ለድሮን አብራሪዎች እና ለድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመን ነጻነቷን ጠብቃ የኖረችው፣ የሰው ልጅ ክብሩ የተረጋገጠባትን አገር ከውጭ ነጣቂ ጠብቆ በነፃነት ለማቆየት በነበራት ቁርጠኝነት ነው። ኢትዮጵያ በነጻነቷ የኖረቸው ሥልጣንና ጥቅም፥ የግል ድሎትና ምቾት፥ ተራ ዝናና ጊዜአዊ ክብርን እንደ ርኩሰትና ውርደት የሚቆጥሩ፣ በምትኩ ለአገር፥ ለሕዝብ፥ ለታሪክ፥ ላለፈው ትውልድ አደራና ለመጭው ትውልድ ቀጣይነት ዋስትና እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ዜጎች ሁሌም ስላሏት ነበር። ይህ ማለት ግን በጊዜያዊ ጥቅም ለጠላት አድረው አርበኞችን ያስገደሉ፣ እየመሩ ንጹሐንን ያስጨፈጨፉ፣ የመንግሥትና የሥርዓት ለውጥ፥ የእምነትና የባህል መበረዝ የታሪክ እጥፋቶችን እየጠበቁ በጠባብ የቡድን ፍላጎቶችና ድብቅ አጀንዳዎቻቸው ተሸንፈው ከጠላት ጋር የቆሙ ባንዳዎች አልነበሩም ማለት አይደለም።
ለጊዜያዊ ጥቅም ብለው የንጹሐንን ደም ያፈሰሱና በባንዳነታቸው ለራሳቸው ሞት፣ ለልጆቻቸውም ደግሞ የኃፍረት ሸማ እንዳጎናጸፉ ታሪካቸው በመጽሐፍ ተከትቦ እስከ ዛሬም መማሪያ የሆኑ ቤተሰቦች አሉ። ባንዳ ሆነው በአደባባይ በገመድ የተሰቀሉ፣ እጃቸውና እግራቸው ተቆርጦ ደግሞ ለትውልድ መማሪያ የሆኑም ብዙ ናቸው። የእነዚህ የውርደት ምሳሌ የሆኑ ሰዎችን ቆሻሻ በፕሮፓጋንዳ አጥበው የማይነጻ ታሪካዊ ነውራቸውን በሐውልት፥ በፋውንዴሽን፥ በሐሰት ትርክት፥ በዘፈንና በተለያዩ ሕትመቶች እያስዋቡ በማቅረብ ባንዳነትን ባህል ለማድረግ የተጣደፉ የጎሣ ፖለቲካ ልሂቃንና ፖለቲከኞችም በዛሬዋ ኢትዮጵያ የተንሰራፉት የቀደመ የባንዳነት እርሾ በመኖሩ ነው።
በአሁኑ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፈለው ብር በተሰሩ ትምህርት ቤቶችና በገነባቸው ወታደራዊ ተቋማት በነጻ ተምረው የኢትዮጵያ አየር ኃይልና የምድር ሠራዊት አባል የሆኑ መኮንኖች በደሞዝና በቪላ ራሳቸውን ሸጠው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከባእዳን በግዥና በብድር እንዲሁም ኢትዮጵያንና ጥንታዊ ማንነቷን ለማጥፋት ለዘመናት ከሚናፍቁ አገራት በነፃ እየተቸሩ በሚገኙ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ሕዝቡን በቤቱ፣ በማሳው፣ በገበያው ላይ እየገደሉት ነው።
ይህንን ወንጀል የሚፈጽሙ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ስማቸውና ማዕረጋቸው፣ የሚኖሩበት ቦታ፣ የሚስቶቻቸው የሥራ አድራሻ፣ የልጆቻቸው ት/ት ቤት፣ ከድሮንስ ግዢና አገልግሎት ያገኙትን ኮሚሽን በአባት፣ በእናት፣ በወንድምና በእህት ስም እያስቀመጡ መሆኑን ጭምር መረጃው በከፊል በእጃችን አለ። ቀሪውንም መረጃ ከሠራዊቱ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንዲሰጡን እንጠይቃለን።
ለድሮንስ አብራሪዎች አስቸኳይ ጥሪ
ፋኖ እርምጃ መውሰድ ከመጀመሩ በፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ለተማሩና የአገርን ዳር ድንበር እንዲያስጠብቁ ለሰልጠኑ ለእነዚህ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከተግባራቸው እንዲጸጸቱና ከነፍስ ማጥፋት ወንጀላቸው እንዲቆጠቡ እድል ሊሰጣቸው ወስኗል። ስለዚህ ለድሮን አብራሪዎች፣ ለድሮን ድጋፍ ሰጪዎች፣ ለድሮን ግድያ አስፈጻሚዎች፣ ለድሮንስ ደላሎች እራሳችሁን፣ ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን ከሕዝባዊ ቁጣ ለማዳን እራሳችሁን ከንጹሐን ደም ማፍሰስ ተግባር እንድትቆጥቡ በምታምኑት ፈጣሪና በኅሊናችሁ እንጠይቃችኋለን። ይህንን ሳታደርጉ የገበሬ ልጆችን ከሰማይ ላይ ሆነን እንደ ኮምፒዩተር ጨዋታ አልመን፣ ተኩሰን፣ ሕጻናትን ገድለን ለራሳችን እናተርፋለን፤ እድገት እናገኛለን፤ ለልጆቻችንም የተመቻቸ ኑሮ መፍጠሪያ ተመራጭ ስራ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል። ሕጻናትንና ገበሬዎችን መግደል በምድር ላይ በስቅላት የሚያስቀጣ፣ በአደባባይ የሚያሰቅል ወንጀል ነው፤ በሰማይ ደግሞ ለዘለዓለም በማይጠፋ እሳት የሚያነድ ነውና እራሳችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁንና ልጆቻችሁን አድኑ።
ልጆቻቸውን በእብሪት የገደላችሁባቸው ዘመዶች እናንተን ለመግደል ድሮንስ አያስፈልጋቸውም። ሽጉጥም፣ ክላሽም፣ ወፍራም የብረት ዱላም በቂ ነውና አትታበዩ። ሰው መሆናችሁን አትርሱ።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል የኢትዮጵያውያንን ዘር ለማጥፋት ታዛዥ አይደለም

ታዝዣለሁ ብሎ የገደለ ከወንጀሉ ነጻ አይሆንም። ምክንያቱም ለሁሉም ወታደር የተሰጠው የሕግ ከለላና መብት አለው። ይሄም ኅሊናዊ ተቃውሞ (Conscientious objection) ይባላል። የኅሊና ተቃውሞ መሠረቱ የሰው ልጅ መልካምና ክፉውን የመለየት ሙሉ ተፈጥሮአዊ ጸጋው ሲሆን ወታደራዊ ግዳጁ የማሰብ፥ የማምለክና የተለየ አኗኗር የመምረጥ ሰብአዊ መብቶችን ለማቀብና በጉልበት ለማጥፋት የሚደረግ የፋሽስታዊና ወንጀለኛ፥ የዘረኛና በአእምሮ በሽተኛ መሪዎች የሚሰጡ ትዕዛዛትን በመቃወም ትዕዛዙን አለመፈጸም ነው፤ ይህ ሕጋዊ መብት ነው። (Conscientious objection is the act of refusing to perform military service on the ground of freedom of thought, conscience or religion. It is a legal right)። ይህ ምክር አንድ ወታደር ከኅሊናው፣ ከእምነቱና ከአስተሳሰቡ ጋር የሚጋጭን ትእዛዝ አለመፈጸም መብት እንዳለው ያስረዳል። ከዛም አልፎ ለአንድ ወታደር አልሞ ተኩሶ በመግደልና ተኩሶ በመሳት መካከል ያለው ልዩነት ተኳሹ ለመግደል ባለው ፍላጎት እንጂ በአለቃ ትእዛዝ አይደለም። ያለመው፣ የተኮሰውና የገደለው ወታደሩ እንጂ አለቃው አይደለምና ከፍርድ አታመልጡም። ይህንን ምክር ተላልፋችሁ በሰማይ ላይ ነን ያለነው ማንም አይደርስብንም የምትሉ የምትገድሏቸው ልጆች ዘመዶች በየቢሯችሁ አሉ፤ ወደ ደብረ ዘይት በምትጓጓዙበት ባስ ውስጥ አጠገባችሁ አሉና ከኛ ሩቅ አይደላችሁም።
እስካሁንም ዝም ያልናችሁ፣ ውትድርና ሞያችሁ የአገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ይጠቅማል በማለትና አርቆ በማሰብ ነው። በዚህ እምነታችንም፣ አስቀድሞ ወያኔ በተኛችሁበት አርዶ፥ ቀጥሎ ወደ ሥልጣን በመመለስ የኢትዮጵያን ውድ ሠራዊት “የደረግ ሠራዊት” ብሎ በመሰየም እንዳጠፋው፣ አሁንም እናንተን “የብልጽግና ሠራዊት” ብሎ ሊያጠፋችሁ በተዘጋጀ ጊዜ ለአገራችን ስንል ከጎናችሁ በቆምንበት ሥራችን ታውቁናላችሁ። ይህንን ለመረዳት የሚያስችል አዕምሮ ከሌላችሁ፣ ጨርቁን ቀዶ ፊቱን ነጭቶ የገደላችኋትን ልጅ አስከሬን ታቅፎ እንደሚያለቅሰው ገበሬ እናንተንም እንዲሁ ማስለቀስ ቀላሉ ስራ ነው። ስለዚህ ለኅሊናችሁም ለፈጣሪያችሁም ብላችሁ በሕጻናት ግድያ ላይ አትሳተፉ። እስከ አሁን በከተማ መካከል በገበያ፥ በገበሬ አውድማና እርሻ መካከል፥ በቤተክርስቲያን፥ በቀብር ቦታ፥ በትምህርት ቤቶችና በገዳማት ላይ የፈጸማችሁትን ፍጅት አስቡና ተጸጸቱ! ይህንን ካላደረጋችሁ ለቅሶው በእናንተ እንዳይብስ ተጠንቀቁ። ጥላችሁ ከግለሰቦች ሳይሆን ከአገር ሕዝብ፥ ከታሪክ፥ ከግል ኅሊናችሁና ከፈጣሪያችሁ ጋር ስለሆነ መጽናኛ አታገኙም፤ የቅጣት እጃችንን መዘርጋት ስንጀምር መጠጊያም አይኖራችሁም።
“ትእዛዝ ተሰጥቶኝ ነው፤ እኔ ወታደር ነኝ” የሚባል ነገር የለም። ወታደር ሰው ነው እንጂ ኅሊና የሌለው በእብድ የሚታዘዝ ማሽን አይደለም። በትግራይ ጦርነት ከመካከላችሁ የነበሩ አብራሪዎች ኅሊናቸው ያልፈቀደውን የሲቪል ተቋማት አንመታም ብለው በመመለሳቸው ትእዛዝ ባለመቀበል ተብሎ ይልማ መርዳሳ ለአንድ አመት አስሯቸው እንደነበረ ታውቃላችሁ። ታስረው ተፈተው በነጻ አዕምሮ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ነው። ይህን ወንጀል አንሠራም ብለው ወደ ጅቡቲ በመኮብለላቸው ተይዘው መጥተው በእሥር ቤት የተጣሉ፥ ግፍ የተፈጸባቸውና የተረሸኑም አሉ። እነዚህ ሁሉ ከኅሊና፥ ከሕዝብ፥ ከእግዚአብሔር እና ለትውልድ ዘርን ከማዋረድ ክስ ያመለጡ በምድርም በሰማይም ክብር ያገኙ ናቸው። ይህ ነውረኛ መንግሥት በትግላችን ይፈርሳል፥ ፍትሕና እውነት ይነግሣሉ።
ይልማ መርዳሳ አዝዞኝ ነው ሕጻናትን የገደልኩት ብትል፣ ይልማ መርዳሳ መጥቶ አይሰቀልልህም። ለመግደል ወስነህ ያነጣጠርከውና ያለምከው አንተ ነህ፤ የተኮስከው አንተ፣ የውጭ ጠላት አለመሆኑን እያወቅህ በአገር ውስጥ ዜጎችን የገደልከው አንተው ነህና፣ የምትሰቀለውም አንተ ነህ። ኮምፒዩተር ኋላ ተቀምጠህ፣ የድሮን አብራሪ ሆነህ የንጹሐንን ደም ያፈሰስክ ሁሉ ተይዘህ፣ ለፍርድ ቀርበህ፣ በጨፈጨፍከው መንደር ላይ ተወስደህ ለመቀጣጫ በገመድ እንደምትንጠለጠል አስብ።
ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለሚመለከታችሁ፣ ይህን እህትህን በድሮንስ እየገደለ ያለውን ታውቃለህና ስሙን፣ መኖሪያውን፣ ያለውን ማዕረግ እየመዘገብክ እራስህን ለአደጋ በማያጋልጥ መንገድ ላክልን ወይ ለፋኖ ታጋዮች እንዲደርስ በሦስተኛ ወገን ላክ።
ይሄንን ምክር አልቀበልም፤ ሕጻናትን ገድዬ፣ ተሾሜ፣ ልጄን በግል ትምህርት ቤት አስተምራለሁ፤ አውሮፓና አሜሪካ ልኬ ኮሌጅ አስተምሬ ለወግ ለማዕረግ አበቃለሁ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጥቆ ለመንግሥት የመሣሪያ መግዣ ከሆነው የራስህ መሬት እየተቆነጠረ የሚሰጥህን የከተማ ቦታና የገጠር የኢንቨስትመንት መሬት አግኝቼ ከብራለሁ ብሎ በንጹሐን ደም የሚታጠብ አባት፥ ባል፥ ባለሥልጣን ሁሉ ይህ ህልሙ በአጭር ቀን ውስጥ እንደሚከስም እናረጋግጥልሃለን። ልጆቹም በነፍሰ ገዳይ አባታቸው አፍረው መንገድ ላይ ይበተናሉ።
ወንጀልና ኃጢአት ለጊዜው አትራፊ ይምሰሉ እንጂ አክሳሪዎች ናቸው። ሂትለርን፥ ስታሊንን፥ መንግሥቱ ኃይለማርያምን፥ የኢሕአፓ መሪዎችን፥ የሕወሓት መሪዎችን፥ ወዘተ አስታውስ። የእናንተ የወታደሮችና ፓይለቶች አደራና ተግባር የአገርን ዳር ድንበር ከውጭ ጠላት መጠበቅ፥ ሕዝብን ከማንኛውም አደጋ መከላከልና መጠበቅ እንጂ ለ33 ዓመታት ደም ሲያስፈስስ፥ ትውልድ ሲያፈናቀል፥ ቤተሰብ ሲያለያይ እና ቁማርተኞችን በሥልጣን ላይ በማስቀመጥ ሕዝብን ለጥቂት የጎሣ ልሂቃን ባርያ ሲያደርግ የቆየውን የኦነግና የሕወሓትን የዘር ሕገ መንግሥት በመጠበቅ ስም ባእዳን ሠርተው በብድርና በስጦታ ባስታቀፉአችሁ የጥፋት መሣሪያ ሕጻናትን፣ ገበሬዎችን፣ አረጋውያንን ከሰማይ ላይ እያዩ መግደል አይደለም። ስለዚህ ከሕግም፣ ከክላሽ ጥይትም በምንም አታመልጡም። የምትድኑት ለኅሊናችሁ በመታዘዝ ንጹሐንን ባለመግደል ብቻ ነው።
ከቻላችሁ ከገዳይ አስገዳዩ ሥርዓት አምልጣችሁ ፋኖን በመቀላቀል የዚህን የዘር ጣዖት አምላኪ ሥርዓት በአጭር ጊዜ ለማስወገድ በምናካሂደው ተጋድሎ በመሳተፍ ስማችሁን በወርቅ ቀለም በታሪክ ላይ አጽፉ፤ ይህ ካልሆነላችሁ እረፉ!


አማራ በትግሉ ህልውናውን ያስከብራል!
የፋኖ አንድነት ምክር ቤት
ታኅሣሥ ፲፰ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *