ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ፋኖነት ቅንጦት ሳይሆን የአማራ ህዝብ ፍትህ በተጓደለበት፣ ነፃነቱ በተገፈፈበት፣ ጠላት አገሩንና ሀይማኖቱን ሊያረክስ በመጣበት እና የመኖርና ያለመኖር የህልውና ትግል በገጠመው ጊዜ ለክብሩ ለማንነቱ ለሀይማኖቱ ሲል በአንድነት የሚነሳበት እሴቱ ነው። በመሆኑም አማራ በአንድነት በተነሳበት በዚህ ጊዜ በተለይም በጎጃም ፈር ቀዳጅ ሆኖ በየወረዳው የተበታተነውን ትግል አንድ አድርጎ አራት ኪሎ ትንሳዔውን ለማክበር በጎጃም ቀጠና ዕዝ ከተመሰረተ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ጥሩ ውጤትን እያስመዘገበ ይገኛል።

ስለሆነም የጎጃም ዕዝ ባደረገው 4ተኛው አስቸኳይ የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ በተለያዩ የትግሉ ቀዳሚ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያዬ በኋላ የሚከተለውን ባለ ሁለት ነጥብ የአቋም መግለጫ በመስጠት ሌሎችን አጀንዳዎች በይበልጥ የማሰቢያ ጊዜ አስቀምጧል።

1ኛ.የዲያስፖራ ክንፉ በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ከሀሳብ እስከ ፋይናንስ በማገዝ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም በጎጃም ዕዝ ፋኖ በውጭ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን እና ሌሎች የፋኖን እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ለማስተባበር እና የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማሰብ በዕዙ ስራ አስፈፃሚ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የውጭ ማህበረሰባችንን እንዲያስተባብሩና አስቸኳይ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ (Emergency Fund Rise Committee) ያዋቀረ ሲሆን በኮሚቴው በኩል ለሁለት ሳምንታት ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። ኮሚቴውም ዘጠኝ አባላት ያሉት ሲሆን ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደስላሴን ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።
ስለሆነም በውጭ የምትኖሩ የአማራ ባለሀብቶች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ዩቲዩበሮች፣ ቲክታከሮችና በሁሉም የሚዲያ ፕላትፎርሞች ውስጥ ያላችሁና የፋኖን የህልውና ትግል የምትደግፉ ወገኖቻችን ትብብራችሁን የምንጠይቅ መሆኑን እየገለጽን እናንተ በምትሳተፉባቸው ሚዲያዎች ያሉትን አድማጭ-ተመልካቾቻችሁን፣ አድናቂዎቻችሁንና ደጋፊዎቻችሁን ግንዛቤ በመፍጠር ጥር አስር ለሚጀመረው ዘመቻ የበኩላችሁን አሻራ እንድታሳርፉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

2ተኛ.ሐሰተኛ በቃሉ፣ ስደተኛ በቅሉ ይታወቃሉ እንዲል ብሂሉ የፋሽስታዊ አገዛዙ ክልል ብሎ ባስቀመጠው በረት/ክልል/ ውስጥ ሰላም ያለ ለማስመሰልና ተማሪዋችን የፕሮፖጋንዳው/የፖለቲካው ሚዛን ማስጠበቂያ ቀብድ በማድረግ የስርዓቱ ስልጣን አስጠባቂ የሆነውን የትምህርት ስርዓት በመጠቀም በአማራ ክልል* ውስጥ የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በኩል በተደረጉ ጫናዎችና በምንጣፍ ጎታች የዩኒቨርሲቲ ፕሪዝዳንቶች አማካኝነት የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ለተማሪዎቻቸው ጥሪ ማድረጋቸው ይታወቃል።
ነገር ግን በክልሉ ውስጥ የአማራ ህዝብ ለህልውናው (ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ፍትሃዊነት) እልህ አስጨራሽ ትግል ከጨፍጫፊውና ፋሽስታዊው አገዛዝ ጋር እያደረገ ይገኛል። በዚህ ትግልም አመርቂ ውጤቶችን በማስመዝገብ የጨፍጫፊውን አገዛዝ እያፈራረሰው ይገኛል።
ስለሆነም ውድ ተማሪዎች ትምህርት ለአማራ ልጅ በዚህ ሰዓት ቅንጦት ሆኖበት ከክርስቲያን እስከ ሙስሊሙ፣ ከህጻናት እስከ ሽማግሌውና ከአርሶ አደር እስከ መንግስት ሰራተኛው/ምሁራን/የአያቶቹን ታሪክ በመድገም በዱር በገደሉና በፀሃይ በብርዱ ለህልውናው በከፍተኛ ደረጃ እየተዋደቀ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ መፈርጠጥ ልምዱ የሆነው ጨፍጫፊው ቡድን በፋኖ ላይ ጥቃት ለመሰንዘርና በሚወሰደው የአጻፋ እርምጃ በሚደርስ ጉዳት ፋኖ በንፁሀን ተማሪዋች ላይ ጥቃት ፈጸመ በማለት ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት እየሰራ እንደሆነ መታወቁ የአደባባይ ሚስጥር ሁኗል።
ስለሆነም የፋሽስታዊ አገዛዙን ጥሪ ተቀብለው በሚመጡ ተማሪዋች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ሃላፊነቱን መንግስት ነኝ የሚለው ጨፍጫፊው ቡድንና እራሳችሁ ተማሪዎች የምትወስዱ መሆኑን እንድታውቁ በአፅዕኖት እናሳስባለን።

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!
ድል ለፋኖ!

ጎጃም ዕዝ ፋኖ!
ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *