ክፍል ሁለት ከ ባለፍው ሳምንት የቀጠለ

የካኪስቶክራሲ አገዛዝና የአማራ ህዝብ አርበኝነት

ሰውነት ይበቃል

የአብይ አህመድ ካኪስቶክራሲ አገዛዝ የአማራን ህዝብና የሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጨቁንበት አግባብ እጅግ በተለያየ መንገድ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ይህንን ልዩነት የማይገነዘቡ ወይም

የሚያለባብሱ ሰወች የአማራን ህዝብ ጭቆና ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋሉ። አብይ አህመድ አማራን ከሌላው ህዝብ በተለየ መንገድ የሚያጠቃው እንዴትና ለምን እንደሆነ ለመገንዘብ የኢትዮጵያን ድህረ-አብዮት ፖለቲካ ማስታወስ ያስፈልጋል። የነገስታቱ ዘመን ከወደቀ በኋላ ከአማራ በስተቀር ሌሎች ነገዶች ራሳቸውን እንደ ብሄር የሚያዩበት የማንነት ትርክት ፈጥረዋል። በዚህ ትርክት አማራን እንደጨቋኝ የሚያዩት ሲሆን አማራ ግን ራሱን የሚያድንበት ወይም የሚገልጽበት የድህረአብዮት ፖለቲካ ትርክት እንዳይኖረው ተደርጓል። ታዲያ ባለፉት 30+ አመታት የፖለቲካ ስልጣን የያዙት የትግራይና የኦሮሞ ፖለቲከኞች አማራ-ጠል ትርክታቸውን ወደህግና ፖሊሲ ሲቀይሩት

ኢትዮጵያዊ አንድነትን አቀነቅናለሁ የሚለው ሃይል ግን አማራን ለመከላከል የሚያስችል ምንም አይነት የፖለቲካ ስራ ሳይሰራ ቆይቷል። ይባስ ብሎም አማራ በማንነቱ እንዳይደራጅ፣ የፖለቲካ ድምጽ

እንዳይኖረውና የጠላቶቹ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጥገኛ እንዲሆን አድርገውታል። አማራ ከገዢው ፖለቲካ ያኮረፉ ሰወች መደበቂያና መደነቂያ ተደርጓል። አማራ ላይ የፖለቲካ ምክነት እንዲደርስበት የመደረጉ ጉዳይ ለኦሮሞ ልሂቃን የሀገር ግንባታ ሩጫ ልዩ

እድል ፈጥሮላቸዋል። በኦነጋዊ አስተሳሰብ “ኦሮሞ አንድ ሁኖ እንደብሄር ለመሰባሰብ የሚችለው እንዴት ነው?” ለሚለው ጥያቄ ላለፉት 50 አመት ሲሰጥ የኖረው መልስ “ጠላቱ የሆነውን አማራን በመበቀል ነው” የሚል ነው። ይህ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ የተግባር ፍሬ አፍርቷል። የአማራ ጥላቻ የኦሮሞ ብሄራዊ ትግል እስትንፋስ ማስቀጠያ ሆኗል። ኦሮሞነት ፀረ-አማራነት እንዲሆን ተደርጓል። እዚህ ላይ አማራ አይኑን መንቀል የለበትም። የኦሮሞ ባህል፣ ሃይማኖት ወይም ቋንቋ ሲፈጠር ጀምሮ ፀረ-አማራ ነው እያልን አይደለም። ባህልንና ፖለቲካን መለየት ያስፈልጋል። በፖለቲካው አለም ኦሮሞ አንድ የብሄር ማንነት ያለው ህዝብ ሆኖ የተፈጠረው አማራን የጋራ ጠላት አደርጎ በመደራጀት ነው። ይህንን

ምበኦሮሞ ህዝብ ውስጥ የሰረጸ የፖለቲካ እምነት አብይ አህመድ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህ የአማራ ጥላቻ ምክንያት ከፍተኛ የበቀልና የተረኝነት ፍላጎት እንዳለም ይረዳል። በኦሮሙማ እሳቤ መሰረት

“በነገስታቱ ጊዜ አማራ ‘ነጻ’ ስለነበረ ኦሮሞን ረግጦታል፤ አሁን ደሞ ኦሮሞ ነጻ የሚባለው አማራን ሲረግጥ ብቻ ነው” ተብሎ እንደሚታመን አብይ ይገነዘባል። በኦሮምማዊው አስተሳሰብ መሰረት ኦሮምያ ሉአላዊት ሀገር እንድትሆን የአማራ ጥላቻን ወደ ጅምላ ዘር ማጥፋት እርምጃ በመቀየር ክልሉን “ከሰፋሪወች” ማጽዳት ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑ ብዙወች ናቸው። ይህ “ፀረ-አማራነት” አብይን ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ብሄርተኞችን ሁሉ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያስተሳሰረ ኦሮምማዊ እትብት ነው። የኦሮሞን ህዝብ በአማራ ደም አጨማልቀው ከዚህ የተነሳ አብይ

የኦሮሞን የበቀልና የተረኝነት ስሜት ከድሮኖቹና ከወታደሩ የበለጠ ይተማመንበታል። ኦሮሞን ባለድል ለማድረግ የሚያስፈልገው አማራን ተሸናፊ ማድረግ ነው። ኦሮሞ ባለበት የህይወት ደረጃ ቆሞ አማራ

ብቻ ዝቅ እንዲል ከተደረገ በቂ ነው። ኦሮሞው ያለውን መብት አማራው ሲያጣ ያኔ ኦሮሞነት የበላይነት መገለጫ ይሆናል ብሎ ያምናል። አማራነት ሲዋረድ የኦሮሞ ጠላት እንደተዋረደ፣ አማራነት

ሲከበር የኦሮሞ ጠላት እንደተከበረ ተደርጎ ስለሚታይ አብይ አማራን የሚፈልገው የኦሮሙማ ማንነቱ ማረጋገጫ የሆነ ጭካኔ መፈጸሚያ እንዲሆነው ነው። በሌላ አባባል አብይ አማራን የሚጨፈጭፈው

ለብልጽግና እንዲገዛለት ሳይሆን የኦሮሞን ጠላት በማጥቃት ላይ እንደሆነ ተደርጎ እንዲታይና የኦሮሞ ህዝብ የእኔ መንግስት ነው ብሎ እንዲደግፈው ለማድረግ ነው። ኦሮሞነት ለአብይ የካኪስቶክራሲ

ጭምብሉ ነው። ከላይ በቀረበው ትንታኔ መሰረት በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ጭቆና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ከሚያደርሰው ጭቆና እጅግ የሚለይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ከአማራ ውጭ ያሉት ህዝቦች የኦሮሞ ህዝብ የፖለቲካ ማንነት ጠላት አልተደረጉም። የሚጨቆኑት እንደ ፖለቲካ ጠላት እየታዩ አይደለም። አማራ ግን የፖለቲካ ህይወት እስካለው ድረስ የኦሮሞ ጠላት ተደርጎ ነው የሚታየው።

ይህን የመገንዘብ ዋና ፋይዳ የአማራ ህዝብ ትግል ከሌላው ህዝብ ትግል የተለየ መሆኑን ለማወቅ ያስችላል። ይህንን ያልተገነዘበ ማንኛውም ሰው አብይን ስለተቃወመ ብቻ የአማራ ትግል መሪ መሆን ይቅርና ደጋፊ እንኳን ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም። ከዚህ አንጻር ወደአማራ የትግል ተግዳሮቶችና መፍትሄወች ከመመለሳችን በፊት አብይ ፋሽስታዊ መንግስቱን ለመገንባት ከፈጸማቸው በርካታ ወንጀሎች ጥቂቶቹን እንመልከት።

ራሱን የሃገሪቱ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መሪ ማድረግ

አብይ በግርገር ወደስልጣን ከመጣ በኋላ ህወሀት እንኳን ያልፈጸመውን አይን ያወጣ ዝርፊያ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፈጽሟል። ካደረጋቸው የዝርፊያ ተግባራት አንዱ የሃገሪቱን ዋና ዋና የሃብት ተቋማት ሰብስቦ በቁጥጥሩ ስር ማስገባት ነው። ለዚህም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚል አዲስ ድርጅት በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ አዋጅ ቁጥር 487/2014 አቋቁሟል። ይህን ድርጅት በአንድ መቶ ቢሊዮን የተፈቀደ ካፒታል ፈጥሮ፣ ራሱን የድርጅቱ ዋና መሪ አድርጎ፣ ዋናዋናወቹን የመንግስት የሃብት ተቋማት በግል ቁጥጥሩ ስር አስገብቷቸዋል። ይህ ድርጅት ከውጭ ሃገርም ሆነ ከውስጥ ባለሃብቶች ብድር ይበደራል፣ ሃብት ይሰበስባል፣ የእዳ ሰነድ ያወጣል በአጠቃላይ በሃገሪቱ የገንዘብ ሃብት ላይ ዳኛ ሲሆን ሌላው ቀርቶ የይስሙላው ፓርላማና የፌዴሬሽን ምክርቤት እንኳን አይቆጣጠሩትም። የሃገሪቱን ሃብት እንደፈለገ ማድረግ ይችላል። በአጭሩ የሃገሪቱ አንጡራ ሃብቶች ሁሉ ተሰብስበው ከዚህ ሰውየ መዳፍ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል። የዚህን ድርጅት መቋቋሚያ አዋጅ ስናይ በቦርድ እንደሚተዳደር ይገልጽና የቦርዱን የመጨረሻ የስልጣን ቁንጮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ይላል። አብይ የሚሰበስበው ይህ ቦርድ ተጠሪነቱ ለራሱ ለመሪው ለአብይ ነው። በአንቀጽ 11 ቁ. 1 እና 2 መሰረት ይህ ቦርድ ስድስት አባላት ያሉት ሲሆን እነዚህን አባላት የሚመረጡት በራሱ በአብይ ነው። ከአብይ በስተቀር ሌሎቹ የአገልግሎት ዘመናቸው 3 አመት ነው። አብይ ከፈለገ በየ3 ቀኑም

ሊቀያይራቸው ይችላል። በአንቀጽ 10 መሰረት በቦርዱ ውስጥ እንዲካተቱ የተፈቀደላቸው ከተራ ሰራተኞች በስተቀር ምንም አይነት ያገርውስጥ ተቋማት ወይም የፓርቲ ተወካዮች የሉም። ይልቁንም አብይ ከፈለገ ከውጭ “ገለልተኛ የሆነ አለማቀፍ አማካሪ ቦርድ” ማቋቋም ይችላል። የድርጅቱ ሂሳብ የሚመረመረው በፌደራል ዋና ኦዲተር ሳይሆን ራሱ አብይ በሚሾመው “ገለልተኛ የውጭ ኦዲተር” ነው (አንቀጽ 18 (1)). ድርጅቱ ግብርና ቀረጥ አይከፍልም (አንቀጽ 16 (1)). አሁን ያሉት የቦርዱ አባላት ውስጥ አህመድ ሽዴና ብርሀኑ ነጋ ይገኙበታል። እንግዲህ የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ያለ ማንም ተቆጣጣሪ አብይ እንደፈለገ ማድረግ የሚችልበት ስልጣን ራሱ ለራሱ ሰጥቷል ማለት ይቻላል።

ማንንም ሳያማክር የኢትዮጵያን አየርመንገድ ላይ አክስዮን ለመሸጥ ይችላል። ቴሌን በ850 ሚሊዮን ዶላር ሽጦታል። በቅርቡ አብይ ከአየር መንገድ ላይ፣ ከግድቡ ላይ፣ ወዘተ አክስዮን ለውጭ ሃይሎች

ስለመስጠት ሲናገር ተሰምቷል። አንዳንድ ድርጅቶች (ለምሳሌ የአየር መንገድ የእቃ ጭነት ማመላለሻው) ለውጭ ሃይሎች እንደተላለፉ እየተነገረ ነው። በአጠቃላይ የሀገሪቱ ሀብት በህግና ስርዓት ሳይሆን በእሱ ፍላጎት ብቻ እንዲንቀሳቀስ፣ መንግስት የእሱ አምላኪወች የሚዘውሩት ማሽን እንዲሆን የሚያስችል ስርዓት በመገንባት ላይ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *