ዐመሓራነት በብሔርተኝነት እንዳይሰናከል የንቃ ደወል ጥሪ!
ወልደማርያም
ይህን ጽሁፍ ያስጀመረኝ በመምህር ፋንታሁን ዋቄ ስለብሔርተኝነት በቪዲዮ የተላለፈ መልእክት ማድመጤ ነው። ነገሩ ኮረኮረኝና ልምዴንም፥ የዓለምንም ዳሰሳ አድርጌ ለመጻፍ ተነሳሁ።
መምህር ፋንታሁን ብሔርተኝነት ስለሚያመጣው ችግር ለውይይት መነሻ የሚሆን እጅግ ኮርኳሪ አንድ ባለሁለት ክፍል ቪዲዮ ለቀው ነበረ። ይሄንን ቪዲዮ ካየሁ በኋላ እኔም የራሴን እይታ ለመስጠት ተነሳሳሁ። ኢትዮጵያ በጎሳ ብሔርተኝነት ስትናጥ ይሄው ወደ 64 ዓመት አለፈው። ቪዲዮዎቹን ለማይት ማስፈንጠሪያዎቹ https://youtu.be/Vy1T26T2z7U እና https://youtu.be/_7IYC51fGyIናችው። ይህን ጽሑፍ ከጻፍኩም በኋላ ሌላ ትምህርታዊ በሆነ መንገድ ያዘጋጁትን ይህን “ነፍሱን ትቶ ልብሱን” በሚል ርእስ ስበአዊ ክብርንና ፍትሕን በመዋራድ ስለ ባህልና ቋንቋ የሚጨነቁ መስለው ራሳቸውን ስለሚያነግሡ የብሔር ፖለቲካ ልሂቃን ስህተት ያሳዩበት ቪዲዮ አጋርተዋል፦ https://youtu.be/cUx8ZIZ9Rn8
ማሳሰቢያ፦
በነገራችን ላይ እንደ ተለመደው ጥራዝ ነጠቅና ዐሳብን የሚያሰራጩ ሰዎች ይህን ጽሑፍ በተሳሳተ መንግድ እንዳይተረጉሙት ስለምሰጋ የሚከተለው ማሳሰቢያ አጥናኦ እንዲሰጥንልኝ እፈልጋለሁ፦ ዐመሓራ “ብሔርተኛ” አይሁን ማለት ዐመሓራ አይደራጅ ማለት አይደለም። ዐመሓራ ሲደራጅ በዐመሓራነት ተደራጅቶ እራሱን እየተከላከለ ነው። ይሄንንም በማድረጉ እራሱን ከመጥፋት አደጋ አድኗል። ለሌላውም ተስፋ ሆንዋል። የዚህ ጽሁፍ አላማ ዐመሓራንትን ወደ ኦነግና ሕወሃት አይነት ብሔረተኝነት እንዳይወርድ ነው። የብሔረተኝነት ችግሮች ቀድሞ እንዲረዳና የብሔረተኝነት መንገድ ጎጂህ ባህሪዎቹን አስቀድሞ ለማስመዝገብ ነው። ህወሓትን ጣጣ ውስጥ የከተተው አይነት ወደፊት ተመልሶ የሚያጠፋውን የብሔርተኞች መንገድ እንዳይከተል ለመምከር ነው። ህወሓት ስልጣን በተቆጣጠረበት ዘመን የሺ ዓ መት ገዢ የሆኑ መስሏቸው ብዙ ስህተት ሰሩ። በመጨረሻው መጠላት፤ መገለል፤ መሞት መራብ መሰቃየትና መዋረድ ሆነ። አሁን እነ ሽመልስ አብዲሳም መሬት አይብቃን ይላሉ። የኦሮሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ 28.8 በመቶ በትክክለኛው የህዝብ ቆጠራ።
አሁን ደግሞ የኦሮሞ የደም ጥራት አስፈላጊ ነው ስለተባለ “ዲቃላውን” ሁሉ አባሮ ግማሹንም ገድሎእ እራሱን አመናምኗል። ልክ ህወሓቶ የትግራይን ህዝብ አንተ “ወርቅ ነህ ሌላው ደግሞ ጨርቅ ነው” “ላንተ ጦርነት የባህል ጭፈራህ ነው” “እኛ ጦርነት መዋጋት ሳይሆን መፍጠር እንችላለን” አትፍራው ተነስ ብለው ወጣቱን እንደ ተለየ የብረት ለበስ ፍጡር እንደሆነ አሳምነው እሳት እንደከተቱት። የኦሮሞ ብሔርተኞችም ውድቀት ከህወሓት የተለየ አይደለም። ሆ ብሎ ደገፋቸው ህዝብ ዝም ስላለ ነው እንጂ የኦፒዲኦ እና የኦነግ ሸኔ ብሔረተኞች ቁጥርም፤ አቅምም፤ እውቀትም የላቸውም። ለአላማቸውም የመሞት ጽንአት አልፈጠረባቸው። የገበያ ግርግር ለሌባ ይመቻል ሆኖ ኦፒዲኦ መንግስት ሆንዋል። ዛሬ 72% የሚሆነው ህዝብ ልብ ውስጥ እያደገ የመጣው ስሜት በኤክስሬ ማየት ብንችል ሊፈነዳ የደረሰ ጸረ ኦፒዶኦ ስሜት ነው።
የጎሳ ብሔረተኝነት መሰረት ጥላቻ፥ ደምና አጥንት ቆጠራ፥ ቋንቋ፥ የሐሰት ትርክት፥ ‘ተጎድቼ ነበር፥ እገሌ ጎዳኝ” በሚል የብሔር ጠላት አበጅተው ነው።
ዐመሐራነት ከብሔእረተኝነት የላቀ ማደራጃ እሤት አለው። በዚህም ምክንያት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ ጭሯል። ብዙዎችን ከብሔርተኞቹ የጥላቻ መንደር በተለይ የኦነግ/ብልጽግና ከሕወሃት በሰብአዊነት፥ በሰው ልክ አንድነትና ክብር፥ በፍትሕ፥ በጋራ አገር እኩል ባለመብት መሆን፥ ታሪክ በሐሰት ሳይመረዝ በእውነት አንዲቀርብ የሚሹ ሁሉ የዐሓራነት እሤት ኃያል የስበት ማግኔት ሆኖ ወደ ሰውነታቸው ይመልሳቸዋል ማለቴ ነው።
የብሔር ፖለቲካ መሠረታዊ ችግሮችና አጥፊነቱ፦
ብሔርተኝነት የታወቀው በሽታው የሚጀምረው፦ “እኔ አንተን ብመስልም፤ እንዳንተ ብለብስም፤ አንድ ቋንቋ ብንናገርም፤ እንዳንተ ብበላም፤ ባንድ ቤተ ክርስቲያን ብንጸልይም፤ ባንድ መስጊድ ብንሰግድም፤ ብንጋባም ፖለቲካዊ እስካደረግነው ድረስ አንተ ጠላቴ ነህ ” ብሎ ይጀምራል። ቀጥሎ እያንዳንዱ ሰው እንደ ክቡር እና ራሱን እንደ ቻለ ፍጡር ሰይሆ ን እንደ ቡድን ብቻ እንዲያስብና በቡድን አእምሮና ዐሳብ ላይ እንዲመሠረት ያደርገዋል። የሚገርመው የቡድን አይምሮ የለም። ስለዚህ የህዝቡ ሁሉ አይምሮ ይሰበሰብና ይቆለፍበታል ከዛ ማሰብ የሚፈቀድለት መሪው ብቻ ነው። መለስ ያለው ነገር ሁሉ ለትግራይ ብሔረተኞች የእግዚአብሔር ቃል ነው። መሬት ሰው ጠፍጥፎ አልሰራውም አይሸጥም ሲል እውነት እውነት ይላል። ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው፤ የትግራይ ህዝብ ማለት ደግሞ ህወሓት ነው ሲል ልክ ነው የሚል መሀበረሰን ይፈጥራል። በራሱ የማያስብና በተውሶ ጭንቅላት የሚከላወስ መሀበረሰብ። ዛሬም ከትምህርትም፤ ከንባብም፤ ከእውቀትም የነጻውን ብርሀኑ ጁላን ሰምቶ እውነት እውነት የሚል የኦሮሞ ፕሮፌሰት ሞልቷል።
ብሔርተኞች ምኞቱ ጠላቴ ነው ያለውም ማጥፋት ነው። ሲመቸው እኛ አንገቱን በሜንጫ ነው ይላል። ሳይመቸው ደግሞ ከስቷለ ጠቁራል ተጎሳቁሏል። ሲመቸው ኢትዮጵያ ከኦሮምያ ውጪ (“Ethiopian out of Oromia”) ይላል፡ ሲቸግረው ደግሞ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን” ይላል።
ብሔረት ከፈጠሩት ግጭት፥ ከዘሩት ጥላቻ፥ ከከፉት የመጠፋፋት በር የተወሰነ ጊዜ ለማረፍና ራሳቸውን ማደላደል ሲፈልጉ የሚቀርቧቸው ደካማ የማስታረቂያ ንንግግሮች አሉአቸው፦
❖ ተዋልደናል
❖ የመከራ ጊዜን አብረን አሳልፈናል
❖ እጣ ፈንታችን አንድ ነው
❖ በመቻቻል እንደ ሌሎቹ አገራት መበልጸግ እንችላለን
❖ ያለፈ ቁስልና የታሪክ ቁርሾን መልሶ መቀስቀስ አያስፈልግም ❖ አጥፍተናል ብለው የታሪክ በደልን የሻሩ አገራት አሉ
❖ እንድ ቤተ እምነት ውስጥ እናመልካለን
❖ ወዘተ
ይላሉ። እንዚህ አነጋገሮች ሁሉ ውስጥ የመለያየት፥ የበቀል፥ የልዩነት፥ እነርሱና እኛ የሚል ድምጸት፥ የታሪክ ካሣን ባልነበሩበት ዘመን አሁን ካለው ትውልድ የመፈለግ፥ ጥላቻ፥ አለመተማመን በግልጽ ይታያል። በሌላ አነጋገር ብንዋለድም እኔ የተለየሁ ፍጡር ነኝ ብቻ ሳይሆን እኔና አንተ ጠላቶች ነን የሚል መልእክት ያዘለ ነው። በዚህ ንግግር ውስጥ ክብረ-ሰብእ፥ እውነት፥ ፍትሕ፥ የትውልድ የመዋሐድ ተስፋ የለም። ሁሉም ተጠባብቀን በጥንቃቄ መኖር ወይንም መጠፋፋት ከደጃችን አለ የሚል በትክክል የሰው ልጅን ክብር፥ የአገርን ምሥጢር፥ የእውነተኝነትና የሕይወት መሠረት፥ የፍትሕና የርትዕና የሰብአዊነት መገለጫ ፈጽሞ የዘነጋ መሠረተ- ፍልስፍናው ጸረ-ሰላም፥ ጸረ-ሰብእ እና ጸረ-ሀገራዊ አንድነት የሆን አስተምህሮ ነው።
የሰከረ ብሔርተኝነት “ተዋልደናል” ይልና እንደ ሁቱና ቱትሲ በፖለቲካ ትርከት ስሜት ውስጥ ሲገባ “ዲቃላ፤ግማሽ ሌላ ደም አለብህ” ማለት ይጀምራ
❖ የመከራ ጊዜን አብረን አሳልፈናል
❖ እጣ ፈንታችን አንድ ነው
❖ በመቻቻል እንደ ሌሎቹ አገራት መበልጸግ እንችላለን
❖ ያለፈ ቁስልና የታሪክ ቁርሾን መልሶ መቀስቀስ አያስፈልግም ❖ አጥፍተናል ብለው የታሪክ በደልን የሻሩ አገራት አሉ
❖ እንድ ቤተ እምነት ውስጥ እናመልካለን
ለምሳሌ እነ አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ውልደታቸው ትግራይ አክሱም ቢሆንም በጣልያን ቅኝ ግዛት ግዜ ጣልያንንም ሆነ አንግሊዝን ሲቃወሙ አልታዩም። እነ አክሊሉ ሀብተወልድ ከጣልያንና ከጣልያን ደጋፊዎች የካቶሊል ሀገሮች ጋር ተናንቀው የኤርትራን ከቅኝ ግዛት ካላቀቁ ቦሀላ እነ በስዊዲን ሚስዮን የተማሩትና የሉተራን ፕሮቴስታንት ሰባኪ የተደረጉት አቶ ወልደአብ ወልደማርያም ጸረ ኢትዮጵያ ሆነው ብቅ አሉ። በአጭሩ ሀማሴንና አክሱም፤ አካለ ጉዛይና አድዋ የሚያገናኛቸው ገመድ የለም በሚል ትርክት ነበር። ትልቁ የሚታወቁበት ጽሁፍ “ኤርትራ ለኤርትራውያን” የሚለው ዘረኛ እሳቦ ነው። በነጻነት ማግስት በደሙ ኤትራዊ አይደሉም የተባሉት የነ አቶ ወለደአብ ወልደማርያም ዘመዶች ሁሉ አጋሜ ተብለው ተባረሩ። ማነም ኤርትራ ውስጥ ገብቶ የማያርስባት ሱቅ የማይከፍትባት ኤርትራ ለኤርትራውያን ሆነች። ይቺ ለኤርትራዊ ደም ብቻ ተብላ የተፈጠረች ኤርትራ ለዜጎቿ የማትመች ሆነች። ዛሬ ደቡብ ሱዳን ለደቡብ ሱዳን፤ ዮጋንዳ ለዩጋንዳውያን፤ አንጎላ ለአንጎላውያን ብለው በዘረኝነት ላይ ሀገር ያልመሰረቱ ሀገራይ በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በሀገራቸው ኖረው ሰርተርው ከብረው ለኢኮኖሚውም አስተዋጾ እንዲያደርጉ እድል ከፍተዋል። ለዚህ ነው ብሔረተኝነት ጠቃሚ አይደለምና ጥንቃቄ ይፈልጋል የሚባለው።
እነ መራራ ጉዲና አትጋቡ ከኦሮሞ ውጪ ሲሉ፤ እነ አባ ሰረቀብርሀን የመንበረ ሰላማ ጳጳስ የተደረጉት “አጼ ኅይለሰላሴ ኦርጅናሉን፤ አውተንቲኩን የሆነውን ትግሬ ከልጆቻቸው ጋር አጋብተው አዳቅለው አጠፉት ይላሉ። አያችሁ ብሔረተኝነት እንዲህ ነው። አውተንቲኩ፤ ኦርጅናሉ ትግሬ ልዩ የሚያደረፈው ጭራ ይሆን ቀንድ እንደነበረው አልነገሩንም።
የአንድነትና የመዋሐድ ጥላቻን የሚፈጥረው የትርክት ምንጭና መነሻ ጠላት መሆኑን ማሰብ የማይችል ምሁር ማንኛውንም ዕሳቤና ፖለቲካዊ ግብ ከማስቀመጡ አስቀድሞ መጠየቅ ያለባቸውን ጠቃሚ ጥያቄዎች ነበሩ። እነዚህም፦
❖ ከረዥሙ የሺ ዘመናት ታሪካችን የቅኝ ገዥ ግማሽ ምዕተ ዓመት የፈጠረውን አስተሳሰብ ለምን መረጥሁ?
❖ ነጻነት ምን ማለት ነው? ከመለያየት በምን ይለያል?
❖ በትልቅ አገር ውስጥ የሚስማማንን ስነ መንግሥት ከሌሎች ጋር መገንባት ነው ወይስ ቅኝ ገዥዎችና አፍሪካን ባርያ ለማድረግ፥ ኢትዮጵያን ከውሃ አካላትና ከልዩ ልዩ አካላቷ መቆራረጥ ከሚሹት ጋር እንድተባበር የሚያሳስበኝ ፍልስፍና ምንድነው?
❖ ነጻነት ከሰብአዊነት፥ ከፍትህ፥ ከእኩልነትና ሰላም፥ ከትውልድ ብሩህ ተስፋ የተለየ ትርጉም አለው? ከሌሎች እነዚህ ጸጋዎች በመለያየትን ጥግ ላይ ክፍለ አገርን ሀገር ማድረግ፥ በተባበሩት ምንግሥታት መምዝገብ ለነጻነት ዋስትና ነው?
❖ —- ወዘተ የሚሉ ይያቄዎችን ጠይቆ ለመመለስ የአእምሮ ነጻነት ያስፈልጋል።
ለመለየትና አገር ለመፍጠር ትግል የሚጀምሪ ብሔርተኞች ወሳኝ ለትውልድና ለአገር የሚተርፉ፥ ከስህተት የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የማንሳት ሙሉ አቅማቸው የተሰለበ ነው። ሙሉ አእምሮአቸውን እንደ ማኅደር ክፍት አድርገው ለባዕዳን ትምህርትና አስተሳሰብ ክፍት አድርገው ከመጋትና ወደ ተግባር ለመለወጥ ከመጋደል የተለየ አቅም ኤይ ኖራቸውም። ሕሃትናና ኦነግን የመሠረቱና በዘመናት የጸጠሯቸው መንጋ ተከታዮቻቸው በዚህ ያለማሰብና በጭፍን የመከተል ደዌ ተጠቂ ናቸው። አቅማቸውና ኃይላቸውን የሚያባክኑት የሐሰት ትርክት በመፍጠርና ቀድሞ የነበረውን በማጠልሸት፥ አሻራ በማጥፋት ላይ ነው። ለምሳሌ ከሸዕብያ፥ ሕወሃትና ኦነግ ጀምሮ የጎሣ ነጻ አውጭዎችና ልሂቃን ሁሉ በሚከተሉት የኢትዮጵያ ታሪክ ምንጮችና ትርክቶች ላይ በአሉታዊነት የዘመቱ ናቸው፦
፩) ክብረ ነገሥት
፪) የኢትዮጵያ የ3000 ዘመን ታሪክ እና የሕገ ልቡና የ2000 አመን ትውፊታዊ ትርክት
5
፫) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ የታሪክ አሻራ ያላቸው ክርስቲያን ነግሥታት ዙና መዋዕልና ታሪክ ፬) የኢትዮጵያ ጥንታዊ ካርታና የሕዝቦች አሠፋፈር ታሪክ
፭) የአህመድ ግራኝ ወራሪነት፥ አውዳሚነትና የኦቶማን ቱርክ ጂሃድ መልዕከተኛነት
፮) የተለያዩ ብሔረሰቦች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ባደረጉት ያደረሱት አሉታዊ ተጽእኖ ታሪክ
፯) የእምነቶች መስፋፋትና መልሶ መዳከም ታሪክ ከውጭ ጣልቃ-ገብነት ጋር ያለው ቁርኝት
፰) በውጭ ጠላት ወረራ አጋጣሚዎች ከጠላት ጋር በማበር አገራቸውን የወጉ ወገኖች ታሪክ እና የልጅልጀጆቻቸው የባንዳነት ስነልቦና ለዛረዋ የኢትዮጵያ ያለው አስተዋጽኦ
፱) አንዳንድ ውጭ-ገብ እምነቶች ቅኝ ገዥዎች መንገድ ጠራጊነትና አንድነትን በማዳከም፥ ትውልድን በመከፋፈል፥ ነባር ባህልን በማዳከም ላይ የነበራቸውን ተጽእኖ ማንሳትና መግለጥ — ወዘተ
በተቃራኒው እነዚህ ልሂቃን የሚከተሉት ጊዳዮችና ትርክቶች በማራመድና በማግነን ነባሩን ለመተካት እጅግ የተጋሉ፦
፩) የምዕራባውያን ወይንም የአረብ ስነ-አስተዳደር፥ የዘመን አቆጣጠር፥ ፊደል፥ ቋንቋ አስፈላጊነትና ልህቀት
፪) የምእራባውያን ወይንም የሌሎች ፖለቲካዊ ርእዮትና የአኗኗር ዘይቤ ከአገራዊው ነባር እንዴት ብልጫ እንዳለው
፫) የአገር ነባር እምነታዊና ባህላዊ የረዥም ዘመናት ሕየወት አገር ያዳበረቻቸው የሕግ፥ የፖሊሲ፥ የማኅበራዊ ሥርዓትና መዋቅራት ኋላቀርነት፥ ቆሞ ቀርነትና የእድገትና የሥልጣኔ እንቅፋትነት
፬) የአርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአጼዎቹ የጭቆና መሣሪያነት እና የአዲስ እምነቶች መስፋፋት አስፈላጊነት — ወዘተ።
እነዚህ የዘመኑ የብሔር የነጻነት፥ የሥልጣኔና የእድገት፥ የዲሞክራሲና የእኩልነት ዘማሪዎች በተግባር ተፈትነው ወድቀዋል። የሚናገሩትና በተግባር የሚያደርጉት ሁሉ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል። እንደ አምላክ የሚመለከቷቸው የውጭ አማካሪዎቻቸውና መሪዎቻቸው የአድዋ ቁስ ባሳከካቸው ቁጥር ኢትዮጵያን ለመበተን አዳዲስ ስልት የሚቀይሱና የሚተገብሩ ናቸው።
እነዚህ አካላት ለዘመናት አሰላስለውና ጠይቀው የመለሱት ጥያቄዎች አሏቸው፦
❖ የአድዋን ድል ያስገኘውን ኢትዮጵያዊ ስነ-ልቦና ያነጸው ማነው?
❖ እነዚያን የድል ጦርነቶች የመሩ ወገኖኝ በአብዝኃኛው ከየትኛው የእመነት ወገንና ባህል ነው?
❖ ኢትዮጵያውያን እኛ ከሌሎች አገራት ሰዎች በፍጥረታችን እኩል ነን! አንበልጥም አናንስም! ስለዚህ በርነት አይገባንም፥ ባሮች ከምንሆን መሞትን እንመርጣለን የሚለውን አስተሳሰብ ከወዴት አገኙት?
በማለት ስህተትም ይሁን አውነት የመለሱት ምላሽ፦.
❖ ኦርቶዶክሰዊት ክርስትና፥
❖ ረዥም የብዝኃ-ማንነቶች ተመጋጋቢ አሐዳዊነት መፈጠሩ፥
❖ በየዘመናቱ የውጭ ወረራዎችን ጦርነት የመሩ ነገሥታትና መሳፍንትን፥ የውስጥ መለያየትን መልሰው አንድ ለማድረግ የጣሩ የእምነትና የመንግሥት ወገኖች በአብዝኃኛው ሥነ ጽሑፍ ያላቸውና ታሪክና ጥበብ የሚያስተላለፍ አቅም የነበራቸው እነ “አገሌ” ናቸው ብለው በየኑ—- እናም ይህን የፈረጁትን ማኅበረሰብ፥ ባህሉን፥ ስነ ጽሑፉን፥ ስነ-ንግሥቱን፥ ባህሉን፥ እምነቱን፥ ሥርዓተ ማኅበሩን፥ ታሪኩንና ትርክቱን የእጠዮጵያውያን የጋራ ሀብት እንዳል ሆነ፥ ሐሰት አንደሆነ፥ የጥቂት በተለይ የዐመሓራና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች፥ የዐመሓራ አጼዎች አንደሆነ ጠንክሮ በማስተማር ሕዝቡን የጋራ እሤት ማሳጣትና ባርያ እንዳናደርጋቸው እንቅፋት በሆኖብን ጸጋዎቻቸው ላእ መዝመት የሚል ስልት ተቀየሰ። በዚህ መሠረት የሮማን ኢምፓየር አፈራርሶ ወደ ትናነሽ መንደር የለወጥ፥ ሂትለርና ሚሲሎኒን የወለደውን ብሔርተኝነት ለኢትዮጵያ በማስተዋወቅ በአገር ውስጥ አገር፥ በአንድ ሕዝብ መካከል ሕዝቦች እንዲፈጠር ፕሮጄክት ተዘርግቶ ከ70 ዓመታት በላይ በመሥራት የዛሬዎቹን ህሊና ቢስ፥ አምላክ-የለሽ፥ የሐሰተኝነትና የደም አፍሳሽነት ሱሰኞች ለመንግሥታዊ ሥልጣን ማብቃት ቻሉ።
የዐመሓራ ሕዝብ የህልውና አደጋ የመነጨው ከዚህ ታሪካዊ ሂደት ነው። ስለዘህ ዐመሓራ የሚዋጋውን አውቆ የሚዋጋቸውን ፋሽት ብሔርተኞ ራሱም ፋሽትና ሐሰተኛ፥ ኢሰብአዊና ኢፍትሐዊ በመሆን አይኖርበትም። የብሔርተኝነት ቅዱስና መድኀኒትነት የለዉም። ሌሎችን በልቶ ራሱ እንደሚጠፋ ማገዲ ያለቀበት የእሳት ነዲድ ነው።
ዐመሓራ እነሲህን ከውጭ ተዘርተው አገር ውስጥ ያደጉ የፖለቲካ ዐረሞች ለማረም ራሱም መርዛማ አረም ሳይሆን ንጹሕ ስነዴተነቱን ሳያበላሽ የሰብአዊነትና የፍትሓዊነት፥ የአውነተኝነትና የሰብአዊ ፍጡር እኩልነት እሤቶቹን ከሚጋሩ ሌሎች የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች ጋር ሁሉ የሚያሰልፈውን ዐመሓራነቱን ከብሔርተኝነት ምረዛ መከላከል አለበት።
ዶሮን ሲያታልሏል በመጨኛ ጣሏት እንዲሉ በበታኝ፥ ከፋፋይና ዘር አጥፊ ብሔርተኝነታቸው የዐመሓራን ሕዝብ በተለይ እና አጠቃላዩን ኢትዮጵያዎ የአገራችንን ማኅበረሰቦች የህልውና አደጋ ላይ የጣሉ፥ ፍትሕና እኩልነት የነፈጉት ብሔርተኞች የላኳቸው አንዳንድ የዐመሓራ ልሂቃን ለዐመሓራ ሕዝብ ለህልውና አደጋ መጋለጥ መንስዔ፦
፩ኛ/ ዐመሓራ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ በመጽናቱ ሌሎች የሚጠሉት ሲደራጁ ራሱን ለመከላከል ሳያዘጋጅ መቅረቱ ነው፥ ፪ኛ/ ብሔርተኝነት ያመጣውን አደጋ ለመቀልበስ ዐመሓራ ራሱ ብሔርተኛ መሆን አለበት፥
፫ኛ/ ከብሔርተኝነት ውጭ አንድ ጠንካራ ንቅናቄ መፍጠር አይቻልም፥ እና ህልውናን ለማረጋገጥ “የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም”
በሚል ስሑት ኢመክንያዊ ተጠየቅ ላይ ተመሥርቶ ፋኖ ከዐመሓራነት እሤቶቹ አንዲያፈገፍግ እና ሁለት አደገኛ ስህተቶችን እንዲያደርግ ግፊት እያደረጉበት ይገኛል። እነዚህም
ሀ) ኢትዮጵያዊነትን ለዐመሓራነት ባዕድ በማድረግ በትርፍነት ደረጃ ማስቀመጥ
ለ) መርዛማውን አግላይ፤ ሌላ የማኅበረሰብ፥ ባህል ቋንቋ፥ ታሪክ፥ እምትና ማንነቶችን በጠላትነት ሳይፈርጅ መቆም የማይችለውን አጥፊ ብሔርተኝነት እንዲጋት እየገፋፉት ይገኛሉ።
በዚህ ጽሁፍ የፋኖን የህልውናና የፍትህ ትግል ወደ ክልላዊ ብሔርተኝነት ካወረድነው ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ለመጠቆም እንሞክራለን።
ፋኖ ብሔርተኛ ከሆነ በሚከተሉት ወጥመዶች ውስጥ ወድቆ ራሱን ያሣሥራል፦
፩) ድንበር የተበጀለትና ብቸኛ አማራ ሊኖርበት መብት የሚያገኝበት የተወሰነ አካባቢ መወሰን፥
፪) ዐመሓራን ዐመሓራ የሚያሰኘው የአማርኛ ቋንቋ፥
፫) ዐመሓራ የሚያሰኝ ቢያንስ እስከ ፯ የቤተሰብ ሐረግ የሚቆጠር የዐመሓራ ወላጅ ቤተሰብ፥
፬) ሌሎች የማይጋሩት የዐመሓራ ብቻ የሆነ አዳዲስ ታሪክና ትርክት መፍጠር፥
፭) ዐመሓራን ከሌሎች ማኅበረሰቦች የላቀ፥ ታላቅ፥ የተሻለ መብት የሚገባው፥ ከአገሩ ልጠዩ ጥቅም የሚፈልግና ለዚህ ሌሎችን እስከማጥፋት የሚጨክን መሆን፤
፮) አገር ውስጥ ጠላት የተባለውን ወገን ለማሸነፍና የብሔሩን “መብት” ለማስከበር ወይንም “ነጻ ለማውጣት” ከሚረዳ ማንኛውም የውጭ አካል “የታወቀ የኢትዮጵያ ጠላም ቢሆን” ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆን፤
፰) ብሔሩ በእምነት፥ በቋንቋ፥ በትርክት፥ በአሠፋፈር፥ በጸሎት ቤት፥ በባህል፥ በዕሤት ከሌሎች ምንም እንዳይጋራ ሁሉንም በአዲስ መልክ ማደረጃት፤
፱) መጽሐፍ ቅዱስ፥ ቁራንና ማንኛውም ነባር ታሪክ ተፍቆ ዐመሓራን ከፍ አንዲያደርግ ተደርጎ እንደገና መጻፍ፤ መጅሊስና ሲኖዶስን ለዐመሓራ ትርክት እንዲያገልግሉ አድርጎ ማዋቀር፥
፲)በመጨረሻ ፋኖ የሚችለውን ተጋድሎ ሁሉ አድርጎ ሕወሃትና ኦነግ በጻፉለት ሕገ መንግሥት መሠረት እንዲሰበሰብበት በተፈቀደለት “የአማራ ክልል” በተባለው የአፓርታይድ ሥርዓት ውጤት ውስጥ ይቀራል።
ጠባብ ወይን ንዑስ ብሔርተኝነት ላይ የተመሠረተ ጽንፈኛ ማንነትን ን ለማጠናከር በትንሹ እነዚህ ፲ ነጻ አጭዎችን፥ ገንጣዮች፥ በአገር ውስጥ አገር ለመፍጠር የሚሠሩ እንደ ኦነግ/ብልጽግና አይነቶች የተጠቀሙባቸው መንገዶች አሉ።
፲ሩም ከዐመሓራነት እሤቶች በተቃራኒ የቆሙ ናቸው፦ ለብሔርተኞች ዋና መሠረታቸው ኢሰብአዊነት፥ ኢፍትሐዊነት፥ ሐሰተኝነት፥ ጥላቻ፥ አገርን መካድ፥ አዲስ ከእውነተኛ እምነት የሚያወጣ ሃይማኖት መፍጠር ናቸው።
ዐመሓራም “ብሔርተኛ” ልሁን ሲል እነዚህ ማንኛውም ብሔርተኝነት የሚያስገድዱትን መሠረቶች ካደረገ አማራኝ የሚናገር ኦነግ/ብልጽግና እና ሕወሃት ነው። ራሱም ዐመሓራ የሚዋጋውን ክፋት ሆኖ ይከሰታል፥ እናም ማንንም፥ ምንንም አያሸንፍም።
የ“የአማራ ብሔርተኝነት ይለምልም” የሚሉት ይህን ያገናዘበና ከዚህ አጥፊ ብሔርተኝን ሩቅ መሆናቸውን ትንተና፥ ፍልስፍና፥ ርዮትና አጸጻም በግልጽ ማኒፌስቶ ያቅርቡ። የላቸውም!!! ኣይኖራቸው መጮኻቸው ምን ያህል ሩቅ ማየት ከተሳናቸው የባእዳን ማደሪያ፥ የዐመሓራነት መልካም እሤቶች ጠላቶች ምክር እየተቀበሉ አንደሚገኙ እገምታለሁ።
ዐመሓራ እንዲያው በስሜት፥ የህልውና አደጋውን ለማስወገድ ብቸኛ መሰባሰቢያ “ብሔርተኝነት” አመራጭ የለዉም ብሎ ከነጎደ — ያን ጊዜ ልክ አርሱን ዒላማ እንዳደረጉት ሁሉ ሌሎች ብሔርተኞች ሁሉ የዐመሓራ ጠላቱ ሌላ ማኅበረሰብ፥ ባህል፥ ታሪክና የሰው ልጅ ይሆናል። ስለዚህ እንደ ሕወሃትና ኦነግ ያሉ ዘር አጥፊ፥ ፋሽስት፥ ሐሰተኛ፥ ኢፍትሓዊ፥ ዘራፊ፥ አፈናቃይ፥ ጨፍጫፊ፥ ታሪክ ደላዥ፥ የባእዳን ተላላኪ ይሆናል።
በምላሹ ደግሞ ሌሎች ማኅበረሰቦች ከዐመሓራ ብሔርተኛ የሚደቀንበትን የህልውና አደጋ ለመከላከል ጫካ ይገባሉ። የ፶ ዓመቱ የሕወሃትና የአኖግ/ብልጽግና የሐሰት ትርክት እውነት ተደርጎ ይወሰዳል፥ ለ፴፮ ዓመታት መከራ የተቀበለው፥ የዘረፈው፥ የተፈናቀለው፥ የተገደለው ዐመሓራ ፍትህን መጠቀይ፥ ወደ ነበረበት ሰብአዊ ክብር መመለስ አይችልም።
ውጤቱ ማንም የማያሸንፍበት የሲቪል ጦርነት ይሆናል። በዚህ ውስጥ የትኛውም ሕዝብ አሸናፊ ሳይሆን የህወሃትና የኦነግ መርዝ ያሳበደው የሚነካከስ ትውልድን በመላው አገሪቱ እንፈጥራለን። ይህ ደግሞ ለአድዋ ቁስለኞች፥ ለኢትዮጵያዊነት ጠላቶችና ዐመሓራንና ኦርቶዶክስ ክርስትና ለማጥፋት ከ፸ ዘመናት በላይ ለደከሙ የውጭ ኃይላት ትልቅ ድል ይሆናል።
ፋኖ ዐመሓራነትን ንቆ አሁን ልሂቃኑ ሊመክሩት እንደሚሞክሩት “ብሔርተኝነት ይለምልም” በሚል ከጠላቶቹ የተኮደጀ የእጥፍቶ መጥፋትን የጥላቻና በማንነት ላይ የተመሠረተ የከሠረ ርእዮት ማራመድ ከመጀመረ ከላይ የጠቀስነውን ፲ ጸረ-ሰብአዊነት እና ኢፍትሐዊነትን ስለሚያዳብር ትግሉ ከህለውና ወደ ዘር ማጥፋት ፋሽዝም ይለወጣል። ቢያሸንፍ እንኳ የአብይን ሠራዊት እንጂ ራሱን “ብሔር” ብሎ ከሰየመ በኋላ ሌላ ብሔር ሆነው የራሳቸውን ህልውና ለመከላከል የሚሰለፉት መላውን የሐገር ዜጋ ማሸነፍ ኤይችልም፥ እናም ብአዴን ቁጥር 2.0 ይሆናል።
ቀጥሎ የዐመሓራን ህልውና ከማስከበር ዐመሓራን ወደ አስፈሪና ኢሰብአዊ መንጋ ቀይሮ የሕወሃእና ዑኦነግን ስህተት በመድገም ሕዘቡን የከፋ አደጋ ውስጥ ይጥላል። ውጤቱም የተነሳለትን የዐሓራን ሕዝብ ህልውናና
ፍትሕ የማረጋገጥ ህልም ከንቱ በማድረግ ለ፶ ዘመናት በላይ ሊያጠፉት ከሞከሩት ስሑታኑ ከበባ ውስጥ ዘለቄታዊ ጥቃት አንዲፈጸምበት ሕዝቡን ለአደጋ መዳረግ ብቻ ሳይሆን በመላው አገራችን የተበተነው ዐመሓራና ዐመሓራዊ እሤቶች ያላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ለበለጠ ጥቃት ያጋልጣል። ከዚሁ የብሔርተኝነት መገለጫውን፡ መንገዱን እና ጉዳቱን በዚህ ጽሁፍ ለማቅረብ ወስኛለሁ። ጽሁፉ ረዘም ስላለ በክፍል 1 እና 2 እንዲወጣ አድረጌዋለሁ።
የዐመሓራነት በጠላቶቹ አይነት ብሔርተኝነት እንዳይጠለፍ ደወል ማሰማት አስፈላጊ ሆኖ ይታየኛል። ዐመሓራነት ዓለም ከለመደው፥ ሕወሃትና ኦሮሙማ ካቀነቀነው በጠላትና በጥላቻ፥ በቡድንና በማጥፋት ላይ ከሚመሠረት የጦርነት ሁሉ እናት ብሔርተኝነት የተለየ ነው። ዐመሓራነት ከሰብአዊነት፥ ፍትሐዊነትና እውነት ወርዶ አያውቅም። ይህን ዕሤት ወደ ቡድን የእኔና እናንተ የቡድን ጦርነት ለመለወጥ መሞከር ለዐመሓራ ሕዝብ ሌላ የማይወጣው የህልውና አደጋ ውስጥ ማስገባት ይሆናል ብዬ አምናለጁ።
የዐመሓረው የህልውና እና የፍትህ ትግሉ ወደታች ወደ ብአዴንነት እንዳይወርድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያን ትቶ የባህርዳር ሥልጣን ጥያቄ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ሰሞኑን ኢትዮጵያኒስ ት የሚል ጨቅላ እሳቤ በየ ሶሻል ሚዲያ ስትደጋገም ታይታለች። ኢትዮጵያኒስት የሚለው ጽንሰ ሀሳብ ባይረዱትም ማርክሲስቶቹ እንደሚሉት ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ከፈለግክ አንደኛ ቃሉን ባለጌ አድርገው፥ ሁለተኛ ደግሞ ደጋግመው ይላሉ (vulgarization and repitition)።
ብዙኃን በቀላሉ ሊተረጉሙት የማይችሉትን ግራ ማጋብያ ባለጌ ቃል እንደ ሰደድ እሳት መኀበረሰቡ ሳእረዳው ብ ይቀባበ ለዋል። ለምሳሌ “ጁንታ” አብይ አህመድ የእንግሊዘኛ እውቀቱ ውሱን ስለሆነ ጁንታ ምን እንደሆነ ትርጉሙን አላወቀም። እንደ ስድብ ቃሉን ተጠቀመብት። ወድያው ጁንታ ማለት ትግሬ ማለት ሆኖ ለመለመድ አንድ ሳምንት አልወሰደበትም። ህወሓትም “ነፍጠኛ” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ዐመ ሓራ ለማለት ነበር። እስከ አሁን ቀጥሏል።
ስለዚህ “ኢትዮጵኒስት” የምትባለው ስደብ መሰል ቃል ካደረች እሱ እኮ ኢትዮጵያኒስት ነው ተብላ የጥላቻ መፈክር ትሆናለች፤ ይህ በጭፍን የመከተል ባህል በተንሰራፋበት ባህል ውስጥ ያለው ትውልድ ሌላ ግራ መጋባትና ጸረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ተላብሶ አሸንፈዋል ብሎ ጨካ የገባለትን ትግል በሚቃረን መንገድ ጠላቶቹን እንዳይገለግል በጽጥነት ማረም ያስፈልጋል። እለዚህ ከፋኖ ጋር ግ ኙነት አለን የሚሉ ነገር ግን ስለ ብሔርተኝነት ያላቸው ንባብና ግንዛቤ ውሱን የሆኑ ሰዎች የዚህ ጥራዝ ነጠቅ ተአምራዊ ቃላት እየነጠቁ መበላሸት ውስጥ እንዳይገቡ ሂደቱን በአጭሩ ለመቅጨት ጽሁፍ ተዘጋጀቷል።
የፋኖ ትግል አነሳስና መሠረት ያደረጋቸው የዐመሓራነት ልዩ ዕሤቶች
ዐመሓራ ራሱን ከማንም በልጣለሁም አንሳለሁም ብሎ አያውቅም። እንደሌሎቹ የሚያጠፋው፥ የሚያፈናቅለው፥ ሐሰት የሚተርክበት ማኅበረሰብ የለዉም። ዐመሓራ የሚገነጥለውና የሚፈጥረው አዲስ አገር የለዉም፥ ለአንዱ የሚገባ ለሌላው የማይገባ ከልልና ቦታ ለመፍጠር አስቦም አልሞ አልተነሳም። ዐመሓራ ከሰውነት የወረደ ሕገ-መንግሥት ጽፎም አጽፎም አያውቅም። “ብሔርተኞች” ግን ይህን ሁሉ በዐመሓራነት ላይ አድርገዋል። የተደረገበተን ለመከላከል ‘“ብሔርተኛ” ወይንም እነርሱን መሆን ግዴታ ነው፥ ኢትያፒያኒስት ዕሳቤ አስጠቅቶናል’ የሚለው ቅስቀሳ አራዊትን ከማሳህ ለማባረር የግድ አራዊት መሆን አለብህ አይነት ከንቱ የዕሳቤ እጥረት ነው።
የሀገርና የዐመሓራ ጠላቶች ለዐመሓራ ጥቁር ምስል መፍጠር ሲሉ በየዘመናቱ የተነገሩ፥ የተጻፉ፥ የተሳሉ፥ ወይን የተቀረጹ ቃላትንመ ዐረፍተነገሮች፥ ምስሎችን፥ ቀለማትን ሳይቀር ከአውዱ ውጭ ለክፋት በመተርጎም የዘሩት የጥላቻ መርዝ ወደ ትርክት ያደገ፥ የጥናት መድረኮች የሚዘጋጁለትና በሕትመት የሚወጡ ተደርገው በትውልዱ አእምሮ አንዲያደርጉ፥ እውነት ሆነው እንዲወሰዱና በዚያ አንጻር የመጠፋፋት፥ አገር የማደፍረስ ፐሮጄክቱ እንዲሳካ ከማድረግ ያለፈ ውጤት አያመጣም።
የፋኖ ትግል የተነሳው ጣልያንና ህወሓት የፈጠሩት ክልል እስከነ አፍራሽ ፖለቲካዊ ርእዮትና መርዘማ ትርክቱ፥ ከፋፋይ ሕገ መንግሥቱ ለመረከብ አይደለም። የመጀመሪያው አንገብጋቢ ዓላመው በመላው ኢትዮጵያ በብሔር ሕገ መንግሥትና ፖሊሲ መሠረት በመጨፍጨፍ ላይ ያለውን ዐመሓራን መታደግ ነው። ይሁን አንጂ ዐመሓራን ከዘር ማጥፋት የብሐየርተኞች ፕሮጄክት ፊት ለፊት ገጥሞ በትጥቅ የመጣውን በትጥቅ ትግል መታደግ የመጀመሪያው ግብ ቢሆንም፥ ሌላ ታላቅ የትግል ተራራ አለ። እርሱም የዐስተሳብ፥ የፖለቲካ፥ የሕግ፥ የመዋቅር፥ የግኑኝነት እና አጠቃላይ አገራዊ አደጋ ያካተተ ተጋድሎ ነው። ሁለተኛው ተጋድሎ ውጤታማ ካልሆነ የመጀመሪያው ድል ሌላ ረዥም የዘር ማጥፋት ፕሮጄክት መክፈቻ ከመሆን አይዘልልም።
ሁለተኛው የትግል መስክና ድል መሥመር የሚሠመረው ወይንም ለድል እንዳይበቃ ሆኖ የሚበላሸው አሁን በትጥቅ ትግል ወቅት በመሆኑ፥ ዐስተሳሰቦች፥ ንግግሮች፥ አደረጃጀቶች፥ ግኑኝነቶች፥ የዐመሓራን ሕዝብ ከወገኖቹ በመነጥል የጎሣ ነጻ አውጭዎች ለ፶ ዓመታት በሐሰት የተረከበትን የሐዳዊነት፥ የጨቋኝነት፥ የወራሪነት፥ የትምህክተኝነት፥ የታሪክ ሌብነት፥ የገዥነት ወዘተ መራዥ የዘረኞች የቆየ ፕሮፓጋንዳ መላልሰውና አድሰው ተጨባጭ የሚያስመስሉበት እድል መዝጋት፤ የዐመሓራን ፋኖ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ግብና ለአገሩና ለዐመሓራ፥ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ ማኅበረሰቦች የሚመኘውን አገር በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። ይህ በጽሑፍ ይገለጽ የሚባለው የዐመሓራ ተጋድሎ መዳረሻ ዐሳብ ከመጻፉም በፊት በተግባር የሚታይ ነው፤ አርሱም፦
(፩) ሥለ አገርና የጋራ ደኅንነት ግለኝነትና በድነኝነትን መሰዋት፦ ፶ ዓመት ሙሉ አገር ብሎ ግፍን፥ ግልጽ መንግሥታዊ ኢፍትሓዊነትን መታገስ
(፪) ክብረ-ሰብ፥ ክብረ-ሐሠገር፦ ከኦጋዴን ጫፍ እስከ ኡርትራ ጫፍ አገር በተደፈረበት አቅጣጫ ሁሉ በመዝመነት የሕወሃትና የኦነግ-ኦሮሙማን አፓርታይድ ከግምት ሳያስገባ ለአገር አንድነት ሲጋደል ሞኖሩ፥ አሁንም ሊያጠፉት የሚመጡትን የአብይ አህምድ አዋራጅና ሴእተ ደፋሪ ሠራዊት ሲማርክ በሰብአዊ ክብርና በጥላቻ ፈንታ ፍቅር በመስጠት መያዙ
(፫) ፍቅር፥ መቻልና እኩልነት፦ በአገር ባለቤትነት፥ በሰብአዊና ሁለንተናዊ መብቶች የሰው ልጆች በሙሉ እናም ዜጎች በአገራቸው እኩል ክብር አንዳላቸው ለማሳየት በሕወሃትና ኦነግ ሕገ መንግሥት ውስጥ ስነኳ አማራን ከመላው ኢትዮጵያ እያጸዱ በአመራክ ክልል የተለያዩ ማኅበረሰቦች ልዩ ዞን ሲፈቅድላቸው፥ ዐመሓራ ስነኳ ልዩ ዞን በአደማና በአዲስ አበባ፥ በሚበዛባቸው ቦታዎች ሁሉ ልዩ ዞን ሊሰጠው ቀርቶ ሰብአዊና ማኅበራዊ መብቶቹ ለ፴፮ ዓመታት ተገፍፎ ሲኖር ትዕግስትና ከመቻቻል ያለፈ ፍቅርን አሳይቷል።
(፬) ፍትሓዊነት፥ እውነተኝነትና የሕዘብ ተዋህዶ፦ አሓዳዊ፥ ትምክህተኛ፥ ነፍጠኛ፥ ዋራሪ፥ ቀኝ ገዥ፥ ወዘተ የሚለው የሕወሃትና የአኖግ/ኦሮሙማ ዐመሓራን ለጥቃት የማዘጋጀት የረዥም ዘመንን ትርክት እንዳልሰማ በማለፍ ስለ ሕዝብ አብሮነት ዋጋ ከፍሏል፤ አይቶ ማለፍ የማይቻለው ህልውና በመሆኑ ተነስቷል— ይህ አነሳስ ስንኳ “ብሔርተኛ” ሳይሆን ፍትህ ፈላጊ፥ እውነትና አጽኚና የህልውና ዋስትና የሆነ ሰብአዎ ተጋድሎ መሆኑን ገልጽሏ፤
እነዚህኑ በግልጽ በወረቅት አስፍሮ ብዙኃን በሚያነቡት የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች ቋንቋ በማቅረብ የዐመሓራነትን ንቅናቄ ወዳጆችና ዋስትና የሚሰጣቸው፥ ከሕወሃትና ከኦነግ/ኦሮሙማ ልክፍት ነጻ የሆኑ ወገኖች ሁሉ እንዲቀላቀሉት መጣራት ይጠበቅበታል። “የአማራ ብሔእረተኝነት ይለምልም!” እና “ኢትዮጵያኒስት የአማራ ትግል እንቅፋት ነው!” የሚሉ ሰዎች ዐስተሳሰባቸውን ቆም ብለው በመርመር ለዐመሓራ ተጋድሎ ግብና ዓላማ ተቃራኒ የሆነ ሚና ከመጫወት ቢታቀቡ ለትግሉ ይበጃል።
ዐመሓራ ታገድሎ ግብና ዓላማ ደጋፊዎች በሙሉ በንግግሮቻቸው የትግሉን ግብ፥ እሤትና የወደፊት የትውልድ ተስፋ ያገናዘበ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።
ንግግሮች፥ መልዕክቶቸ፥ አደረጃጀቶች፥ ተግናራዎ የምርኮኛ አያያዝና ወንድማዊነት፥ የፕሪፓጋንዳ ይዘቶች ሁሉ ከርእዩ፥ ከሚመኛት አገርና የወዲፈት የሕዝብ የጋራ ዕጣ ጋር የተናበቡ መሆናቸውን በማረጋገጥ ለቁማርተኛው የህወሃትና የኦነግ/ብልጽግና የማያባራ በጥላቻና በሐሰት ላይ የተመሠረተ ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ይኖርበታል። በመሆኑም በአስተሳሰብ መዛባትና በትውልድ በብሔር ፖለቲካ መበከል የመጣውን በአስተሳሰብ፥ በፖለቲካ፥ በፖሊሲ፥ በመዋቅር፥ በትምህርት የመጣውን አጠቃላይ ጸረ-ዐመሓራ የፖለቲካ ልሂቃንና በዐመሓራ ማኅበረሰብ መካከል በቅሎ የተንሸራፋውን ባንዳነትና ከአፍንጫ አርቆ አለማስብ መቅጨት የሚችል አካሄድ መምረጥ የፋኖ ግዴታ ነው። እንደ እነ አረጋ ከበደን፤ ደሳለኝ ጣሰው እና አገኘሁ ተሻገር አይነት የሚሆን ፋኖ የሚከሰተው ፋኖ በክልልና በብሔረሰብ ስሌት የጠላቶቹን ፍልፍናና ሕገ መንግሥት ተከትሎ መሄድ ከጀመረ ነው። የፋኖ ግብም መላውን የዐመሓራ ሕዝብ መታደግና ለዐመሐራና ሌሎች ወገኖቹ የህልውና አደጋ የሆነውን ሥርዓት የሚተካ ኢትዮጵያዊ ሥርዓት እንዲወለድ ሌላውን ማኅበረሰብ ሁሉ የማስተባበር ኃላፊነትን ጥሎ አዲስ ብአዴንን ከመሆን አያልፍም።
ስለዚህ ይህ የዐምሓራ ብሔርተኝነትና “ኢትዮጵያኒስት” ከንቱና ከጠላት ለዐመሓራ የተወረወረ የእኩል እንርከስ ወጥመድ መበጣጠስ ይኖርበታል። ሰውን በመንጋነት ለመንዳት ፋሽቶችና ኮሚኒስቶች የሚጠቀሙባቸውን የፕሮፓጋንዳ ስልት መውረሰን በራስ ወገን ላይ መጠቀም ወደኋላ የማይመለስ የሐሰተኝነትና የቁማርተኝነትን ባህል የሚያወርስ የሕወሃትና የኦነግ/ብልጽግና ጎዳና እኩይ አቻ ይሆናል።
ብሔርተኝነት ለዐምሓራው ህዝብ መጥፊያው እንጂ መጠቀሚያው አይሆንም
ዐምሓራ ማለት ነጻ ህዝብ ማለት ነው። ነጻ ሕዝብ ለመባልና ለመሆን አስቀድሞ አንድ ሕዝብ ግለሰብ አባላቱን በተፈጠረበት ክብር ደረጃ ሊመለከተው፥ ሊጠብቀው፥ ሊያከብረውና ሊያስከብረው ቁርጠኛ መሆን ይኖርበታል፥ ሁለተኛ ፈትህና ርትዕ፥ እውነተኝነትና እኩልነት፥ ባለርስትነትና ጋርዮሻዊ ተስፋን በመጻነት የመጠበቅ ባህል መፍጠር ነው። ዐመሓራ በዚህ የታደለና ይህም መንገድ ለሺ ዘመናት ያሳየ፥ የጠበቀ፥ የተከላከለ፥ አዲስ ወደ ማኅበረሰቡ የሚጨሩ ወገኖችን ሁሉ ያወረስ ሕዝብ ነው። አም ህዝብ ሲሆን ሓራ ደግሞ ነጻ ማለት ነው። ሁለቱ በግዕዝ ቃል ሲገጣጠም አም-ሓራ ማለት “ነጻ ህዝብ ማለት” ነውና የደምና የአጥንት የትውልድ የቦታ የጎሳ ጉዳይ ከሆነ አዲስ ህወሓት አዲስ ኦ ነግ ከመሆን አልፎ የአምሓራውንም የኢትዮጵያንንም ህዝብ መብትና ፍትህ ጥያቄ አይመልስም።
ያው ብአዲንን መሆንና የዚህ ሚኒስቴር ለኔ ይገባል፥ የመሬት አስተዳደር ስልጣን ለጎጃም ይሰጥ፤ የገቢዎች ደህሞ ለጎ ንደር እየተባለ በህዝብ ስም እንደ አሳማ ለሆድና ለድሎት የሚኖሩ ህሊና ቢስ መሪዎችን ማውጣት ነው። በችግር ጊዜ ከመጣው ጋር ተሰልፎ የራሱን ወገን የሚወጋ ብአዴን በሕወሃት ተጠፍጥፎ ሲጋለብ ከኖረ በኋላ ሕወሃት ወደ ሰጀር ተመልሳ ለጦርነት ስተዘጋጅ ብአዴን በአብይ አህመድ ብልጽግና ተጋላቢነት ጀርባቸውን ያመቻቹ ራስ አልባ ሆዶች ተገኙ።
አሁን የተንሳውን ጫጫታ ለማስቆም ብሔርተኝነት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ለማስረዳት ተሞክሩዋል።
በጽሞና አንብባችሁ ተወያዩበት ስህተትም የመሳላችሁ በጽሁፍ ተቹት። አሁን በፋኖ የተጀመረው የህልውናና የፍትህ ትግል በአፈቀላጤና በአክቲቪስት ስሜታዊ የቃላት ውርወራ ሊመራ የማይችል ከባድ ኃላፊነትና የትውልድ ተስፋ ያረፈበት ክቡር ትግል ነው።
በዚህ አይነት ትግል የግለሰቦችን ቁንጽልና ግልብ አስተሳሰብ፥ ከውጭና ከጣለት የተዋሱትን የፖለቲካ ርእዮት በመጠቀም ዘለቄታዊ፥ ጠቃሚና ተደራሽ የድል ውጤት ማስመዝገብ አይታሰብም። በመሆኑም በእርጋት፥ ለዐመሓራ ተቆርቋሪና ዐሳቢ በመምሰል አሰናካይና ለግዜው ድል አድራጉነትን የሚያፋጥኑ የሚመስሉ ነገር ግን ውለው ሲያድሩ ለዐመሓራና ለአጠቀላይ ማኅበረሰብ ካንሸር በመሆን ከሕሃትና ከኦነግ የማይተናነስ መርዛማ አዝመራን ለትውልድ የሚያሳቅፉ ሊሆኑ ይችላሉ። መጥኖ መደቆስ ድስት ጥዶ ከማልቀስ እንዲሉ ተረጋግተን ማሰብና መተለሙ ላይ ጊዜ ማጥፋት ይበጃል። በዚህ መሠረት የውይይት ነጥቦችና መከራከሪያዎች ቀርበዋል፦
ብሔርተኝነት ምንድ ነው? ልምድ፥ ታሪክና ጥናት ምን ይነግረናል?
ብሔርተኝነት በጥላቻ እና ፍርሀት ላይ የሚመሰረት ስሜት ነው። ብሔር የሚገለጸው በነሱ እንጂ በራሱ ትርጉም የለም። የብሔር ፓለቲካ ሰላምም፤ እኩልነትም፤ ፍርህም፤ ዲሞክራሲም አምጥቶ አያውቅም። የብሐየርተኝናት መገለጫዎቹ አራት ናቸው። አራቱን የህዝብ ጥያቄዎች ሳይሆኑ እራሳቸውን በህዝብ ስም ለመጥቀም የተነሱ የነጻ አውጪ ድርጅት መሪዎች ጥያቄ ነው።
ክፍል ፪
የብሔርተኝነት መገለጫዎች
ብሔርተኝነት ስድስት መገለጫዎች አሉት። እነዚህም
፩ኛ፣ ጠላት መፍጠር
፪ኛ በብሔር እሳቤ የተለከፈ ሰውና ቡድን መልሶ ሰው መሆን አይችልም ፬ኛ ብሔርተኝነት ኢፍትሓዊ የሆነ ስግብግብና (ትልቁ ዳቦ ለኔ ይገባኛል) ፭ኛ ብሔርተኝነት ከንጉሳዊነት ነው
፮ኛ ብሔርተኛ የጠባብ አስተሳቡ ባርያ ነው
ናቸው።
እነዚህ መገለጫዎች የሚደጋገፉና አንዱ ሌላውን እያጠናከሩ ሄደው ብሔርተኛውንም፥ ጠላቴ ያለውንም ወገንና አጠቃላይ አገርን አደጋ ላይ የሚጥሉ ክፉ ደዌዎች ናቸው። በዚህ ጽሑፍ ለማሳየት የሞከርኩት የተቀደሰው የዐመሓራ የህልውና ትግል ከታላቅነቱና ከሰብአዊነቱ፥ ከታሪካዊነቱና ከኢትዮጵያዊነቱ ወርዶ ሕወሃትንና ኦነግን የመሰለ ሰው የሚበላ ከአራዊት የከፋ የቡድን ሀልዮት ሰለባ እንዳይሆን ከወዲሁ ማስጠንቀቅና “ምነው ያኔ ተናግሬቢሆን” ከሚል ጸጸት ለመዳን ነው።
ዐመሓራነት አሁን ባለው አስተሳሰቡና ግብሩ አንድነቱን ካጠናከረ ለራሱ ሳይሆን ለአፍሪካ የሚተርፍ፥ በዘመን የማይሻር የክብረ-ሰብእ፥ የፍትሐዊነት፥ የእውነተኝነት፥ የአገር ወዳድነት፥ የብዝኃ-እሤት አልሚነት እና የፍቅር እሤቶች አሉት። ብሐየርተኛ ልሁን ካለ ግን እነዚህ ፮ ደዌዎች ተረባርበው ለህልውናው አደጋ የሆኑበትን ወገኖች ባሕርይ ይወርሳል። ከእውነት፥ ከሰብአዊነትና ከፍትህ ርቆ መቼውንም ክፋትንና ክፉዎችን ድል አያደርግም፥ ራሱም ከፍቷልና።
፩ኛ፣ ጠላት መፍጠር
የብሔር ጥያቄ የግድ ጠላት መፍጠር አለበት። ብሔርተኝነት ጠላት ሳይፈጥር መኖር የሚችል ንቅናቄ አይደለም። የእሔርተኝነት እስትንፋሱ በቡድን ጠላት ላይ የተመሠረተ “እኛ” እና “እነርሱ” የሚል ነው፥ መጠጡና ምግቡ ግጭትና ጦርነት ነው፥ ባህሉና ደስታው ግፍ በመፈጸም አዲስ ትርክትና ሁኔታው እውን ማድረግ ነው። “እኛና እነሱ” በሚል ትርክት መፍጠር አለበት። ተከታይን ሁሉ “ እነርሱ” በተባሉ ቡድኖች ጥላቻና ፍርሀት ጠርንፎ በመያዝና ህዝብን የመሪዎቹ አገልጋይና አሽከር ማድረግ ግድ ይላል። ድርጅት ማለት ህዝብ ወደ ማለት ያድጋል። ድርጅትን መተቸት ህዝብን መተቸት ይሆናል። ህዝብን እኛ ከሌለን እናንተ አትኖሩም ወደ ማለት ያድጋል።
ለምሳሌ ጄ/ር ሳሞራ የኑስ “ህወሓት ማለት የትግራ ሕዝብ ማለት ነው፣ ትግራይ ህዝብ ማለት ደግሞ ህወሓት ማለት ነው” ፡ሕሃት የለም ማለት ትግራዋይ የለም ማለት ነው” በሚል የአግዚአብሔርን ቦታ በመውሰድ የመመለክ በሽታ ነው። በዚህ ፕሮፐጋንዳ “ተጨባጭ” ያልሆነውን በጠመንጃ፥ በሕግና ፖሊሲ ወደ ተጨባጭ ማሸጋገር ሲሞክሩ ላለፉት ፶ ዓመታት በሕቡና በአጠቃላይ በአሪቷ ላይ የመከራን ዝናብ አዝንመው፥ የትግራይን ሕዝብ ባርነት እንዳገቱ ሌላውን ለኦኦነግ-ኦሮሙማው ልጅና ንጉሥ ለአብይ አስረክበው አሁንም የመከራውን ሕይወት ያስገፉናል። ሳሞራ የኑስ በ40ኛ ዓመት የህወሓት በአል ላይ ንግግር ሲያደርጉ ይህ እብደት ይቅር ብለን ነበር። ትዝ ይለኛል ለበአሉ ላይ እንዲያሽቃብጡ ካኪ ተሰፍቶላቸው ወደ ትግራይ የተወሰዱ እነ ሰራዊት ፍቅሬ እና ብዙ አርቲስቶች ነበሩ። ከእነርሱ መሀል አስቴር በዳኔ ብቻ ነበረች የሳሞራ የኑስ ንግግር ህሊናዋን የቆረቆራት። ይህ ንግግር “ምን ማለት ነው” ብላ በድፍረት ጄኔርልሉን የጠየቀችው!
በወቅቱ በጭለማ ውስጥ ትንሽ ህሊና ብልጭ ስትል በአስቴር በዳኔ አየን። አሁን የትግራይ ህዝብአና ጀነራል ሳሞራ አንድ እንዳልሆኑ ታየ። እሳቸው ባለ ሁለት ሺ ካሬ ሜትር ቪላ ተሰጥቷቸው አንድ ቀን ስለህዝቡ ችግር ትንፍሽ አላሉም። ህዝቡ ደግሞ በረሀብና በጥይት ለሁለት ዓ መት ተቆላ።
እሳቸው ከበሩ ህዝቡ ደግሞ እጅና እግሩ አስ ቆርጦ ህጻነት ልጆቹን ቀብሮ በየ ስታድየሙ በጅምላ ማቅ ለብሶ መርዶ ሲነገረው ሳሞራ ለቅሶ እንኳን አልደረሰም ። የብሔር ወኪሎች በብሔር ስም ማስፈረረትና መጠቀም እንጂ በህዝብ ጋር አያለቅሱም።
ብሔርተኝነት ሁሌም “እነሱ” መጥፎ “እኛ” ደግሞ ጥሩ፤ ተበዳይ፤ተጨቋኝ በሚል እሳቤ ላይ ነው የሚቆመው። አዳጊም ተለዋጭም አይሆንም። በኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ ስነልቦና የተቀረጹ ጠላት ብለው የመደቡ ሰው ሲለወጥ እነሱ ግን መለወጥ አልቻሉም። ሰው ከልቡ እየደገፋቸው፤ እኔ ልሙትልህ እያላቸው እነሱ ግን የደገፋቸውን “እነሱ” ለማረድ ቢላ ሲስሉ ነው የሚያነጉት።
ለምሳሌ ላስረዳ። ኦፒዲኦ መሪዎች እነ አብይ አህመድ አሊ እና እነ ብርሀኑ ጁላ በህወሓት ተማርከው ዐመሓራ ጠላትህ ነው ተብሎ ነው የተደራጁት ። ይሁንና የዐመሓራው ህዝብ አብይ ሺ አመት ንገስ ብሎ ቢደግፍም እነ አብይ አህመድ እነ ሽመልስ አብዲሳ ውስጥ ያለው ጥላቻ ከድንጋይ የደነደነ ስለሆነ መለስለስ አልቻለም። ይልቁንም አብይ ድጋፍ የሰጠውን ህዝብ ማሳደድ አጠናክሮ ቀጠለ። የእኛና የእነርሱ ትርክት እስረኛነት የሆኑትን የነ አብይና የነ ብርሁኑ ጁላ እራሳቸውን ከእስር መፍታት አልቻሉም፤ መፍታትም አይችሉም።
የሚገርመው ግን ብሔርተኝነት ጥላቻ ነው የሚያስብለው አብይ ለምሳሌ ኦሮሞም አይደለም። የጃዋር ደጋፊዎች ንጹህ ኦሮሞዎች ነን ለሚሉት አብይ “ዲቃላ” ነው። የእንግሊዛዊው ጸሀፊ ቶም ጋርድነት የተባለው ጸሀፊ ደግሞ ባደረገው ጥናት የአብይ የዲቃላነትም ንክኪ አይሰጠውም። እንደውም አህመድ አሊ አብይን አሳደጉ እንጂ የአብይ አህመድ አሊ ልጀ አይደሉም። አባታቸው ስልጤ ወይንም ኤርትራዊ ሳይሆኑ አይቀሩም ብለው በቅርብ የሚያውቁት ነገረኝ ብሎ ጽፏል። (“The Abiy Project: God, Power and War in the New Ethiopia” by Tom Gardner.)። አቶ አህመድ ኢሊም ከልጆቼ ሳልለይ ነው ያሳደኩት ብለው ቃለ መጠይቅ አሁን ስናስበው ልጄ አይደልም ማለታቸው ነው። የሚገርመው ደግሞ የአብይ አህመድ ልጆች ደግሞ እንግዲህ ኦሮሞነት የለባቸውም። እነ ሽመልስ አብዲሳና አነ ጃን ማሮ የሚያርዱት ጠላት ተብሎ ከተዘመተበት ከዐምሃራ ነገድ ናቸው። ይሁንና አብይ በ16 ዓመቱ የተጠመቀበትን የጥላቻ መንፈስ መፋታት አልቻለም። ስለዚህ ለልጆቹ የሚታረዱበትን ስርአት እየፈጠረ ነው።
ብሔርተኝነት መኑሴና ጳጳስም አይመርም። ህሊናን የማሳውር አቅሙ ከፍተኛ ነው፤ እግዚቸብሔርንም ያስክዳል፥ ዘረኝነትን ከሃይማኖት ይበልጥብናል ያሰኛቸው የትግራይና የኦሮሚያ የብሔር መነኮሳት ሲነዶስ ለመበተን ለአብይ አህምድና ጌታቸው ረዳ ሲላላኩ ታይተዋል። በመጨረሻም “አባ” ሠረቀ-ብርሃን፥ የአሁኑ “አቡን” ሰላማ በአደባባይ “የትገራይ የመከራ ምንጭ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጋብቻ ከትግራይ ንጹህ፥ ኦሪጂናል፥ ኦረጋኒክ ዘር ጋር ያዳቀሉት ዲቃላ መኖሩ ነው” ብለው ሰበኩ። በክርስትናው ከወንድና ከሴት ወይንም ከሥጋና ከደም መወለድ ሳይሆን አዲሱ፥ የዘላለም ሕይወት የሚያሰጠው በጥምቀት ከሥላሴ መወለድ ነው የሚለውን ትምህርት በሕወሃት የፖለቲካ ርእዮእ ተኩት።
በተመሳሳይ እነ ሳዊሮስ፥ ገብረ ማርያም ነጋሳ፥ በላይ መኮንን፥ አዊስታጢዎስ፥ ዜና ማርቆስ፥ ዋሲሁን አመኑ፥ ኃይለ ሚካኤል፥ አፈወርቅ፥ ወዘተ የተባሉ የሐሰት ካህናትና ክርስቲያኖች በቋንቋ አገልግሎት ስም የኦነግ- ኦሮሙማ ፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለምን የሚደግፍ አዲስ “ኦርቶዶክስ” የተባለ ሃይማኖት ለመፍጠር ተንቀሳቅሰው ትውልዱን ክህነትና እምነት በሌላቸው ዋለጌዎች እጅ አስገቡ። ሃይማነተ አበው፥ የሶኖደሳዊ ሥርዓት ውርርስና የቀደምት አበው ውግዘት ሁሉ ከሽመልስ አብዲሳና አብይ አሀምድ ቃል አንሶ ታያቸው። ብሔርተኝነት እንዲህ ነው። ሂትለርንና የተከተሉት የጀርመን የዘመኑን ክርስቲያኖች ስሕተት መዘንጋት ሁለት ጊዜ በእባብ እንደ መነደፍ ያለ ታላላነት ነው።
፪ኛ ሁለተኛው በብሔር እሳቤ የተለከፈ ሰው መቀየር እጅግ አስቸጋሪ መሆኑን ታሪክና ልምዳችን ያመለክታል። ለምሳሌ ከስሜትና ወቅታዊ የፕሮፓጋንዳ ትርፍ የሚያሰጡ አስተሳሰቦችና የመንጋ ፖለቲካ በመውጣት የህወሓትን አነሳስ እና ውድቀት በጥንቃቄ በማጤን ብዙ መማር ይቻላል፥ የትግራይን ሕዘብ ከደርግ ነጻ አወጣሀለሁ በሚል 17 ዓመታት ማገደው፥ ደርግ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ብቻ እንዳልነበረ በመሰወር፥ በደርግ ላይ ዐሓራ ገዥ መደብ የሚል ጠላት ደርቦለት አሰከረው፤ ከዚያም ማእከላዊውን መንግሥት ተቆጣጥሮ በሚችለው መንገድ ሁሉ ለምሳሌ በወሊድ ቁጥጥር፥ በበሽታ በማስጠቃት፥ ርስቱን ቀምቶ ለሌሎች በማከፋፈልና በማፈናቀል፥ በትምህርትና በመሠረተ ልማት ወደኃላ በማስቀረት፥ በተጫሩ ጦርነቶች ሁሉ ከፊት በማድረግ፥ በማደኸየት፥ ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጥቃት አንዲፈጸምበት አመራር በመስጠት 27 ዓመታትን ፍጅት ፈጽሞበት ጽዋው ሲሞላ በሕዝብ ቁጣ ወደ መቀሌ ተመለሰ። ህወሓት ዳግም ስልጣን ለማስመለስ ዘመቻ ሲጀምር ሊቀልበው፣ ሊደብቀው፣ ሊያበላው፣ ሊያጠጣው፣ ሊያሻግረው የሚችለውን መኀበረሰብ በጠላትነት መመደቡን መተው አልቻለም።
የ27 ዓመቱ ግፍ አልጸጸተውም፤ ለጊዜአዊ ድል ይጠቅመኛል በሚል ስሌት ስንኳ ጥላቻውን መሰወር አልቻለም። ከዚህ የምንማረው የብሔርተኝነት የማይፈወስ፥ ወደ አእመሮ በሽተኝነት የሚያድግ የቢድን እብደት በመሆኑ አይፈወሰም።
ብሔርተኝነት ንስሐ፥ ይቅርታ፥ ካሣ አያውቅም። ብሔርተኝነት ስሜታዊነት እንጂ ምክያታዊ አይደለም። ስልጣን ላይ እያሉ አብይ ትግሪኛ ተናገረ ብለው ተደስተው አብይን ከተራ ወታደርነት ከሥር ውጭላላኪና ጆሮ ጠቢ “ኮነሌል” አደረጉት። ትልቁን የስለላ ተቋም እንዲመራ ያደረጉት ኮለኔል አብይ አህመድ አሊ ትግሪኛ በመናገሩ ብቻ ነበር ። ይህ ለመጠቀሚያነት በዘረኝነት ስሜት ያሳደጉትና ህሊና የሚባል የሌለው አብይ ነው ጦር የላከባቸው። ሰረዊቱን የሚመራው ማርከው ለአገር ባለማሰባቸው ምክንያት የሚታዘዝ ውሻ እናደርገዋለን በሚል ያለአቅሙ ጀነራል ያደረጉት ብርሁኑ ጁላ ነው። አየር ሀይሉን የሚመራውና የትግራይት ወጣት በድሮን ሲፈጅ ትንሽ እንኳ የማይሰቅቀው ያሳደጉት ይልማ መርዳሳ ነው። ፉዴራል ፓሊስን የሚመራል እና የትግራይን ሰው እየለቀመ የሚያስረው ከኤርትራ አባት እንደሚወለድ እያወቁ ኦሮሞ ነህ ብለው ያሳደጉት ደመላሽ ነው።
ብሔርተኝነት ምክንያታዊ ቢሆን ኖሮ ሕወሃት በጦርነቱ ሂደት በመቶዎች ኪሎ ሜትሮች ርቀት አቋጦት በመሀከሉ ሊያቋርጥና አዲስ አበባ ለመድረስ የሚፈቅድለትን ህዝብ በጥይት እየደበደበ፥ ሰብሉን እያቃጠለ፥ ሴቶቹን እየደፈረና እየሰደበ ጠላት ከማድረግና መልሶ ከመወጋት ይቆጠብ ነበር። ብሔርተኝነት ምክንያታዊ ቢሆን ኖሮ ጀነራሎች ነን የሚሉት እነ ጻድቃ ን፤ ምግበና፤ ታደሰ ወረደ፥ የፖለቲካ አዋቂና መሪ ነኝ የሚለው ጌታቸው ረዳ፥ የደኅንነት አውቀት አለው የሚባለው ጌታቸው አሰፋ በአንድነት ሆነው መክረው ከማይጠቅማቸው ንግግርና ድርጊት በመቆጠብ፥ ጎረቤቶቻቸውን ይቅርታ ጠይቀው፥ ስሐዑት የክልልና የዘረኝነት ህልማቸውን ትተው፥ አንድ ላይ እንተባበርና የቀደመውን ስህተታችንን በማረም ታላቋን አገራችንን እናድን ብለው ከአማራው፥ ከአፋሩ፥ ከኦሮሞው ሁሉ ውስጥ ለውስጥ ጨርሰው ጦርነቱን በቀላሉ በጥቂት ሰብአዊና ቂሳዊ ኪሣራ ይጨርሱት ነበር። የ50 ዓመት ወነጀልና ኃጢአታቸውንም ያጥቡት ነበር። እነርሱ ግን “ከአማራ ልሂቃን ጋር ገና የምናወራረደው ሂሳብ አለን” ይሉ ነበር።
ጭራሽ ለነ ሰለሞን ተካልኝ ዴንቨር ላይ ኮንሰርት ጠርተው “በለ ው በለውና አሳጣው መድረሻ፤ የሰው ልክ አያውቅም አማራና ውሻ አስባሉ”። ይህ የብሔርተኝነት ብልግና ወደ እገር ኳስ ተጫዋቾችና ስፖርተኞች ሁሉ ተጋብቶ የክልሉ ቡድን ወልዲያ ለጨዋታ ከተማ ሲገባ ሕዝቡን እየሰደበ፥ ሽንቱን በላስቲክ ኮዳ ቀድቶ መኪና ላይ በመሆን መንግድ ዳር በሚሄዱ የከተማ ሰዎች ላይ “ሓድጊ” እያለ እያርከፈከፈ ብጥብጥ በማንሳት በሰላም አብረው በሚኖሩ ወገኖች መካከል የማንነት ግጭት አስነሱ።
አስፖረት ለሰላም፥ ለወዳጅነት የሚል መሪ ቃል ቢለጥፍም ብሔርተኛ በሽታው የሚለውን መልካም ነገር በተቃራኒ ድርጊቱ ያበላሸዋል። ጸረ-ሙስና ኮሚሽን መሥርቶ ሙስናን በሕጋዊነት ለወገኑ ያመቻቻል፤ የሰላም ምንስቴር መሥርቶ የሰላም ምልክት የሆኑ የሃይማኖት ሰዎችን በጎሣ ከፋፍሎ ደም ያፈሳል። በሽታው ጥልቅ ነው።
ለዚህ ነው ብሔርተኝነት መጀመሪያ የሚገለው ምክናያዊነትን ነው የሚባለው። አንዲህ ከሆን የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም የሚሉ ወትዋቶች ሌላ የአንድነት፥ የጥንካሬና የትግል መርህ ማመንጨት ተስኗቸው ከጠላት መርዝ ተውሰው ዐመሓራን ኢምክኒኣተዊ አራዊት ሊያደርጉት ይፈልጋሉ። በእርግጥም እነዚህ መካሪዎች ምናልባት በበሽታው አስቀድመው የተለከፉ ሊሆኑ ይችላሉና እነርሱን ሰምቶ የሚተገብር ሰው ራሱን ከሚያጠፋ ይቆጠራል።
ሕወሃት ያሐለጠናቸው ሠራዊቶችና መሪዎቻቸው በሚያልፉበት መንገድ ላይ ያለው ህዝብ ቢቻል እንዲደግፋቸው ባይቻል ደግሞ እንደ ጠላት እንዳያያቸው ማሰብ እንዳይችሉ የተለከፉበት የእሔርተኝነት በሽታ አእምሮአቸውን ተቆጣጥሮታል። ከአንረሱ ውጭ ያለ ሰው ሁሉ በተፈጥሮው ከእነርሱ ያነሰ፥ ክብር የማይገባው፥ የሚሸኘፍ፥ መጥፋት ያለበት፥ ርካሽ ይመስላዋል።
ብሔርተኝነት ጭፍን ስሜታዊ ስለሚያደርግ በመሃሉ ጦርነት እያደረጉ ስንኳ ያንንኑ የተለምደውን ጸረ አምሓራ ዘፈን ለቀቁት።
እነ ጌታቸው ረዳ የትግራይን ህዝብ ወክሎ “ከአማራ ልሂቃን ጋር ሂሳብ የምናወራርዳለን” በማለቱ ሕወሃትን ለማስደሰት የሄደበት የብሔርተኝነት ርቀት ነበር፤ ዛሬ ግን ራሱ አቶ ጌታቸው ረዳ የራያ አማራ ተብሎ ሲዋረድ በዓይናችን አየን።
‘አባ’ ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙዔል የተባሉ ብሔርተኝነት ክርስትናቸውን የነጠቃቸው የሐሰት መነኩሴ “ትግራይን የበጠበጠ የአማራ ዲቃላ ነው” ሲል ጌታቸውን ይመለከተዋል።
እነ ገብሩ አሽራት፥ ሴኮ ቱሬ፥ ዛዲክ አብረሃና ሌሎች ከአማራና ከኦሮሞ፥ ከአፋርና ከሌሎች የሚወለዱ ናቸው፥ ነገር ግን የሠሩት ስሕተትና አጥፊም እንኳ ቢሆን ዓላመውን ተቀብለው ከሕወሃት ጋር የታገሉና የመሩ ሰዎች ነበሩ፤ አሁን ግን ብሔርተኝነት ወደ ደምና አጥንት ቆጠራ እየወረደ ሲሁድ ዲቃላ ተብለው የደም ጥራታቸው የሚያግልላቸው ሆነ። እንደውም አስፋ ጀለታ በጻፈው መጽሐፍ የመጀመሪያው የወያኔ አመጽ ከትግራይ ጋር ምንም አይገናኝም የራያ ኦሮሞ ጸረ አምሓራ ትግል ነው ብሎ ጻድቃንና ጌታቸውን ኦሮሞዎች አድርጓቸዋል። ይህን በሕይወት የምናውቀውን የብሔርተኝነት ሂደት ስንመለከት የብሔርተኝነት ጤናማ የለዉም። እሔርተኝነት ሰብአዊነትን፥ ፍትሕን፥ እውነትንና አገርን አያውቅም።
ለዚህ ነው ዐመሓራነት ወደ ብሔርተኝት አዘቅት እንዳይወድቅ የንቃ ደወል መደወል የፈለግሁት።
እንደ ምሳሉ፡ በዐመሓራ ጠላትነታቸው የተጋቡ የሕወሃትና ኦነግ ብሔርተኝነትን ወደ ዐመሓራ የማጋባት ሙከራ
ነጋዴ ለራሱ ስለከሰረ ሳይሆን ጎረቤቱ ከመክሰር ስለተረፈ ይንገበገባል ይባላል። ይህ ምቀኝነትና ክፉ ራስን ችሎ ያለመኖር የስነ ልቦና ደዌ ነው። ሕወሃትና ኦነግ የፖለቲካ ሀሁ እና ፍልስፍና ወይንም ዕውቀት፥ ወይንም ታሪክ ሲጀምሩ “ዐመሓራ እንዲ አድርጎን” ብለው ነው። ጠቃሚ ዐሳብ የላቸውም፤ ዜጎችን ሁሉ በእኩልነት፥ በሰብአዊ ክብርና ፍትሕ ዋስትና የሚያገለግል አንድ መሥመር ስንኳ ፍልስፍና መጻፍ ያልቻሉ የ50 ዓመት ዘገምተኛ የአእምሮ ሕጻናት ናቸው። ድውይ ናቸው።
እነዚህ ድውያን የሚጠሩበት ፖለቲካ ስሙ “ብሔርተኝነት” ነው። ዐመሓራነትን በዚህ መጥራት ወንጀልም ኃጢአትም፥ የፖለቲካ ሞትም ሆኖ መቆጠር አለበት። ምክኒያቱም ዐመሓራ የማኅበረሰብ ጠላትን አጀንዳ አድርጎ፥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከባእዳን የአገሪቱ የረዥም ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶችና የጂኦ ፖለቲካ ባላንጣዎች ጋር ተማክሮ አይደለም። የዐመሓራ ንቅናቄ የህልውና፥ የሰብአዊነት፥ የእውነትና የእኩልነት ነው። ጠላቶቹም የታወቁ ናቸው፦
✔ ዐመሓራን እንደ ማኅበረሰብ ከኢትዮጵያ ምድር ለመፋቅ የጥላቻ ርእዮተ ዓለም አመንጭተው ወይንም ከናዚ ፍልሰፍና ተውሰው፥ ሐሰት ተርከው፥ ሠራዊት አሠልጥነው፥ መንግሥታዊ መዋቅር ዘርግተው እያጠፉት የሚገኙ ድርጅቶች ናቸው
✔ ይህን ፕሪጄክት የሚያገለግል ማንኛውም መዋቅር፥ ኢፍትሓዊ ድርጊት፥ በባህል ስም ተደራጅቶ ደም የሚያፈስስ ማኅበራዊ ሥሪት፥ ጥላቻን የሚያሰራጭ የትምህርት ይዘት፥ “ነፍጠኛን አርድልሻለው” የሚል ዘፈንና መዝሙር (ኪነ ጥበብ)፥ ካህንና ዐመሓራን ካልሰዋ ለሚያመልከው አምላኩ ጸሎት ማሳረግ የማይችል እምነት መሰል የዘር ማጥፊያ ስብከት ሁሉ ናቸው —
✔ከዚህ ውጭ እንደ ኦነግና ሕወሃት ዐመሓራ የማኅበረሰብ፥ የቋንቋ፥ የባህል፥ የአሠፋፈር፥ የኢኮኖሚ፥ የቅርሥ፥ የፊደል፥ የሃይማኖትና ባህል ጠላት የለዉም። የሚያደርሰውና የሚሠራው አዳዲስ ሪፐብሊክም የለዉም። ሌላውን በማጥፋት፥ በማፈናቀል፥ ዲሞግራፊ በቀየር፥ በመግደልና በማሳደድ ነጻ የሚያወጣው ልዩ ወገን የለዉም።
ሕወሃትና ኦነግ በዘር ትንተና ሀልዎታቸው የተለያዩ ቢሆኑም ዐመሓራን በመጥላት ርእዮተ ዓለማቸው የአንድ እናት ልጆች ይመስላሉ። ወለጋ፥ አርሲ፥ ሸዋና በመላው ኦሮሚያ በአብይና በሽመልስ ይሁንታ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስቲያንን የሚያፈናቅሉና የሚገድሉ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የኦሮሚያ መንግሥት አማጽያን አስመስሎ ጫካ ያስቀመጠው አራጅ ከኤርትራ ሲመለስ በስበሀት ነጋ የሕወሃት ነፍስ አባት ምሳ ተጋብዞና መመሪያ ተቀብሎ፥ እንዲሁም ኦሮምኛ ተናገሪ የሕወሃት አሠልጣንና አማካሪ ተመድቦላቸው ነው የመተሰማሩት።
ከዚህ መማር ያለብን ለነጻነት፥ ለሰብአዊነት፥ ለፍትሕና ለዘለቄታዊ ሰላም የሚታገል ፋኖ ራሱን በዚህ የብሔርተኝነት በሽታ እንዳየስለክፍ በጊዜ መጮህ ለዐመሓራ ሕዝብ ህለውና ታላቅ አገልግሎት ነው።
እነ ጌታቸው ረዳ ፤ ስታሊን እና እነ አሉላ ሰለሞን ዘመቻቸውን ጸረ ዐመሓራ ቅዱስ ጦርነት ወደሚል አደገኛ የዘር ማጥፋት ድብቅ ይሀወሃት ርእዮትና ፖሊሲ መሆኑን በስሜት ከፍ አድርገውት ነበር። ስታሊን ገብረ ሥላሴ የወያኔ ግስጋሴ ትዕግሥቱን ስለተፈታተነው የደበቁትና በአንደበት የማይናገሩትን፥ ነገር ግን ሥልጣን ይዘው በተግባር ሲፈጽሙ የኖሩትን ኢትዮጵያን አፈራርሰው፥ ዐመሓራን በኦነግ/ኦፒዲኦ ትብብር ወደ አናሳነት አውርደው ጎንደርን ከፊል፥ ቤኒሻንጉልን አስከነ ታላቁ ግድብና ሕዝቡን የሳሳሱትን ጋንቤላን አጠቃለው ታላቅ የትጋራይ ሪፐብሊክ የመመሥረት ሂደታቸውን እንዲህ ሲል ሚዲያ ላይ ተፋው፦ “የእኔ ተውልድ የሚኮራበት አንድ ታላቅ ነገር ቢኖር በወሬ ሳይሆን በተግባር ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ማየት ነው፥ የእኔ ትውልድ በዚህ ይኮራል” ሲል ነበር።
በዚህ የጥላቻ ቅስቀሳ ምክንያት በመጀመሪያው የህወሓት ዘመቻ ያልተዘጋጀው የዐምሓራ ገበሬ ተጨፈጨፈ፤ ሴቶች ተደፈሩ ከብቶች ሳይቀር ተረሸኑ። ከዛ እራሳቸው በብሔርተኝነት ጠላት አድርገው የቀስቀሱት ዐመሓራው ተመልሰው ሲመጡ እሾህ ሆኖ ጠበቃቸው። እነ ይታገሱ እሸቴና አባቱ እሸቴ ሞገስን የቀሰቀሳቸውና ክላሻቸውን ይዘው በቤታቸው የጠበቁዋቸው በህወሓት በሚለቀቀው ጸረአምሓህራ ፕሮፓጋንዳ እና ነውረኛ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ነበር። ስለዚህ ብሔርተኝነት ያለ ጠላት የማእፈጠር፥ ያለ ግጭትና ጦርነት የማይተነፍስ፥ ከጥላቻ ውጭ ውሎ ማድር የማይችል ከሰብአዊነትና ለአመክንዮ ጋር የተፋታ የድንቁርና ሁሉ ቁንጮ ነው።
የዐመሓራን ሕዝብ ከታወቀው የቅርቢን ብቻ ብናሰብ በ50 ዓመታት የግፈኞች ግርፋት ተፈትኖ ሰብአዊነቱን፥ ፍትሐዊነቱን፥ እውነተኛነቱን፥ እና ርቱዕነቱን ያስጠበቀ የዐመሓራነትን ክብር “የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም”በሚል አማራን ወደ ሕወሃትና ወደ ኦነግ-ብልጽግና አይነት የድንቁርና አዘቅት ለማውረድ የሚደረግ ሙከራ መቆም ይኖርበታል።
ዐመሓራ እነዚህን በሐሰት፥ በውረኝነት፥ በክህደት፥ በኢሰብአዊነት፥ በቁማርተኝነት፥ በሌብነት፥ በደም አፍሳሽነት ተመሥርተው የሚኖሩ የብሔር ድርጅቶች የደቀኑበትን የህልውና አደጋ ቀልብሶ “ሰውነትን” ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የግንድ እነርሱን መምሰል አይጠበቅበትም፥ ኢትዮጵያኒስት በሚል አፍራሽና የጠላት ወጥመድም መጠለፍ ግዴታው አይደለም። ከሰብአዊነትና ከፍትሕ፥ ከእውነትና ከፈጣሪው ሳይለይ የሚጠቀምባቸው በቂ የስነ ልቦና፥ የማኅበራዊ፥ ባህላዊ፥ ሃይማኖታዊ፥ ታሪካዊና ጸጋዎቹ ሳይቃረን ጠላቶቹን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን እነርሱም ከድል ማግሥት ራሳቸውን ፈትሸው ወደ “ሰውነት” እሤት ለመመለስ የሚያስችለው ትጥቅ አለው።
የዐማራን የህልውናና የፍትሕ ተጋድሎ ለመደገፍ ከምሁራን ምን ይጠበቃል?
ምሁራን የማሰላሰል፥ ዓለም አቀፍ ልምዶችን ዳስሶ የመቀመር፥ በተውሶ የማይፈቱና አገራዊ ፈጠራ የሚሹ ኢትዮጵያዊ እና በተለይ ዐመሓራን የሚመለከቱ አዳዲስ ጠቃሚ ዐሳቦችን በማመንጨት የፋኖን ተጋድሎ መደገፍ ነው። ድጋፉ ምን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባውም በጥለቀት ተወያይቶ መንገድ ማሳየት ነው። ለምሳሌ ፋኖ ጸረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችን ካሸነፈ በኋላ ሕዝቡ አንዴት ይኖርል፥ ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር የሚኖረው መስተጋብ ምን መምሰል አለበት? ክብረ-ሰብእ፥ ፍትህ፥ እኩልነትና መታመመን ብሎም መወሐድ የሚፋጠነው እንዴት ነው? ትግሉ ብዙ ኪሣራ ሳያደርስ እንዴት ይጠናቀቃል?
ለ፶ ዓመታት ከብበው ጨቋኝ፥ ዘራፊ፥ ወረሪ፥ የታሪክ ዘራፊ፥ የኋለቀርነት ምክንያት ወዘተ ተብሎ ተሰይሞ ግፍ ሲፈጸምበት የኖረው ዐመሓራ ራሱን ለመከላከል ሲነሳ ከደረሰበት ሁለገብ ግፍ አንጻር ቁጣው ከወሳኝ ማንነቱ ማለትም ከሰብአዊነት፥ ፍትሐዊነት፥ እውነተኝነት፥ በዓለ አገርነትና የመወሐድ እሤቶቹ ተንስፈንጥሮ በመውጣት “የዐመሓራ ብሔርተኝነት” ወደሚባል እና ጠላቶቹን ወደሚያስመስለው ደረጃ እንዳይወርድ ምን አይነት መሰባሰቢያ ይሰየምለት? ወዘተ ላይ ጠቃሚ መንግድ ማሳያ ብርሃን መፈንጠቅ ከምሁራን ይጠበቃል።
ከምሁራንና አዋቂዎች የሚጠበቅ ዐመሓራ የግድ እንደ ጠላቶቹ ሰብእናው ሳይዋረድ መልካም ጸጋዎቹን እንዴት አቀናጅቶ፥ ወደ ጽኑና ግልጽ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ርእዮት ዓለም አሳድጎ ይጓዝ የሚለውን ቀመር ማምጣት ነው። ከዚህ ውጭ ውስኪ እየጠጡ፥ የኳስ ጨዋታ ይመስል የጦርነት ድልና ሞት በሚዲያ እየተመለከቱ በተመቻቸውና በነሸጣቸው ጊዜ ሁሉ ወደ አፋቸው እንዳመጣላቸውና ቀድመው በትምህርት ወይንም በንባብ ስም የባእዳን አስተምህሮ ውቅር መሆናቸውን ባለማስተዋል ለጠላት የሚጠቅም ነገር ግን የትግሉት ወደ ድል መደራረስ ፍጥነትና ከድል ማግሥት የሚጠበቀውን ፍትሓዊ የሁሉም የሆን አገርና አንድ በብዝኃነቱ የሚመጋገብ የፍቅር ሕዝብ እንዳይፈጠር ጋሬጣ ማሰቀመጥ ይቁም እላለሁ።
ፋኖም ይህን የማይጠነቀቁ ልሂቃን፥ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ጥሬና ብስል የሆነ መልዕክት ይቃወም። ለምሳሌ በደጋጋሚ የሚነገሩና ወጥ ትንተናና ትርጉም ያለተሰጣቸው አነጋገሮች፦
❖ የዐመሓራ ብሔርተኝነት ይለምልም (ይህ ቃል የሕወሃት አገርለጋይ ብአዴን ይጠቀምበት ነበር፥ ቀጥሎ አብን አሰማው)
❖ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ
❖ መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ
❖ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
❖ አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ — ወዘተ
እንድምታቸው በብዙ ዘርፍ ተፈትⶄና ተመክሮበት የሚወጡ መሆን አለባቸው። አባባሎቹ የአማራን ሕዝብ ምን አይነት አዎንታዊና አሉታዊ ስነ እቦና ያሰድሩበታል፥ ለተቀረው የኢትዯጵያ ማኅበረሰቦች በተለይ ሕወሃትና ኦነግ ለ፶ ዓማተት በዓማራ ጥላቻ ያሳወረው ትውልድ ምን ትርጉም ይሰጠዋል፥ ጠላት ምን አይነት ለፕሮፓጋንዳ የሚጠቀምበት አሳሳች ትርጉም ሊሰጠው ይችላል? ለኤርትራ፥ ለሱዳን፥ ለኬንያና ሱማሌ ጎረቤቶቻችን ምን መልዕክት ያስተላልፋል? የጂኦ ፖለቲካ ተዋንያኑ ምእራባውያንና አረቦቹ እንዴት አድርገው እንዲመለከቱን እነፈልጋለን? ወዘተ ተብሎ መወሰን አለበት። በሌላ በኩል ሃይማኖት ባለው ማኅበረሰብ መካከል የሚነገሩ ቃላት፥ መፈክሮችና ምልክቶች በባህልና እምነት ላይ፥ በመጭው ትውልድ ላይ ምን አይነት አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ አላቸው? በመባል ይገባል።
የታወቁና የማይፈወሱ የብሔርተኝነት ደዌዎች
፩ኛ ብሐየርተኝነት ሰላም ካለ እና ጠላት ከአጣ መኖር አይችልም።
በተልይ እንደ ብሔርተኝነት ያለ መርዝ ዝም ተብሎ አይጋበዝም።
Robert Mallett የእንግሊዝ ጸሀፊ “Mussolini never believed in perpetual peace” ብሎ የጻፈው ትዝ አለኝ። ብሐየርተኛ በዘላቂ ሰላም አያምንም። ጠላት የፈጠረ ደግሞ እንቅልፍ አይኖረውም፤ ሁሌም እየተዋጋ ነው መኖር የሚችለው። ለዚህ ነው የትግራይ ብሐየርተኞች እና የነሱ ፍጡር የሆኑት እነ አብይ አህመድ ያለ ጦርነት መኖር ያልቻሉት ለዚህ ነው። ጠላት ከሌለ እንወክለዋለሁ የሚለው መሀበረሰብ ስለመብቱ መጠየቅ ይጀምራል። አሁን በትግራይ እየታየ ያለው የመብት ጥያቄ ይኼው ነው፤ ህወሓት በፕሪቶርያው ስምምነት ሰለ ጦርነትና ስለ ጠላት መጣ መቀስቀስ የማያስችል ስምምነት ላይ በመድረሱ ሕዝቡን የሚያሳውርበትና የሚያሰክርበት መርዙ ከእጁ ላይ ወደቀ። በፕሬቶርያ ስምምነት “የጠላት መጣ” ለጦርነት ተዘጋጀ ማለት በግልጽ አንዳይነገር ስለተባል ውስጥ ለውስጥ ዝግጅት እንደሚያደርግ ቢታወቅም በአደባባይ ለሕዝቡ የሥጋት አጀንዳ እያሳየ የሚገባውን የአስተዳደርና የልማት ጥያቄ ለማረሳሳት አልቻለም። ህዝቡ ከ፶ ዓመታት ፍርሀት በኋላ ስለመብቱ መጠየቅ ጀመረ።
፪ኛ፣ ራስን ማንገሥ/Self electing፡
የእሔርተኛ ንቅናቄዎች ጠንሳሽና ትግል አስጀማሪዎች ሁሉ ራሳቸውን ካነገሡ በኋላ ሌላው ለትግሉ አንዲሰዋ ጋብዘው እነርሱ ራሳቸውን ለዙፋን አጭተው፥ ጠባቂ አደራጅተው፥ የሚገደደራቸውን እነዳይኖር እየሰለሉ፥ ለሥልጣን እስከጠቀማቸው ድረስ የተነሱበትን ግብ ስንኳ አሳልፈው የሚሰጡ ይሆናሉ። ከብሔርተኝነት ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊና ሰብአዊ ሊሆን አይችልም ።
ሁሉ ነገር ዐሳቡን በጠነሰሱት ትንሽ የቡድን አባላት እጅ ለዘላለም ተይዞ ብዙኃኑን የትርክትና የተስፋ ባርያ በማድረግ ጠላት እያሳዩ፥ ከሰረቁት ላይ ትንሽ እያቀመሱ፥ በኢፍትሐዊነት በዘረፉት ወረዳና አውረጃ መሬት ላይ እያሰጀሩ፥ የአገሪቷን የትምህርት እድል ለተወሰነ የፓርቲ ደጋፊዎችና ካድሬ እያከፋፈሉ ንግሥናቸውን ያስቀጥላሉ።
እርዳታ ሰጭ ምእራባውያንን ለማታለል የይስሙላ ምርጫ እያደረጉ ሥልጣኑን በቡድናቸው መካከል ተራ በተራ ያሽከረክሩታል። ለምሳሌ ሕወሃት ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ በትገሉ እና በእድሜ ከሞቱት ውጭ መሥራቾቹ ከፈላጭ ቆራጭነት ወንበር፥ ከንግሥናቸው ፈቀቅ ብለው አያውቁም። ወራሽ አዲስ ኃይልም ሲቀላቅሉ በራሳቸው አምሳል እየቀረጹና አእመሮውን አጥበው ነው። ስነኳንስ የሕወሃት አባል ባይቶና፥ አጋዚያን፥ ሳልሳይ ወያኔ ወዘተ ተብለው የሚፈለፈሉ አማራጭ የሚመስሉ ስብሶቦች ሳይቀሩ ከዋናው የብሔርተኝነት መርዝና ጥላቻ መላቀቅ አልቻሉም።
አንድ የህንድ ጸሀፊ Kanchan Chandra የብሔር አደረጃጀት መሪዎቹን ህዝብ ሳይሆን የሚመርጣቸው እራሳሸውን ነው የሚመርጡት ትላለች ( Self electing) ። እኔ የዚህ ህዝብ ወኪልና ጥቅም አስከባሪ ነኝ ብሎ ነው የሚነሳው። አሁን በየ ቦታው የሚጮሁትን መሪ ነኝ ባይ ብሐየርተኞች ማን መረጣቸው ? ስለዚህ ሁለም እኔ እኔ ነኝ ስለሚል አውራ ለመፍጠር መጀመሪያ እርስ በእርሱ መፋጀት አለበት። አሁን እኔ የዘመነ ነኝ እኔ ደግሞ የእስክንድር ችፍራ ነኝ እኔ የመከታው ነኝ የሚልና የመከታው የአሰግድን ቤት ወሮ ሲያባርረው የታየው የዚህ የብሔርተኝነት የጥሎ ማለፍ ትግል የብሔርተኝነት መገለጫው ነው። አሁን እረፉ ካልተባለ መጀመሪያ እንደ አህአፓና መኢሶን ወዛደር ላብ አደር ተብሎ እንደተዋጋው አሁንም ኢትዮጵያኒስትና አማራኒስት ተብሎ ሊታኮስ ይችላለ። ከዛ ደግሞ ጎንደር ጎጃም፤ ሸዋ ወሎ፤ ከዛ ወረድ ሲል ደግሞ ምንጃርና መርሃቤቴ ጠገዴና ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜን ጎንደርና ደቡብ ተብሎ ለስልጣን መዋጋት አይቀሬ ነው። የብሔር አደረጃጀት አንድ ጨቋኝ የብሔር ወኪል እስከሚፈጥር እርስ በእርሱ ነው የሚዋጋው።
በምሳሌ ላስረዳ፦ ሁለት የኤርትራ ነጻ አውጪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ 70-72 ዓመተ ምህረት አስመራን ከበው ለመቆጣጠር ደርሰው ነበር። በአቶ ኢሳያስ አፈወርቄ የሚመራው ሻቢያና በ አህመድ ሞሀመድ ናስር የሚመራው ጀበሀ በጋራ አስመራን መቆጣጠር የሚችሉበት እድል ነበራቸው። ይሁንና ለኤርትራ ነጸነት ቢታገሉም በብሔር ፖለቲካ ሁለት አውራ በአንድ ቤት አይፈቅድም። ስለዚህ የኢትዮጵያን ሰራዊት አንድ ግዜ አንተ ረጋ ብለ፤ እኛ የምንገረታ ችግር አለ ብለው እርስ በእርሳቸው መታኮስ ጀመሩ። እየተታኮሱ እየተጨራረሱ ወደ ሱዳን ድንበር ተመለሱ። የሻቢያ አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ የጀበሀውን አህመድ መሀመድ ኑርን ወደ ሱዳን መግባቱን ካዛ ወደ ሲዊዲን መሰደዱን አረጋግጠው ነው ወደ ኢትዮጵያ ጦር ጠመንጃቸውን ያዞሩት። የጀበሀ ጦር ወደ ሱዳን ሸኝቶ አንድ ብቸኛ የነጻ አውጪ ድርጅት መሪ አቶ ኢሳያስ አፈወርቈ መሆን ሲችሉ ነው አጠንክረው የታገሉት። አቶ አህመድ መሁመድ ኑር የትግሉ ጠንሳሽ በኢራን የሰለጠኑና የተመረቁ ወታደራዊ መኮንን ቢሆኑም የኢሳያስ አፈወርቄን ጦር ድል ማድረግ አልቻሉም። ከነጻነት ቦሀላም ወደ ሀገር እንዲገቡ አልተፈቀላቸውም፤ እሳቸውም አልደፈሩም። ኤርትራን ሳይረግጡ በሲዊድን ከሶስት ዓመት በፊት ሞቱ።
የትግራይ ሁለቱ ነጻ አውጪዎች
ትግራይን ነጻ እንወጣለን ብለው የተነሱ ሁለት የትግራይ ነጻ አውጪዎች ቡድኖች ከዩኒቨርስቲ ወጥተው ትግራይ ገቡ። አንደኞቹ በአብዛኛው የአዲግራት ልጆች ሲሆኑ ሁለተኞቹ ደግሞ የአድዋ ልጆች ነበሩ። እነዚህ አንድ ሆነው ወይንም ለየብቻቸው ትግራይን ተባብረው ማውጣት ይችሉ ነበር። የአድዋው ቡድን የመሀሃ ሀገር ደምና ብልጠት ስላላቸው የአዲግራቶቹን የገበሬ ልጆች አታለው የወባ መድሀኒት ብለው በመርዝ ኪኒን አስዋጥዋቸው። እነዚህ የገበሬ ልጆች ጠላቶቻቸው የሰጡዋቸውን መድሀኒት ቅመሰው ሳይሉ ዋጡ። ሰው ጠላ እንኳን ሲጋብዝ እራሱ ቀምሶ ነው። ይሁ ንና ከዩኒቨርስቲ ወጥተው ትግራይን ነጻ እንወጣለን ያሉ የገበሬ ልጆች መርዝ ውጠው፤ ተፈራግጠው አሰቃቂ ሞትን ተቀበሉ። የብሔር አደረጃጀት እስከዚህ ድረስ ለስልጣን ሲባል በራስ ወንድም ላይ የሚያጨካክን ነው። ይህ እንግዲህ በታሪክ ቢመዘገብም እንደ ስብሀት ነጋ ጨካኝነት እንጂ እንደ የብሔር አደረጃጀት መገለጫ ሆኖ አልቀረበም። አሁን በወንድማቸው ላይ ይሄንን ጭካኔ የመፈጸም ያላቸው እንደነ መከታኦው ያሉ በአምሓራው ትግል ውስጥ ብቅ ያሉ የምንጃሩን ፋኖ አደራጅ ታዴንና እና ወንድወሰንን ረሽነዋል። ይህ እንግዲህ የነ ሻለቃ ዳዊት ወደ ፓለቲካው መመለስ ከደርግ ይዘውት የመጡት የመበላላት ባህል ነው።
፫ኛ ብሔርተኛ የጠባብ አስተሳቡ ባርያ ነው
ብሔርተኞች ሲነሱ አሁን እጃቸው ላይ ካለው “ችግር ነውና መለወጥ አለበት” ብለው ከሚያስቡት ጠባብ፥ ትናንትን በስህተት፥ ነገን በባእዳን ፍልስፍና የሚመለከት፥ በነባርነት ላይ ያመጸ ንቅናቁ ነው። ጭግር ፈታለሁ ብሎ ጀምሮ ያለነበሩ አዳዲስ ጭግሮችን እየፈለፈ “ነጻ ላውጣችሁ” የሚላቸውን ወገኖች የተወሳሰብ ባርነት ውስጥ የሚጨምር ነው።
የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ነን ያሉትም እንደ ትግራይ አቻዎቻች እርስ በእርሳቸው ሲታገሉ ነው ያረጁት። ኦነግ (OLF)፣ ኢስላማዊ ግንባር ለኦሮሞ ነጼነት (IFLO) OLA- Shene፣ OLF የነዮሃንስ ለታና (ሌንጮ ለታ) የጃዋር OLF እና የአብይ OPDO ወዘተ። ሰሞኑን ደግሞ ጃል መሮና ጃል ሰኚ ተፈትተዋል። የኦነግን ጽንሰ ሀሳብ አዋለዱ የሚባሉት እነ ባሮ ቱምሳ ሳይቀር በሌላኛው የእስላም ኦሮሞ ነጻ አውጪ ነን የተረሸነው። አሁንም አራት እራሳቸውን የኦሮሞ ወኪል ነን ያሉ ኦፒዲኦ፣ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ፣ በጃል ማሮ የሚመራው ኦነግ እና በጃዋር መሀመድ የሚመራው ንቅናቄ እየተቧ ቀሱ ነው ። አንዱ አሸንፎ ሌሎቹን ሁሉ አጥፍቶ ህዝቡን ረግጦ አንድ ካላደረገ የኦሮሞ ነጻነት የሚባል ነገር ውጤት አያመጣም።
የዐሳብ አባታቸው የሆኑት መሠረታቸውን ጀርመን ያደረጉ የኦሮሙማ ብሔርተኝነት ደጋፊዎች Germenness (ጀርመንነት) ከሞለው የናዙ ጽንሰ ዐሳብ ተነስተው እንዚህን የኦሮሞ አንጃዎች አንድ ለማድረግ Oromoness (ኦሮሞነት) በሚል ሊያስሟሟቸው አዲስ አበባ ከርመው ጋዲሰ አሮሞ (የኦሮሞ ጥላ) የሚባል አንድነት ሊፈጥሩ ሞክረው ነበር፥ ግን አብይ በመጨረሻው ቀን ብቅ ብሎ ውሃ ቸለሰበት። ሁሉም ጎን ለጎን ከመሄድ ጫካና ቤተ መንግሥት ተቀምጠው አንድ መሆን አልቻሉም። ቢቸግራቸው እነ ሽመልስ ሕዝቡን ጉሬ ዙሪያ ኮልኩለው “ኢሬቻ ከሃይማኖቶች ሁሉ በላይ ሆኖ ኦሮሞን አንድ ያደርጋል” የሚል ተደጋጋሚ ንግግሮችን ከሐሰተኛ ትርከቱ የአማራ ጥላቻ ጋር እየቀየጠ ማቅብ ከጀመረ 6 ዓመት አለፈ። ይሁንና ብሔርተኝነት ለኦሮሞ ልጆች መተው የማይችሉትን ሰውነት፥ ፍትሓዊነት፥ እወነተኝነት፥ ሰው ሰው ሁሉ ሰው ነው ብሎ ማመመንን ተተውለት በአርሱ ልኬታ ብቻ በጥላቻ፥ በገዳይነት፥ በስግብግብነት፥ በሐሰተኝነት፥ በኢአማኒነት፥ በአፈናቃይነት ላይ አንድ እንዲሆኑ ስለሚጠይቃቸው አልተሳካለትም። እርሱን የሚሰሙት በእሤት የሚስማሙት ሳይሆኑ አበል የሚከፈላቸውና በብዙ ዘመን ስብከት በጥላቻ የታወሩ ሕሊና ቢሶች ብቻ ናቸው።
ለምሳሌ የአሁኑን የኦሮሞ ድርጅቶች ጥሎ ማለፏን ሂደት ስንመልከት፤ ጃዋርና ዳውድ ኢብሳ ተሸንፈው ወደ ታችኛው ሊግ ወርደዋል። ማጣርያውን ያለፏት ጃን ማሮና የአብይ ኦፒዲኦ ናቸው።
ጃል ማሮ አሸናፊ የመሆን እድሉ የሰፋ ነው። አብይ ትግራይ ተሸንፎ ለቆ ወጥቷል፣ ከአማራ ወጥቷል፣ ከልቡ የደገፈው የአዲስ አበባ ህዝብ አድፍጧል፣ ሱማሌና ግብጽ መጥተውብታል። አገር መራለሁ እያለ ምናባዊ የግል ፍተወቱን ሲመራ አገሩን ዘነግቶና ከፋፍሎ ተጋላጭ አድርጓታል። ድንበር ክፍት አድርጎ የዐመሓራ ጥላቸውን ለማርካት መከላከያውን ወደ ዐመሓራ ሕዝብ አዝምቷል።
ከሌላ አገረ ብሔርተኝነት ምን እንማራለን?
ሌላው ብሔርተኝነት ለራሱ ነጻ አወጣዋለሁ ለሚለው ህዝብ አደገኛ መሆኑን የሚያሳየው በስሪላንካ የታሚሎች የብሔርተኝነት ትግል ነው። የታሚልን ማለትም ጠቆር ያሉት ህንዶችን ነጻ እንወጣለን ብለው የተፈጠሩ ከ10 በላይ የታሚል ህዝብ ነጻ አውጪዎች ነበሩ።
Tamil Eelam Army (TEA)
እነዚህ ሁሉ ከተማሪ ንቅናቄ ውስጥ ወጥተው ታ ሚልን ነጻ እናውፕጣለን ብለ ው ጫካ የገቡ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ እስከ በእርስ ተዋግተው ነው ከተጨራረሱ ቦሀላ Velupillai Prabhakaran የሚመ
Liberation Tigers of Tamil Eelam (LTTE)፣Also known as the Tamil Tigers
Tamil United Liberation Front (TULF)
People’s Liberation Organisation of Tamil Eelam (PLOTE)
Eelam People’s Revolutionary Liberation Front (EPRLF)*
Tamil Eelam Liberation Organization (TELO)
Eelam Revolutionary Organisation of Students (EROS)
7. Tamil Makkal Viduthalai Pulikal (TMVP): A breakaway faction of the LTTE, this group was led by Karuna Amman and later became a po litical party.
Tamil National Liberation Front (TNLF)**: Another political organization that has been part of the Tamil liberation movement.
Tamil Eelam Liberation Army (TELA). A lesser-known militant group that was part of the broader Tamil struggle.
Tamil Eelam Army (TEA)
እነዚህ ሁሉ ከተማሪ ንቅናቄ ውስጥ ወጥተው ታ ሚልን ነጻ እናውፕጣለን ብለ ው ጫካ የገቡ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ እስከ በእርስ ተዋግተው ነው ከተጨራረሱ ቦሀላ Velupillai Prabhakaran የሚመ
ራው በጣም ለህይወታቸው የማይሳሱና ጨካኝ ተዋጊዎች ያ ፈራው ታሚል ታይገር ብቸኛ የታሚል ህዝብ ወኪል ሆኖ የወጣው።
የፋኖ ትግል እንዲህ ቁጥሩ በዝቶ ወደ ችግር እንዳይገባ ወይንም በአንድ ጨካኝ እጅ እንዳይወድቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው። ብሔርተኝነት ወደላይ ሳይሆን ወደ ታች ነው የሚያድገው። አሁን እያቆጠቆጠ ያለው የጎጃሜነት፤ የጎርንደሬነት፤ የወልቃይቴነት፤ የወሎየነት ስሜት በሰዎች መጥፎነት ሳይሆን የብሔርተኝነት መገለጫው ነው። ዐምሓራ ነው ያሉ የጠገዴ ወኪል ነን ሲሉ የነበሩ ፋኖ ወደኛ ከመጣ ግንባር ግንባሩን እንለዋለን ሲሉ ለሰማ የብሔርተኝነት አይቀሬ መዳረሻ እኛና እነሱን አውርዶ ወልቃይቴና ጎንደሬ ሊከፋፍል ይችላል።
ወደ ስሪላንካ ስንመለስ የሁላችንም የጆግራፊ እውቀት ውሱን ነውና በንጽጽር ላሳይ።
ሲሪላንካ ከህንድ በታች ያለሽ ትንሽ ደሴት ነች። የኢትዮጵያን 5.8% ነው የምታክለው። ይህ ማለት ከኢትዮጵያ አንድን ክፍለ ሀገር ታንሳለች። ለጨዋታው አርሲ ክፍለ ሀገር በሏት። ከሱ ውስጥ ታሚል ታይገር ገንጥዬ ሀገር አደርገዋለሁ ብለው የታገሉበት መሬት የስሪላንካን 1/3ኛ የሚሆነውን ነው ። ይህ እንግዲህ የአርሲን ሁለት ወይንም ሶስት አውራጃ በሉት። ይሁንና ይህችን ትንሽ መሬት ለመገንጠል የተነሱት 10 በላይ ነጻ አውጪ ድርጅቶች ነበሩ። ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉም ከተማሪ ንቅናቄ የወጡ ናችው።
እነዚህ እርስ በእርሳቸው ተዋግተው አንዱ የታሚል ታይገር የሚባለው የሌሎችን ቡድኖች ደምስሶ የራሱን ብቸኛ ወኪል አደረገ። ይሁንና በዚህ እርስ በእርስ ጦርነት የራሱን ታጋይ ቁጥር አስጨርሶ ዋነኛው የታሚል ነጻ አውጪ በሆነ ማግስት የቀዝቃዛው ጦርነት አበቃ። ድጋፍ ጠፋ፣ ምእራባዊያን በአሸባሪ ፈረጁት፣ ቻይና ትልቅ ወደብ ኢሪላንካ ላይ መስራት ፈለገች። ስለዚህ ታሚል ታይገርም በ ስሪላንካ ጦር ተደመሰሰ። ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎቹን ይዘው ያመለጡት ኤርትራ ገቡ። አንድ ቀን ጀልባ አስነስተን እናጠቃለን ብለው የተመኝተው ለኢሳያስ በአደራ ጀልባቸውን የሰጡ ይሄው ከጠፉ 15 ዓመት አለፈ። የ26 ዓመት የታሚል የነጻነት ትግል ውሀ በላው።
የዐመሓራውም ትግል እንዲህ እንዳይሆን እኔ የዘመነ ነኝ፤ እኔ የእድክንድር ነኝ፤ እኔ የኮለኔል ደመቀ ነኝ፤ እኔ የሻለቃ ዳዊት ጭፍራ ነን ማለቱ በአስቸኳይ መቆም አለበት።
የቤሔርተኝነት ትግል የቁልቁለት ነው የሚባለው አሁን የጎጃም፤ የጎንደር፤ ሸዋ ውሎ ከማለት ወርዲ ወልቃይቴና ጎንደሬ መባባል መጀመሩ ነውና ይሄንን ጽሁፍ አንብባቸሁ ከውልቃይቴነት ወደ ጎንደሬነት፤ ከጎንደሬነት ወደ ዐምሓራነት ከዛ ወደ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለ ደግሞ ሰብአዊነት ማደግ ነው የሚያስፈልገው። ይህ ሲሆን የ120 ሚሊዎን ህዝብን ድጋፍ ያመጣል።
ብሔርተኝነት ብዙኃኑ ሕዘብ በእርጋታ በታወቀ መሥፈርት አንዲገመግሙት አይፈቅድም። ስሜትና ወቅታዊ ነገሮችን ብቻ እያሳየ ወደ ገድል ይወስዳል። ሕወሃት፥ ተሐድሶ፥ ጥልቅ ሐሰድዎ፥ ጥልቅ ግምገማ ወዘተ እያለ መበስበሱን እንደ መታደስ እየቆጠረ 30 ዓመት አስግሞ ወደ ሰፍር ከተመለሰ በኋላ “ኦረጋኒክ እና ዲቃላ” ትግራዋይነት ወደ ሚል ደረጃ አዘቅዝቆ ታየ። የእርስ በእርስ የወረዳና የአውረጃ ቁርቋሶውን እስታግሶ የቆየው የዐመሓራን መሬቶች በመዝረፍና በመከፋፈል፥ የመሐል አገሩን ሀብት በምሰኛ ነገዳዎችና ባልሥልጣናት መካከል በመቀራመት ነበር፤ ተመልሶ ሲፋጠጥ ግን ከትግራይ ውጭ የሚያሳብበው አጀንዳ ስላጣ እርስ በርሱ መባላትን ቀጠለበት። ብሔርተኝነት ልጓምና የትክክለኝነት መመዘኛ የለውም፤ የጥላቻ ስሜት፥ ስልጣን፥ ዘረፋና ክብር ይጋልበዋል። ይህ ለዐመሓራነት አይስማም እያልኩ ነው።
እሔርተኛ ከሆንክ ዐሳብ መቀበል አትችልም። ለዚህ የኔ ለዐምሓራ ተቆርቋሪነት ካንተ ይበልጣል። እኔ ትክክለኛ አንተ ደግሞ ባንዳ ወደሚል ያድጋል። መከታውና አሰግድ ሰሜን ሸዋ ከጠበባቸው እኛም እንደ ስሪላንካ የመሆን እድላችን ሰፊ ነው።
ብሔርተኝነት ሲሆን ትግሉ ከስርዓቱ ጋር መሆኑ ይቀርና በመከታው፣ በዘመነ፣ በእክንድር ነን በሚባሉ ጭፍሮች መሀከል ይሆናል። ከዛ ደግሞ ሸዋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ አዲስ አባባ፣ ኦሮምያ ፋኖ፣ ደቡብ ፋኖ ወደሚል ያድጋል። ፋኖ ከመላው ኢትዮጵያ ከመጡ፣ ከውጪ ሀገር በመጡም ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ነው። ፋኖ ብሎ ነው የጀመረው እንጂ የሸዋ የጎጃም የጎንደር ብሎ አልነበረም። ለአደረጃጀት ከታች ወደላይ እንዲወጣ ሲደረግ አውራጃ ይዘው ከዛ ደግሞ ከፍለ ሀገር ላይ አንቀው ለማቆም የሚሞክሩ በዝተዋል።
ስለዚህ ሸዋ ከጎንደር ወሎ ከጎጃም መራቤቴ ከማጀቴ፣ መንዝ ከከሰ መባባል መጀመሩ በአስቸኳይ መቆም አለበት።
ለምሳሌ ሸዋን መርሀቤቴ ላይ የተቋቋመው ከኦሮምያ፣ ከአርሲ ነጌሌ፣ ከሻሸመኔ፣ ከመታህራ፣ ከአርሲ ወዘተ በጃዋርና ከሀጫሉ ጭፍጨፋ አምልጠው በመጡ ታጋዬች ነው። የቱለማ፣ የአዲስ አበባ፣ የአፋር የደቡብ ፋኖ በመቋቋምና መሰልጠን በጀመረበት ግዜ ነው መንግሥት ጦርነት ሲያውጅ የአዲስ አበባውም፣ የወለጋውም፣ የደቡቡም፣ የውጪ ሀገሩም ወደ ዐመሓራ ህልል ፋኖን ለማዳን ሙልጭ ብሎ የገባው።
ብሔርተኝነት ያለ ንጉስ ማለትም ያለ አንድ አንባገነን ፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ አይኖርም። ይህንን ፈላጭ ቆራጭ ለመፍጠር ፋኖ እርስ በእርሱ ተዋግቶ አንድ ረግጦ የሚገዛ ሰው መፈጠር አለበት። ምክንያቱም ብሔርተኝነት ብዝሀነትን፣ ዲሞክራሲን፣ ሀሳብ ልዩነትን፣ ሀሳብ የመስጠትን፣ የመቃወምን፣ የመምረጥን የመመረጥን መብት አይቀነልም። ይህ ቢቻል ኖሮ ትግራይ ኤርትራ የዲሞክራሲ ተምሳሌቶች ይሆኑ ነበር። ስለዚህ የዐመሓራው ህዝብ ከ50 ዓመታት ከመንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ከህወሓትና ከኦፒዲኦ መንጋጋ እላቀቃለሁ ብሎ የጀመረው ትግል በሌላ አንባገነን እጅ እንዳይወድቅ መታገል ያስፈልጋል።
እኛና እነሱ ተብሎ ነው የሚጀመረው። አሰግድ ተነስቶ ሌላ ሀይል በሸዋ ውስጥ ያለ እኛ ፈቃድ እንዲንቀሳቀስ አንፈቅድም ሲል ተው ተብሎ ነበር። መከትልው ደሳለኝን ሲያፍን ሁሉም ተረባርቦ ጮሆ ስፈታው። ምክንያቱም እንደ ታደሰ ያሉ ፋኖን የመሰረቱ ታጋዮችን መከታው እንደገደለ ሁሉም ያውቃልና። ሰሜን ሸዋ ብሔርተኝነት እንደ ስሪላንካ ነገ ቦታ አይበቃውም።
ብሔርተኝነት ከንጉሳዊነት ነው
የብሔር አደረጃጀት መገለጫ ንጉሳዊ ወይንም ጳጳሳዊ የሚባለው ነው። patriarch system. አንድ አዛዥ ናዛዥ ነው የሚኖረው። ህወሓት ለምሳሌ ሁለተኛ ሰው አልነበረውም። መለስ እኩል ድምጽ አለን ብለው ያሰቡትን እነ ስዬ አብረሀ፣ እነ ታምራት ላይኔ ሁለተኛ የሚባል ሰው በድርጅቱ ውስጥ እንደማይኖር ለማሳየት ነው ሰዬንና ቃሊቲ፣ ታምራት ላይኔን ደግሞ በቴሌቭዥን ፊት ሌባ ነኝ ያስባለው። አምላካቸው መሆኑን ለማሳየት ነው። ታምራት ላይኔ ያ ሁሉ ፍዳ ደርሶበት ሲፈታ ለምኖ ቀጠ ሮ ይዞ ገብቶ ነ አልተቀየምኩህም ያደረከው ነገር ትክክል ነበር ይቅርታ አድርጌለሀለሁ ያለው መለስ ዜናዊን ነው። ለምን ታምራት ላኡኔ ያባረሩትን እነ በረከት ስማኦንን እነ አዲሱ ለገሰን ሄዶ ይቅር አላለቸውም። የስነልቦናው መደረት የብሔር መሪ ለተከታዮቹ መሪ ብቻ ሳይሆን አምላክም ነው የሚሆነው።
ታምራት ጽድቅ ፍለጋ ከሆነ የበደልካችፕውን የገደክካችፕውን ልክ እንደ መለስ ያለ ፍርድ ያሰቃየሀቸውን ሰዎች ነው ፈልጎ ይቅርታ አድርጉልኝ ማለት የነበረበት። ስለዚህ ይህን ብሔር አደረጃጀት የሚፈጥረው አንድ እንደ አምላክ የሚታይ አንባገነን ነው የሚፈጥረው።
፬ኛ ብሔርተኝነት ኢፍትሓዊ የሆነ ስግብግብና (ትልቁ ዳቦ ለኔ ይገባኛል)
የህንድ ጸሀፊ ethnic headcount ትለዋለች። ይሄም ያ የብሐየርተኛ ድርጅት መሪ የኔ የሚላቸውን ሰዎች ራስ ይቆጥርና ከድፎ ዳቦው ትልቁ ይገባኛል የሚል ጥያቄ ነው የሚያቀርበው። ይህ ማለት ዳቦው ስልጣን እንጂ ለህዝብ የሚወርድ ሙልሙል አይደለም። ይሄንን ይሄንን ሚኒስቴር ለኔ ስጠኝ፣ ቪላው፣ V8ቱ፣ አጃቢው ጉቦ የሚበላበት ቦታ፣ መሬት የሚቸበቸብበት፣ ዘመድ አዝማዴን ቅቅታቸውን የማራግፍበት ቦታ ይሰጠኝ ነው የሚሆነው።
ሽመልስ አብዲሳ ቀፈቱ እስኪገለበጥ በበላ የቦረና ህዝብ ረሀቡና ጥማቱ አይቆረጥ። እነ ጃዋር መሀመድ የብሔር ጥያቄ የሊህቃኑ ድርድር ነው የሚሉት ተስማምተን ተከፋፍለን በህዝባችን ስም እኛ እንብርታችን እስኪገለበጥ እንብላ የሚል ጥያቄ ነው።
እነ ደመቀ መኮንን፣ እነ አገኘሁ ተሻገር፣ እነ አበባው፣ እነ ይልቃል ከፋለ ቪላ ስለተሰጣቸው መሬት ስላገኙ ለዐምሓራው ጠብ አይልለትር ም። ሁሌም የተራበ ይመጣል። እነ አረጋ ከበደ ቆዳው ከአጥንቱ ጋር ተጣብቆ የነበረው የመጣው አሁን ጉንጭ በማውጣት ለዐምሓራው ጠብ ያለለት ነገር የለም ።
አሁንም የፋኖ መሪዎችን በድርድር ወስደን የአረጋ ከበደ አልጋ ላይ ልናስተኛ የመሬት ክፍል ዳይሬክተር ለማድረግ አይደለም ትግሉ የተገባው።
አሁን ኢትዮጵያኒስት ኢትዮጵያኒስት እያሉ ጨቅላነታቸውን እያሳዩን ያሉት የፋኖን ትግል ብአዴን ቁጥር ሁለት ዛው ባህር ዳር ላይ አንቱ ለመባል የጓጉ ናቸው።
ስለዚህ ፈኖ
፩ኛ / የብሐየርተኛ፥ የጎጠኛ፣ የክፍለሀገር፤ ነጻ አውጪ ድርጅት አይደለም። ይህ ሊናፍቀው አይገባም። አመራጭ መሪ ፍልስፍና ማዋለድ እንደተሳነው የመካን አእምሮ ስብስብ የሕወሃትንና የኦነግን መርዝ ማለትም “ብሔርተኝነት ይለምልም” ከሚል የተውሶ ድንቁርና ራሱን ይጠበቅ!
፪ኛ/ የዐመሓራ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነች። ደሙን ያፈሰሰባት አጥንቱን የከሰከሰባት ምድር ሁሉ የዐመሓራ ነው። ስለዚህ በኦነግና በሕወሃት የሤራ ሕግ መንግሥት ተሰምሮ በተሰጠውና ከሌሎች ቦታዎች ዐመሓራን ለማጽዳት ምክኒያት በሆነ የአፓርታይድ የክልል አስተሳሰብ ራሱን ከሚወስን ስነ-ልቦና በላይ ወጥቶ ይታይ። እየታየ ነው፥ ነገር ግን “ብሔርተኝነት ይለምልም” የሚሉ ስንኩል ልሂቃን እንዳያሳስቱት ይጠንቀቅ!
፫ኛ/ ዐመሓራው ትግል ውስጥ የገባው በመላው ኢትዮጵያ የሚታረደው የሚፈናቀሉው የሚገደለው _ዐመሓራው፣ ጉራጌው፣ ጋሞው፣ጌዲዮው፣ ቱለማው፣ ኦርቶዶክሱ፣ እስላም ሁሉ ነው። ወላሂ ሁለተኛ ዐመሓራ አልሆንም ብላ አንጀታችንን ለበላችው ህጻን፣ ፲፪ ቤተሰባቸውን ቀብረው አፈር እየበተኑ ለሚያነቡት አባት፣ ቤታቸው ለፈረሰሻቸው፤ ከእርሻቸው ተፈናቅለው ወደ ልመና ለወረዱት ተበዳዮች ነው እንጂ ባህርዳር ላይ የብአዴንን ወንበር ለመረከብና አንቱ ለመባል አይደለም። ለህልውና፥ ለፍትሕ፥ ለእውነት የሚታገል ዐመሓራ ወንዝና ተራራ ምልከቱ አይደለም። ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ እውነት፥ በዓለ አገርነት በመላው ኢትዮጵያ በእኩልነት እንዲከበር ነው። ይህ ሁሉ ግን አስቀድሞ ዒላማ የተደረገው ዐመሓራ ራሱን ሲያድን ነው፥ ራስን ማዳን ሌሎችንም ማነቃነቅን፥ ፍልስፍናን ማቃንትን ይጠይቃል። ወደ ኦነግና ሕወሃት ብሔርተኝነት ካዘቀዘቀ ፋኖ ማንንም አያሸንፍም፥ ህልውናንም አይረጋግጥምና ይጠንቀቅ!
ስለዚህ እቺን የመንደር፤ የአውራጃ ፣ የጎጃሜ፣ የጎንደሬ፣ የሸዌ የወሎዮ ጨዋታ አቁሙ። ምክር ስሙ ይህ የጨቅሎች ኢትዮጵያኒስት የሚል ጨዋታ አቁሙ ። ኢትዮጵያ መሆን ያልቻለ ዐመሓራም መሆን አይቻለዉም ። ከኢትዮጵያ ወደ ዐመሓራ ወደ ከተወረደ በዚያው ፍጥነት ወደ ጎጃሜነት፣ ሸዌነት፣ ጎንደሬነት ይወረዳል። ከዚያ ደግሞ መርሀቤቴ ምን ጃር፡ መንዝ፡ ወልቃይቴ ይወረዳል። ብሔርተኝነት ታኮ ካልተደረገበት ወደ ቤተሰብነት ይወርዳልና አይጠቅምም።
ፋኖ ትግል ውስጥ የገባው ኢትዮጵያ የፍትህ ሀገር ለማድረግ ነው። ዐመሓራን በሌላው ላይ ለማንገሥ አይደለም። የዐመሓራ ቦታ በልኩ እና ላለፉት ፶ ዓመታት የተሠራበትን ሁለገብ ሤራና ኢፍትሓዊነት በግልጽ ሕግና ፍትሕ፥ ዳግም ትውልድ ውስጥ መርዙ አንዳያገረሽ አድርጎ አገር መመሥረት ነው።
ፋኖነት የዐመሓራነት እሤቶች መገለጫ ሆኖ ይቀጥል! በወደቁት እና አገራችንን ይዘው ወደ ገደል እየገቡ ከሚገኙት ዘረኛ ስነኩላን የሚዋሰው ምንም ትምህርት አይኑር እላለሁ!
ሰላም፥ እኩልነት፥ መተማመን፥ ፍትሕ፥ ሰባአዊ ክብር፥ በዓለ አገርነት የተከበረባት ኢትዮጵያን በደማችሁ ብቻ ሳይሆን በመልካም እሤቶቻችሁ እየዋጃችሁ ለምትገኙ ፋኖ ወንድም እኅቶቻን ፈጣን ድል አድራጊነትን እመኛለሁ።
በሌላ ምክረ ዐሳብ እስክነገናኝ በርቱ!!!