልት መንገድ ጋ ደረሰና ቆመ። ልትወልቅ እግሩ ሥር ደርሳ የነበረችው ልቡ ወደ ሆዱ ተመለሰች። ግራና ቀኙን ሲያማትር አንድ ቀዥቃዣ መኪና በአጠገቡ አጓርቶ አለፈ። ወደ ኃላ አፈገፈገና የአንዱን ግቢ አጥር ተጠጋ። ከግቢው ውስጥ ያለ ውሻ እንደ መብረቅ ሲጮህበት በድንጋጤ ጎዳናው ውስጥ ገባ። ውሻ በውሻ ላይ ከጨከነ፣ ሰው በውሻ ላይ ቢጨክን ምን ይገርማል አለ በልቡ።” መጽሐፏ ከመከበር፣ ከመፈራት፣ከምቾትና ድሎት የወደቀ የባለ ስልጣን ውሻ በፌዴራል ሰባረርው ነው የሚጀምረው። ይሁንና ብዙ ቁም ነገሮችን በውሾቹ አፍ እያስገባ አቶ ዳንኤል የልቡን ተናግሮ ነበር። አሁን እሳቸው የሚያማክሩት ስርአት እንኳን በውሻ አፍ በወፍም አድርጎ እንዲህ አይነት ጽሁፍ ማሳተም አይፈቅድም።
ይህ መጽሐፍ የተዋጣለት ብቻ ሳይሆን የትንቢትም መጽሀፍ ነው። አቶ ዳንኤል የእንባገነን ስርአት አገልጋዬች ህይወት እንዴት እንደሚደመደም ያሳዩበት ቆንጆ መጽሀፍ ነው።
አንድ ሉሉ የሚባል ቅምጥል ውሻ ጌታው “በሁለት እጅ የማይነሱና” የሚፈራ ባለ ስልጣን ነበር። በድንገት ከስልጣን ተባሮ ወደ ቃሊቲ በወረደ ማግስት ቤቱን ለቃችሁ ውጡ ተብለው ቤተሰቡ ሁሉ ተባሩሩ። ልክ ሰሞኑን የአቶ ታዬ ደንድአ ቤተሰቦች እንደተባረሩት ማለት ነው።
የአዲሱ ባለስልጣን ጠባቂዎች ደግሞ ቤተሰቦቹ ጥለውት የሄዱትን ሉሉ የሚባለውን ታማኝና ቅምጥል ውሻ በድንጋይ ልቡ እስከሚፈርስ ሲያሯሩጡት ታሪኩ የሚጀምረው። ሉሉ መከራው መጥቶ ሲወድቅበት “ጌታው በበሉት እጸ-በለስ እሱ ለምን ከገነት እንደተባረረ” አልገባውም። ይሄም ይመጣል ብሎ አስቦ ወይንም የስነ ልቦና ዝግጅት አድርጎም አያውቅም።
ድንገት መከራው ዱብ ሲልበት የነ ሉሉ ዘበኛ የሚያንጎራጉሩት ትዝ አለው።
“መከራ ሲመጣ አይነግርም ባዋጅ
ሲገሰግስ አድሮ ቀን ይጥላል እንጂ” አለ።
ይህንን የዘበኛቸውን እንጉርጉሮ ሉሉ ብዙ ግዜ ሰምቶታል ይሁንናን ምን ማለት እንደሆነ እስከዚህ ቀን አላስተዋለም ነበር። ይህ ጌታውን የተማመነ ቅልብና ክፏ ውሻ አሁን መንገድ ላይ ተጥሎ አንዱ በድንጋይ፣ አንዱ በመኪናው ጡሩንባ፣ ሌላው በጎማው ለጥቂት ሲስተው ሁሉ ነገር እንደ ብርሀን ግልጽ ብሎ ታየው። ከዱላው፣ ከረሀቡና ከመቆሸሹ ጋር ተደርቦ ጸጸት ልቡ ይገባል።
ለካ ይላል ሉሉ “አሪፍ ውሻ ማለት ጥሩ ክፏ ውሻ ነው እንደማለት ነው። አንተ ክፏ ውሻ ከሆንክ ለጌታህ አሪፍ ውሻ ነህ። ትናከስላቸዋለህ፣ ትጮህላቸዋለህ፣ መንገድ አላፊውን ታስደነብርላቸዋለህ ታስፈራራላቸዋለህ ለሌሎች ክፏ ስትሆን ለጌቶች ምርጥ ውሻ ትሆናለህ። ቦሀላ ግን እዳው አንተው ላይ ይወድቃል። በመጨረሻው አንተው ትወረወራለህ፣ ለጂቦቹም ተላልፈህ ትስጣለህ” ይላል። ይህቺ የአሀ ግንዛቤ እነ ሉሉና ኮለንበስ መንገድ ላይ ከወጠና የተራቡ የአዲስ አበባ ውሾች ጋር ከተዋወቀ ቦሀላ ነው።
ሉሉ የተቀማጠለ የባለ ጊዜ፣ የባለ ስልጣን ውሻ ነበር። ይህ ውሻ የሚፈራ፣ ከልጆች እኩል አማርጦ የሚበላ፣ ለባለስልጣኑ የተመደቡት ፌዴራሎች ገላውን የሚጥቡት፣ ባለስልጣኑን ለማስደሰት የሚመጡ ሀብታምች ሁሉ እኔ እኮ ውሻ እወዳለሁ የሚያስብል፣ ልብስና መኝታ ቤት ያለው፣ በ v8 ላንድ ክሩዘር ተጭኖ ህዝብን በመስኮት እያየ አዲስ አበባን የሚዞር ቅምጥል ነበር። ይሁንና የኢህአዴግ ስልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነበርና ይህ የተከበረ ባለስልጣን ድንገት ከስልጣን ተባሮ ታሰረ። ማለትም ልክ እንደነ ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ስዬ አብረሀ፣ የደህንነት ምክትል ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ እብዲ ኢሌ፣ ወይንም የቅርቦቹ ሚኒስቴር ዴታዎች እንደነ አቶ ታዬ ደንደአ እና አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደ ማለት ነው። ስም አይጠራ እንጂ ሉሉ እንዲህ ይፈሩ የነበሩ ባለስልጣን ውሻ ነበር።
ያ “በሁለት እጅ የማይነሳ” የነበረው የሚፈራው፣ ሁሉ የሚርድለት ባለ ስልጣን ሉሉን፣ ሚስቱንና ልጆቹን በትኖ ወደ መአከላዊ ምርመራ ተሸኘ። ባለስልጣኑ በበላው እጸ-በለስ በ24 ሰአታት ውስጥ ሁሉም መንገድ ላይ ወጥተው ተጣሉ።
ይህ ውሻ ለብቻው መንገድ እንኳን አቋርጦ የማያውቅ ነበር። ፌዴራል ፓሊስ አጅቦት ከግቢ ሲወጣ ፌዴራሉን ያየ ባለ መኪና አቁሞለት ተፈርቶ የሚሻገር ነበር። አሁን መንገድ ላይ ሲወጣ ፍጥነቱን ሳይቀንስ ለጥቂት የሚስተው፣ ዝሆንን የሚያደነቁር ጡሩንባ የሚነፋበት ከተማ ውስጥ ዱብ አለ። ከአንዱ ጎማ ሲያመልጥ ሌላ በጡሩምባና ጎማ እየሳተው ወደ አትላስ አካባቢ ይደርሳል። እዛ መንገድ ላይ የተጣለ ንካው የሚባል የከተማ ውሻ ያገኛል። ሉሉ ይህ ንካውን ሲያይ ለምን “በአጥንቱ ላይ ቆዳ ጣል አደረገ፣ ለምን አልታጠበም፣ ለምን ቆሸሸ፣ ሽታውስ ለምን አፍንጫ ይቆርጣል፣ ጉስቁልናው የየሚያስፈራ፣”ስጋ ቅን ውሻ” ከየት መጣ ብሎ ሰያስብ ንካው ጆካው ብሎ በተረብ ተዋወቀው።
ንካው ደግሞ ይህ የተመቸው በጀርባው ላይ ልብስ የለበሰ ውሻ በቅርብ ከሙስና ሰፈር የተባረረ ቅምጥል መሆኑን ገብቶታል።
ይህ “ስጋ ቅብ ውሻ ጆካው” ብሎ በተረብ ሉሉን ይተዋወቀዋል። የዳንኤል ክብረት መጽሐፍ የነዚህ የሁለት አለም ውሾች ጭውውት ነው። በመሀከሉ እንዲሁ እንደ ሉሉ ግዜ የጣላቸው ውሾች ይቀላቀላሉ። ሁለተኛው በጆሴ ሞሪኒዮ የተሰየመው “ጆሲ” የሚባል ውሻ ነው፣ ሶስተኛው ባለቤቱ ከኒዮርክ አምጥቶ ሲከስር ጥሎት የሄደው “ኮለምበስ” የሚባለው ውሻ ነው። አራተኛው ደግሞ ከአላህ በላይ ለመንግስት ጠበቃ የነበሩት በመጨረሻ የተባረሩት የሀጂ ኤልያስ “ባሲል” የሚባል ውሻ ነው። አንዱ ደግሞ በርቀት የተወረወሩ የደብር አለቃ “ውቃቤ” የሚባል ውሻ ታሪክ ነው። ስም አይጥራ እንጂ የቱጃሩ አረብም ውሻ አለ።
እነዚህ ውሾች ምግብ ፍለጋ ሲንከራቱ የቤተ መንግስቱ ቅልብ ሶሎግ ውሾችን፣ ከሰፈራችን ካዛንቺስ ውጡልን የሚለው “ሲባ” የሚባለው የብሄር ነጻ አውጪ ውሾች መሪን፣ በእስር የተጣሉ ውሾችን፣ የሚሰልሏቸው የሚከታተሉዋቸው የመንግስት ታማኝ ውሾች ያገኛሉ። በታሪኩ ውስጥ ብቅ እያሉ ትርክቱን አሳምረውት የሚያልፍ ብዙ ውሻች ናቸው። የቱጃሩ አረብ ውሻም፣ የዲያስፓራውም እንግሊዘኛ ተናጋሪ ጆሲም፣ የደብር አለቃውም ውሻ ግዕዝ ጣል ጣል እያደረጉ ታሪካቸውን እያወሩ ፈተናቸን ይጋፈጣሉ
እነዚ ሁሉ የባለ ጊዜ ጥሩ ውሾች ነበሩ። እነሱ ከውሻነት ስራ ያለፈ ሀጥያት አልሰሩም ይሁንና ጌቶቻቸው በበሉት እጸ-በለስ ፍዳ የወረደባቸው ነው።
ይህ እንግዲህ በውሾች ይመሰል እንጂ የእንባገን አገልጋዮች የህይወት ታሪክ ነው። ሉሉ የባለ ጊዜው ውሻ ምሬት የሁሉንም ጸጸት ይገልጸዋል።
“አሪፍ ውሻ ማለት ጥሩ ክፏ ውሻ ነው። አንተ ክፏ ውሻ ከሆንክ ለጌታህ አሪፍ ውሻ ነህ። ትናከስላቸዋለህ፣ ትጮክላቸዋለህ፣ መንገድ አላፊውን ታስደነብርላቸዋለህ ታስፈራራላቸዋለህ ለሌሎች ክፏ ስትሆን ለጌቶች ምርጥ ውሻ ትሆናለህ። ቦሀላ ግን እዳው አንተው ላይ ይወድቃል። በመጨረሻው አንተው ትወረወራለህ፣ ለጂቦቹም ተላልፈህ ትስጣለህ”
ይህ ትርክት የዛሬ የበርካታ የመንግስት አጃቢዋች፣ የፌዴራል ፓሊሶች፣ የመከላከያ አባላት፣ የጠቅላይ መኒስታር አማካሪዎች፣ የብአዴን ባለ ስለስልጣናት፣ የገቢና የታክስ ስራተኞች፣ የቀበሌ ዘበኞች፣ የደንብ አስከባሪዎች፣ የአድማ በታኝ ታጣቂዎች፣ የትራፊክ ፓሊሶች፣ የሚኒስቴሮች፣ የጄኔራሎች፣ የጋዜጠኞች፣ የአቃቤ ህጎች፣ የዳኞች፣ የአክቲቪስቶች፣ በየ መንደሩ ቁጭ ብለው የሚሰልሉ ጆሮ ጠቢዎች፣ የተደራጁ የቤት አፍራሾች ግለ ትርክት ነው። ሉሉ እንዳለው በጌቶቻቸው ጥሩ ውሾች ለመባል ክፏ ውሻ የሆኑ ብዙ ሚሊዮኖች ታሪክ ነው።
ሰዎች ለአለቆቻቸው ጥሩ ውሻ ለመባል ህዝብ ይናከሳሉ፣ በቆመጥ ህዝብን ያቆራጥጣሉ፣ ህዝብን ዘቅዝቀው ይገርፋሉ፣ በሀሰት ሰነድ ህዝብን ይከሳሉ፣ የታክስ ክፍያ በማጋነን ጉቦ ይጠይቃሉ ወይንም የሰው ጉሮሮ ይዘጋሉ፣ ፍርድ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ፍትህን አጣመው በንጹሀን ይፈርዳሉ፣ ጋዜጠኛ ለጌቶቹ ጥሩ ውሻ ለመባል የውሸት ዘጋቢ ፊልም ይሰራሉ። የጎረቤቶቻቸውን ቤት በ24 ሰአት አፍርሱ ብለው ቆመጥ ክላሽ ይዘው የሚያስጨንቁ ይሆናሉ።
አቶ ዳንኤል ፈርተው ራድዋን፣ ሽመክት፣ ሀጎስ፣ ደምመላሽ፣ቀልቤሳ፣ መሀመድ፣ ጢሞቲዎስ፣ ብርሀኑ፣ የሚባል የቀበሌው ሊቀመንበር፣ መነስቴር፣ የልዩ ጥበቃ ሻለቃ እከሌ፣ የገቢዎች ኦዲተር ወይዘሮ እንትና ማለት ስለፈሩ ሀሳቡን ሁሉ ለውሾች ሰጥተው ውሾቹን እውነቱን አናግሯቸል።
ሰው ሆነው የገበት የነ ሉሉ ዘበኛ ናቸው። እሳቸው ግጥሙንና ታሪኩን በሉሉ አፍ እየመጡ ይመክራሉ።
ሉሉ ከዘበኛው የሰማውን የመንግስት ለማን ግጥም ትዝ ይለዋል።
“የተለመደ ነው የመጣ ከጥንት
ከተጠቀው መራቅ አጥቂን መጠቃት”
ንካው የተጣለ ህዝብ ሲሆን፣ ሉሉ፣ ጆሲ ይባሉ እንጂ በየቀኑ የምናገኛቸው የባለ ጊዜ የክፏ ሰዎች ታሪክ ነው። አቶ ዳንኤል በተረትና በቀልድ አዋዝተው የጻፏት የኢህአዴግ/ብልጽግና ክፏዎችን የቀን ተቀን ውሎና ተግባር ነው።
ዛሬ አንድ ነጋዴ ገቢዎች ሲሄድ አለቆቻቸውን ለማስደሰት “አሪፍ ውሻ ለመባል” ክፏ ሆነው ፊታቸውን ከስክስው ይጠብቁሀል። በክፍለ ከተማ ሀላፊዎች፣ ገቢዎች ቢሮ ኦዲተሮች፣ በህግ አስከባሪ ፓሊሶች ፏክክራቸው በጎ መስራት ሳይሆን ክፏ መሆን ነው። ገና ወደ ጠረጴዛቸው ጠጋ ስትል “ደግሞ እንዲህ ማድረግ ጀመራችሁ ብለው በወል ስም በጅምላ ለማሸማቀቅ የሚጥሩ ብዙ ናቸው።”
እራሱ የፌዴራል ፓሊስ ሆኖ ወይንም ወታደር ሆኖ ሲዘምት የሚይዘው ሰንደቅ አላማ፣ ሲሞት የሚጠቀለልበትና የሚቀበርበትን ሰንደቅ አላማ የአማቱ ጥለት ላይ በጥምቀት በአል ሲያገኛት ጥሩ ውሻ ለመባል “አንቺ ነይ! ብሎ በጥፊ የሚያልሳት ቀሚሷን የሚቀድ ብዙ ነው።
ትንሽ ኩታራ የቀበሌ ዘበኛ ለሀገሩ ያገለገለውን አዛውንት ይዘረጥጠዋል፣ አንተ ና፣ ቁጭ በል ተቀመጥ፣ ውጣ ከዚህ ሲልና ለአለቆቹ ጥሩ ውሻ ለመባል ሲጋጋጥ ይታያል። ካልሲና ሙዝ ሸጦ ነፍሱን ለማቆየት የሚጥረውን የደንብ አስከባሪ ጥሩ ክፏ ውሻ እንዲባል በዱላ ሲዠልጣት ቆሎዋን ሲደፋባት ማየት የተለመደ ነው።
ሉሉ ከገነት እንደተባረረ የገጠመው “ውሻ በውሻ ላይ ይሄንን ያህል ከጨከነ፣ ሰው በውሻ ላይ ቢጨክን ምን ይገርማል ያለው ለዚህ ነው። አንድ የፈረንጅ ፈላስፋ “ደሀ ደሀን ሲያባርረው ካየህ እግዚኦ በል። ከያዘው ምህረት አይኖረውምና” ብሎ ጽፋል።
አብሮ የኖረውን ከጎረቤቱ ቤት ገብቶ ክርስትና የበላ፣ ልጅ ስትዳር አብሮ የጨፈረ፣ ከቀብር መልስ በድንኳን አብሮ ንፍሮ የቃመ፣ ደንብ አስከባሪ ሊቀመንበር ሲባል የጎረቤቱን ቤት አስፈርስ ሲባል አረ ጡር ነው አይልም። ለማፍረስ የሚያሳየው ጭካኔን እንደ ምሳሌ ማየት ይችላል። በአንድ ሰአት ውስጥ ለቀው ባትወጣ ወየውልህ በማለት ቆመጡን የሚዞር ክፏ ሰው በከተማችን፣ በሰፈራችን ብዙ ነው።
በያዘው ዱላ አንቆራጥጥሀለሁ፣ ወይንም በታጠቀው ክላሽ አጋድምሀለሁ የሚሉ የመሀበረሰባችን ክፏ ሰዎች ታሪክ ነው አቶ ዳንኤል ክብረት በሚጣፍጥ አማርኛ የከተቡት።
የአቶ ዳንኤል ግለ ታሪክ ይመስላል። መጨረሻቸው እንደ ሉሉ ነው
ezkZuQRpoyDPMVW
LhegJvxQCl
yVLYEfSAo
XHMIPRQa
ZavNlnjCJuLdobPI
PFAvTDlVpH