ክፍል ሁለት የአማራ “ፋኖ አንድነት ምክር ቤት” መቼ ተቋቋመ?

የዛሬ 12 ወር ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወሎ እና ከሸዋ የመጡ የፋኖ መሪዎች ተሰብስበው ህዳር 12 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት በርማጭሆ፣ ሱዳን ድንበር ላይ ኮረደም በርሀ ውስጥ “የፋኖ አንድነት ምክር ቤት” በአንድ እዝ ተዋቅሮ ተመሰረተ።
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ከተግባሩ ይልቅ ወሬው እየቀደመ ጠላት እያዘጋጀ ስላስቸገረ ይህንን ስብሰባ ከማጯጯህ ሚስጥራዊ ማድረጉ ግድ ነበር። ይሁንና ፋኖን በቅርብ ሲያግዝ በነበረው በማገር ሚዲያ እና በሌሎች ቅርብ የመገናኛ ብዙሀን ዜናው ተገልጿል። ሁሉም በጉግል ፈልጎ ሊያነበው ይገባል።
“የፋኖ አንድነት ምክር ቤት” ከሁሉም የአማራ ክፍለተ ሀገራት በመጡ የፋኖ የወታደራዊ መሪዎች የተመሰረተ ነው።
ለደህንነታቸውና ለትግሉ ሲባል ሁሉንም መዘርዘር ይከብደና። ይሁንና ከጎንደር እነ ሻለቃ አርጋው፣ ሻለቃ ሰፈር፣ ሻለቃ ሲሳይ፣ ኢንጂነር በየነ፣ ሻለቃ ጎበዜ፣ በርካታ የአርማጭሆ ፋኖዎች እና በርካታ የጎንደር ፋኖ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል። ጎንደር መሰባሰቢያና አሰባሳቢ ስለነበረ ብዙ ሰው ከጎንደር የተገኘው።
ከጎጃም ፋኖ ደግሞ ከባህር ዳር እነ ቴዎድሮስ፣ ፋኖ ጥላሁን፣ ፋኖ እሸቱ ተገኝተዋል። (በዛን ግዜ ዘመነ ካሴ እስር ቤት ስለነበረ መካፈል አልቻለም)
ከወሎ ደግሞ የምስራቅ አማራ የነ መሬ ወዳጆ ብርጌድ፣ እነ መንበር አለሙ እና ሌሎች ተገኝተዋል። ከሸዋ ደግሞ እነ ኮለኔል ማነገነገረው እነ ሻልቃ አበባ ሙላቱ እና ሌሌችም ስማቸው በዚህ እንዳይጠቀስ የተፈለገ የፋኖ መሪዎች አደራጆችና ደጋፊዎች በተገኙበት ነው የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የተመሰረተው።
በዚህ ጉባኤ ላይ በጊዘው በደህንነት ስጋትና በትራንስፖርት ችግር መገኘት ላልቻሉ በምክር ቤቱ ወንበር እንዲኖራቸው ተወስኖ ነበር። ክዛም ቦሀላ ለሚፈጠሩም እንዲሁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተወስኖ ነበር። በዚህ ላይ ወታደር ማደራጀት ላልቻሉ ነገር ግን በፖለቲካ ንቅናቄው ይረዳሉ የተባሉ ወንድሞችም አንዲካተቱ ተደርገዋል።
ለምን ማጯጯህ አልተፈለገም?
ፋኖ ለማስፈራራት ሳይሆን ውጤት ለማምጣት የተዘጋጀ በከፊል ሚስጥራዊ ወታደራዊ ኃይል ስለሆነ ማጯጯህ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ነበር። ዜናና ማጫጫህ በእርግጥ ደጋፊ ያስደስታል፣ ገንዘብና ደጋፍን ከዲያስፖራ ያስገኝ ነበር ይሁንና ጠላትን ያነቃል።
ወታደራዊ ዘመቻው እስከሚጀመር ብልጽግና ፋኖ የተከፋፈለ ነው፣ መሪ የለውም፣ በቅንጅት ማጥቃት አይችልም፣ ሽፍታ ነው ብሎ ማሰቡን እንዲቀጥልና ስርአቱ እንዲዘናጋ ነበር።
ሌላው ምክንያት ሁሉም እንደሚያውቀው ቀደም ብሎ በባህር ዳር በድብቅ የተጠራው የፋኖ መሪዎች ስብሰባ ሚስጥጥሩ የመንግስት ደህነቶች ስለደረሱበት በተላላኪው የብአዴን ካድሬዎች በርካታ የፋኖ መሪዎች ታስረው ነበር። ከሁለት ወር እስር ቦሀላ በሕዝብ ተጽእኖ፣ በረሀብ አድማ፣ የህግ እስረኞች ሳይቀሩ የረሀብ አድማ አድርገው ብአዴንን ስላስጨነቁና ዳኞችም በቂ መረጃ ስላልቀረበ የፋኖ መሪዎች ተፈተው ወደ ትግሉ ተመለሱ።
ስለዚህ የአርማጭሆን ስብሰባ ሚስጥራዊነቱ መጠበቅ ግድ ነበረበት። ከዛም ውሳኔ አሳልፈው ከሸዋ፣ ከወሎ፣ ከጎንደር፣ ከአዲስ አበባ እና ከሩቅ ቦታዎች የመጡ መሪዎች ብልጽግና በየመንገዱ እያደፈጠ እንዳያጠቃቸው ሚስጥር መጠበቅ ግድ ሆነ።
የፋኖ አንድነት ምክር ቤት ጥንስስ?
መንግስት ዘመነ ካሴን አጠፋለሁ ብሎ ጎጃም ሰራዊት ልኮ ሲያምስ የሁሉም ክፍለ ሀገራት ፋኖዎች ምን እናድርግ ብለው ለመወያየት ባህርዳር ላይ ተቃጠሩ። ይህም የፋኖ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለማቋቋም ነበር። ጥሪውም የተላለፈው ለዋና ፋኖ መሪዎች ሳይሆን በቀላሉ ሊታወቁ የማይችሉ ምክትሎቻቸውን እንዲልኩ ነገር። ይሁንና ብዙዎች ተገኝተው ነበር። እንዲህ አይነት ስብሰባዎች ቀደም ብሎ በደብረ ብርሀን፣ በምንጃር፣ በጎጃም፣ በወሎና በጎንደር ተደርገው የመነሻ ሀሳብ ተሰብስቦ ነበር። ውይይቱ ዘመነ ካሴን እይዛለሁ ብሎ ወደ ጎጃም የዘመተው ጦር ሀገር ሲያጠፋ ዝም ብለን እናያለን ወይ? ምን አይነት ወታደራዊና ህዝባዊ ንቅናቄ እንፍጠር የሚለውን ለመወያየት ነበር።
ይሁንና በዛ ቀን የደረሱ የፋኖ መሪዎችንና በሚስጥር ባህር ዳር ገብተው ነበር። ሌሎች ደግሞ መመንገድ ላይ ስለነበሩ አልተያዙም። እራት ተበልቶ ስብሰባ ሳይጀመር ፌዴራልና ልዩ ኃይል ግልብጥ ብሎ ገብቶ ሰፈሩን ሁሉ ቀውጢ አደረገው።
አንዳንዶቹም በፋኖ ጭንቅላት ላይ ሽጉጥ ደግነው መንግስቱ ኃይለማርያም መጥፎ ስም ሰጠው እንጂ እዚሁ ነበር “ቀይ ሽብር” ማካሄድ የሚገባው የሚሉ የብአዴን ቡችሎች ነበሩ። ነጻ ሊያወጣቸው የተሰበሰበን ፋኖዎች ረሽነው ቪላ ቤትና V8 መኪና ከአብይ ለመቀበል የቸኮሉ ነበሩ።
በዶ/ር ይልቃል ከፍያለና በሰማ ጥሩነህ የሚመራው ብአዴን በዛች ምሽት የተገኙትን የፋኖ መሪዎችን አሰረ። ለፋኖ ይህ ከጉዳቱ ጥቅሙ አዘነበለ። አንድ ወይንም ሁለት ቀን በድብቅ ተወያይተው ሊበተኑ ያሰቡት የፋኖ መሪዎች በአንድ እስር ቤት ውስጥ ለሁለት ወራት ረጃጅም የፓለቲካና ወታደራዊ ውይይቶችን እንዲያደርጉ እድል ከፈተ፣ ወታደራዊ የይሆናል እቅዶች (scenario analysis) ሰርተው ገመገሙ፣ የፋኖን ጥንካሬ፣ ድክመት እድልና ፈተናን (SWOT) ሰሩ፣ የመንግስትን የተቃዋሚውን የአለማቀፍ አሰላለፍን ገመገሙ።
ከሁሉም በላይ የኔነትን (ego) አፍርሰው በፏራሽ ላይ መተኛት፣ በእስርቤቱ አፈርና ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ መወያየትን እስረኞችን ማንቃትን ቀጠሉ። ከአንዴም ሁለቴ የፌዴራል ፓሊስ እስረኞቹን ልውሰድ ብሎ ሲመጣ እስረኛው ግልብጥ እያለ እኛን ገላችሁ ነው እንጂ የምትወስዷቸው በህይወት እያለን አይሆንም ብሎ አስጣለ።
የፋኖ ወኪሎች በአንድ ላይ መታሰር እንዲወያዩ፣ እንዲከራከሩ፣ እንዲነቡ፣ ከዛም የፖለቲካና ወታደረዊ እቅድ እንዲያወጡ በር ከፈተ፣ የፋኖን የፓለቲካ ዓላማን ግብን ለመወያየትና ስምምነት ላይ ለመድረስ ቻሉ። በየተራ እንደ ዘመነ ካሴ ስለሚዘመትብን አንድ መሆን ግዴታ ነው የሚለው ስምምነት የተደረሰው በእስር ቤት ነው።
ከተፈጠረው የዓላማ አንድነት ወንድማማችነት በላይ የብአዴን ካድሬዎች በአሉባልታ ለመከፋፈል ‘እንትና ስድስት ሚሊዮን ብር በልቷል፣ እንትና ደግሞ ቅማንት ነው፣ ያኛው ደግሞ የብአዴን ቅጥረኛ ነው” እያሉ ይነዙት የነበረውን አሉባልታ ጥርጣሬ ለማጥራትና የፋኖ መሪዎች ልብ ለልብ ተዋውቀው ወንድማማች ሆነው እንዲወጡ ረድቷል።

ከእስሩ በፊት የፋኖ መሪዎች ለሁለት አመት በተለያየ ቦታ ሲገናኙ ቆይተዋል። በርካታ ጥናታዊ የይሆናል (Scinario analysis) ሰርተዋል። ለምሳሌ ህወሀት ወደ ሰሜን ሸዋ ሲቃረብ ባህር ዳር ላይ 5 የይሆናል ግምት አስቀምጠው ለያንዳንዱ የይሆናል ግምት መፍትሄ ሰጥተው ነበር።
ለምሳሌ
፩ኛ ህወሀት አሸንፎ አዲስ አበባ ቢገባና ታንኩን ባንኩን ቢይዝ ምን እናድርግ?
፪ኛ በሰሜን ሸዋና በደሴ መሀከል ሰራዊቱ እየተገፋፋ ለረጂም ጊዜ ቢቆምና የአማራን ሕዝብ ሰቆቃ ለመቀነስ ምን እናድርግ?
፫ኛ መንግስት አሸንፎ ገፍቶ ራያን ሳይዝ ቢቆም ምን እናድርግ?
፬ኛ መንግስት ህወሀት እያሸነፈ ራያን አስመልሶ በትግራይ ድንበር ላይ ቢቆም ምን እናድርግ? እና
፭ኛ መንግስታት መቀሌ ቢገባ ምን ይከተላል ተብሎ ውይይት ተደርጎ ለእያንዳንዳቸው የይሆናል ጥያቄ መፍትሄ እና ዝርዝር ፕላን ቀርቦ ነበር።
ከነዚህም ውስጥ ለአማራም ለኢትዮጲያ ሕዝብም በጎው የቱ ነው? መጥፎው የትኛው ነው ተብሎ ተለይቶ ነበር።
በጎው የተባለው ፬ኛው ነበር። መንግስት ወደ መቀሌ ሳይገባ ዘር መጥፋት የተጋረጠበትን የራያን ሕዝብ ነጻ አውጥቶ እንዲቆምና ጊዜ ወስዶ የትግራይን ሕዝብ የህወሓት ስህተት በማሳየት ላይ እንዲያተኩር ነበር።
በዚህም የይሆናል ግምት ስር አማራውን እየሰደበ፣ እያዋረደ፣ እየገደለ፣ እበቀለዋለሁ ያለውን የነ አሉላ ሰለሞን የህወሀት ኃይል የራያን ሕዝብ ሳያጠፋ ማስቆም የሚል ነበር።
ከነዚህ ከአምስቱ መጥፎ ተብሎ የተበየነው በ፫ኛ ላይ የተጠቀሰው የራያን ሕዝብ ለህወሀት የዘር ማጥፋት አጋልጦ መቆም ነበር።
ፋኖ ከመጀመሪያው የሚጠረጥረው እነጃዋር ለኦፒዲዮ ያስጠኑት “የኩሽ” ፓለቲካ እያደገ የመንግሥት ፓሊሲ መሆኑ ነው።
ኦፒዲኦ ለስልጣኔ ተቀናቃኝ ይሆነኛል ብሎ የሚያስበውን ሕዝብ “ የሴም ዝርያ (ሴማቲክ)፣ ወራሪ፣ ሰፋሪ፣ ጠላት” ብሎ መፈረጁን እና እኛ ስልጣን ላይ የምንቆየው አማራውን ከትግሬው፣ ትግሬውን ከኤርትራ፣ ኦርቶዶክሱን ከኦርቶዶክሱ ጋር በማጋጨት የኦሮሙማን የበላይነት ማረጋገጥ የምንችለው ብለው እንደተስማሙ ፋኖ መረጃ ነበረው። አብይ አህመድ ፕሮቴስታንት የሆኑ የኦፒዲኦ ፓለቲካና ወታደራዊ መሪዎች መርጦ የሰጠው ሴሚናር ቅጂ ደርሶን ነበር። በዛ ጽሁፍ ውስት አብይ ሶስቱን ሴማቲክ ጠላት ብሎ የፈራጃቸውን በበጌምድርና በራያ መሬት ለማጫረስ እቅድ እንደያዘ ለፋኖ ቅርብ የሆኑ ውስጥ አዋቂዎች ሹክ ብለው ነበርና የሶስተኛው ይሆናል ውሳኔ እቅዱን አጋለጠው።
ስለዚህ አብይ ራያንና የበጌምድር ለአማራና ለትግሬ መፋጃ አጥንት አድርጎ፤ ኤርትራን ደግሞ ስቦ አስገብቶ ካዳከመ ቦሀላ አፋርን፣ ሱማሌን፣ አገውን ይዤ የቀይ ባህር ባለቤት እሆናለሁ ብሎ ማሰቡ የፋኖ መሪዎች ደርሷቸው ስለነበረ ይሄንን ለማክሸፍ ወሰኑ።
ለምን የአማራ በፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪካ ልወከል ጥያቄ አነሳ?
የፋኖ መሪዎች የኩሽ ተንኮል ቀድሞ መረጃው ስለደረሳቸው የደቡብ አፍሪካ ሰላም ስምንነት ይደረጋል ሲባል የፋኖ መሪዎች ፈጣን የዙም ስብሰባ አድርገው ይሄንን የኩሻውያን ሴራ ለማፍረስ ሶስት የአማራን ጥቅም ያስጠብቃሉ ያሏቸውን ዶ/ር ወንድወደን አሰፋን፣ ብርጋዴል ጄኔራል ተፈራ ማሞን እና ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ውክልና ሰጡ።
አብይ አህመድ ያለው የአይምሮ መታወክ የሰጠው አንድ ትልቅ ተስዕጦ ፋኖ ተረድቷል። አብይ ሊገለው የፈለገውን ሄዶ አቅፎ፣ ስሞ፣ ከአንገቱ ላይ ሀብል ከጣቱ ላይ ቀለበት አስሮ እያሳሳቀ ወስዶ ከገደል ላይ የመገፍተር ችሎታው የሚገርም ነው።
ለማ መገርሳ ጉልበት ላይ ወድቆ እስከ ምርጫ ድረስ ለሁለት አመት ስልጣኑን ለኦፒዲኦ ላስጠብቅ ብሎ ስልጣኑን ከተረከበ ቦሁላ እስከሚደላደል ለማን እያቀፈ ከአንገቱ ላይ ሀብል እያወለቀ እየሰጠ ወደ ገደሉ ውስዶ ገፈተረው። ለማ ዛሬ ፖለቲካ ማውራት ቀርቶ በሀገሩ ላይ በሰላም መኖር የማይችል ሰው ሆንዋል።
ይሄንን ባህሪውን እንደ በጎ ነገር በማሰብ ለማስተማሪያ ጽፎታል።
ሌላው የፋኖ ግምገማ ህወሀት ተሸንፏል ይሁንና ህወሃት መለስ ከሞተ ቦሀላ ጭንቅላቱ ተቆርጦ ተቀብሯል የሚል ነው። እየተመራ ያለው በነ አሉላ ሰለሞን፤ በነ ስታሊንና በነ ዳንኤል ብርሀኔ ጭንቅላት ነው። “ለኛ ጦርነት የባህል ጨዋታችን ነው፣ ፎጣ ለባሹን እንቀጣዋለን፣ ኢትዮጵያ ስትፈርስ በኛ እድሜ በማየታችን ደስ ብሎኛል” እያሉ መላው ህዝብ እንዲነሳባቸው የሰሩ መሀይማን ናቸው። በአደባባይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳ ሀይል እንዲሆነ፣ አማራን ሊቀጣ የሚመጣ እንደሆነ አድርገው የሚያቀርቡ አብይ ቢያቅፋቸውና ቢያሻሻቸው መጠቀሚያው ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምገማ ነበር። ፋኖ አስቅውድሞ እንደ ተነበየው አብይ እነ ጌታቸው ረዳንና እና ታደሰ ወረድን አቃቅፎና ሸልሞ የቀሩትን የትግራይ ህጻናትን በበጌምድርና በኤርትራ የማስፈጀት አቅም እንዳለው ታየ። ይሁንና እስከአሁን ለአብይ የሚሞት ወጣት ከትግራይ አልተነሳምና ይህ የህቡን ብስለት አመላክሷል። ይህ ተንኮል አልሳካለት ሲል በበጌ ምድርና በራያ ህዝበ ውሳኔ ጠርቶ ግጭት ለመፍጠርና ላማጋጨት አሁንም እየሞከረ ነው።
የአብይ የኦሮሙማ የበላይነት በምስራቅ አፍሪካ የሚነግሰው “በሴማውያን መጨራረስና መጥፋት ላይ ነው” ብሎ ስለደመደመ የህወሃት መሪዎች በድጋሚ ወጣቱን ከኤርትራና ከአማራ ጋር በማፋጀር የሴማውያንን ቁጥር በመቀነሱ አሁንም የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም።
ስለዚህ በትግራይና በአማራ መሀከል ያለው ልዩነት በአማራና በትግራይ መሀከል በሚደረግ ውይይት እንጂ በኦፒዲኦና በህወሓት መሀከል በሚደረግ ድርድር አይደለም ብሎ ወስኖ በውይይቱ ላይ እንዲገኙ ሶስት ተደራዳሪዎች መረጠ። ለአሜሪካ አደራዳሪዎች ይህ የተናጠል ድርድር ሰላም ስለማያመጣ ሁላችንም እንገኝ ብሎ ቢጽፍም አማራው የትም አይደርስም ስለተባለ ሰሚ አጣ።
በዲያስፓራ ያሉ አንዳንድ ሚድያዎች ይህ ተንኮል ቀድሞ ስላልተረዳ የአማራውን ጥቅም እንዲወክሉ በተመረጡት ላይ አሉባልታና ወደ ማሳነስ ሄደ። ይሁንና ፋኖ የቀደውን አሳካ።
ይሄውም አማራ በራሱ ጉዳይ እንዳልተወከለ ለታሪክ እንዲመዘገብና አማራን በሚመለከተው አጀንዳ ላይ አማራ ተሳታፊ እንዳልሆነና በስምምነቱም እንደማይገዛ ለሚዲያም ለአደራዳሪውም ለመንግስታትም አስመዝግቧል። የሰሜን ኢትዮጵያ ችግር መፈታት ካለበት አማራው ያገለለ፣ በጸረ ሴማውያን በሆነው በኦፒዲኦ በህወሀት በመወከል የለበትም ብሏል።

አብይ የሚፈራው የትግራይና የአማራ ድርጅቶች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ከፈቱ የሴማውያኑ ቁጥርም ኃይልም አይቀንስም ብሎ ስለሚሰጋ ነው። አማራ በትግራይ ውስጥ የለም፣ ይሁንና በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ሰው በአማራ ይኖራል። አማራ ክልሌ ነው፣ ስራ አትቀጠርም፣ አስተማሪ አትሆንም፣ አታክምም፣ አትነግድም፣ አትከብርም፣ አትቀድስም፣ አታገባብ፣ አትወልደም አትከብድም የሚል ጠባብ ስነ ልቦና የለውም። ማንኛውም ሰው በሀገሩ ላይ የትም ሄዶ የመኖር መብት እንደሚችል የሚያውቅ መሀበረሰብ ነው።
ሌላው ህወሀትና የምዕራብ ሚዲያ እንደሚያቀርቡት ፋኖ መቼም መንግስትን አልደገፈም። ፋኖ እሰፈሩ ድረስ መጥቶ ፎጣ ለባሽ እያለ የሰደበውን፣ የገደለውን፣ የዘረፈውን፣ ሴቶችን የደፈረውን የህወሀት የጥጋብና የእብደት ሀይል ነው የተዋጋው። ፋኖ የተዋጋው ቤት ለቤት አማራን እየመረጠ የገደለውን የሳምሪ ሰራዊት ነው። እነ እሸቴ ሞገስና እና ልጁ እነ ይታገሱ እሸቴ ተታኩሰው የሞቱት በሰሜን ሸዋ በቤታቸውና በማሳቸው እንጂ ትግራይ ሄደው አይደለም።
ፋኖም ሆነ አማራ በጎሳ አስቦ ያደላው ያገለለው ብሄርም ሰውም በዘመናት እድሜው አልታየም። ይልቁንም ህወሀት እንኮኮ ብሎ ለስልጣን ያበቃውን አማራ የመታገያ ጠላት አድርጎ መድቦ ከየቦታው ሲያስገድለው “ዛፍ ቆረጠ” እያለ ሲያፈናቅለው የኖረ የፖለቲካ ሀይል መሆኑን ፋኖ በደንብ ይረዳል።
ብሄረተኝነት የሚፈጠረው መጀመሪያ ጠላት በመፍጠር ነው። የትግራይን ብሄረተኝነት የፈጠሩትን አማራን ጭራቅና ጠላት አድርገው በመፈረጅ ስለሆነ አማራው በኔ ላይ ታንክ እየነዳህ፣ ቤቴን እየዘረፍክ፣ ሚስቴን እየደፈርክ አታልፍም ብሎ በቀዮው፣ በምርንደሩ እና በማሳው ላይ ነው እንጂ ለአብይ አህመድ ስልጣን አይደለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *