ፋኖና የዲያስፓራ ሚድያ። ሚድያው ፋኖን እየደገፈ ወይስ ድጋፍ እያሳጣ ነው?

የዲያስፓራ ሚዲያ በፋኖ ስምን በጠራ ቁጥር ከሚያገኘው ገቢ 20% ለፋኖ ቢሰጥ ኖሮ ዛሬ አዲስ አበባ በተገባ ነበር። ይልቁንም ትግሉ እንደተጠናቀቀ፣ ድል እንደመጣ፣ ስርአቱ እንደወደቀ፣ በመቶ ቢሊዮን ድጋፍ እንዳገኘ ተደርጎና ተጋኖ የሚቀርበው ዜና ሰዉ ድጋፍ እንዳያደርግ፣ የትግሉ ተመልካች እንዲሆንና ነጻ አውጪ ጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል። 

 መቶ ሀያ ሚልዮም ህዝብ በቻለው ሁሉ ስርአቱን እንዲያዳክም ከመቀስቀስ ይልቅ  ቁጭ ብሎ እንደ የቃና ቴሌቭዥን መዝናኛ ፕሮግራም እንዲመለከትና ለቴሌ ብሩን እንዲሰጥ ተገዷል። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት የዛሬ አንድ አመት ከሁለት ወር ገደማ በአርማጭሆ ከተመሰረተ ቀን ጀምሮ በውጪ ያሉ ወዳጆችን እባካችሁ እንደምንም ብላችሁ 30 የሳተላይት ስልክ ብትገዙልን ስርአቱን ከክሉ ማስወጣት እንችላለን ብሎ ለምኗል። እስከዛሬ አንድ አልመጣም። እኛ ህይወታችንን ልንሰጥ ተዘጋጅተናል እናንተ ደግሞ ዶላራችሁን ስጡ ብሎ ለምኗል። አንድ ጥሩ የሳተላይት ስልክ 2.0ሺ ዶላር ይገኛል። ስለዚህ በ60 ሺ ዶላር 30 ስልክ መግዛት ይቻላል ብሎ ለምኗል። 

ከዛ አንድ ሚሊዮን ዶላር ተሰበሰበ ሲባል እሰይ ችግራችን ሊፈታ ነው ሁሉም አለ። ይሁን እንጂ አንድ የሳተላይት ስልክም ህይወታቸውን እየሰጡ ላሉ መሪዎች አልደረሰም። ተሰባሰቡ ይላል ሳይገናኙ ሳይወያዩ እንዴት ነው የሚሰባሰቡት? ተሰባሰቡ የሚለው የ80 አመቱ የደርግ  ሻለቃ ዳዊት ይምራችሁ የምትል ኮድ ሆናለች።

አሁን እንደምንሰማው በፋኖ ስም የተሰበሰበውን ዶላር በአይሮፕላን ትኬትና ከሆቴል ሆቴል እየተዘዋወሩ እየ ተጠቀሙበት ነው። ሌብነት ዋነኛው አትራፊ ንግድ የሆነው በሀገር ውስጥ ብቻ ይመስለን ነበር። በዲያስፓራም ብሶበታል።

ሻለቃ ዳዊት የፋኖ መሪ መሆን ቀርቶ አባል እንኳን አልነበሩም። በተነሳው ግርግር የፋኖ ወኪል ነኝ ብለው አንድ ሚሊዮን ዶላር ወደ ባንክ አካወንታቸው አስገቡ።  የሰበሰቡት አንድ ሚሊዮን ዶላር  60ሺ አውጥተው ለስልክ መግዣ አልሰጡም። አሁን ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን ተብሏል። 

ይህ ደግሞ ለመጀመሪያ ግዜ አይደለም። አብይ አህመድን በአለማቀፍ ፍርድ ቤት አቅርቤ እንዳስቀፈድደው ብር አዋጡ ብሎ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር ሰብስበው ነበር። አብይ በሄግ እስርቤት ስንጠብቀው ብሩን/ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን ብለው ጠፏ።  ክሱ ከቀረ ሁሉም በባንክ ቁጥሩና እና በgofundme ያስገባው ቁጥሩ ይታወቃል። ባይሆን ወለዱን በልቶ ዋናው አይመለስም።

የሚገርመው ደግሞ  ብዙው ዲያስፓራ ካልተዋሸ፣ ካላጋነነ ዲያስፓራው በጭራሽ አይደግፍም። ስለዚህ ቅጥፈትና ውሸት የንግድ ፈቃድ ያልወጣበት ስራ ሆንዋል። ሀያ ፋኖ ያላደራጀ፣ አንድ ቀን ያልተኮሰ ፎቶውን በቲፎዞ እየለጠፈ ብር ይሰበስባል ጫካ ውስጥ የሚያድረው በየቀኑ የሚተናነቀው ደግሞ በረሀብ ይጠበሳል።

ይህ ጽሁፍ ለማማረር አይደለም። ዲያስፓራው በተለይ ደግሞ ከፋኖ መስዋዕትነት እያተረፏ ያሉ ዩቲዩበኞች ከትርፋቸው 20% እንኳን ለፋኖ እንዲረዱ።

ይባስ ብሎ አቶ ወርቁ አይተነው ለፋኖ መቶ ሚሊዮን ሰጡ ይላል። መቶ ሺ ብር ቢሰጡ ታሪካቸው ይመዘገብ ነበር።  የዩቲዊበሮች ለፋኖ መርዳቱ ቢቀር ትግሉ እንደተጠናቀቀ ተጋኖ መቅረቡ ብዙ ወጣቶች ወደ ትግሉ እንዳይቀላቀሉ፣ ብዙዎቹ በመላው ኢትዮጵያ ተደራጅተው ስርዓቱን እንዳይገዘግዙ አድርጓቸዋል። 

ትላንት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የኢትዮጵያ ትንሳኤ መሪ ናቸው ብለው ኢሳትን አቋቁመው እነ ሀይሉ ሻውልን የሰደቡ ዛሬም ያንኑ እየደገሙ ከትግሉ እያተረፏ ነው። ፋኖን ለቀቅ አርገው ለምን ለስልጣን ያበቁትን ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን ጠበቅ አድርገው አይዙም። እስቲ የትላንትና የትላንት በስቲያ በዩቲዩብ የተለጠፏትን ርዕሰ አንቀሶችን እንመልከት። ትግሉን ይደግፋሉ ወይስ ድጋፍ እያሳጡ ነው? እናንተው ፍረዱ

• “ሀብትሽ የጎንደረን ድል ሲያበስር መስመር ላይ ገብቷል” ብሎ የሀብታምን ፎቶ ለጥፎ ብር ሰብስክራይብ አድርጉኝ ይላል።

• ሌላው ደግሞ ‘ጀነራሉ ለጥቂት አመለጡ” ይልና ስትገኩ ማን ምን መቼ አይገለጥም። 

• “ጎንደርና ባህርዳር በቁጥጥር ውስጥ ገቡ”

• “የመከላከያ እሬሳ ተከመረ አብይ መርዶ ተቀመጠ”

• “ታላቁ ኤርፓርት ነጻ ወጣ”

• “ወርቁ አይተነው ታሪክ ሰሩ፣ 100 ሚሊዮን ብር ለፋኖ ሰጠ”

• “ብራቮ ደመቀ መኮንን ታሪክ ሰሩ” ብሎ ይለጥፍና ብርሀኑ ጁላና ሽመልስ አብዲሳ ተማርከው ያሳያል።

• “ማርሽ ተቀይሯል ቤተ መንግስት ታመሰ”

• “በጠራራ ጸሐይ 4ኪሎ እንገባለብ”

• “ዘመዴ አፈነዳው”  ምን ሰባል ምንም የለም።

  • “ጠቅላይ ተመታ፣ አብይ ጥሎ ሸሸ”

• “እንኳን ደስ አላችሁ! አበቃ” ይላል።

• የአብይን ፎቶ ለጥፎ “ሠውዬው ከስልጣን ለቀቁ” ብሎ ለጥፎ ስትገቡ ስለ ሱማሌ ላንድ የማናውቀው ሰው ስራ መልቀቅ ይዘግባል።

በዚህ ሁሉ ብር ይሰራል። በእውነት የኢትዮጵያ ልጆች ብር በማግኘታቸው ደስ ይለናል። ይሁንና የፋኖ ትግል የህልውና እና የርዕዮተ አለም ትግል መሆኑ ተረስቶ የመዝናኛ entertainment ፕሮግራም ሆንዋል።

የፋኖ እባካችሁ ስልክ ግዙልን፣ ከሱዳን 50 የትከሻ ላውንቸር ብትገዙልን የብርሀኑ ጁላ እግረኛው ጦር እንዳይንቀሳቀስ በድብቅ ፋኖ እንደ ይዘው በሞርታር ደግሞ ሜካናይዙን በርቀት አምስቱን ቢያጋየው ክልሉን ጥሎ ይወጣ ነበር። 

እባካችሁ የምትሉት ነገር ሁሉ ፋኖን የሚያጠናክር እንጂ የሚያዘናጋ አይሁን። ከቻላችሁ ፕሮፓጋንዳው በርካታ ሰዎች ከመላው ኢትዮጵያ እንዲቀላቀልና አብን በአጭር ቀን እንዳባርረው እንጂ ዜናው ለማዝናናትና ለማዘናጋት አይሁን።

 አግዙን ባይሆን ባይሆን በኛ ስም ከለመናችሁት ዶላር ወደ ሱዳን ላኩና በርካሽ የሳተላይት ስልክና ሞርታር ግዙልን።

ድሮ ዮፍታሄ ንጉሴ እንዲህ ብለው ገጥመው ነበው

 “ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላለ

  የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *