የፋኖ ትግልና የሌሎች ቀዳሚ ተጋድሎዎች ልዩነትና አንድነት

ህልውናን ማስቀጠል ድካም ይጠይቃል። ያለ ድካም ህልውና የሚኖረው ነገር ቢኖር ግዑዝ ወይንም በድን ብቻ ነው። አለትና አንዳንድ ማዕድናት መኖራቸው ዘለቄታዊ የሚሆነው ቀድሞውኑ ሕይወት አልባ ስለሆኑ ነው። የሰው ልጅ የፍጥረት ሁሉ ንጉሥ ሆኖ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ክቡር፥ ሕያው፥ ባለ አእምሮና ባለ ልቦና ነው።

የሰው ምድራዊ ህልውና ከሰማያዊ ተስፋው ጋር ተቆራኝቶ ሲታሰብና ሲኖር የሰው ልጅ እንደ ሰማያውያን መላእክት ንጽሕ፥ ትሁት፥ ስለ ሌላ መስዋዕት የሚሆን፥ አፍቃሪ፥ ሕብረታዊና ጀግና ይሆናል።

የሰው ልጅ ከምድር ሌላ አገር ሲሰወርበት፥ የመኖር ትርጉሙ መብላትና ዝሙታዊ ተራክቦ ብቻ ሲሆን የሰው ልጅ መገለጫ ስስት፥ ጥላቻ፥ ውድድር፥ ሽሚያ፥ ግድያ፥ ርኩሰት፥ ሐሰተኝነትና ለበላይነት የሚፈጠር ዘረኛ፥ የተከፋፈለ አራዊት ይሆናል።

የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያ ሰው መታወቂያው ኅብረት፥ ፍቅር፥ ቅድስና፥ እውነት፥ ፍትሕ፥ ሰብአዊነት፥ ቅድስና፥ የአገር ፍቅር ነበር። ስንኳስን እንደ ዛሬው የአራዊት ሥርዓት ሰው ሰውን ሊያሳድድ፥ ሊገድል፥ ሊያዋርድ፥ በሐሰት ሊያጠቁር፥ በዝሙት ሎረክስ፥ በክህነት ሊመነፍቅ ቀርቶ ያለውን ለወገኖ ትቶ በዛፍ ፍሬ በመኖር የኪሩቤልና ሱራፌል ጓደኛ ሆኖ ይኖሩም ነበር።

ሕዝቡ ከአንድ ቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ ከዚያም እስከ ሀገር ተዋራዳዊ የሥልጣን ሰንሰለት አለው። ሥልጣኑ የዕድሜ መበላለጥ ፥ የመንፈሳዊ ጸጋ፥ የኽህነት፥ የቤተሰብ ኃላፊነት፥ የመንደር ማኅበራዊ ኃላፊነት፥ የመከራ ጊዜ የጀግነነትና ጭግር የመፍታት ጥበብ የሚያሰጠው ክብር፥ የአካባቢና የአገር አስተዳደር፥ በቤተ እምነት የሚቀባ ተወራራሽ እልቅናና ንግሥና የክብር፥ የኃላፊነትና የተጠያቂነት ሰንሰለት ነበረው። ይዚህ ሰንሰለት ክብሩና ዘለቁታዊነቱ የሚመነጨው ከእምነት፥ ከባህል፥ ከረዥም ታሪካዊ የማኅበረሰብ መስተጋብርና በጽሑፍ ከሚገኝ ነባር ትርክት ማኅቀፍነት ሲሆን ከሁሉ በላይ በየደረጃው የሚገኘው ተዋረዳዊ ሥልጣን ተጠሪነቱ ከበላዩ ለሚገኝ ሁለተኛ ባለሥልጣን እና ለሚመለከው ፈጣሪም ነው። ሁለተኛው ባለሥልጣን ክብር የሚያገኘው በመጀመሪያ ደረጃ በጋራ በሚመለከው ፈጣሪ ሕግ ሲዳኝና እርሱን መፍራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። በፈጣሪው ላይ ላመጸ የበላይ አለመታዘዝ የተፈቀደ ሲሆን ፈጣሪውን በሚፈራና በሕጉ ለሚኖር፥ ክህነደትንና መለያየትን ለማይፈቅድ መሪዎ አለመገዛት ወንጀል ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ትርጉሙም ኃጢአት ነው።

በኢትዮጵያ ከዚህ ታላቅ፥ ነባር፥ ታሪካዊ፥ ምድራዊና ሰማያዊ ትርጉም ካለው ከቤተሰብ እከ ሀገር የተዘረጋ ተዋረዳዊ የኃላፊነት ሰንሰለት የተቆረጠችው ልጆቿ የራሳቸውን የዕውቀት፥ የእምነት፥ የባህልና የስነ መንግሥት ምሥጢራት ጠንቀቀው ሳየውቁ የባእዳንን ትምህርት ተግተው በማደጋቸውና በነባርነት ላይ ጠላት ሆነው በመነሳታቸወ እነው።

የፋኖነት ምሥጢርና እሤት፥ ጀግንነትና ጽናት መሠረቱ ይህ ለእግዚአብሔር፥ ለሰው ልጅ ክብር፥ ለበረዥም የተቀደሰ ትወፊትና ታሪክ ውስጥ የተላለፈ ሰብአዊነትና አገራዊነት ነው። ፋኖነት በወቅታዊነት የማይለዋወጥ፥ በስብሰባና በካድሬ ስብከት የማይቀየር፥ የዘመንና ንገሥታት ጠባይ መቀያየር የማይለውጠው ሆኖ የሚቀጥለው ከማይለዋወጥ የሰማይና ምድር ፈጣሪ፥ ሰውን በክብር ፈጥሮ ለዘላለማዊ ሕይወት በዚህ ምድር በመሬት በጊዜአዊነት ያኖረ፥ በጊዜአውነት ውስጥ ዘላለማዊነትንና የትውልድ ውርርስ መንፈስን ያሳደረ እግዚአብሔርን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ነው።

ባለፉት 70 ዓመታት ገደማ የተነሳው ትውልድ አዲስ ናፋቂ እና የነባርነት ጠላት ሆኖ የተቀረጸ ። ለዚህ ያበቃው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችን የባእዳን ትምህርት ብቻ አንዲማርና የራሱን ለሺዎች ዘመናት የአገር ነፃነት፥ የሕዝብ ሰላምና ውህደት፥ የእምነትና የባህል መሠረት የሆነውን በአጠቃላይ እንዳያውቅ በመደረጉ ነው። ዘመናውያኑ ልሂቃን የሚያቀነቀኑትና የሚጀመሩት ማንኛውም ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ የታዩት ፖለቲካዊ፥ ታሪካዊ፥ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ለውጦች ሁሉ በሚከተሉት መንገድ የነባር ጠልነታቸውን አረጋግጠዋል፦

፩) የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ፥ ታሪክ፥ ማኅበራዊ ሥሪት፥ ቅርሥ፥ የእምነቱ ተከታይ የሆነ ሕዝብን የአገር ባለቤትነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባትና ከፖለቲካዊ ተሳትፎ ማግለል፥ ኪነጥበብና ሀብትን ማውደም፥ መንጠቅ፥ በሌላ መተካት፥ በሐሰት ትርክት ማጥልሸት እና ምእመናኖቿን ከማፈናቀል በጅምላ እስከ መጨፍጨፍ፦

  • ኦርቶዶክስ ክርስትናን የድኽነትና የኋላቀርነት መንስዔ አድርጎ ያለ አንዳች ነቁጥ መረጃ በፕሮፓጋንዳ ብቻ መክሰስና ትውልድን ማሳሳት፥ ስም የማጥፋት ጋዜጦች፥ መጽሐፍት፥ ዘፈኖች፥ ንግግሮችን ማሳተምና ማሰራጨት፤
  • በኦርቶዶክሳዊት የሁለት ሺ ዘመናት የስነ መንግሥትና ማኅበራዊ ሥሪት ላይ በመዝት የተቀቡ ነገሥታትን በአከላ ከመግደል ታሪካቸው እስከማጠልሸት የምንግሥትና የፖለቲካ ፖሊሲ አድርጎ እሤቶቿን በማጥቃት ክርስቲያኖችን መግደል፥ የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሥፍራዊችን መንጠቅ፥ አቢያተ ክርስቲያናትን ማቃጠልና ማፍረስ፥
  • የቤተክርስቲያኒቷን አስተምህሮ በመቃረን የጎሣ ሲኖዶስ ለመፍጠር ጣልቃ ገብቶ በወታደር ጭምር ግድያዎችን መፈጸም፤
  • ገዳማውያንና የወደፊት አባቶች የሚሆኑ የአብነት ተማሪዎችን መፍጀት
  • ቅርሶቿን መውደምና፥ እርሷ አሳድጋ፥ አስተምራ፥ ታላላቅ ታሪክ አንዲሠሩ አድርጋ የታሪኳ አካላ ያደረገቻቸውን ነገሥታትና ታላላቅ ሰዎች ስም ማጥፋት፤
  • የመሬት ወራሪ፥ የነፍጠኛ ፊት መሪ በሚል ሐሰተኛ ክስ ለይ በመመሥረት ልጆቿን ማፍለስ፥ አቢያተክርስቲያኖቿን ማውደም፥ ጳጳሷን አንቆ መግደል፥ ፓትሪያርኳን ማሳደድ፥ በፖለቲካ መሥፈርት መሪዎች ማስⶄም፥
  • በመደበኛ ሠራዊትና በእርስ በእርስ በማዋጋት ክርስቲያኑን መጨረስ። ባህልና እምነቶች ያዳበሩትን እሤቶች መደምሰስ

፪) ነባር ባህልና እምነቶች ያዳበሩትን እሤቶች መደምሰስ

  • ንጉሥና ዙሃኑን እስከነ አሻራው በማጥፋት በምትኩ የሕፃናት ፍርድ ሸንጎ፥ ከባህል ውጭ የሆኑ ደም አፍሳሽ አብዮተኞችን ለሥልጣን ማብቃት
  • የረዥም ታሪክ የብዝኃነት መስተጋብር የፈጠሯቸውን ባህሎች፥ እምነቶችና ተቋሞቻቸውን በጠላትነት ፍርጆ በማፈራረስ በጎሣ ልሂቃን የቡድን ጥርነፋ ዜጎችን እርስ በእርስ ማፋጀት፥ ማሥበራዊና መንፈሳዊ ተቋማትን ማፈራረስ፥

፫) የታሪክ መዝገቦችን ማጥፋት፥ ይዘታቸውን በሐሰት ትርክት ትርጉም በማጥፋት አዳዲስ የሐሰት ትርክቶችን መተካት

  •  ንግሥተ ሳባ ተረት ተረት ናት በሚል የመጽሐፍቅዱስ፥ የትውፊት፥ የከርሠ ምድር ጥናቶች ምስክርነቶችን ሁሉ መካድ፥ በዚህ አስተሳሰብ የአገሪቷን የባህልና የቱሪዝም ፖሊሲዎች በመቃኘት አሻራን መደምሰስ፤
  •  ክብረ ነገሥት፥ ፍትሐ ነገሥት፥ ሌሎች የታሪክ መጽሐፍትና በሐሰተኛ ትርክት እና የአእምሮ ሕፃናት ተማሪዎችን በማሳመጽ ከትምህረት አውድ ማስወገድ፤
  • አጼዎቹ ጨቋኞች፥ ዘር አጥፊዎች፥ እጅና ጡት ቆራጮች ነበሩ፥ እናም በእነርሱ ቋንቋ የሚናገሩ፥ ተመሳሳይ እምነታቸውን የሚከተሉ በጭካኔ መቀጣት ይገባቸዋል በሚል ፖሊሲ ሐሰትን በመጽሐፍት ማሳተምና ማስተማር፥ የጥላቻ ሐውልቶች መትከል፥ ከመንግሥት መወሰኛ መዋቅር አስወግዶ መፍጀት፤
  •  ነባር ሕጎችን፥ ሥርዓተ ማኅበሮችና እምነቶችን በኋላቀርነትና በጎጅነት ፈርጆ ከአገራዊ የፖለቲካና የማኅበረሰብ አውድ ማስወገድ፤
  •  ገዳማትን ቀስ በቀስ ወደ መናፈሻነትና ወደ ሰዶማውያኑ ቱሪስቶች መዝናኛ ለመለወጥ በገዳማትና አብያተክርስቲያናት ዙሪያ መናፈሻ መገንባት፤
  •  የታሪክ ሐውልቶችን ማፍረስ፥ ባለታሪኮችን በሐሰት ትርክት በማጠልሸት የታሪክና የትውፊታዊ ውርርስ እንዲቋረጥ ማድረግ፤ በዚህ በተጠቀሰው አውድ ውስጥ ምን ተፈጠረ? ፩) ጥፋት ታውጆባቸው ለ36 ዓመታት ሁለገብ ጥቃት የተከፈተባቸው ወገኖች ራሳቸውን ከህልውና አደጋ ለመታደግ የትጥቅ ትግል ለመጀመር ተገደዱ፥ ሌላ ሰላማዊ መፍትሔ ሁሉ ሥልጣን ላይ በሚገኘው መንግሥት በሮቹ ተጠረቀሙ። የተጋድሎ ተናስኦት ፪) በህልውና ተጋድሎ የሚሳተፉ ሰዎች የሕይወት ትርጉም
    በዚህ ህልውና ተጋድሎ የሚሳተፉ ወጣቶች፥ አረጋውያን፥ ሴቶች፥ ካህናትና ሌሎች መነሻቸውና የሕይወት ትርጉማቸው፦
    •  ሰው ምንጩ አንድ አዳም በመሆኑ የሚበላለጥ የለም፥ ቋንቋ ማኅበራዊና በሰው ልጆች ኃጢአት በባቢሎን የተደባለቀ ነው፤ አንድነታችን በመንፈስ ቅዱስ አንዱን ቋንቋ ለሌላው በመግልጽ በጥመቀት ልጆች አጥር መሆኑ የተወገደበት የክእስቶስ ጸጋ ሆነ፥
    •  ሰው ክቡር ነው፥ በአምላኩ አምሳልና አርአያ ተፈጥሯልና፤ ሰውን የሚገድል የኅላሴን ህንፃ የሚያፈርስ ነውና ፈጣሪው እርሱን ያፍረሰዋል፥
    •  ሰማይና ምድር የተፈጠሩት ለሰው ልጆች አገልግሎት ነው፥ በዳግም ምጽዐተ ክርስቶስ ሰማይና ምድር ያልፋሉ የሰው ልጆች ግን ለዘላለም ሕይወትና ለዘላለም ኩነኔ ተጠርተው የሚገባቸው በተድላ፥ በሥራቸው ራሳቸውን ያስገሙ ክፉዎች በመከራ ለዘላለም ይኖራሉ፤ በዚህ ምድር በመሬት ስንኖር የዘላለም ሕይወትን ከሚያሳጣ ክፋት ሁሉ በመራቅ በግብረገብነት፥ ከሁሉ በላይ ሰውን በማፍቀርና እግዚአብሔርን በመፍራት መኖር፥
    • አገር ከእግዚአብሔር ለሚኖሩባት የተሰጠች፥ ሰዎች ሁሉ በየእምነታቸው፥ አቅማቸው፥ የማስተዋል ጸጋቸው አንዱ ለሌላው በነፃነት መልካም አስተዋጽኦ እያደረገባት እግዚአብሔርን የሚያስደስትባት ቦታ ናት፤ በሌላ መብትን በሚነፍግ፥ ሃይማኖት በሚያስቀይር፥ ዝረ በሚያጠፋ፥ ሰውን በሚያዋርድ ወራሪ፥ መሪዎች ልትገሀዛ አይገባም፤
    • ግፈኛ መንግሥት ከውጭ ወራሪ ጠላት ተለይቶ የማይታይ ከአገር ርስት ገዥነት ሊወገድ የሚገባው ነው።
    • በህልውና ተጋድሎ የሚሳተፉ ሰዎች መገለጫ፦
      • ትሁታን፥ጀግኖች፥
      • እውነተኞች፥
      • ከዝሙትና ከገንዘብ ፍቅር የራቁ፥
      • ምንደኝነትና ባንዳነትን የሚጸየፉ፥
      • በትዳርወይንምንጽህበመጠበቅየጸኑ፥
      • ጸረኢትዮጵያናጸረሃይማኖትአቋምባላቸውየፖለቲካተቋማትውስትተሳትፈውየማያውቁ፥

፫) ተጋዳዮች አገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚሰዉለት ዋና ምክኒያቶች

  •  አንድ ታጋይ የሚኖረው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ፥ ለእውነት ለመመስከር፥ ትውልድን ለአጠቀላይ ጥፋት በመዳን በእግዚአብሐሬእ ፊት በነፍስ ለመክበር፥ ለታሪክ የሰብእናና ክብር ጽፎ ለማሳየት፥ ነውረኞች ነውራቸውን ወደ ትውልድ አንዳያጋቡ በመከላከል የአባቶችን አደረጋ ላመስቀጠል
  •  የመጣው ጠላት ፈሪሐ እግዚአብሔር የለለው በመሆኑ “ስለ እግዚአብሔር ማረኝ” ብለው የሚያራሩት ሳይሆን እንደ አበድ አራዊት ማጥፋት የሚችለውን ሁሉ የሚያጠፋ ልቅ በመሆኑ መፍትሔው ማሸነፍ ብቻ ስለሆነ፤
  •  ያጋጠመን ጠላት የኅሊና፥ የታሪክ፥ የባህል፥ የሃይማኖትና የዓለም ሕግ ሁሉ የማይዳኘው ዲዳና ደንቆሮ እብድ መስሎ ከሕፃናት እስከ አረጋውያን የሚፈጅ፥ ሃይማኖት የሚያጠፋ፥ አገር የሚያፈርስ፥ በዘራፊዎችና ሐሰተኞች የተደራጀ፥ ካልተሸነፈ የማይገታ በመሆኑ፤
  •  ያጋጠመን ጠላት እንደ ሂትለርና ሞሶሎኒ፥ አንደ እስታሊንና እንደ አይሲስ እስላማዊ መንግሥት የሰው ልጆችን እንደ ዶሮሞ አንገት እየቆረጥ የሚጥል ዘር ለማጥፋት ግን ያለው በመሆኑ ካልተሸነፈ የማይገታ በመሆኑ —– ፬) ፋኖ እና የተለመደው የጎሣ ነፃ አውጭዎች ፍጹም ተቃርኖ አላቸው፤ የፋኖ ተኳሽነት
  •  ፋኖነት “ከነጻ አውጪና ነጻ ወጪ ትርክት” መፋታት አለብን በማለት ብዙ ተወያይቷል። ትግሉ ለውጥ ማምጣት ካለበት የኢትዮጵያ ህዝብ እያንዳንዱ “አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ” መሆን አለበት። ይህ ጥልቅ ፍልስፍና የቋጠረ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ለፋኖም ፈጣን እድገት “ እነሱ ይሄንን ቢያደርጉ” ከሚለው እሳቤ ተላቆ እኔ እኛ ምን እናድርግ ወደሚለው ነባር ባህል የተመለሰ ነው። በዚህ ውስጥ ቅጥረኝነት፥ አዛዥ መጠበቅ፥ ለቅሶና፥ ሽሽት፥ ተስፋ መቁረጥና እጅ መስጠት የለም።
  •  የኢትዮጵያ ህዝብ ለሶስት ሺ ዘመን በነጻነት የኖረው ከገነት ጦር ትምህርት ቤት ወይንም ከሀረር አካዳሚ በተመረቁ መኮንኖች ሳይሆን በራሳቸው መተማመን ባላቸው “አራሽ፣ ቀዳሽ እና ተኳሽ” ዜጎች ነበር። ዚያድ ባሬም ከብዙ አገሮች ጋር ተባብሮ፥ አንዲሁም በውስጥ ከሀዲዎች፥ ገንጣይና አስገንጣዮች እየተባሉ በወቅቱ መንግሥት ሲጠሩ ከነበሩት አካል ጋር ተናብቦ አገሪቷን በከበቡ ጊዜ 3 ወራት ለብለብ ኅልጠና ብቻ ከድሬ ደዋ እስከ ወልወልና ጎዴ ጠላትን አሳዶ ዋጋ ከፍሎ አገርን ከወረራ ያዳነ ሥልጠናው ሳይሆን ነባር የፋኖነት ባህል ነበር። ጣሊያንን ያንበረከከው ይኼው ፋኖነት ነበር። ይህ ባህል በሰንበት ነጭ ለብሰው ከነሱ በላይ ሀያል ልኡል ፈጣሪ አለ ብለው ተንበርክክው የሚጸልዩ የሚቀድሱ፣ ግፍ፣ ሀጥያት፣ ጭቡ መዘዝ አለው ብለው የሚያምኑ ኢትዮጵያኖች ናቸው። በራሳቸው ላይ ሊደረግ የማይፈልጉትን በሌላ ላይ የማያደርጉ፣ ትልቅ የሞራል ልዕልና ያላቸው ሰዎች ናቸው ግፍ መፈጸምና ፈጻሚውን የሚፋለሙት።
  •  በአዘቦት ቀን ደግሞ ቁምጣቸውን ታጥቀው ሞፈራቸውን ጨብጠው አፈር የሚገፏ፣ አርሰው የሚያበሉ ሲሆኑ ሀገር ሲወረር፣ ፍትህ ሲጓደል ደግሞ ጭስ የጠጣውን ጎራዴ፣ ጋሻና መውዜራቸውን ይዘው የሚዘምቱና ለነጻነታቸው ማንም ሳይሆን እራሳቸው ብቻ እንደሆኑ የተረዱ ሰዎች ስለነበሩ ነው።
  •  ዘመናዊ የአውሮፓውያን ትምህርት ሊያጠፋ የሞከረው ይሄንን ነው። ዘመናዊ ጦር ተቋቋመና ተኳሽነት ለሆለታና ለሀረር አካዳሚ ሰዎች ብቻ ይተው ተባለ። ዘመናዊ ትምህርት ቤት ተቋቋመና ገበሬ በየ ጥላው ስር፣ በየ ገዳሙ፣ በየ የኔታ ታዛ ስር ሀሁን መቁጠር ዳዊት መድገም ቀረ። ትምህርት ለራስ ጥቅም መሆኑ ቀረና ተቀጥሮ ሌላን ለማገልገል ሆነ።
  •  ሁለቱ ተወስደው ለህዝቡ የተተወው አፈር መግፋቱ ብቻ ሆነ። በዚህ ምክንያት በማጨው፣ በሱማሌ ጦርነት፣ በኤርትራ አማጭ፣ በህወሀት ታጣቂ የሚሸነፍ። እንደነ ብርሀኑ ጁላ አይነት አፈሙዝ ሲያዩ እጃቸውን ወደላይ የሚሰቅሉ የፈሪዎች መሰባሰቢያ ሆነ። በዚህ ምክንያት በወያኔ ተሸንፎ ተበተነ። አሁንም ይህ ነው ጉዞው።
  •  የፋኖ ጽንሰ ሀሳብ አቀንቃኞች የጠፋውን የተናቀውን የተረሳውን “አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ” ጽንሰ ሀሳብ አቧራውን አራግፈው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ እንዲሆን ትምህርት ተሰጠ።

የፋኖ የቀዳሽነት እሤቱ ነው

ቀዳሽ ማለትም ቤተ ክርስቲያን ገብቶ መቀደስን ብቻ ዪመለከት አይደለም፤ የእምነትና የአስተሳሰብ ማኅቀፍ ነው (worldview)፤ ቀዳሽንት የሰውን ክብር፥ ለእግዚአብሐሬእ የመገዛት የፍቅር ግዴታውን የማወቅ ምሥጢር ነው። በዚህ ምሥጢር ውስጥ ሰውን በሥጋ ግዘፉ የሚበላ የሚጠጣመ ቦታና መጠለያ፥ ማኅበራዊ ሥይወትና የተፈጥሮ ሀብት የሚያሻው በግልና በወል የሚኖር፥ በመንፈሱ በሥጋው በዘሚዘራው የዘላለም ሕይወትን የሚያገኝ ወይንም የሚያጣ እንደሚሆን አውቆ በመልካም ስነ ምግባር የመኖር የተከፈለ ነገር ግን ደግሞ የተዋሐደ ማንንተ ማለት ነው። ይህ ማንነት በአካለ ሥጋ መሥራትን ከመንፈሳቀዊ ዓለም መውረሻ መሥፍርት ጋር አዋህዶ ለመቅጽበትም ሳይለዩና ሳይከፋፍሉ ማሰብ፥ መናገርና ማድረግ ነው።

ፋኖ አራሽ ነው ሲባል ጠቃሚ ሥራዎችን ሁሉ በትጋት ይሠራል ማለትነው፥ ተኳሽ ነው ሲባል ጠቃሚ ሥራ የሚሠራበትን ማኅበረሰብና አገር፥ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚፈጽምበት ቤተ እምነትና ማኅበሩን ከአጥፊዎች ይከላከላል ማለት ነው። ፋኖነት የሥጋዊና መንፈሳዊ ዕወቀት ባለቤት፥ የሥጋዊና መንፈሳዊ አገልግሎት ፈጻሚነት በተዋህዶ የሚገለጹበት ሰብእና ማለት ነው።

ፋኖነት ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፈቃደ ያገናዘበ ፖለቲካ፥ አስተዳደር፥ የማምረት፥ ጠፍትሕ አሰጣጥ፥ የመከላከልና የመንገሥን ሁለገብ ሰብዊ ጸጋዎች አክብሮ መኖር ማለት ነው። ይህን የተሟላ መንገድ ለማደናቀፍ የሚሞክርን አስተምህሮ፥ የካል ጥቃት፥ የመንግሥት ሥርዓት ሁሉ በመዋጋት ወደ እውነተኝነት፥ ፍትሐዊነት፥ አንድነት፥ ፍቅርና ሰላም መመለስ “ቀዳሽነት” ነው። መከላከል ተኳሽነት ነው፥ አራሽነት ሠርቶ፥ አስተዳድሮና ዳኝቶ በሰላም መኖር ነው።

ዘመናውያኑ የምእራብና የሌኣለው የውጭ ገብ ትምህርት ልሂቃን እንደሚያስቡት አሁን ማሰብ መምራት የሚገባው ከኮሌጅ ሰርቲፊኬት የተስጣቸው ነጻነት ትርጉሙን ሳያውቁት ነጻ አውጪዎች ነን ለሚሉ ሰዎች ብቻ እንደሚገባ በመደምደም ራስን ማንገሥ ሳይሆን ሁሉም ባንገቱ ላይ ጭንቅላት የተገጠመለት ሁሉ በእግዚአብሔር አምሳልና አርአያ ተፈጥሯልና በተግባር በሚገለጽው ጸጋው መሥራት፥ መከላከልና መቀደስ የተሰጠውና ግዴታው ነው የሚል ነው።

አሁን በአማራ ክልል የአብይ አህመድን የኦነግ/ኦሮሙማ ዘር አጥፊ ቡድንም ሆነ ሌላው በሆዱ ብቻ የሚያስብ የዘር ሠራዊት ወይንም ባህር ተሻግሮ የሚመጣ ጠላት በየቦታው እንደ ቆቅ የሚያስደነብረው እያንዳንዱ ፋኖ ሀሳቢና የሀሳብ ሰው በመሆኑ ነው። ከላይ ወደታች፣ ከመሪ፣ ከፓሊት ቢሮ ከነጻ አውጪ ሊቀመንበር ጠባብ ጭንቅላት የሚመነጭ ሳይሆን ከእያንዳንዱ ሰብአዊነትን፥ ፍትሐዊነትን፥ ክብረ-ሰብእና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ከታጠቀ የፋኖ ታጋይ የሚመነጭ የድኅነት ኃይል ነው።

ለዚህ ነው ዛሬ ከደንብ ልብሱ በስተቀርና ኮኮቡ ውጪ እያንዳንዱ ፋኖ ከተማራኪው ብርሀኑ ጁላ ወይንም ህወሓት በጉዲፈቻ ካሳደገው ጄኔራል አበባው የማያንሰው። የሀሳብ ሰው/ቀዳሽ/ ያስባል፣ ያቅዳል፣ ይተገብራል። በጦርነት መሀከል ለውጥ ሲመጣ አስቦ ራሱን አሰላለፍ ይቀይራል። አለቃው መሪው በዚህ ሂድ በዚህ አጥቃ የሚለው አይጠብቅም። ለዚህ ነው ትግሉ ሲጀመር የተንቀሳቀሰው 55ሺ ፋኖ እንደ ተራ ወታደር ሳይሆ እንደ 55ሺ ጀነራል የተንቀሳቀሰው። ለዚህ ነው በ6 ቀናት ውስጥ ኦነጋውያን በፈረሳቸው በብአዴናውያን በኩል ሕዝቡን ሊያጠፉበት ያከማቹትን የመሳሪያ መጋዘን ወርሶ ፣ እስር ቤት አፍርሶ እስረኛ ነጻ አውጥቶ የብአዴንን መዋቅር አፈራርሶ የተመለሰው። ሁሉም ስለሚያስብ ተናቦ 54 ከተማ ተቆጣጥሮ ያለ ጀነራልና ኮለኔል ትዕዛዝ ተጠቃቅሶ ከተማን ጥሎ የወጣው።

ፋኖ ከመአከል በጀነራል ትዕዛዝ ሳይሆን በራሱ አይምሮ አስቦ አስልቶ ተከራክሮ ወስኖ የሚያጠቃ በመሆኑ መንግስት ከመአክል ወደ እዝ የሚፈስ መረጃ ያለው መስሎት እንቅልፍ አጥቶ ያድራል። ይሁንና የሚጠለፍም የሚደመጥም ከላይ ወደታች የሚፈስ መረጃ የለም። ሐሰት መፈብረክ፥ ማጭበርበሪያ መፍጠር፥ ሤራ መጎንጎን፥ ፕሮፓጋንዳ መንዛት፥ ብዙ ጉባኤ መጥራትና ካድሬ ማሰማራት ለፋኖ አያስፈልገዉም። መንግሥትና ዘረኞች በዘር ማጥፋት እቅዳቸው በተግባር የሚፈጽሙት ራሱን የቻለ አንቂ ነው፥ ትጥቁ ከአጥፊው መንግሥት ሠራዊት የሚገኝ ነው፥ ጉልበት፥ ልበ ሙሉነት ከእውነትና ከእግዚአብሑር ይሰጣል።

ለዚህ ነው ፋኖ ለአብይ አህመድ ዘረኛ መንግሥትና የንግሥና እቅድ ታላቅ የማይገፋ ቋጥኝ ሆኖ የተከሰተበት። ፋኖነት ከቁማር፥ ከከህደት፥ ከአስመሳይነት፥ ከዘራፊነት፥ ከሌብነትና አመንዝራነት የነጻ መልካም ልቦናዎች ሁሉ ውስጥ የሚገኝ የአግዚአብሔር ጸጋ በመሆኑ በሁሉም ቋንቋ ተናጋሪዎች ውስጥ የሚቀጣጠልና ጊዜውን የሚጠበቅ በመሆኑ ሲጥል፣ ሲገል፣ ሲቆጣጠር እንጂ በሬዱዮ ሲያወራ ሲንቀሳቀስ የማይታያቸው።

ዘረኝነት፥ ራስ ወዳድነት፥ የመንገሥ ብቻ ሳይሆን የመመለክ ፍተወት ያጨለመው በጠባብዋ በአብይ ጭንቅላት የሚመራው ትግል ማሸነፍ የሚችለው ሙሉ ሰብእናቸውን ለጠበቁ፥ ኅሊና ያላቸውና በፈርሐ እግዚአብሔር እየተመሩ፥ ፍትሕና እውነትን ታጥቀው በነፃነት የሚያስቡ ሰዎችን ማሸነፍ አይችልም። አብይና ሥርዓቱ

ፋኖ በራሱ አሳቢ ማለትም ቀዳሽ ባይሆን ኖሮ ግንኙነት ሲቋረጥ ትዕዛዝ ሲጠብቅ ይጠቃል፣ ይመታል፣ ይፈርሳል ብለው ነበር። በውስጡ የተተከለው የሰብአዊነት እሤት የሚፈርስ አገር፥ የሚደፈር ቤተሃይመኖት፥ የምትደፈር እናት፥ የሚገደል አረጋዊ እያየ ቆሞ አንድ ኦነግ-ኦሮሙማው መንግሥት

በሻሸመኔና በወለጋ አልታዘዝኩም እያለ ቆሞ ሰው ማስፈጀት አይችልም። አዛዡ ጄኔራሉ ሳይሆን ኅሊናውና ፈሪሐ እግዚአብሔር ነው። ፋኖ ጠባቂ ሳይሆን አሳቢና ወሳኝ በመሆኑ ይሄው ትግሉ ተፉጠነ እንጂ አልተዳከመም። እኛም የምንከታተለው ዛሬ ሌሊት አስር ሰአት ላይ ፋኖ አራት ኪሎን፣ ለገጣፎ ወይንም ደሴ እንደሚያጠቃ አናውቅም። ስለዚህ ሚስጥርም አይባክንም።

ተኳሽነቱ በምን ይገለጻል?

ሁለተኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊነት ሰበብ እንዲጥል የተደረገው ተኳሽነትን ነበር። የግድ ከገነት ጦር ትምህርት ቤት፣ ከሁርሶ፣ ከብላቴ ወይንም ከብር ሸለቆ መመረቅ ለተኳሽነት ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ አንዲታሰብ የሚያስገድዱት ሁኔታዎች የተጀመሩት የዛሬ 70 ዓመት ገደማ ነው። ይህ አጭር ዕድሜ ያለው አሠራር የ3000 ዘመናት ባህልና እሤትን ሊያደበዝዘው አልቻለም። የጠፋ መስሏቸው አገርና ሕዝብን የደፈሩት እሳት እንደገላመጠው ላስቲክ ተኮማትረው እስኪያንሠራሩ አድርጠዋል።

የፋኖ መሪዎች ይህን በዘመናዊነት ስም ኅሊናውንና ፈርሐ እግዚአብሔርን፥ አገርና ሰብእና ወደ ጎን አድርጎ በምንዳ ገመድነት እየተጎተተ በጄራል ትዕዛዝ እናት አባቲን ሳይቀር በቦንም የሚያጋይ፥ ሕፃናት የሚደፍር፥ ከተባ በጀት የሚያጋይ አገልጋይ የሆነውን፥ ድምበሩን ክፍት አድርጎ ሠፈር ለሠፈር ለአብይ አህመድ አሊ የንጌሥነት ቅዠት አዉን መሆን ወገኑን የሚፈጅ የስሕተት ማኅቀፍን ነው ያረመው።

ናበሩ ወታደር የአንድ ዜጋውን ነፍስ ማዳን ቢያቅተው ደሙ የፈሰሰበት አፈር ፈልጎ በመቆፈር በክብር የሚቀብር ነበር። የዛሬው ከአረቦችና ከቱርክ፥ አንዲሁም ከሜሎቹ የአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተባብሮና ተበድሮ በጅምላ ጨራሽ መሣሪያ የሚፈጅ ሆኖ ተገኘ። ቀድሞ አንዲህ አልነበረም። የኢትዮጵያ ወቷደር ለመሆን ለዘመናት አባት ለልጁ፣ ታላቅ ወንድም ለትንሽ እያስተማረ እንጂ ልጁን ሆለታ ወይንም ብላቴና ልኮ አይደለም የሚያሰልጥነው። ተኩስ የሚያስተምረው አባቱ አጎቱ እንጂ ግድ የሁርሶ መቶ አለቃ ወይንም ሻምበል አይደለም። ስለዚህ ስልጠና በግድ በዳስ ተቀምጦ ግራ ቀኝ ሰልፍ በመማር፣ ሰላምታ መስጠት ልብስ መተኮስና ስልፍ ማሳመር ሳይሆን መፍታት መግጠም፣ ትንፋሽን ዋት አድርጎ አልሞ መተኮስ ነው። ይህ ደግሞ አባት ለልጁ እውቀቱንም ጠመንጃውንም የሚያወርሰው ብሂል ነው። ስለዚህ የፋኖም ስልጠና በየቤቱ እንዲሆን ተወሰነ።

መንግስት ስልጠና የፈቀደበት ግዜ በምንጃር፣ በቡልጋ፣ በደብረብርሀን፣ በደሴ በጎንደር ወዘተ በአደባባይ ስልጠና ተደርጓል። ከዛ አብይና አበባው ዘመነ ካሴን እንገላለን ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን ብለው ከዘመቱበት ቀን ጀምሮ ስልጠና ባደባባይ ተከለከለ። ከዛ በአደባባይ በስታዲዮም ሳይሆን በቤት፣ በጓዳ፣ በሰፈር፣ በመንደር ሆነ። ለተኩስ ብቻ ቆላ ወርዶ በመተኮስ ሆነ።

ለዚህ ነው ይህ ሁሉ ፋኖ ከየት መጣ እስኪባል ድረስ የአማራን ከተሞችና ገጠሮች በአንድ ግዜ ያጥለቀለቀው። አባት ለልጁ ፋኖ ለጓዱ እሳት ዳር ቁጭ አርጎ ስልጠና ይሰጣል። አሁንም በየቤቱ በየመንደሩ ስልጠናው ቀጥሏል። እድሜ ለብርሀኑ ጅሎ የነበረው የጥይትና ይክላሽ ችግር ተፈቷል።

ከጥይትና ክላሽ ቀጥሎ የሰው ቁጥር አስፈላጊ ነው። ይህ ችግር መንግስት ቀይ ሽብር በማወጁና በተቆጣጠራቸው ከተሞች በንጹሀን ላይ ነጻ እርምጃ በመውሰዱ የሰው ሀይል እጥረት የለም። ያመነበትም የፈራውም ፋኖን ተከትሎ ወጥቷል። የሚቀጥለው ዘመቻ በኮማንዶና ደረጃ በሰለጠነ ፋኖ ነው። ስለዚህ እንደ ጥንቱ ፋኖ የሀሳብ ሰው/ ቀዳሽ ከሆነ፣ አንድ ስው ተኳሽ ከሆነ ነጻነቱን ለመቀዳጀ አራሽም መሆን አለበት።

አራሽነት ምንድ ነው?

አራሽም እንደ ቀዳሽ ጥልቅ ጽንሰ ሀሳብ ከጀርባው አለ። ይሄም እራስን መቻል ነው (self sufficiency) ። ፋኖ ጠመንጃ ገዝቶ የሰጠው ስው የለም። የመጀመሪያዎቹ ስልጠናዎች ሲሰጡ ጠመንጃ የሌለው ስው አናሰለጥንም ተብሎ ብዙ ተመልሷል። ከዛ ሄዶ በሬውን ሸጦ፣ ባጃጁን ሸጦ፣ እቁብ ሰብስቦ፣ ዘመድ አዝማድ አስገድዶ ጠመንጃውን ገዝቶ ወደ ስልጠና የተመለሰው። ጎንደር የመጀመሪያው ህወሀትን ለማስቆም ሲዘምቱ ምንሽር፣ ክላሽ፣ መውዜር የያዙ ነበሩ። የዛሬውን ቁጥር ባላውቅም የደብረ ብርሀን ባህርዳር ጎንደርና ወሎ፣ጎጃም እና 54 ከተሞች ዘመቻ ሲካሄድ 55ሺ ክላሽ ታጣቂ ተንቀሳቅሷል። ይህንን ክላሽ የገዛለት ማንም የለም። ማስፈታትም ያልተቻለው ለዚህ ነው።

አራሽ ማለት እራሱን የሚመግብ እራሱን የሚያስታጥቅ እራሱን የሚያለብስ ማለት ነው።

ለዚህ ነው ፋኖ በውጪ እርዳታ ላይ ያልተመሰረተው። ግማሹ ንብረቱን ሸጦ፣ እቃውን ሸጦ ትጥቁን ቀለቡን ይዞ ወደ ጫካ የገባው። ለዚህ ነው የማይዘርፈው የማይቀማው። ባንክ መዝረፍ ወታደር ካንፕን ከመደምሰስ በጣም ቀላል ነው። ግን የባንክ ብር አላጓጓውም። እንዲያውም ባንክ እንዳይዘረፍ ዘብ ቆመ።

ህዝብም ይሄንን ስላወቀ አካፍሎ ያበላል ያስጠልላል ጥይት ይሰጣል።

ፋኖ ከባለ ሀብቶችና ከውጪ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ለማግኘት ብዙ ሞክሮ ነበር። አንድ ባለ ጸጋ አንድ ብር አልስጠውም፣ ጥቅማቸውን መንግስት ይቀማናል ብለው ፋኖም የትም አይደርስም ብለው ምንም አልረዱም። የዲያስፓራውም ድጋፍ ከድል ቦሀላ ተነቃቃ እንጂ ትግሉን ለማስጀመር የሚያስችል የሳተላይት ስልክ እንኳን የላከ የለም። አሁን ግን ተነቃቅቷል ሁሉም የሚችለውን እያደረገ ነው ። ይህንን ስል ቀድሞ ገብቶት ያገዘ የለም ለማለት አይደለም። ከጅምሩ የገባቸው ያላቸውን የረዱ አርቆ አሳቢዎች ነበሩ። ይሁንና ጥቂት ነው።

ፋኖ ግን ለድል የሚበቃው ቀዳሽ፣ ተኳሽ እና አራሽ የሚለውን የአባቶቻችንን ጽንሰ ሀሳብ አቧራውን አራግፎ ስለ ተላበስ ነው። ይህንን ጽንሰ ሀሳብ 120 ሚሊዮኑም ኢትዮጵያዊ ሊያጠናው ሊረዳውና ሊለብሰው ይገባል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ አውጪ መጠበቅ ማቆም አለበት። ነጻ እራስን ማውጣት እንጂ ማንም ነጻነትን አይሰጥም።

ስለዚህ ነጻነት የሚፈልግ ስው አራሽ መሆን አለበት። ይህ ማለት መሬት መቆፈር ሳይሆን በራስ ሀብት ጉልበትና ጥረት ላይ የተመሰረተን ትግል ማካሄድ ነው። ይህ እነሱ ብር ቢልኩ፣ ራዲዮ ቢልኩ፣ ቀለብ ቢልኩ፣ እንዲህ ቢያደርጉ ከማለት ያድነናል። ሁሉም እጅ እግር አለው። ባለው ሀብትና ጉልበት መታገል አለበት።

ሁሉም ለመብቱ ተኳሽ መሆን አለበት። ተኳሽ ማለት ቃታ መሳብ ብቻም አይደለም። የተግባር ሰው መሆን ማለት ነው። ጸሀፊ በብእሩ፣ ዶ/ር በመርፌው፣ የህግ ባለሞያው በጥብቅናው፣ መምህሩ በማንቃት፣ ነጋዴው በብሩ፣ ውጪ ያለው በሰልፍ በተቃውሞው በመዋጮው፣ ወታደሩ አልታዘዝን ወንጀል አልፈጽምን በማለት፣ አቃቤ ህጉ በሀሰት አልከስም፣ ዳኛው አልፈርድም በማለት ነው። ተኳሽ ማለት ይህ ነው። እኔ ፋኖ ነኝ ማለት በዚህ ነው።

አራሽ ደግሞ እነሱ እንዲህ ቢያደርጉ ሳይሆን እኔ ምን ላድርግ። ለነጻነቴ መብቴ ሀገሬ ወገኔ ባንዲራዬ ምን ላድርግ ማለት ነው። ዛሬ መቶ ብር የረዳ ሁለት ጥይት ገዛ ማለት ነው። ነጻ የምንወጣው ሁላችንም አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ስንሆን ብቻ ነው። እነሱ እንዲህ ቢያደርጉ ለ50 አመት ተሞክሮ ነጻነት አላመጣም።

ስለዚህ እርሶስ ለመብቶና ነጻነትዎ አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ለመሆን ተዘጋጅተዋል? ቢዘጋጁ ይሻላል። የሩዋንዳ የፓል የካጋሜ ፓትርዬቲክ ፍሮንት ወደ ኪጋሌ ሲጠጋ የሁቱ ሚሊሻዎች 900 ሺ ንጹሀን ቱሲዎችን አርደው ጠበቋቸው። አሁንም እነ አዳነች አቤቤና እነ ሽመልስ አብዱሳ አብዮት ጠባቂ እያሰለጠኑ ያሉት ሊያርዷችሁ ነውና ብትዘጋጁ ከመታረድ ትድናላችሁ።

ዝግጅቱ ድግሞ ቀላል ነው። መጀመሪያ ቀዳሽ መሆን ነው። ይህ ማለት ለራስ ለሚስት ለልጅ ህይወት ፋኖ ግንቦት ሰባት ኢህአፓ ሳይሆን እራስ ማሰብ አለብህ ማለት ነው። የአዳነች አቤቤና የሽመልስ ልዩ ሀይል ለጭፍጨፋ ሲመጣ ተስልፌ እታረዳለሁ ወይስ መጥረቢያዬን ይዤ በሬን ዘግቼ ልጆቼን አድናለሁ ብሎ ማሰብ ማለት ነው። ስለዚህ የቤት የሰፈር የመንደር የቀበሌ የከተማ የመከላከል እቅድ በየአንዳንዱ ጭንቅላት መጎልበት አለበት። እነሱ እንዲህ ቢያደርጉ በህይወት አያስቀጥልህም። ከወለጋ ተማሩ። መንግስት እንዲህ ቢያደርግ፣ ሰራዊቱ ቢመጣ፣ የአለማቀፍ ሀይል ቢያወግዝ እያሉ ታረዱ በዶዘር ተቀበሩ። መጨረሻው ከራሳቸው በቀር ማንም እንደማይደርስላቸው ሲረዱ፣ ዱላቸውን ዘነዘናቸውን ማጭዳቸውን ታጥቀው እራሳቸውን መከላከል ገቡ። ይሄው የጅምላ ግድያውን አስቆሙ።

ለነገ አትበል። ነገ ጥዋት ሚስቴን ሊያርድ ልጄን ሊደፍር ሀይል ቢመጣ ምን አደርጋለሁ ብለህ ጠይቅ። ከዛ ከጎረቤትህ ከሰፈርህ ሰው ጋር ሆነህ እራስህን ልጅህን ሚስት እንዴት ለመከላከል እንዳለብህ አስብ ተዘጋጅ። ያልጠረጠረ ተመነጠረ ተብሏልና እንዳትመነጠር። ፋኖ የተፈጠረው ያደገው

ወለጋ ላይ የሚያርደው የትልጠቀ ሀይል ቢመጣ ምን አደርጋለሁ ብሎ ስለጠየቀ ነው። ይህንን ሲጠይቅ መልሱ መዘጋጀት፣ መታጠቅና መታገል መሆኑ ቁልጭ ብሎ ታየው። አብን ኢዜማ መንግስት ይጠብቅብል ቢል ይትልረድ ነበር።

በድጋሜ የአዲስ አበባ ናዝሬት አሰላ ጎባ ጅማ ድሬደዋ ሻሸመኔ ህዝብ ከወለጋ ሰዎች ተማሩ። መንግስትን አምነው ታረዱ። ቁርጣቸውን ሲያውቁ ግን አራሽ፣ ተኳሽ፣ ቀዳሽ ሆነው እራሳቸውን እየተከላከሉ ነው።

ስለዚህ ነጻ አውጪ የምትጠብቅ ሁሉ ተነስና እራስህን አደራጅ። አራሽ ተኳሽ ቀዳሽ ሁን። ይህንን አልሰማ ብለህ ብትታረድ በፌስ ቡክ ሻማ ይበራልሀል እንጂ ፍትህ አታገኝም። ንቃ!

የፋኖ ትግልና የሌሎች ቀዳሚ ተጋድሎዎች ልዩነትና አንድነት

ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ የተነሱ የትጥቅና የፖለቲካ ትግል ንቅናቄዎች ከፋኖ ተጋድሎ በቅርጽ፥ በፍልስፍናና በግብ የተለዩ ናቸው። ሁሉም መነሻቸው የተውሶ ፖለቲካዊ ርእዮት፥ በነፃነት ስም መለያየት፥ “እኛ እና እነርሱ” የሚል የጠላትና የዳጅ ጎራ፥ የሐሰት ትርክትና የጥቂት ልሂቃን ለዚያውም በተውሶ ትምህርት አነቱ ተብለው የአገራቸውን አስተሳሰብ ከፍተኛ ድንቁርና ውስጥ የሚኖሩ የልሂቃን አእምሮ የሚበይነው ግብና ርእይ ነው።

የፋኖ ትግል እውነት፥ ፍትሕ፥ ሰብአዊነት፥ የሰው ልጅ ክብርና የዜጎች ሁሉ በእኩል በአገራቸው ላይና በአገራቸው ጉዳይ ባለቤትነት፥ ሁሉም ሰው በህልውና የመኖር ዋስተናው በአገሩ ውስጥ እና ከውጭ ሲሆን በመንግሥት አስተባባሪነት፥ መንግሥት ሲጠፋ በሕዝብ ፋኖነት የማስከበር ተጋድሎ ነው። ፋኖነት የሚመለክ መሪ፥ በዘርና በፕሮፓጋንዳ ድጋፍ፥ ወይንም ከውጭ አካላት እየተላላከ የሚመራ ቡድን የማይቀበል ትግሉ በሚወልዳቸው፥ ሕዝብ እውቅና በሚሰጣቸው ጀግኖች መካከል የሚወለድ ነው። የአመራር ጥበቡም በተግባር የተፈተነ፥ ከፊት ፊት እየሄደ ራሱን ለሌሎች ሰጥቶ የሚደምቅ አንጂ ከሩቅና በቡድን የተክለ ሰውነት ግንባታ ገዝፎ በትግሎ ሜዳ ላይ እየተሽሎከሎከ የወደፊት ንጉሣችሁ እኔ ነኝ በሚል ብልጠት የሚኖር አይደለም። የፋኖ ተጋድሎ የህልውና እንጂ የቡድን የዘረፋ፥ የመክበርና ሥልጣን የማስጠበቅ የቀደሙት የጎሣ ነፃ አውጭዎች የዘረፋ ማኅበር አይደለም። ሁሉም ሰብእናውን ክብር ያወቀ፥ ኅሊናውን ያከበረ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ አገሩን የሚወድ፥ የሕዝብ ሉዓላዊነትን የተቀበለ፥ ራሱን ስለ ወገኑ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኖ በተግባር የተያየ ከሶማሌ እስከ አፋርና ትግራይ፥ ከቤኒሻንጉል ጋንቤላና ሞያሌ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፋኖ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *