ናሁ ሰናይ ብዙ የተደላደለ ሕይወትና ሌሎች የሚመኙት የወደፊት እድል በእጁ ነበር፡፡ ሰው እንደ እንስሳ ሲታረድ፣ እናቶች ሆዳቸው ተቀዶ ሲጣሉ፣ ድሆች በጅምላ በዶዘር ሲቀበሩ፣ መናኞች በገዳማት ሲታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች ሲፈርሱ፣ ሕጻናት “ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም” ሲሉ፣ ሕዝብ በወጠጤዎች ተንቆ ቤቱ በላዩ ላይ ሲፈርስ ከዳር ሆኜ ከማየት እኔ ሕይወቴ ትሰዋ ብሎ ነው። ናሁ ሰናይ አንዳርጌ የንጹኃን ደም እንደጎርፍ ሲፈስ እንደ አብዛኛው ሰው ዳር ይዞ የተደላደለ ኑሮ መኖር ይችል ነበር። ወይም እንደ አብዛኛው አሜሪካ አውሮፓ ተሰዶ፣ ሰዎች ሲታረዱ በፌስ ቡክ ሻማ እያበራ፥ በሌሎች መስዋዕትነት የሚመጠ ነፃነት ጠብቆ የድል አጥቢያ አርበኛ በመሆን የተደላደለ ኑሮው ሳይነካ መቀጠል ይችል ነበር።
ሌሎች ይታገሉ እኔ በገንዘብ፣ በሐሳብ፣ በጽሁፍና በአመራር አግዛለሁ ማለትም ይችል ነበር። በአርግጥ ይህም ዋጋው የሚናቅ የትግል አስተዋጽኦ ባይሆንም ራስን ከመስጠት አንጻር ሲመዘን የሞተ እባብን በረዥም ዘንግ ከመንገድ ላይ ሕፃናት እንዳይደነግጡ ዞር የማድረግ ያህል አስተዋጽኦ ነውና ነው። ይሁንና ናሁ ሰናይ አንዳርጌ የልጆችን መታረድ፣ የእናቶችን ሆድ መቀደድ፣ የአዛውንቶችን መዋረድ፣ የገዳማትን መፍረስ እያየ አርፎ የሚተኛ ልብ እና ሕሊና አልነበረውም። ይህ ሂደት አጠቃላይ የህዝብ እልቂት፥ የእምነቶች መደምሰስና የአገር መፍረስ ጎዞ መሆኑ ገብቶታል።
ናሁ ሰናይ አንዳርጌ ሻማ በፌስ ቡክ በማብራት፣ በጸሎትና በተማጽኖ የነ አብይ አህመድን፣ የነ ሽመልስ አብዲሳን፣ የነ ብርሀኑ ጁላን፣ የነ አዳነች አበቤን እና የነ ይልማ መርዳሳን የአማራን፥ የክርስቲያንና የእስላም ደም ጥማት ማስቆም እንደማይቻል ሲረዳ፤ የሞቀ ህይወቱን፣ የተደላደለ ኑሮውን እርግፍ አድርጎ ትቶ የንጹኃንን ደም ለመታደግ አምባገነኖችን ለማስቆም ጫካ ገባ። ቆሎ ቆርጥሞ፣ በወንዝ ውሀ በሶ በጥብጦ፣ ጭቃ ላይ ቅጠል ጎዝጉዞ፣ አንድ ሸርጥ ተከናንቦ መተኛትን መረጠ። በመጨረሻም ሕጻናት የሚያርዱትንና ሕዝብን የናቁትን ለመበቀልና ከእኩይ ስራቸው ለማስቆም ተመልሶ አዲስ አበባ መጣ፤ ለሚሞቱትና ለሚፈናቀሉት እሱ ሕይወቱንም ሰጠ። በጠላቶቹ ልብ ፍርሀት ዘርቶ፣ ለበርካታ ወጣቶች ደግሞ አርዓያ ሆኖ አልፏል።
ናሁ ሰናይ ከኛ ሲለይ ልባችን ቢሰበርም የትግሉን ችቦ በማቀጣጠሉና በጀግንነት ጠላቱን ጥሎ በመውደቁ፣ ለአዲስ አበባ ወጣት የትግሉን መንገድ አመላክቷል። በዚህ ዘመን የኢግሊዝ ሊግ ኳስ፥ ጃንቦ ድራፈት፥ የፑልና ሌሎች ጨዋታ፥ የዝሙትና የጭፈራ ቤት አዳር፥ የኮንድሚኑየም ስጦታና ጠአነስተኛ ብድር እድል፥ “የእየመጡ ነው መዝሙር”፥ ጡንቻን በጅምናዝየም አውፍሮ በደካማ ወንድም ላይ መንጠራራትና ለሴቶች ደረት ማሳየት፥ ካህንና መነኩሴ እያስፈጁ ለስደት ዲቪ ሞልቶ እየተሳሉ መጠበቅ ላይ የተጠመደውን ወጣት ሁሉ የናሁ ሰናይ ሞት የሕሊና ፍርድና የእምነት ምስክርነት አቁሞበት ወደ አምላኩ ሄዷል።
ናሁ ሰናይ የጀመረውን ይህንን የክብር ጎዳና ሌሎች እንደሚጨርሱት ጥርጥር የለውም። አምባገነኖች ሕጻናትንና እናቶችን እያረዱ፣ ደማቸውን እየጠጡ ካሁን ወዲያ የሰላም እንቅልፍ መተኛት እንደማይችሉና፣ ለቅሶው በአማራና በኦርቶዶክስ በሙስሊም ገበሬ ቤት ብቻ ሳይሆን በኦፒዲኦና በብአዴን ነፍሰ ገዳዮች ቤት ይገባል።
ናሁ ሰናይ አንዳርጌ በተኩሱ ለአዲስ አበባ ወጣት የማንቂያ ደውል ደውሏል። በደሙ ደግሞ አዲስ እንደ ናሁ ሰናይ ሞትን የሚንቁ ጀግኖች ችግኝ ተክሏል። በቅርብ ቀን ያብባል፤ ፍሬው ያፈራል። ካሁን ወዲያ አንዱ ለብዙው መስዋዕት ልሁን ብሎ ይሽቀዳደማል እንጂ አያፈገፍግም። ናሁሰናይ እንደ ዘረኞቹ በኢሰብአዊነት፥ በኢፍትሓዊነት፥ በጸረ አገርነትና በሐሰት ተተክሎ የስውነት ስትወጣበት እንደሚጠወልገው ፖለቲከⶉች የመርዝ አረም አይደለም የተከለው። ይህ ተክል የእውነት፥ የፍትሕ፥ የክብረ-ሰብእና የትውልድ ልዕልና አምድ ነው።
እነ አብይ እኛው መሀል እንደ ወጥ ቁጭ ብለው ከበናችኋል እያሉ የስነ ልቦና ጨዋታ ሊጫወቱ ይሞክራሉ። ማን ማንን እንደከበበ በቅርብ ቀን ይታያል።
ሚሊዮኖች ነን የአብይን አራት ኪሎ ግቢ ከበን ያለነው። እኛ ሚሊዮኖች ነን የነ አዳነች አቤቤን የኦልድ አይሮፕላን ግቢ ከበን ያለነው። እኛ ሚሊዮኖች ነን የነ ሽመልስንና የነ ይልማ መርዳሳን ቪላ ከበን ያለነው።
አዲስ አበባንም ከበን ያለነው እኛው ስብእናችን የተሟላ፥ ለእውነት መሰዋት ባህላችን የሆነ፥ ሕፃናትና ሴቶችን፥ ካህናትንና መነኮሳት ከሚያርዱት ፈሪዎች ቁጥር እጅግ የምንበልጥ የኢትዮጵያ ልጆች ነን። አብይን ሽመልስ በአበልና በፕሮፓጋንዳ መግደያ አስታጥቀው ካሰለፉት በሚበልጥ መቶ እጥፍ እውነትን፥ ፍትሕን፥ ሰብአዊነትንና ጀግንነትን የታጠቅን ማኅበረሰቦች ነን አዲስ አበባን ከበን ያለነው። “እጠራጋለሁ” የሚለው ትእቢት ቅዠት ሆኖ ስትንበረከኩ የምናሳይበት አቋም ላይ እንገኛለን።
ሲወጡ ሲገቡ ጫማ እያስጠረግን፣ ካፌ ቁጭ ብለን፣ ትራፊክ ፖሊስ ሆነን፣ ፌዴራል ሆነን እናጠናቸዋለን። ባለ ቀይ ኮፍያ ሆነን፣ በቅርብ ርቀት ሆነን ቀን እንቆጥራለን፣ በሞተርና በእግራችን በአጠገባቸው እናልፋለን። ታዛዥ ሴክሬተሪ፣ ጠራጊ፣ በር ጠባቂ ሆነን ጉዳቸውን እናያለን። እኛ ባሕር ነን፣ እኛ ሕዝብ ነን፣ እነሱ አሳዎች ናቸው።
እኛ አፍንጫቸውን ሲጎረጎሩ፣ ሰያዛጉ፣ እንጥላቸውን እናያለን። እኛ እናያቸዋለን፤ እነሱ ግን እያዩንም። እኛ ሚሊዮን ነን፤ እኛ ባሕሩ ነን፤ እነሱ ትናንሾቹ አሳዎች ናቸው።
ሲገቡ ሲወጡ፣ ውስኪ ሲራጩ፣ ሲሳደቡ፣ አምቦ ውኃ እየቀዳን፣ በረዶ እያቀረብን፣ በአዲስ አበባ በባሕር ዳር እናደምጣቸዋለን።
እኛ ሕዝብ ነን፣ ባሕር ነን፣ እነሱ ጥቂት ገዢዎች ናቸው።
ከተማዋን በአስቸኳይ ለቀው ካልወጡ በአማራ ገበሬ ቤት፣ በገዳምና በመስጊድ የሚሰማው ለቅሶ በነ አብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አበቤ፣ አበባው ታደሰ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ዳንኤል ክብረት ቤት ይሆናል።
ሕዝብ ተነስቷል፣ አምሯል፣ አቂሟል፤ ፊሽካው እስኪናፋ እየጠበቀ ነው። በሠራዊቱ ውስጥም አንጀቱ የቆሰለ፣ የእናቱ ቤት በድሮን የነደደ፣ ዘመዶቹ የታረዱበት፣ እህቱ የተደፈረችበትና አምላኩ የተሰደበበት ቀኑን በጉጉት የሚጠብቅ በመቶ ሺህ ነው። የመጨረሻው ፊሽካ ሲነፋ ክላሹን ይዞ አለቆቹን በኤሌክትሪክ ሽቦ እየጠፈረ ያቀርባቸዋል።
ናሁ ሰናይ አልሞተም፤ እንደ ሰናፍጭ ዘር አንድ ሆኖ ወድቆ ብዙ ሆኖ ተወለደ እንጂ።
ስለዚህ ፊሽካው ተነፍቷል። ለቅሶው ኦፒዲኦ ቤት ይሆናል።
የናሁ ሰናይ ቤተሰብን መጽናናት እንዲሰጥልን፣ ለታረዱት ሕጻናት፣ ሆዳቸው እየተቀደደ ለተገደሉ እናቶች፣ በጅምላ ለተፈጁት ክርስቲያኖች እምቢ ብሎ ሕይወቱን ሰጥቷልና፣ ፈጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት ያኑርልን።
እንሆ ይሄም ያልፋል። የመንግሥቱ ቅልብ የግቢ ዘበኛ ሆኖ ሕዝብን ሲረግጥ የነበረው ተዋርዶ ተበትኗል። የመለስም አጋዚ ጦር ስንዴ ጠባቂ ለማኝ ሆኗል። ለሀገሩ፣ ለመብቱ፣ ለነጻነቱ የሚሞት ግን ሀውልቱን እራሱ ገንብቶ ነው የሚያልፈው። የዛሬ ሃምሳና መቶ ዓመት ከወለጋና ከአርሲ ከእርድ የተረፉት ዜጎች የልጅ ልጆች፣ ናሁ ሰናይ ለኛ ሕይወቱን ሰጠ ይላሉ። ሀውልት ያቆሙለታል።
ናሁ ሰናይ ያስጮኸው ጥይት ካሁን ወድያ ተሰልፈን አንታረድም የሚል ነው። ገድለን እንሞታለን እንጂ። የናሁ ሰናይ ጥይት አንዴ ከአፈሙዝ ወጥቶ የካርቶን ዒላማ መለማመጃ ላይ በማረፍ የሚረሳ ጥይት አይደለም፤ በገዳዮቻችን የአብይ እና የሽመልስ አብዲሳ ወንጀለኛ ህሊና ውስጥ ወደእንረሱ የሚተኮስ፤ እንጣፋችሁ ተብለን ዒላማ ለተደረግነው ከእኛ አፈሙዝ ሳታቋርጥ የምትወጣ ጥይት ናት። የህች ጥይት ጸጥ፥ እረጭ የምትለው ሰብአዊነት፥ ፍትህ፥ እኩልነት ስፈኖ ወንጀለኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫነቃ ወርደው ለፍርድ ሲቀርቡ ብቻና ብቻ ነው!
ከፋኖ አንድነት ምክር ቤት ለሕዝብ የቀረበ ጥሪ፡
ትላንት የናሁ ሰናይን ሞት ሲሰሙ ከማንም ትዕዛዝ ሳይጠብቁ ጥቁር ለብሰው የወጡ፣ በየ ቤተ እምነቱ ያሰቡት ብዙ ነበሩ። ሕዝብ ሲበቃው አስታዋሽ አይሻም። ስለሆነም፡-
፩ኛ፣ በነጻ መሬት ያላችሁ በመላው ኢትዮጵያ ከመጪው እሮብ ጀምሮ ጥቁር ለብሳችሁ በየቤተ እምነታችሁ ጀግናው ወንድማችንን እናስበው።
፪ኛ፣ በአዲስ አበባ የምትኖሩ ድፍረቱ ያላችሁ አድርጉት፤ ያልቻላችሁም በልባችሁ ጥቁር ይዛችሁ ይሄንን ነፍሰ ገዳይ ስርዓት ለማስወገድ “ከእኔ ምን ማድረግ ይጠበቃል” ብላችሁ በቀን አንድ ነገር ለማድረግ ወስኑ። በትንሹ የመንግሥትን ሚዲያ ያለማየት፣ በስብሰባ ተገኝቶ ለካድሬ አለማጨብጨብ፣ የካድሬን ትእዛዝ አለመቀበል፣ ለስርዓቱ የሚገድለውን የሚደልለውን ፊት መንሳት፥ መመዝገብ፥ በምስል/ድምጽ መረጃ ይዞ ማጋለጥ፥ ማግለልና መተባበር መተው ይበቃል።
፫ኛ፣ ፋኖ በአጠገቡ የሌለ ሰው የለም። በግላችሁ አግዙ፣ ለዘመዶቻችሁ ብር ላኩ። እነሱ ከድሃ መሶባቸው እያካፈሉ ነው። እነሱ የሚበሉት አላቸው ማለት፣ ለፋኖ የሚያካፍሉት አላቸው ማለት ነው። እኛ ሕዝብ ነን፣ እኛ ባህሩ ነን። ለሊስትሮ የምንሰጠው 20 ብር በመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሲባዛ 200 ሚሊዮን ብር ነው። የማኪያቶዬን ለነጻነቴ በቀን ብንል በአጭር ቀን ነጻ እንወጣለን። የራሳችንን ነጻነት ማወጅ ስንችል፣ ነጻ አውጪ ጠባቂዎች አንሁን። ጭፈራ፥ ስካር፥ ምንዝር ቤት ማደር፥ ቴሌቪዥንና ጌም ስር ተንበርክኮ የወገን ደም እንደ ጎርፍ በሚፈስባት አገር ለመዝናናት መሞከር፥ ሰርግ መደገስ፥ የልጆች ልደት ማክበር፥ በእግዚአብሔርና በታሪክ ፊት ፍርድ እንዳለበት እናስታውስ።
፬ኛ፣ ከእሮብ ጀምሮ እስከ አርብ የሶስት ቀን ሀዘን ታውጇል። ይሄንን የሀዘን ቀን በኦሮሚያም ያላችሁ በኦፒዲኦ ከአልጋው ተቀስቅሶ ወጥቶ በሽመልስ አብዲሳ ትእዛዝ ለተረሸነው አቶ በቴ ኡርጌሳ የሀዘን ቀን እናድርገው። በግፍ ለሚሞቱት አብረን እንቁም።
፭ኛ፣ በነጻ መሬት ያላችሁ ከጄኔራል ይልማ መርዳሳ ድሮንስ ጥቃት እየተጠበቃችሁ ጥቁር ለብሳችሁ በቤተ ክርስቲያን በመስጊዳችሁ ናሁ ሰናይን አስቡ። በአዲስ አበባ ያላችሁ በምትችሉት ሕሊናችሁ እና አቅማችሁ በፈቀደው ሁሉ ኃይላችሁን አሳዩ። ለናሁ ሰናይ ጸልዩ፣ ሻማችሁን አብሩ።
፮፣ በውጪ ያላችሁ ጥቁር ለብሳችሁ በፌስ ቡክ በሶሻል ሚዲያ ግለጹ። የምሳችሁን ወጪ አንድ መቶ ዶላር በምታውቁት መንገድ በናሁ ሰናይ ስም የምትገዛ ጥይት መግዢያ ላኩ። ምክንያት አትደርድሩ። አንድ ዘመዳችሁን ፋኖ መርዳት ሀገርን መርዳት ነው። ጉራ ምስጋና አትሹ ደብቃችሁ ስጡ። ናሁ ሰናይ ተሰዶ የዲሲ ብርጌድ መሆን ይችል ነበር ነገር ግን ለሚታረዱት ሕይወቱን ሰጠ። እኛ ባሕር ነን፤ እኛ ሕዝብ ነን፤ ትንሽ ትንሽ ካደረግን በአጭር ቀን ውጤት እናመጣለን። እኛ ቀኑን ሙሉ የዩትዩብ የድል ዜና ከምናዳምጥ አንድ ሰዓት ተጨማሪ ሰርተን ሕይወታቸውን ለሚሰጡት ብናግዝ ውጤት እናመጣለን። አንድ የእግር ኳስ ቡድን በአድናቂዎቹና በተመልካቾቹ ብዛት ብቻ ውጤት አያመጣም። በሜዳው ገብተው በሚጫወቱት ብርቱዎች እንጂ። ስለዚህ እኔም ናሁ ሰናይ ነኝ ከዛሬ ጀምሬ የአቅሜን እታገላለሁ እንበል። ለሴኔተሮቻችን የሚታረዱ ሕጻናትን ፎቶ እንላክ፣ ደብዳቤ እንጻፍ፤ 20 ዶላር በቀን እንመድብ፣ ስርዓቱን ሊጠቅም የሚችል ነገር ባለማድረግ እንታገል። ታጋዮችን እየቀለቡ ያሉ ዘመዶቻችንን ሸክም እናቅልላቸው። እርዳታ ስታደርጉ ብራችሁን ለሚያባክኑ፥ ሰው ለመከፋፈልና ራሳቸውን ለማስተዋወቅ በሚወራጩ ከንተዎች በኩል ከማድረግ ተጠንቀቁ!!
፯: የአዲስ አበባና የመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች በቃ በሉ። ቆማችሁ አትታረዱ፤ በማንም ፈሪ በጥፊ አትወልወሉ፤ በየ እስር ቤቱ አትታጎሩ። እምቢ በሉ። ለእምቢተኝነቱ የአካል ብቃታችሁን አጠናክሩ። የዛሬን የጫትና የድራፍት ብር ለናሁ ሰናይ ለወገኔ በሉ። ሱሰኞች ሱሳችሁን መልካም የመስዋዕትነት ዝግጅት በማድረግ በመልካም የጀግንነት ሱስ ቀይሩት። ተወያዩ ተነጋገሩ፣ ከቤታችሁ ከግቢያችሁ ሳትወጡ የአካል ብቃት ወታደራዊ ስልጠና ሊሰጧችሁ የሚችሉ ሚሊዮኖች ናቸው። እኛ ሕዝብ ነን፣ እኛ ባሕሩ ነንና ሁሉ ነገር አለን። የተሰለበው ስነ ልቦናችን ነው።
ዩቲዩብን ትታችሁ የአባቶቻችሁን የጀግንነት፣ የነጻነት፣ የፋኖነት፣ የአልገዛም ባይነት ታሪክ አንብቡ። ራሳችሁን ለታላቅነት ለመሪነት አዘጋጁ። ሱሪያችሁን ከፍ አድርጋችሁ ታጠቁት፥ በአሰብአዊነትና በስግብግብነት ተመርዘው ዘር ለማጥፋት ጥፍርና ቀንድ አብቅለው ባገጠጡት የነውር ሠራዊት ፊት አትቅለስለሱ። ፈሪዎች እንደ ጀግና ምህረት አያውቁም፥ ምሳቸው ልካቸውን ማሳየት ብቻና ብቻ ነው። እርሱም ናሁሰናይ መሆን!!!
ሙሉ እጅ እግር ይዞ የሚበላው አጥቶ በየመብራቱ ላይ ከመለመን ሂድ ወደ ምንጃር፣ ወደ ቡልጋ፣ ወደ ወሎ፣ ወደ ጎጃም፣ ወደ ጎንደር፣ አጥበው አብልተው አጠጥተው አዲስ ናሁ ሰናይ ያደርጉሃል። መብትህንም እንጀራህንም አትለምን። ሰው ሁን።
ወጣቶች በቃችሁ። እኛ ባሕሩ ነን፣ እኛ ሕዝብ ነን! አንድ መቶ የማይሞሉ የኦፒዲኦ ወጠጤዎችን አትፍሩ። ጫት የምትቅሙበትን፣ ድራፍት የምትጠጡበትን ለሶስት ቀን አቁማችሁ ለሚታገሉ ስጡ። የሚታገሉት ለናንተ ምስጢር አይደሉም። ታውቋችኋላችሁ አድርሱልን በሉ።
እናንተም የአካል ብቃት ላይ አተኩሩ፤ የአካል ብቃት ካለ፣ ተኩስ መማሩ የሁለት ቀን ልምምድ ነው። እናንተ የናሁ ሰናይ አዲስ አበባ ፋኖ የመጀመርያ ምሩቃን ናችሁ። እኔም ለሚታረዱት ለሚፈናቀሉት ፋኖ ነኝ በሉ።
እንደ ናሁ ሰናይ ለሚነደው ቤተ እምነቴ፣ ለተደፈረችው ውዲቷ እህቴ፣ ለሚጨፈጨፈው ወገኔ ብላችሁ ዘምሩ።
እኛ መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮኖች ነን፣ እኛ ባሕሩ ነን። ነፍሰ ገዳዮቹ ግን አንድ ሺ አይሞሉም። በሠራዊቱ ውስጥም አንጀታቸው አርሮ፣ ጠመንጃቸውን አቀባብለው የመጨረሻው ፊሽካ እስኪነፋ በተጠንቀቅ ያሉ ብዙ መቶ ሺ ናቸው።
እውነቱ ይህ ነው፦ የክልል ታጣቂዎች፥ ልዩ ኃይል ፖለቲሶች፥ የትግራይ ሠራዊት፥ የኦሮሚያና የሶማሌ፥ የአፋርና የደቡብ ጠቅላላ ከእውነትና ከሰብአዊንት ጋር የቆመ ነው። መውጫና የተመቻቸ መንግድ ነው እየጠበቀ ያለው። በየቋንቋው እየተነጋገራችሁ መንገድ አሳዩት። በቅርብ የአብይ መከላከያ ከፋኖና ከሁሉም ታጣቂዎች ጋር ተቀላቅሎ በአንድነት ለኢትዮጵያ ይቆማል። አትጠራጠሩ።
ናሁ ሰናይ የሞተው “ለእኔ ነው”፣ ካሁን ወዲያ “ወላሂ አማራ አልሆንም” እንዳለችው ልጅ አንልም በሉ። ኢትዮጵያ አማራም፥ ኦሮሞም፥ አፋርም፥ ትግሬም፥ ሱማሌም፥ ጋሞም፥ ኾንሶም ወዘተ ሆኖ ሰው በእኩልነት፥ በሁሉ ቦታና ሁኔታ ውስጥ በቤተሰብነት የሚኖራበት ትሆናለች። ይህ የሚሆነው አንተ ናሁሰናይ ስትሆን ነው።
በቅርብ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌና፣ ኦልድ ኤርፓርት ቁጭ ያሉት በእኛ ተከበው ልጆቻቸውን ማሸሽ ይጀምራሉ። እነ አበባው አሽሽተዋል፣ አዳነች አቤቤ አሽሽታለች፣ ብአዴኖችም መውጫ ቀዳዳ አብይ ዘግቶባቸው እንጂ ወጥተው ያልቁ ነበር። ቪዛ ዛሬ በሚሊዮን ብር በየኤምባሲው እየተሸጠ ነው። እኛንም ሀገራችንንም ጥለው የሚፈተለኩበት ቀን ቀርቧል።
አንድ ወጠጤ አምባገነን በኛ ተከቦ መካከላችን እንደ ወጥ ቁጭ ብሎ የሚያላግጥበት ዘመን አልፏል። ፋኖ በሁሉ ቦታ አለ፤ በቀይ ኮፍያ ሪፐብሊካን ጋርድ ውስጥም መንገድ እስከሚጠርገውም ድረስ ፋኖ አለ።
የመጨረሻው ፊሽካ ይነፋል፤ ጠብቁን።