ወልደማርያም
መጀመሪያ ከሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የፋኖ መሪ ነወይ ካላችሁ መልሱ አዎ ነው። እስክንድር በመጀመሪያ መሪ አልሆንም ብሎ ነበር። በዳዊት ጭቅጨቃና አንዳንዴም ስድብ ጭምር ነው የአንድነት ግንባር ብሎ የዳዊት ምናባዊ ድርጅት ሊቀመንበር የሆነው።
ሻለቃ ዳዊት የእስክንድር የሀብታሙና የመከታው ነፍስ አባት፣ የዶላር ምንጭና የዚህ ሁሉ መርዝ ጠማቂ እሱ ነው። እንደ ጣልያኖቹ ማፍያ ከፊት ብቅ ሳይል ሁሉን የሚያሽከሩክረው ግጭት የሚጠምቀው፣ ቁረጠው ፍለጠው የሚለው God father እሱ ነው።
ጠላት ከግጭት ይጠቀማል ብለን በርካታ የፋኖ አደራጆችና ደጋፊዎች እስቲ ይሞክረው አይሳካለትም፣ ከሱ ጋር አተከሮ መግጠም ከትግሉ ያዘናጋል ተብሎ ተተወ። ያኔ “ታላቁ እስክንድር” የሚል የልብወለድ ገጸ ባህሪ ይዞ ብቅ ሲል ግዴለም ይሞክር የፋኖ ግንባር የሚባል ምድር ላይ ያለ ሀይል የለም። የፋኖ አንድነት ምክር ቤት በወንድማማችነት በፈቃደኝነት አርማጭሆ ላይ የተመሰረተ አንድነት ነውና አያፈርሰውም የሚል ግንዛቤ ነበር።
ሻለቃ ዳዊት እንደለመደው ብሩን ከሰበሰበ በኋላ የዩቲዩብ ጉራ ሲያልቅ የፋኖ ግንባር ይከስማልና ተዉት አተካሮ አትግጠሙ ተብሎ ተተወ።
አንድ ሰሞን እነ ሀብታሙ አያሌው ‘ሆያ ሆዬ” አሉ። ተጨፈረ ታላቁ እስክንድር ግን ታላቁ መሆኑ ቀረና የጎጃም ፋኖዎች እባክህ አትበጥብጠን፣ አትከፋፍለን፣ ከፈለግክ የውጪ ግንኙነት ሀላፊ ብለን እንሹምህ አሉት። አንተ ባላደራጀኸው፣ አንተ ወታደር አይደለህ ተኩሰህ አትገድል፣ ሮጠህ አታመልጥ፣ ወታደራዊ አመራርና እቅድ ከአንተ አቅምና እውቀት ውጪ ነው ተብሎ ተመከረ። መጀመሪያ ተስማማ ከዛ ዳዊትን ሲጠይቀው ከሊቀመንበርነት ውጪ እንዳትቀበል አለው።
ሻለቃ ዳዊት በደርግ ሽኩቻ ውስጥ ያለፈና አሁንም አስተሳሰቡ እንደ ሻለቃ መንግስቱና ለገሰ አስፋው ነው። ስለዚህ የእስክንድር በእንግድነት መጥቶ አዛዥ ካልሆንኩ ሲል ሁሉም ከፋው፣ ሁሉም ናቀው። ከዛ ሁሉም ፊት ሲነሳው ወደ ሸዋ ተሻገረ። የጎጃም ፋኖ በሰላም ሸኝቶት ተመለሰ።
ከዛ በፊት ግን በዚህ በደርግ ሻለቃ ተጠልፎ እስክንድር ባክኖ እንዳይቀር ለትግሉ ብቁ ሰው ባይሆንም ከዚህ በፊት በመታሰሩ ከዳዊት ስር ነጻ እናውጣውና ተብሎ ረጅም ልብን የሚነካ ደብዳቤ ተጻፈለት።
ጭብጡም በእምነት እንጂ በብር የሚገዛ ፋኖ ላንተም አደጋ ነው። በግድ መሪ ነኝ አትበል። ስራህ መሪ ያደርግሀል ተባለ። እባክህ የዚህ የሻለቃ ዳዊት መሳሪያ አትሁን ተጠቅሞ ይጥልሀል። አንተን በስም የማያውቁህ አንተን ለማዳን ከ570 ገዳማውያንና ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ፋኖ ወንድም እኅቶቻችን በደብረ ኤልያስ የተጨፈጨፉት የአንተን እንድ ነፍስ ሊያተርፏ ነው። የአንተ አንድ ነፍስ ከአምስ መቶ በላይ በሆነ ሰው ነፍስ የተመነዘረው የፋኖነት እሤትና የአማራ ሕዝብ ለታጋይ ያለውን ክብር ያሳያል። እባክ ከአሁን በኋላ ደም በሚያፋስስ ነገር ውስጥ አትግባ፤ አርፈህ ተቀመጥ ተብሎ ተለመነ።
ላንተ የሞቱት ወጣቶች ሊቀመንበር ስለሆንክ ሳይሆን አንድ የዓላማ ወንድማቸው ስለሆንክ ነው። የአንተ መሞት ወይም መያዝ ለፋኖ መጥፎ ዜና ስለሚሆን ነው ተባለ። ደብዳቤው ጊዜው ሲደርስ ይታተማል። እስክንድርን ወንድም ይሆነናል ብለው ያስጠለሉ፣ አብረውት የኖሩ፣ ስለ ፋኖ እሱን ያስተዋወቁ ሰዎች ስም በደብዳቤው ውስጥ ስላለበት እነዚህን በከተማ ያደራጁ የነበሩ ሰዎችን ስም ላለማውጣት ነው እስካሁን ያልወጣው።
ይህ በጽሁፍ በጥንቃቄ በብዙ ጓዶች ታርሞ ተዘጋጅቶ ተሰጠው። እሱ ግን ከዳዊት አሽከርነት እራስን ማላቀቅ አልፈቀደም። ከዛ ሁሉም እንትን እንደነካ እንጨት ተጠየፈው፤ እናም ጎጃምን ጥሎ ተሰደደ።
ጎጃም ሰላም አገኘ። እስክንድር ሸዋ በገባ ማግስት ግን ሸዋ መታመስ ጀመረ። የመጀመሪያ የነ ደሳለኝን ድሽቃና 600 ጥይት አስታጥቆ እብድ ፋኖ ገዛ። ፋኖ መሳሪያውን ይዞ ወደ መከታው እንዲያመጣ ገንዘብ ከፈለው። ልጁ ሰርቆ ጠፋ። የነ ደሳለኝ ብርጌድ ተከታትሎ ሊያስመልስ ሲል በነ መከታው ተኩስ ተከፍቶ ከደሳለኝ አንድ ፋኖ ከመከታው ሁለት ቆሰለ። ይህ ነገር ለመጀመሪያ ግዜ ፋኖ ሌላ ፋኖ ላይ የተኮሰበት ቀን ነው። የደሳለኝ ፋኖዎች ወደ ካንፓቸው ተመልሰው ሽማግሌ ላኩ። ሽማግሌዎቹ መከታውን እና ደሳለኝን እንዲገናኙ ቀጠሮ ያዙ። ከዛ ደሳለኝ ሁለት አጃቢ ይዞ ከወንድም ፋኖዎች ጋር ለመነጋገር ሄደ። መከታው ግን ጦር ይዞ ነበር የጠበቀው። ደሳለኝ ስብሰባው ላይ ሲደርስ ከበውትጥቁን አስፈትተው አሰሩት። ይህ ወሬ በወደ ደሳለኝ ካምፕ ደረሰ። ሌሎች ብርጌዶችም ይህንን መከታው የሚባል ሰውዬ ብልግና ያዩ ሁሉ በንዴት ሄደን ደምስሰን እናስፈታዋለን ብለው ጉዞ ጀመሩ። በሀገርም በውጪ ያሉ ደጋፊዎች እባካችሁ በፋኖ ላይ ተኩስ አትክፈቱ መጥፎ ነው። እኛ ደሳለኝን እናስፈታዋለን ለአንድ ሌሊት ታገሱ ተባለ። እሺ ብለው ከበባውን አቆሙ። እስክንድርና መከታው የመጣውን ቁጣ መቋቋም እንደማይችሉ ሲገባቸው ደሳለኝን ለቀቁ። ይህ ደም መፍሰስ በብልሀት ታለፈ። መነሻው በሻለቃ ዳዊት ባርነት ሥር የሚኖረው የእስክንድር ፋኖነትን የማይመጥን ትንሽ አስተሳሰብ ነው።
አሁንም በአርበኛ በአሰግድ ላይ የተደገመው ይህ ነው። ፋኖ ያጠቃኛል ብሎ ባላሰበበት ግዜ በራሱ ጠባቂ ሊያስገድሉት ሞከሩ። ጠባቂው ተሸብሮ ቃታ መሳብ አቃተው። ከዛ ሸሽቶ እስክንድር ባቀረበለት መኪና ሸሸ። ይህ እንዳልተሳካ ሲረዱ ድንገት ማጀቴን ከበው ጦር ከፈቱ። የመከታው ሰዎች ልክ እንደ ደሳለኝ ፋኖን አንገልም ብለው ከማጀቴ ሸሽተው ቆላ ገቡ። መከታውና እስክንድር ጭፈራቸውን ይዘው የአሰግድን ቤት እየበረበሩ በዚህ ፋራሽ ላይ እየተኛ በዚህ ፍሪጅ እየተጠቀመ ታገልኩ ይላል የሚል ቪዲዮ ለቀቁ።
እንግዲህ ሲረዳዱ የነበሩ ፋኖዎች፣ ደብረ ብርሀንን ለመቆጣጠር አንድ ላይ ተቀላቅለው የዘመቱ የአሰግድ፣ መከታው፣ የኢንጂኔር ደሳለኝ ብርጌዶች እስክንድር ሸዋ ከገባ በኋላ መከታው ሁሉንም ገሎ ብቸኛ የሸዋ ፋኖ መሪ ለመሆን ለምን አሰበ? ይህንን ሀሳብ ከየት አመጣው? ይህ በደርግ ውስጥ የነበረ መፈጃጀት እንዴት አንደኛ ግብ ሆኖ ፋኖነ ንን በሚሉ ሰዎች መካከል ሊታይ ቻለ? መልሱ ቀላል ነው የሻለቃ ዳዊትን አሻራ ታገኛላችሁ።
እየተሳደደ ያለን ሰው ያለበትን መረጃ ሰጥተው አሰግድ እንዲያዝ አደረጉ። ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደምም ከውጪ መጥቶ ሲታገል የነበረን ፋኖ አንተ “የአንድ አማራ” እና የእነ አሰግድ ሰላይ ነህ ብሎ መከታው አስሮ የሞት ፍርድ ፈረደበት። ልጁ በስብሰባ ያነሳው ነገር “ለፋኖ የተላከ ብር የት ነው ያለው?” የሚል ነገር ብቻ ነው። ይህን ለምን ተጠየቅሁ የሚለው መከታው ተቆጣ። የፋይናስ ክፍል ሀላፊው የሚባለውን ሰው ከመከታው ውጪ ማንም የሚያውቅ የለም፤ ጥያቄውን መመለስ የሚችለው እርሱ መከታው ብቻ ነው በሚል በስብሰባው ጥያቄውን በግልጽ አስቀምጦ እራሱን ነጻ ያወጣል። በዚህ ቂም የያዘው መከታው ስንት ትግል የታገለውን ዲያስፓራ ፋኖ እንዲታሰርና እንዲረሸን ትእዛዝ ሰጥቶ ይሄዳል። ከዛ የከተማው ወጣቶች እስር ቤቱን ወረው ልጁን ያስፈቱና ወደ አዲስ አበባ እንዲሄድ ያደርጉታል። አዲስ አበባ እንደገባ በደህንነቶች ተጠልፎ ታሰረ። ማን አዲስ አበባ እንደገባ ጠቆመ? ማን ስልኩን ሰጠ የሚለው እስካሁን መልስ አላገኘም። ግን የመከታውና የእስክንድር ስራ መሆኑን መገመት ይቻላል። አሁንም ከግድያና ከወረራ ያመለጠው አሰግድ በድንገት እንዲያዝ ተደረገ።
ወደ ሻለቃ ዳዊት ስንመለስ። ዳዊት ተወልዶ ያደገው ለስልጣን ደም በማፍሰስ ነው። ይህ 50 ዓመታትን የዘለቀ የታሪኩ አንኳር ነው።
ሻለቃ ዳዊት ለምን ድል አያመጣም?
መጀመሪያ “ከስህተቱ የማይማር ስህተቱን ይደግማል” ይባላል። ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በ80 አመት እድሜው አንድ ቀን አሸንፎ አያውቅም። ዕድሜ ልኩን እያደራጀ ወደ ሽንፈት የመራው፣ ከዚህ በላይ እሱ ከፍ ከፍ የሚያድርግ ከመሰለው ደግሞ ምንም አይነት ሚስጥር መጠበቅ የማይችል ወንፊት ነው።
ዳዊት ወንፊትነቱን የሚያጋልጥ ሁለት መጽሀፍት ጽፏል። አንብቡት። አንደኛው የክህደት መሬት የሚል ነው። ይሄም ለሻቢያና ወያኔ ሰርቶ መጨረሻ ላይ እንዴት በእነመለስ ዜናዊ እንደተከዳ የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ደግሞ What a Life ብሎ ጉራ ብቻ የተነሰነሰበት የራሱ ግለ ታሪክ ነው። ሶስተኛም በቅርብ ጽፏል። አላነበብኩትም።
በሁሉቱም መጽሀፍት ውስጥ እንዴት እነ ጄኔራል ፋንታ በላይን፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ፣ ጄኔራል አምሀ ደስታ ያቀዱትን መፈንቅለ መንግስት እንደተቀላቀለ። ከዛ የነገሩትን ሚስጥር ይዞ ናቅፋ ድረስ ሄዶ ለኢሳያስ አፈወርቄና ለመለስ ዜናዊ ነግሮ እንደተመለስ በራሱ ላይ ይመሰክራል።
እገነጠላለሁ ብሎ ለ30 ዓመት የተዋጋ ለሻቢያ መሪ ዋነኛ አላማው የኢትዮጵያ ጦር መደምሰስ እና ከኤርትራ መውጣት እንጂ የመንግስቱ ኃይለማርያም መባረርና በሌላ የህዝብ ድጋፍ ያለው ጠንካራ ወታደራዊ መንግስት መቋቋም አይደለም። ይሄንን እንኳን ማመዛዘን የሚችል ጭንቅላት የሌለው እንደ ቁመቱ ሀሳቡም ድንክ የሆነ ነው።
ለሻቢያና ለወያኔ ከመንግስት መገልበጥ በላይ የጀነራሎቹ መረሸንና የሰራዊቱ መበተን ወደ ነጻነት ያቀርባቸዋል። ስለዚህኢሳይያስና መለስ ለመንግሥቱ ይህን መፈንቅለ መንግሥት እንደታቀደ ሹክ አሉት። መንግስቱ ከወ/ሮ ገነት ጋር በሰጠው ቃለ መጠይቅ ጀነራሎቹ መፈንቅለ መንግስት እንዳሰቡ። ሁለት ሁለት እየሆኑ ታመምን እያሉ የጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደሚተኙ እንደሚያውቅ መስክሯል። አሁን የዳዊትን መጽሀፍ ሳነብ የመፈንቅለ መንግስቱን እቅድ ሻቢያና ወያኔ ለመንግስት እንዲደርሰውና አድፍጦ እንዲጠብቃቸውና በመጨረሻም ጀነራሎቹን ረሽኖ በኤርትራ እና በትግራይ ሲፋለም የነበረው ጦር እንዲበተን ያደረጉት።
ሻሉቃ ዳዊት እንግዲህ What a Life ብሎ 600 ገድ መጽሀፍ የጻፈው እንዲህ አይነት አርቆ ማሰብ የማይችል ጭንቅላት ተሸክሞ ነው።
ሁለተኛው መጽሀፍ ደግሞ የክህደት መሬት ብሎ ያሳተመው መለስንና ህወሓትን የሚያወግዝበት የምሬት መጽሀፍ ነው። መፈንቅለ መንግስት ሲከሽፍ የኢትዮጵያ ጭቁን መኮንኖች ንቅናቄ የሚል ፈጥሮ ከህወሀት ጋር በመስራትና የኢትዮጵያ መኮንኖች እንዲከዱ ሰራ። እነ መለስ ዜናዊ ሀሳቡን ወስደው የሱን ቅስቀሳ ተጠቅመው እንደነ ጀኔራል በረታው ገሞራን፣ እነኮለኔል ሰረቀ ብርሀንን ይዘው የኢትዮጵያ ሰራዊት ድርጅት ብለው ቀምተውት ሮጡ።
ወያኔ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለማፍረስ ፕሮፓጋንዳና የእርሱን የዳዊትን ስም ተጠቅመው የኢትዮጵያ መኮንኖችን ከተጠቀሙባቸው በኋላ( አዲስ አበባ ሲገቡ እነ ኮለኔል ሰረቀ ብርሀን እነ ጄኔራል በረታ ገሞራውም ረሽነው ቀበሩ። በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች የዳዊትን ቅስቀሳ ሰምተው ወደ ወያኔ የገቡ ስመጥር ተዋጊዎች የኢትዮጵያን ጦር እንዳይዋጋ፣ ቢሸነፍ ደግሞ ምንም እንደማይደርስበት በየቀኑ በወያኔ ሬዲዮ እየተነገረው እውነት መስሎት ሳይዋጋ ጠመንጃውን ጣለ።
ሻለቃ ዳዊት ማለት እንግዲህ አደራጅቶ ለሽንፈት የሚዳርግ እንጂ ታግሎ ድል ያመጣበት ቀን የለም። አሁንም እስክንድርንና ሀብታሙ አያሌውን እንደ ኮንደም ተጠቅሞ ፋኖን እያጠቃ ነው። ዳዊት በአጭሩ Organizer of Defeat እንጂ ምንም የመሪነት አቋም የለውም።
የኢትዮጵያ ዲያስፓራ ደግሞ ክስተት የማይማር፣ ከአድራሻ ለውጥ በቀር የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ያልቻለ። የዲያስፖራውን ስነ ልቦናና ወቅታዊ ስነ ልቦና እየሰለለ ዲያስፖራው የሚፈልገውን የሚነግረውን አሜን ብሎ አጎንብሶ ሁሉ እንደ አጋሰስ ይጋለባል። ስሜታዊነት ያጠቃዋል፤ ግለሰብ ጀግኖችን በመከላከል ላይ ያተኩራል፤ ጠቃሚ ሀሳብ አድምቶና እቅድ አቅዶ ለመነጋገር አይፈቅድም።
ከዚህ ቀደም ድርጅት ፈጥረው፣ ታግለው መኢአድንና ኢደፓን አቋቁመው፣ ከዛ ቅንጅትን መስርተው እንዲያግባቡዋቸው የጠሯቸውን እነ ብርሀኑ ነጋን ዲያስፓራው አዳንቆ፣ እነ ልደቱንና ኢንጂነር ሀይሉ ሻውልን በዲሲ ብርጌድ፣ በነ ሀብታሙ አያሌውና ሲሳይ አጌና ዘርጥጠው፣ ሰድበው፣ አባረው ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን አነገሡ።
አረ ተዉ ብርሃኑ ለትግል የተፈጠረ ሰው አይደለም ብሎ ምክር የሚለግሰውን አዋቂ ሁሉ እየተሳደቡ ከትግል አግለው ብርሀኑ የኢትዮጵያ ብቸኛ መሪ አደረጉት። እነዚሁ ሰዎች በድጋሜ ግር ብለው መጥተው ለሻለቃ ዳዊት ጭፍራ ሆነው 2 ሚሊዮን ዶላር ሰጥተው ፋኖን እንዲከፋፍልና እንዲበትን ሀይል ሆኑት። ብራችንን ለምን አዋልከው ብሎ እንኳን የሚጠይቅ ዲያስፓራ የለም። ያሳፍራል። በየ ሶሻል ሚዲያው አሁን ማን መሪ ይሁን፥ አገሌ የተባለ ክፍለ-ሀገር-ጠልነት አለ፥ እገሌ ካልተሾመ ወዘተ የሚል ጭቅጭቅ እንጂ ፋኖን ወደ አንድነት የሚያመጣው “ይህ ሲደረግ ነው” በማለት ሁነኛ ሀሳብ የሚያቀርብ የለም።
ለፋኖ መሪዎች
ብር ያጓጓችሁ የፋኖ መሪዎች ዳዊት እነ ፋንታ በላይንና እነ አምሀ ደስታ እንዳይረሸኑ ለዓለማቀፍ መኀበረሰብ ደብዳቤ አልጻፈም፣ ሰላማዊ ሰልፍ አልጠራም። ኮኛኩን እየጠጣ ሲጋራን እያጨሰ ኑሮውን ነው የቀጠለው። ያለ አባት የቀሩ የጀነራሎች ልጆች CIA ከሚከፍለው ቀንሶ ጥብቆ አልገዛም ወይንም እስኮላርሺፕ አላፈላለገም። ረስቷቸው ጥሏቸው ነው ኑሮውን የቀጠለው።
ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ከደርግ ጋር ሲሰራ እነ አክሊሉ ሀብተወልድን፣ እነ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፣ እነ ራስ መስፍን የረሸነ። ከጅምሩ ጸረ ኢትዮጵያ ፣ ጸረ አምሓራ መንፈስ የተቆራኘው ሰው ነውና እሱን ሰምታችሁ ደማችሁ ደም ከልብ እንዳይሆን ተጠንቀቁ። እናንተም ነገ በራሳችሁ ጠባቂዎች በብር እየገዛ እንደ ፋኖ አሰግድ ያጠፍፋችኋል።
ለዲያስፓራዎች። እስቲ በተግባራችሁ ላይ ሀሳብ ጨምሩበት። እስከ መቼ በመንጋ ፓለቲካ ኢትዮጵያን ያለ ሰው ታስቀራላችሁ። ማሰብ ጀምሩ ዝም ብላችሁ እንደ አጋስስ አትነዱ። ስሜት ሮጦ ለማምለጥ፥ ከፍታን ለመዝለል ይጠቅማል አንጂ እንደ አማራ እጅግ ውስብስብ፥ ተለዋዋጭና ብዙ ጣልቃ ገብ ተዋንያን ከቀንዱ ቀጠና፥ ከአረብ፥ ከአውሮፓና አሜሪካ ድረስ እጃቸውን የሚያስገቡበትን ፈተና ለማለፍ አይጠቅምም።
ዩቲዩበሮች እናንተ ሳንቲም ለመልቀም ብላችሁ ስልክ እየደወላችሁ ፋኖን አታስመቱ። ምን ጥቅም አለው? ባወሩ ቁጥር እንርሱ እንደናንተ ሳንቲም አያገኙም ወይ እናንተ ከምታገኙት አታካፍሏቸው። የፋኖን ትግል እንደ entertainment ቀይራችሁታል። ማዝናናት እንጂ መደገፍ ላይ አይደላችሁም። ድምጻቸውን አጥፍተው የሚታገሉትን አቀጭጫችሁ ፎቶአቸውን የሚለቁትን አጋንናችሁ ፋኖን እየወጋችሁ ነው። መለስ ዜናዊን፣ ሰዬ አብረሀን፣ ታምራት ላይኔን በምስል የሚያውቀው ሰው ነበር? ትግልና ጉራ ለየቅል ነው።
ለፋኖ መሪዎች እባካችሁ ትግል ላይ ከሆናችሁ ፎቶ አትነሱ፣ ፎቷችሁን አትለጥፉ። ልታይ ልታይ አትበቆስል እንኳ ሆስፒታል ገብቼ እንዴት እታከማለሁ፣ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አዲስ አበባ ላይ ፈጽም ብባል ሰው በቀላሉ ያውቀኛል ወይ ብላችሁ አስቡ። ስራችሁን ስሩ። ፎቶዋችሁ ሳይሆን ተግባራችሁ ነው የሚመሰክረው። አንዳንዶቻችሁም ልንገሥ፥ እኔ ብቻ ልምራ በሚል ክፉ መንፈስ የተለከፋችሁ አንድነታችሁን አታውኩት። መሪ ራሱን አይመርጥም፥ በጦር ሜዳና በአመራር የተፈተነውን ተመርቶ ድል ያገኘው ብዙኃኑ ተከታይ ያውቀዋል። በፕሮፓጋንዳና በካድሬ ስምሪት ራሱን መሪ የሚያደርግ ሰው በመጨረሻ ለትግሉም ለጓዶቹም እዳ ይሆናል፥ ጨካኝ አምባገነንና ነፍሰ ገዳይ ይሆናል፥ ሥልጣኑ አደጋ ላይ የወደቀ ሲመስለው ትግሉን ሸጦት ይጠፋል። ተጠንቀቁ
አመሰግናለሁ።
ለናንተ አይተኛም።