የቄስ ሞገሴ፤ የዶ/ር ብርሀኑ እና የአታተርክ ጉዳይ
ያሬድ ኃይለመስቀል የእልፍኝ “ምሁራን” ሲሳይ አጌና ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ አዳመጥኩ። የዶክተር ብርሀኑን ቃለ መጠይቆች ሳዳምጥ በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ ያሉትን የቄስ ሞገሴን ገጸ ባህርይ ያስታውሰኛል። ለነገሩ ይሄንን ሀሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ የከተተው አንድ ወጣት ነው። ይህ ወጣት አባቱ እዚህ እንግሊዝ ሀገር ይዞት ሲመጣ ትንሽ ልጅ ነበር። ይሁንና ቤተሰቦቹ በሀገር ጉዳይ ላይ ጽኑ…