ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ. ም.
አዲስ አባባ
ኢትዮጵያ
የአማራን ህዝብ ገድዬ፣ አፈናቅዬ፣ አሥር ቤት እና በድሮን ጨፍጭፌ እጨርሰዋለሁ ብሎ የተነሳው የአብይ አህመድ የፖለቲካዊ ኦሮሙማ ሀይል በሁሉም መንገድ አማራን ሙሉ በሙሉ የማጥፋት፣ ይህም ካልተሳካ ቁጥሩን ለመቀነስ በእጁ ያለውን መሳሪያ ሁሉ እየተጠቀመ ነው።
ከኢትዮጵያ ህዝብ ለልማት የሚሰበሰበውን የገበሬ የመሬት ግብር፥ የንግድና ኢንዱስትሪ ታክስ ብር፣ በእርዳታ የሚመጣውን ዶላር፣ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጭምር ዶላር እየለመነ በሚያመጣው መሳሪያ በህዝብ ላይ እያዘነበ ነው። ይህንን ብር ተጠቅሞ በርካታ እናቶችን፣ ህጻናትን፣ ቄሶችን፣ ሀጂዎችን፣ ገበሬዎችን ሳይቀሩ በገበያ፣ በመስጊድ፣ በገዳም፣ በቤተ ክርስቲያን እና በመኖሪያቸው እያሉ በድሮንስ እና በመድፍ እየጨፈጨፈ ነው።
ገበሬውን በራሱ የግብርና ታክስ ወጪ የተገዛውን ማዳበሪያውን በመከልከል በረሀብ እንዲያልቅ እየሰራ ነው። በድርቅ የተጠቃው ደግሞ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ ከሀገርም እርዳታ እንዳይሰበሰብ፣ ከውጪም የሚሰጠውን እርዳታ ለአማራ እንዳይደርሰው እያደረገ እየጨረሰው ይገኛል። ነጋዴውና ገበሬው ያመረተውን ሽንኩርት ጎመንና ቲማቲም ወደ ከተማ ይዞ እንዳይሸጥ ኬላ አቁሞ ያመረተውን አትክልትና ወተት ስብስቦ እንዲጣል እና እንዲደፋ ፓሊሲ ቀርጾ እየሰራ ነው። በከተማ ሰርቶ የሚበላውን ደግሞ በአማራነቱ ብቻ ከየቤቱ እያደነ ወደ ማጎርያ ጣብያ እየከተተ ነው። ይህ ለአማራው አዲስ አይደለም ጣልያንም ሰላሳ ሺ ሰው በአካፋ፥ በምሣርና እና በሳንጃ ጨፍጭፎ፣ የኮንሰንትሬሽን ካምፕ በሶማልያ በዲናኔ አቋቁሞ የአዲስ አበባን ወጣትና ለሀገሩ ሊቆረቆር ይችላል ያለውን ዲናኔ ማጎርያ ከቶ ነበር። ይሁንና ይሄንን ያየው ከተማ ተቀምጦ አልተጫነም። የዛኑ ማታ ጠመንጃውን ወልውሎ ወደ አርበኞቹ ነው የተቀላቀለው። የአብይና የሽመልስ ሥርዓት አፈሳ እና አጠቃላይ ዘር የማጥፋት ተግባር ይህችን ማምጣት አለበት።
ነጋዴውን ባለሀብቱን በቀረጥ በጉቦ አራቁቶ ለማኝና ረሀብተኛ እያደረገ ነው። ሀብታሙ ግን ገና አልገባውም፥ እያሳሳቀ ወደ ባህር ሳይጥለው ሀብቱን ለነጻነቱ ቢያውለው ያተርፋል።
ዛሬ ሙዝ፣ ሽንኩርት በባሬላ አዙረው የለት እንጀራቸውን የሚያገኙ በዘር ጥላቻ በተለከፉ የነ አዳነች እቤቤና የፌዴራል ፓሊስ አዛዥ ደመላሽ ንብረቱ እየተቀማ በረሀብ እንዲሞት እየተደረገ ነው። ንብረትና ቤት ያለው ደግሞ ቤቱ በዶዘር እየተናደ የዘር ማጥፋት በሁሉም መንገድ ተጧጡፋል። የከተማ ነዋሪው በላቡ የሠራውን ቤት በግብር ስም የክራይ ዋጋ የሚያህል ከፍሎ ቀስ በቀስ እንዲሰደድ ፖሊሲ ተቀርፆ እየተሠራበት ነው።
ሰሞኑን ጦርነት ይብቃ ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር የሄዱ የቀድሞው የኢዜማ አመራሮች፣ የእናት ፓርቲ፣ የኢህአፓ፣ የመኢአድ እና በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ ያሉዋቸውን ሁሉ በየ ቤቱና በየመስርያቤቱ እያደኑ እያሰሩ ይገኛሉ። ይህ ተግባር ከጣልያን ወረራ የካቲት 12 ጭፍጨፋ ጋር ይመሳስሰላል። ሰላማዊ ሆኖ ተለማምጦ መኖር እንደማይቻል የሚያሳይ ሲሆን ለገባውና ኅሊና ላለው ሁሉ በፍጥነት ተነስተህ ራስህን፥ ሕዝብህንና አገርህን አድን የሚል ደወል ነው።
ደወል ተደውሏልና ተነስ። ከተማውን ለቀህ ውጣ፣ ሰልጥን ታጠቅ በወራት ውስጥ ወደ ሞቅ ቤትህ ትመለሳለህ።
የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የ50 አመቱ መጃጃል “ይሄንን ተግባር ያወግዛል” የሚል መግለጫ አይሰጥም። ፋኖ ይህንን አረመናዊ ተግባር ማስቆም የሚቻለው በማውገዝ ሳይሆን ሥርዓቱ የምንሊክና የዮሐንስን ልጆች ሡሪ አስፈታለሁ፥ የደበቡብ ሕዝቦችን ጨፍልቄ ባርያ አደርጋለሁ፥ ታላቋን ኦሮሚያ ቀይ ባሕር ድረስ ዘረጋለሁ፥ በብልጽግና ፖለቲካዊ ኦሮሙማ የምትመራ ምሥራቅ አፍሪቃን በአማራ መቃብር ላይ እመሠርታለሁ ብሎ የተነሳውን ጥቁር የናዚ ጨፍጫፊ መንጋ በጠመንጃ ተፋልሞ መልክ ሊያስይዘው ጀምሯል። እንደ ጫጩት እየተለቀሙ ከመወሰድ በአዋሽ አርባና በኦሮምያ እስር ቤት ከመቀጥቀጥ ወደ ፋኖ ነጻ መሬቶች እየገባችሁ በህይወት የመኖር እና በነጻነት የመኖር ዋስትናችሁን በሚያረጋግጥ ትግል ለመሳተፍ ቀጠሮ አትስጡ እንላለን።
አሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ አብይና ሽመልስ ያቀረቡለት ሁለት መርጫ ብቻ ነው። ይሄውም እየታደኑ መጨረስ ያለበለዚያም ቆሞ ታግሎ በህይወት መኖርንና የሀገር ባለቤትነትን ማረጋገጥ ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለህበት ሁሉ
፩ኛ፣ ምንም ሥርዓቱን ሊጠቅም የሚችል ተግባር ተቆጠብ። አትደግፍ፣ አታጨብጭብ፣ አታሽቃብጥ፣ አይሆንም በል፣ የሱን ፕሮፓጋንዳ አታራባ፣ የህልውና ታጋዮችን በተቻለህ መንግድ ሁሉ ደገፍ፥ ሀብትህንና እውቀትህን፥ መረጃህንና ጥበብንህ ሁሉ ለትግሉ አዋጣ፣ ብሶትህን አታምቅ ተናገር፣ ጉቦ አትስጥ፣ በራስህ ላይ አጥፊህንና ጠላትህን አታደልብ። በቃ ባርያ መሆን በቃኝ በልና ስው ሁን። ተለማምጠህ ተልመጥምጠህ መኖርም አልተፈቀደልህም። ቁርጥህን እወቅ። ዘርህን፥ ሃይማኖትህ፥ ታሪክህ፥ ስነ ልቦናህ እየተጠና ተለይቶ እንድትገድል ከተፈረደብህ አንሆ 50 ዓመታት አለፈውታል። የአሁኑ የመጨረሻው ሰልፍ ነው!!
፪ኛ፣ ለሥርዓቱ በማገልገል ላይ ያሉ ወታደሮችን፣ ፓሊሶችን፣ አድማ በታኞችን፣ ልዩ ኃይሎች፣ አቃቤ ህጎችን፣ የእስር ቤት ዘበኞችን፣ የመንግሥት ቀረጥ ሰብሳቢዎች፣ የመንግሥት የፕሮፓጋንዳ ሰራተኞችን፣ የመንግሥት አሽቃባጭ ነጋዴዎችን የመጨረሻው ደወል ተደውሏልና እራሳቸውን የመጨቆኛ መሳሪያ መሆናቸውን እንዲያቆሙ ብለህ ምከር። በሚነሳው እሳት አብረው እንዳይነዱ ልጅህን ወንድምህን ዘመድህን ጓደኛችን እንበላለን ብላችሁ ከአጥፊና ከዘረኛ ሥርዓት ጋር በመቆም ወይንም በአድርባይነት ቀጥላችሁ እንዳትበሉ ለህ ምከር። የኢትዮጵያ ህዝብ በቅቶታል። ግልብጥ ብሎ የወጣ ቀን አርባ ጅራፍ ቁጭቱን አያበርድለትምንና ሥርዓቱ ወሬ አቀባባዬ፣ ጉቦ አቀባብዬ እበላለሁ ያልክ እንዳትበላ በሉት።
፫ኛ አብይንና ሽመልስ የዘር ማጥፋት እቅዱን ጨርሷል። ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ የሽመልስ አብዲሳ በጥላቻ ያበደ ሰራዊት አደራጅቷል፣ ሁሉንም የወታደራዊ መዋቅር የተቆጣጠሩ ጸረ እማራ፥ ጸረ ታሪክ፥ ጸረ ነባር ባህልና እምነቶች የኦፒዲኦ መኮንኖች ታንኩን፣ ድሮኑን መድፉን በእጃቸው አስገብተዋል። በጫካ በጸረ አማራ ጥላቻና ያደራጁት የኦነግ ታጣቂ በየ ቁጥቋጦው በመደዳ ጨፍጭፍ የሚል ትእዛዝ ይጠባበቃል። እነ አዳናች አቤቤ በአዲስ አበባ የሚያደራጁት ግማሽ ሚሊዮን አብዮት ጠባቂ ጣልያንን ለመመከት እንዳይመስልህ። አንተን ለመፍጀትና ለማረድ ነው። ስለዚህ በወለጋ እንዳሉ ኢትዮጵያውያን እራስህን በየሰፈርህ አደራጅ፣ ዱላህን ዘነዘናህን ይዘህ ተሰባስበህ የራስህን፣ የሚስትህን፣ የልጅህን፣ ነፍስ ለማዳን ክጎረቤትህ፣ የሰፈርህን ሰው ይዘህ ተነጋገር። በሀሳብ የምትግባባ ጎረቤት ጋር በዚህ ቢመጡ በዚህ ቢያጠቁን ብለህ በየሰፈርህ ተደራጅ። የኢትዮጵያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ፓሊስ የሚባል የለም። ባምስት መቶ ካሪ ሜትር ቦታ ሀገሩንም ክብሩንም ሚስቱንም የሸጡ ጄኔራሎች የሚመሩት የአብይ መገልገያ እቃ ሆነዋል። ህሊና ቢኖራቸው ለሀገራቸው ለወገናቸው ከሆዳቸው በላይ ቢያስቡ ኖሮ ህጻናትና አሮጊቶች ሲታረዱ እኔ ቆሜ ብለው ወለጋ ይገቡ ነበር። ስለዚህ የአዲስ አበባ ህዝብ ሲታረድ ጀነራሎቹ ዘራፍ ብለው መትረየሳቸውን በጂፕ ላይ ደግነው ወጥተው ከህዝብን ከመታረድ ያድናሉ ብለህ አታስብ ተስፋ ቁረጥ። ለዚህ ነው በሚስትህና በልጅህ ፊት እየተጠፈጠፍክ እያለቀስክ ከምትታሰርና ከምትታረድ፥ ለልጅህን እናት ለሚስትህ አንድ ቀን ወንድ ለመሆን ተዘጋጅ። ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነ ሁሉ ልጁ እፊቱ ስትደፈር ሚስቱ ስትታረድ ያያል። ፋኖ በቅርብ አለ ይሁንና 120 ሚሊዮን ህዝብን የማዳን አቅም የለውም። ይልቁንም 120 ሚሊዮን ህዝብ ሆ ብሎ ዘነዘናውን ይዞ ከተነሳ በአንድ ቀን ውስጥ ገዳዩን ዘረኛ መንግሥትና ሠራዊት አፈራርሶ ራሱን ያድናል፣ ሀገርንም ነጻ ያወጣል።
፬ኛ፣ በየ ከተማው ያለህ ወጣት ሙዝ ሼጬ፣ ሽንኩርት አዙሬ፥ ሎተሪ ቲኬት ቸርችሬ፥ ባጃጅ ነድቼ ያልፍልኛል ብልህ በየመንገዱ እየታፈስክ ከምትጠፈጠፍ ቆፍጠን በል። ወንድ ወንድ ሽተት። ከአዲስ አበባ 30 ኪሜትር ሳይርቅ ነጻ ምድር አለ። አትልፈስፈስ ውጣ፣ ሰልጥን፣ ታጠቅ ነጻነትህንና በህይወት የመኖር መብትህን በክንድህ ብቻ ነው የምታረጋግጠው።
፭ኛ፣ ፓለቲከኛች፣ ምሁራን፣ አስተማሪዎች፣ ጋዜጠኛች፣ ቢሮክራቶችና መኀበራዊ እንቂዎች በቃ በሉ። መለማመጥ፣ ማባበል፣ መምከር አልሰራም። በምክር፣ በጽሁፍ፣ በክርክር በሰላማዊ መንገድና አቤቱታ ለውጥ እንደማይመጣ እያየህ ነው። ፈራ ተባ እያሉ ሰላም ይምጣ፣ ጦር ይብቃን ያሉ እስከ ቅርብ ጊዜ የስርዓቱ ደጋፊ የነበሩ የኢዜማና የአብን አባሎች ሳይቀሩ እየታደኑ ወደ ዲናኔ ( አዋሽ አርባ) እየተወሰዱ ነውና ሙከራችሁ ከሽፏል። እናንተ ወደኛ ብትመጡ ትጠቅሙናላችሁ። እንፈልጋችሀለን ምንጃር፣ ቡልጋ አረርቲ፣አሳግርት በግማሽ ቀን በእግር ጉዞ ነው። ከዛ ሆናችሁ በጽሁፋም በክርክሩም በማንቅልቱም ልታገለግሉ ትችላላችሁና በቃን ብላችሁ ትግሉን ተቀላቀሉ። ጳጳሳት፥ ሼኪዎች፥ ወንጌላውያን፥ ዑስታዞች ከዚህ ሥርዓት ደም ማፍሰስና ዘር ማጥፋት የምትጠቀሙ አንዳች ደብቅ ነገር ከሌላችሁ በስተቀርና የወንጀሉ ሽፋን ሰጭዎች ሆናችሁ ካልተመደባችሁ በስተቀር ውጡና እውነቱን በአደባባይ ተናገሩ፥ አማኞቻችሁን ከሰው በላው ሥርዓት ራሱን አንዲያድን ቅስቅሱን፥ በተራ መግለጫና ቅልስልቅ ንግግር አታዘናጉት። ሰይጣንን የምታገለግሎ ደም አፍሳሾች ትበላችሁ በታሪክም በፈጣሪም ፊት ላለመጠየቅ ወስኑ።
ክርስቲያን ታደለንና ዮሐንስ ቧያለውን ያየ የዚህን ሥርዓት ጭካኔና ዘር ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። የፓእረላማ አባል፥ ቄስ፥ ሼኪ፥ ሕጻን፥ አረጋዊ፥ ገዳማዊ መሆን ሁሉ የማያቆመው ባህልና እምነት የሌለው የአራዊት መንጋ የመሠረተው ዘር አጥፊ መንግሥት ነው።
ስለዚህ ፋኖን በመቀላቀል እራሳችሁን ከባርነት ነጻ አውጡ የምንለው። የኢትዮጵያ አርበኞች ካልዲስ ካፌ ተቀምጠው አይደለም ነጻ ሀገር ያስረከቡን። ስለዚህ ተለቅመህ፣ ተሰድበህ፣ ተዋርደህ፣ ተርበህና ተቀጥቅጠህ በአዋሽ አርባ ከምሞት ካኪ ሱሪህንና የሚመች ጫማህን አድርገህ ና። ለሌላው አታስብ። ገበሬው ወፍራም እንጀራ በሽሮ ያበላሀል አትራብም፣ አትጠማም ወንዝ ወርደን ቀድተን አፍልተን እናጠጣሀለን፣ በአካል ብቃት እናጎለብትሀለን። የሰውንና የነጻነትን ክብር ሊያዋርዱህና ሊሳለቁብህ የተነሱትን ታሳያቸዋለህ። ከዛ እንደ አባቶቻችን “ አሉ ጎንበስ ጎንበስ አሉ በርከክ በርከክ አውሬ መስያቸው፣ ከሰው መፈጠሬን ማን በነገራቸው ትላቸዋለህ።
ውርደት በቃኝ፣ ባርነት በቃኝ በል። ተነስ ማንም ነጻ አያወጣህም። ነጻ የምታወጣው እራስህን ነውና። ለትግል የውጡ ወንድሞችህ እጃቸውን ዘርግተው ይጠብቁሀል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገሩንና በህይወት መኖሩን በክንዱ ያረጋግጣል
የአማራ የህልውና ተጋድሎ ለሁሉም ኦትዮጵያውያዊ የዋስትናውና የተስፋ ፋና ነው!!!