፫/፪/፳፻፲፮ ዓ/ም
ትግሉ ውስጥ ገብተህ ህይወትህን ለአደጋ በማጋለጥህ ትልቅ አክብሮት አለን። ከዚህ ቀደምም የአንባገነን ስርአሮዓቶችን ለመዋጋት የከፈልከውን መስዋዕትነት እናውቃለን እናከብራለን።
አሁን ይህንን ደብዳቤ እንድንጽፍልህ ያስገደደን አንዳንድ የስትራቴጂክ ስህተቶች እያየን በመሆኑና ይህም የፋኖ ትግልን ከፋፍሎ ለግጭትና ለመዳከም ይዳርገዋል ብለን ስለሰጋን ነው።
ፋኖ ገና በቂ ኃይል፣ ትጥቅና ስንቅ የለውም ። ፋኖ ማንም መልምሎ፣ አሰልጥኖና፣ አስታጥቆ በዲሲፕሊንና በድርጅታዊ አሰራር ተጠርንፎ የተያዘም ሀይል አይደለም።
አንተም ታውቃለህ ፋኖ በራሱ ጠመንጃ፣ በራሱ ቀለብ፣ በራሱ ልብስ፣ በራሱ ህይወት ትግል ውስጥ የገባና እስካሁንም ያስመዘገበው ድል በዲያስፓራ ድጋፍ የተገኘ ሳይሆን በራስ ሀብትና ቁርጠኝነት ነው።
ፋኖ ለሀገሩና ለወገን ፍቅር ብሎ ህይወቱን ለመስጠት የወጣ እንጂ አንዱን ለማንገስ ሌላውን ለማቅሰሰ የወጣ ኃይል አይደለም። በትግሉ ውስጥ ገብቶ፣ ታግሎ የሰውን ልብ ገዝቶ የሚነግስ የሚቀስ ግን አይኖርም ለማለት አይደለም። በትግል ውስጥ ታጋይም መሪም ይወለዳልና።
ፋኖ የፈቃደኛ ጦር ስለሆነ ልቡ ከሻከረ ስሜቱ ከተጎዳ በትግሉ አላማና ግብ ጥርጣሬ ካደረበት ጠመንጃን ይዞ ወደ ቤቱ ከመመለስ የሚያቆመው ኃይል የለም።
ፋኖ የተያዘው በሀገርና በወገን ፍቅር እንጂ በዲሲፕሊን፣ በድርጅታዊ ጥርነፋ ወይም በደሞዝ አይደለም ።
የፋኖ ታጋያች ፈቃደኛ (volunteers) ናቸው። ስለዚህ የልቡን ያልተረዳን ሲመስለው፣ ስሜቱን የሚጎዳ ነገር ሲደረግ ካየ፣ እየከፋፈልነው ከመሰለው፣ ያታለልነው ከመሰለው፣ እየተጠቀምንበት ከመሰለው ወይንም ከሀገር ጥቅምና ነጻነት በላይ ለራስ ስልጣንና ጥቅም በህይወቱ እየነገድን እያተረፍን የመሰለው ሰዓት ጠመንጃውን ወደ መሪዎቹ አዙሮ ረሽኖ ወደ ቤቱ ከመመለስ የሚያስቆመው ምንም አይነት ኃይል የለም። የብአዴን እጣ ፈንታ ከኛም እሩቅ አይደለም።
ፋኖሀገርነጻአወጣለሁብሎ“የበላውቀብድምየለም”። ስለዚህቤቱንጥሎበፈቃዱእንደወጣሀሉልቡየሻከረወይንም የተጠቀምንበት የመሰለው ቀን፣ አለ ብለን ስንኮፈስ የት ገባ የሚባል ኃይል ሊሆን ይችላል።
የቀድሞዎቹ ኮሚኒስቶች ሊረዱት ያልቻሉትና አንተንም ጠልፈው ያስገቡህ ይህ በሌኒኒስት ድርጅታዊ ጥርነፋ የተፈጠረ መስሏቸው ነው። ይህ ተዋጊ በፍቅር እንደመጣ በጥርጣሬ ጥሎ ሊሄድ ይችላል። ከዛም አልፎ መሪዎቹን ሊበቀል ይችላል።
ይህንን ከማድረግ የሚያስገድደው ምንም ክር ወይንም ያሰረው ገመድ የለም ። ስለዚህ የፈቃደኛ ጦርን መምራት እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ወታደራዊ ክንፍ ቀላል አይደለም። እንደ ህወሓትና እንደ ሻዕቢያ ጦር አይደለም። ከፍቅር በቀር ምንም ያሰረው ክር የለም። ለዚህ ነው ትልቅ ጥንቃቄና ትልቅ የስነልቦና ብልጽግና (Emotional Intelligence) ያለው አመራር የሚያስፈልገው ።
አሁን የሻለቃው ችግር ይሄንን መርዳት ያለመቻሉ ነው። ለሀምሳ አመት ሞክሮ፣ ከሻበያና ከወያኔ ጋር ተባብሮ መፈንቅለ መንግስት እመራለሁ ብሎ የኢትዮጵያን ጀነራሎች አስጨርሶ ሀገሪቷን ለሻቢያና ለወያኔ ያስረከበውን ጭንቅላቱን ይዞ አሁንም አውቃለሁ ይላል።
እእውነት እንንገርህ ድርጅቱን ተረክባችሁ መርታችሁ ለድል የምታበቁ ቢሆን ቁልፏን ሰጥተናችሁ፣ ባቄላ ቀረ ቢሉ ፈስ ቀለል ባልን ነበር። ተለምኖ ለመስዋዕትነት የመጣን ሀይል በጨቅላ አስተሳሰ ለመከፋፈልና ለመበተን ትልቅ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ነው።
እነ ዳዊት ንጉሱን በማነቅ ጳጳሰን በመግደል ኦርቶዶክስን በማጥፋት አማራውን ከእርስቱ በማፈናቀል ኢትዮጵያን እንጠቅማለን ብለው እንደ ሞከሩት አይነት ጨቅላ አስተሳሰብ ይዞ ማሸነፍ አይቻልም።
አሁን ትልቅ ችግር እየተጋረጠ ነው። በርካታ ታጋዬች ሚስቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ስራቸውን፣ የእርሻውን፣ ንግዳቸውን፣ አሮጊት እናታቸውን፣ እቁባቸውን ጥለው የወጡት የወገናቸው መጠቃት እና በፋኖ ውስጥ የተፈጠረው ወንድማማችነት ስሜትና ትብብር ነው።
ይህንን የስነልቦና ትስስር (psychological contract) የሚሸረሽር ነገር ከተሰራ ሁሉም ነገር እንደ የካርድ ቤት ይበተናል።
‘እነዚህም አይረቡም” የሚል ስሜት ከተፈጠረ አሁን ብቻ ሳይሆን ለረጅም ግዜ እራሱን ከትግል እንዲያገል ያደርገዋል። ስለዚህ ጥንቃቄ የሚደረግባቸውን ነገሮች ልናስገነዝብህና እንዲሻሻል ከዛም አልፎ የመሪነቱን ሀላፊነት ወስደህ አደባባይ ወጥተህ እርምት እንዲሰጥበትና ከፍ ያለ የሞራል ልዕልና እንድታሳይ እንፈልጋለን።
ስለዚህ
፩ኛ ሁሉም ፋኖ አንዲት ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀ ነውና የሚበላለጥ የፋኖ ነፍስ እንደሌለና መከራውንም ይሁን ድጋፉን እኩል ማግኘት እንዳለበት መናገር አለብህ። አሁን ህዝባዊ ሀይሉን የዳዊት የግንባርና ብሎ ለመክፈል መሞከት የሀገር ክህደት ነው። በዳዊት መንገድ ሌላውም በል እንግዲህ ብር የበላህ ሙት እኛ የለንበትም ካለ በአማራው ላይ የባርነት ቀንበር በማልበሳችሁ እንደ ባንዳዎች ታሪክ ይዘክራችሀል።
፪ኛ፣ ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ ድጋፍ ለሁሉም ፋኖና ትግሉ እንጂ ለሻለቃ ዳዊት ወይ ለእስክንድር ነጋ ስልጣን ፍላጎት መግዣ የተሰጠ እንዳልሆነ መረዳትና ይህንንም በአደባባይ ወጥተህ ይህ ገንዘብ እስከተቻለ ድረስ ለሁሉም ፋኖ እንደሚደርስ መናገርና አሁን እየተሰራ ያለው አድልዎና ህይወታቸውን ሊሰጡ ለተዘጋጁ ፋኖዎች በብርና በጥቅም በመግዛት ለግል ጥቅም ለማዋል መሞከር ስህተት እንደ ሆነና በአስቸኳይም እንደሚታረም መግለጽ አለብህ። ህይወቱን ሊሰጥ የተዘጋጀውን ህዝብ የላከለትን ጥይት አለመስጠት ትልቅ ኃጥያትም ወንጀልም ነው።
ይህ አድልኦ ማውገዝ የመሪነትና የሞራል ልዕልና ይሰጥሃል። ይህንን አለማድረግ የሚመጣው የህዝብ ገንዘብ እንዲነጥፍና ከግንባሩ ውጪ በተበታተነ መንገድ በቀጥታ ለፋኖዎች መስጠት እንዲጀመር በር ይከፍታል። አሁንም ተጀምሯል።
ይህም ዛሬ የጎረፈውን ድጋፍ የሚያነጥፍና፣ ያለውም እንዲያልቅ የሚያደርግ ይሆናል። ይህ ደግሞ ትግሉ እንዲዳከምና የ8 ትሪሊዮን ብር በጀት ይዞ ሀገርን የሚያምሰው የኦነግ/ኦፒዲኦ ስርዓት ሁላችሁንም በተናጠል በድሮን እያደነ እንዲጨርሳችሁ ወይንም እየማረከ አዋሽ አርባ ወስዶ እንዲቀጠቅጣችሁና የአማራ ማፈርያ የምትሆኑበርን በር መክፈትና መተባበር ነው ።
በደርግ ለኢህአፓ በማርክሳዊ አደረጃጀት ያደጉ ሰዎች ይህ ነገር አይገባቸውም። ፋኖን ለመቆጣጠርና መሪው ለመሆን የሚያደርግ ከፍቅር በቀር ምንም ነገር የለም።
ለጊዜው በብር የተያዘ ይመስላል ይሁንና ዛሬ የመጣ ብር ዛሬ ይበላል ለነገ ወዳጅነት ማሰሪያ አይሆንም። ከኢትዮጵያዊነት ከሀገር ፍቅር በላይ ብር ሊያስረው የሚችል ኃይል አይኖርም። ብሩ ከሻለቃ ወይንም ካንተ ባንክ የወጣ አይደለም። ብሩ ሲያልቅ ፍቅሩም ያልቃልና ዘለቄታዊ የትግል አንድነት አይኖርም። ይልቁንም ይሄንን ሴራ የሰሩትን ያዳከሙትን፣ በወንድሞቹ ደም የቀለዱበት መሆኑን ሰረዳ ከፋኖ በቀል ማምለጥ ማንም አይችልም።
፫ኛ ክብርን የጥቅም መዘዙ። ብር ከተከበረና ህይወትን መስጠት ከተቃለለ ትግሉ ያከትማል። ብር የጭፍራ መሰብሰቢያ ከሆነና በፋኖ ውስጥ ይህ ስነልቦና እንዲሰርጽ ከተደረገ ከግንባሩ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ባለ 8 ትሪሊዮን በጀት ያለው አብይ አህመድ አለ። ፋኖ ፋኖን ለትርፍ መሸጥ ይጀምራል። ባንክ መዝረፍ ወርቅ መቀማት ህዝብ መዝረፍ ስርአት ይሄናል። ዳዊት በምሳሌ እያስተማረ ያለው ይህንን ውንብድና ነው። (The most corruption influence in the struggle the power of money)
በፋኖ ጭንቅላት ውስጥ ብር ሀይል ሆኖ እንዲታይ ካደረግክ ትልቅ የስነልቦና ቀውስ ይወለዳል ድልም ይርቃል።
በብር ስነልቦና ካዋቀርከው ነገ እነ አብይ በመቶ ሚሊዮን እያወጡ ጦር ከሚልኩ፣ የእስክንድርን ጭንቅላት ቆርጦ ላመጣ 10 ሚሊዮን ወረታውን እሰጣለሁ ቢል ዛሬ በዳዊት የልመና ብር የተገዛ ነገ የእስክንድር አንገት ይቆርጣል።
ዳዊት ለ50 ዓመት ሲሸነፍና ውርደት ቀለቡ የሆነ ሰው ነው። ያ ሁሉ ጄነራል አስጨርሶ ሽጉጡን አልጠጣም ። ውስኪውን እየጠጣ ኑሮውን ቀጥሏል ። አንተም ከጀነራሎቹ በላይ አይደለህም ይጠቀምብህና በሚቀጥለው መጽሀፍ ውስጥ አንድ ምእራፍ ትሆናለህ እንጂ ላንተ ብሎ አይሞትም። ላንተ ብለው ግን ብዙ ወጣቶችና መናንያን ተጨፍጭፈዋል። ስለዚህ ከታች ገፍቶ ወደላይ የሚያወጣህ ህዝብ እንጂ ከላይ ሆኖ ጎትቶ ከራሱ ላይ የሚያስቀምጥህ አይኖርም።
ስለዚህ በልመና ብር የሚገዛ ሽንፈት እንጂ ወንድም አንደማይኖር ተረዳ።
የEric Hoffer, the true believers ካነበብክ የህዝባዊ ንቅናቄ ዋናው ሀይሉ self renunciation ነው። እንደ ገዳማዊ መነኩሴ ሀብትና ጥቅምን renounce ያላደረገ ታጋይ ውጤት አያመጣም። ስለዚህ የዲያስፓራ ብር ተከታይ መግዢያና መከፋፈል ከሆነ ትግሉ ይሞታል።
Eric Hoffer, an American philosopher, once said, “A mass movement attracts and holds a following not because it can satisfy the desire for self-advancement, but because it can satisfy the passion for self- renunciation”
This quote highlights the idea that people are often drawn to movements that require them to renounce their individuality and merge with a larger group. Hoffer believed that this desire to belong to something greater than oneself was a fundamental human
አንድ ታጋይ at the early stage of a movement በትግል ውስጥ ጥቅም እንዲያስገባ ከተደረገ ትግሉ ይሞታል። ታጋይ መስዋዕትነት self renunciation ሳይሆን ጥቅም ካሰበ ከጦርነት በላይ በጭቆና ውስጥም ባጃጅ መንዳት አዋጪ ሃኖ ይታየዋል። ስለዚህ
በዳዊት በኩል የሚመጣው ብር ታጋዬች እነ እንትና ስንት አገኙ ለእኔስ ስንት ሊደርሰኝ ነው ብሎ እንዲያስብ ካደረጋችሁ ትግሉን ገደላችሁ።
የፋኖን የማቴርያል ፍላጎት የሚያሟላ ምንም አይነት ኃይል በኢትዮጵያም በዲያስፓራም የለም።
ስለዚህ ገንዘብ በፓለቲካ እምነት ውስጥ እንዳይገባ ካልታገልክ ድካምህ ሁሉ ከንቱ ሆኖ በጨካኞች እጅ ትወድቃለህ።
፫ኛ እያቶቻችን ሲመክሩ “የድሮ ወዳጅህን በምን ቀበርከው ቢሉት በሻሽ፣ አዲሱ እንዳይሸሽ” ይላሉ። የፓለቲካ መሪ የሚመዘነው በድሮ ወዳጆቹ ላይ በሚሰነዝረው አስተያየትና ውሳኔ ነው። ለምሳሌ እነ ሻልቃ በነ ዶ/ር ወንደሰን እና በነ መስከረም ላይ እነ ዘመድኩንንና እነ
360 አዝምተው የሀሰት ዘመቻ ጀምረዋል። ይህ አንተንና ዳዊትን እንድናከብር ሳይሆን በፍርሀትና በጥርጣሬ እንድናያችሁ ነው ያደረገን። ያው የደርግ እና የአህአፓ ዘመን ብልግና አሁንም እንዳለ ነው የጠቆመን።
ወንድወሰን ስለ አንተ በጎ እንጂ ክፉ ነገር ተናግሮ አያውቅም። አንድ ቤት ውስጥ ተኝታችሁ፣ በአንድ ትሪ በልታችሁ፣ በሳሎን ውስጥ ቆማችሁ ፀልያችሁ፣ በክብ እስፓርት ሰርታችሁ አብራችሁ የተስፋ ግዜ አሳልፋችኋል። ወይ አንተ ወይ እሱ ልትታሰሩ ትችላላችሁ።
ይሁንና አንተ ብትሆን የታሰርከው ወንድወሰን ሀገሩን ብቻ ሳይሆን ፈጣሪውንም የሚፈራ ስለሆነ እስክንድር ሲዘለፍ የተቀነባበረ ዘመቻ ሲካሄድበት ዝም ብሎ አያይም ነበር። ወንድወሰን ሰው እንጂ ፓለቲከኛ አይደለም። አሁን አንተን ሳይ ግን እነ ዳዊትን እንኳን እባካችሁ ተዉ ስትል አትሰማም። ይህ ህይወቱን ለመስጠት ስራውን ልጆቹን ትቶ በእስር ቤት ለሚማቅቅና እራሱን መከላከል እንኳን በማይችልበት ሁኔታ እያለ በግራ ፓለቲካ ጥርሳቸውን የነቁሉና ንጉስ ጳጳስ አንቀው የገደሉ ዛሬም ለሀገራቸው ፍቅር ወደ ትግሉ የገቡትን ሲያጠፏ ዝም ማለት ማለት ግን አጥያት ነው። ትግሉን መጀመር ሰታሰብ ብየፋኖ መሪዋች ገዳም ገብተው ሱባኤ ገብተው ነበር። በመቨረሻ አንድ የገዳም አባት ለሀገር ለወገን ብላችሁ በእግዚአብሔር ስም ከታገላችሁ ታሸንፋላችሁ ነገር ግን ለራሳችሁ ጥቅም በእግዚአብሔር ስም ብትለምኑ
እግዚአብሔር አሳልፎ ይሰጣችሀል ያሉት በሁላችንም አይምሮ ላይ ተቀርጿል። ለኔ ገብር የሚለው ለጊዜው ጥቅም ያመጣ ይመስላል ግን አሳልፎ በጨካኝ እጅ የሚያሰጥ ነው።
፬: ለ 50 ዓመት የኢትዮጵያ ትግል ድል ያላመጣው ገና ድል የታየ ቀን እርስ በእርስ መጠፋፋት ስለሚጀመር ነው። አሁንም ትግል በዚህ መንገድ ከሄደ እንደምንሸነፍ ጥርጥር የለውም። የኢትዮጵያ ፓለቲካ ስልጣኑ ሳይያዝ የስልጣን እንቅፋት ይሆናል ተብሎ የታሰበውን ለማጥፋት ሲሮጥ መንግስት ተጠናክሮ ሁለቱንም ያጠፋል።
ኢህአፓና መኢሶን ደርግ ሳይወድቅ እርስ በእርስ ተፋጅተው መጨረሻ ላይ ብርሃነ መስቀል ረዳና ኃይሌ ፊዳ በአንድ እስር ቤት ታስረው፣ በአንድ ጅራፍ ተገርፈው፣ በአንድ ቀን ተረሽነው በአንድ ጉድጓድ ተቀበሩ።
የቅንጅት ውጤት የመኢአድና የኢዴፓ ድርጅታዊ ጥንካሬ ነበር። ይህንን መዋቅር ለመረከብ በቀስተ ዳመና በሚባል ሱቅ በደርግ ዶ/ር ብርሀኑና አንዳርጋቸው ተወዳጅ የሆነችውን ብርቱካን ሚደቅሳን ከፊት አስቀድመው ሀይሉ ሻውልን ለማጥፋት ሲሄዱ ሁሉም ተያይዞ ጠፋ።
አሁንም አንተን መሪያችን የሚሉህ ለነሱ ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትሆንላቸው እንጂ ላንተ ክብርም መሪነትህንም አይቀበሉትም። ጅል ካልሆንክ አንተ ለእነሱ መሪም የእውቀትም የጥበብ ሰውም ነህ ብለው አያስቡም። አንተ ለእነሱ ፈረስ ነህ።
መሪ መሪ የሚሉህ ሰይጣን በሄዋን ላይ የፈጠረውን ተንኮል ለመድገም ነው። ሄዋን ይሄንን ብትበዪ እንደ ፈጣሪ ትሆናለች ነበር ያላት። ከተሰጣት ጸጋ በላይ የፈጣሪዋን ደጋ ተመኘች። ሰይጣን የሚገባው በኢጎ ነው። ዳዊትም ከጓደኞችህ ለመነጠል ዛሬ መሪያችን ይላል ነገ ግን ጫማውንም እንድታስር አይፈቅድልህም። ታየዋለህ።
መጀመሪያ መሪ ሁን ሲልህ አልሆንም ባልክበት ሰዓት “እሱ አይረባም፣ መሪ አይሆንም፣ ፈሪ ነው ወባ ታሟል” እየተባለ ያበሻቅጥህ ነበር። ወድያው ተስማምተህ እሱ ወኪላችን ነው ስትል መሪያችን እስክንድር ማለት ጀመረ።
ዳዊት የዛሬ ሀምሳ አመትም ይህቺን ተንኮል ተጠቅሞባት በመጽሀፏም ጽፏታል። አራተኛ ክፍለጦር ስንፍናን መንግስቱ መጥቶ አውቅሀለሁ አለኝ እኔ ግን ላስታውሰው አልቻልኩም። ቦሀላ ወደ መሪ ምርጫ ስንገባ አጥናፏን ለምረጥ ስናስብ አጽናፏ አማራ ስለሆነ የአማራውን ገዢ መደብ ማስቀጠል እንደሆነ, ነረዳን። ከዛ ተፈሪን ስንሞክር ኦሮሞ ሁሉ “ያ ተፈሪ” እያለ ሲጨፍር ይሄም ትልቅ ድጋፍ (power base) እንዳለው ተረዳን። ስለዚህ በቀላሉ አስወግደው ስልጣኑን ሊቀሙትና የሚችሉት አንድ ያልተማረ፣ አጭር፣ ጥቁር ወታደር ሻለቃ መንግስቱ ሆኖ አዩ። ስለዚህ የህዝብ ድጋፍ ሊኖራቸው ይችላል ያሉዋቸውን አጽናፏ አባተንና ተፈሪ በንቲን ገለው መንግስቱን አነገሱ። መንግስቱ እንደ ገመቱት ጠቋራ፣ ኩሩሩ፣ መሀይም ሳይሆን ማፍያ ነበር። ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ አደረሰን ብሎ ሁሉንም ጨረሳቸው። ዳዊትም ቁጭ ብሎ የሰቀለውን ቆሞ ማውረድ ስላልቻለ እግር አውጪኝ አለ።
እነዚህ በስታሊን ጽንሰ ሀሳብ ያደጉ the end justifies the means ብለው የሚያምኑት ጊዜው ሲደርስ ታሪክህን ሰርዘው ነው የሚቀብሩህ። ስለዚህ አንተን በጭራሽ መሪ አያደርጉህም። ልክ በነ ወንድወሰን ላይ ዛሬ የማጥላላት ዘመቻ የሚያደርጉት አንተንም በመንጋው ለማስመታት አንድ ቀን አይወስድባቸውም። ስለዚህ ከወጣቱ፣ ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀው፣ ጋሼ ከሚልህ እንጂ ከላይ በሚጠቀሙብህ ሰዎች ላይ አትንጠላጠል።
አንተንም አዋርደው ያጠፉሃል። የገደሉህ ቀን ይህ መቃንርህ ላይ ይህ ይነበባል። ለንዋይና ለስልጣን ብሎ ጓዶቹን ከድቶ ከአራጆቹ ጋር አብሮ ለእርድ እራሱን ሰጠ ይባልልሀል። ስለዚህ ወደ ህሊናህ ተመልሰህ እንደ ሄዋን ለጊዚያዊ ሙገሳ ሳይሆን እውነቱን ለሚነግሩህ ድክመትና ጥንካሬህን ለሚያሳዩህ ወጣታች ጆሮህን ስጥ። እውነትና ታማኝነት ለውጤት ያበቃሀል። የገዳም አባት እንዳስጠነቀቁት ለፈጣሪና ለሀገር ብላችሁ ከሰራችሁ እግዚአብሔር ይባርክላችሀል በእግዚአብሔር ስም ግን የግላችሁን ጥቅም ካስቀደማችሁ አሳልፎ ይሰጣችሀል ያሉት ባንተ ላይ እንዳይፈጸም። ሙገሳው እንደሚያደልቡት በግ ጨው እንደ ማላስ ነው። ለውድቀት ነው።
ለማንኛውም መሪ መሆን ከፈለክ መሪ እንጂ ለሌሎች መገልገያ አትሁን። በመጨረሻው ታሪክህንም አንተንም ያጠፉኃልና። በእነ ወንድወሰን ላይ የተከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ባንተ ትዕዛዝ እንዳልሆነና ያንተም እጅ እንደሌለበት ለማሳየት እጅህን እንደ ጲላጦስ ታጠብ።
ሰውን መፍራት አያስፈልግም እግዚአብሔርን አለመፍራት ግን ካንተ አይጠበቅም። እግዚአብሔር እስከዛሬ ጠብቆሀል እንዳቆየህ አውጥቶ እንዳይጥልህ።
ትግሉንም በወንድማማችነትና በሀገር ፍቅር እንጂ በብር ለመግዛት አትሞክር ምክንያቱም ሌሎቹ ዝም ማለት አቁመው መናገር ሲጀምሩ የብሩም ምንጭ ይደርቃል የተሰበሰበውም ያልቃል። ያኔ ደጋፊም ጠባቂም ዳዊትም አይኖርም። መንጋው እነወንደሰን ባደራጁት ስነ ልቦና ላይ ቆሞ ድል በመታየቱ ነው ብሩ የመጣው። ከዛ በፊት ምን ያህል ልመና እየተደረገ ሬዲዮ እንኳን ገዝቶ የሰጠ የለም።
አንድ ፋኖም ከትግሉ አዝኖ ከወጣ አንድ ሺ ሰው ትግሉን እንደወጣ አስብ። የደቡብ ጎንደር ጥይት አጥቶ ቢሸነፍ ብር የተሰጠው ሰሜን ይጠቃል። ሰሜን ጥይት ቢጨርስ ደቡቡም ይጨረሳል። ፋኖ እንደ አንድ አካል ሆኖ ካልተንቀሳቀሰ ይሸነፋል። መምሬ ብስራት በ1904 አሳትመው ለምኒሊክ በሰጡት መጽሃፍ እንዳሉት ሀገር እንደ አንድ አካል ካልሰራ አይጸናም ብለው ነበር። ለምሳሌ እጅ እኔ ደክሜ ሰርቼ ለሆድ ለምን እቀልባለሁ ካለ፣ ሆድ ሰራብ እጅም ይዝላል። እግር እኔ ምን በወጣኝ ይሄንን ሁሉ የምሸከመው ብሎ ቢለግም እግር ካልተንቀሳቀሰና ካልሰራ ሁሉም ይደክማል። አይልም ጆሮም ሁሉም አንድ አካል ሆኖ ካልሰራ ጤና አይመጣም። እናንተም በሚኒሊክ የተሾማችሁ ሚኒስትሮች እንደ አንድ አካል እንደ አንድ አምሳል ሆናችሁ ካልሰራችሁ መንግስት አይጸናም ብለው መክረው ነበር። ዛሬም ይህ ምክር ይሰራል።ስ
ዛሬም ፋኖን አንደ አንድ አካል ፋኖን ማቆም ካልቻክ መሪም ድልም አታይም።
በጥቅም ይዘን እመራዋሁ ብሎ ከማሰብ የሁሉም መሪ በተግባር፣ በአላማ ጽናትና ለፋኖ በምናሳየው ፍቅርና ወዳጅነት ተከታይ ሳይሆን ወንድም አደርገዋለሁ ብለህ አስብ። ተከታይ በፈተና ግዜ ይበተናል ወንድም ግን አብሮ ይሞታልና። ስለዚህ ይህ ሻለቃ ዳዊት ከደርግ ተውሶእየዘራየጥላቻናየመከፋፈልመንገድአንተመሪነኝካልክአስቁም። የሱጭፍራካልሆንክደግሞእራስህንበግዜአግለህ ከወንድሞችህ ጋር ቁም። ፈጣሪውን የማያውቅ አሳማውን እየበላ የጥቁር ፈረንጅ ልሁን ያለ ወታደር ምኞትህን ብቻ ሳይሆን ገሀነም ይዞይ ይወርዳል።
ስለዚህ ጸልይ፣ ከራስህ ጋር ተነጋገር፣ ከፈጣሪህ ፊት ቆመህ ራስህን ጠይቅና ወስን። እራስህን ህዝብን እኛን መዋሸትና በፓለቲካ ቋንቋ እኛን መሸንገል ትችላለህ ግን ፈጣሪህን መዋሸት አትችልም። የገዳም አባት በእግዚአብሔር ስም የራሳችሁን ጥቅም ካስቀደማችሁ እግዚአብሔር አሳልፎ ይሰጣችሀል ያለው ባንተ እንዳይፈጸም።
ጸልየህ አስበህ ወስነህ ወደ እውነት ምን ግድ ተማለስ።
ወንድሞችህ ከትግል ሜዳ።በድጋሜ አርሜዋለሁ። አንተ የገዳም አባት አሉ ያልከኝንም ጨምሬበታለሁ።
በስመአብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ይድረስ ለእስክንድር
ትግሉ ውስጥ ገብተህ ህይወትህን ለአደጋ በማጋለጥህ ትልቅ አክብሮት አለን። ከዚህ ቀደምም የአንባገነን ስርአሮዓቶችን ለመዋጋት የከፈልከውን መስዋዕትነት እናውቃለን እናከብራለን።
አሁን ይህንን ደብዳቤ እንድንጽፍልህ ያስገደደን አንዳንድ የስትራቴጂክ ስህተቶች እያየን በመሆኑና ይህም የፋኖ ትግልን ከፋፍሎ ለግጭትና ለመዳከም ይዳርገዋል ብለን ስለሰጋን ነው።
ፋኖ ገና በቂ ኃይል፣ ትጥቅና ስንቅ የለውም ። ፋኖ ማንም መልምሎ፣ አሰልጥኖና፣ አስታጥቆ በዲሲፕሊንና በድርጅታዊ አሰራር ተጠርንፎ የተያዘም ሀይል አይደለም።
አንተም ታውቃለህ ፋኖ በራሱ ጠመንጃ፣ በራሱ ቀለብ፣ በራሱ ልብስ፣ በራሱ ህይወት ትግል ውስጥ የገባና እስካሁንም ያስመዘገበው ድል በዲያስፓራ ድጋፍ የተገኘ ሳይሆን በራስ ሀብትና ቁርጠኝነት ነው።
ፋኖ ለሀገሩና ለወገን ፍቅር ብሎ ህይወቱን ለመስጠት የወጣ እንጂ አንዱን ለማንገስ ሌላውን ለማቅሰሰ የወጣ ኃይል አይደለም። በትግሉ ውስጥ ገብቶ፣ ታግሎ የሰውን ልብ ገዝቶ የሚነግስ የሚቀስ ግን አይኖርም ለማለት አይደለም። በትግል ውስጥ ታጋይም መሪም ይወለዳልና።
ፋኖ የፈቃደኛ ጦር ስለሆነ ልቡ ከሻከረ ስሜቱ ከተጎዳ በትግሉ አላማና ግብ ጥርጣሬ ካደረበት ጠመንጃን ይዞ ወደ ቤቱ ከመመለስ የሚያቆመው ኃይል የለም።
ፋኖ የተያዘው በሀገርና በወገን ፍቅር እንጂ በዲሲፕሊን፣ በድርጅታዊ ጥርነፋ ወይም በደሞዝ አይደለም ።
የፋኖ ታጋያች ፈቃደኛ (volunteers) ናቸው። ስለዚህ የልቡን ያልተረዳን ሲመስለው፣ ስሜቱን የሚጎዳ ነገር ሲደረግ ካየ፣ እየከፋፈልነው ከመሰለው፣ ያታለልነው ከመሰለው፣ እየተጠቀምንበት ከመሰለው ወይንም ከሀገር ጥቅምና ነጻነት በላይ ለራስ ስልጣንና ጥቅም በህይወቱ እየነገድን እያተረፍን የመሰለው ሰዓት ጠመንጃውን ወደ መሪዎቹ አዙሮ ረሽኖ ወደ ቤቱ ከመመለስ የሚያስቆመው ምንም አይነት ኃይል የለም። የብአዴን እጣ ፈንታ ከኛም እሩቅ አይደለም።
ፋኖ ሀገር ነጻ አወጣለሁ ብሎ “የበላው ቀብድም የለም”። ስለዚህ ቤቱን ጥሎ በፈቃዱ እንደ ወጣ ሀሉ ልቡ የሻከረ ወይንም የተጠቀምንበት የመሰለው ቀን፣ አለ ብለን ስንኮፈስ የት ገባ የሚባል ኃይል ሊሆን ይችላል።
የቀድሞዎቹ ኮሚኒስቶች ሊረዱት ያልቻሉትና አንተንም ጠልፈው ያስገቡህ ይህ በሌኒኒስት ድርጅታዊ ጥርነፋ የተፈጠረ መስሏቸው ነው። ይህ ተዋጊ በፍቅር እንደመጣ በጥርጣሬ ጥሎ ሊሄድ ይችላል። ከዛም አልፎ መሪዎቹን ሊበቀል ይችላል።
ይህንን ከማድረግ የሚያስገድደው ምንም ክር ወይንም ያሰረው ገመድ የለም ። ስለዚህ የፈቃደኛ ጦርን መምራት እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ወታደራዊ ክንፍ ቀላል አይደለም። እንደ ህወሓትና እንደ ሻዕቢያ ጦር አይደለም። ከፍቅር በቀር ምንም ያሰረው ክር የለም። ለዚህ ነው ትልቅ ጥንቃቄና ትልቅ የስነልቦና ብልጽግና (Emotional Intelligence) ያለው አመራር የሚያስፈልገው ።
አሁን የሻለቃው ችግር ይሄንን መርዳት ያለመቻሉ ነው። ለሀምሳ አመት ሞክሮ፣ ከሻበያና ከወያኔ ጋር ተባብሮ መፈንቅለ መንግስት እመራለሁ ብሎ የኢትዮጵያን ጀነራሎች አስጨርሶ ሀገሪቷን ለሻቢያና ለወያኔ ያስረከበውን ጭንቅላቱን ይዞ አሁንም አውቃለሁ ይላል።
እእውነት እንንገርህ ድርጅቱን ተረክባችሁ መርታችሁ ለድል የምታበቁ ቢሆን ቁልፏን ሰጥተናችሁ፣ ባቄላ ቀረ ቢሉ ፈስ ቀለል ባልን ነበር። ተለምኖ ለመስዋዕትነት የመጣን ሀይል በጨቅላ አስተሳሰ ለመከፋፈልና ለመበተን ትልቅ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ነው።
እነ ዳዊት ንጉሱን በማነቅ ጳጳሰን በመግደል ኦርቶዶክስን በማጥፋት አማራውን ከእርስቱ በማፈናቀል ኢትዮጵያን እንጠቅማለን ብለው እንደ ሞከሩት አይነት ጨቅላ አስተሳሰብ ይዞ ማሸነፍ አይቻልም።
አሁን ትልቅ ችግር እየተጋረጠ ነው። በርካታ ታጋዬች ሚስቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ስራቸውን፣ የእርሻውን፣ ንግዳቸውን፣ አሮጊት እናታቸውን፣ እቁባቸውን ጥለው የወጡት የወገናቸው መጠቃት እና በፋኖ ውስጥ የተፈጠረው ወንድማማችነት ስሜትና ትብብር ነው።
ይህንን የስነልቦና ትስስር (psychological contract) የሚሸረሽር ነገር ከተሰራ ሁሉም ነገር እንደ የካርድ ቤት ይበተናል።
‘እነዚህም አይረቡም” የሚል ስሜት ከተፈጠረ አሁን ብቻ ሳይሆን ለረጅም ግዜ እራሱን ከትግል እንዲያገል ያደርገዋል። ስለዚህ ጥንቃቄ የሚደረግባቸውን ነገሮች ልናስገነዝብህና እንዲሻሻል ከዛም አልፎ የመሪነቱን ሀላፊነት ወስደህ አደባባይ ወጥተህ እርምት እንዲሰጥበትና ከፍ ያለ የሞራል ልዕልና እንድታሳይ እንፈልጋለን።
ስለዚህ
፩ኛ ሁሉም ፋኖ አንዲት ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀ ነውና የሚበላለጥ የፋኖ ነፍስ እንደሌለና መከራውንም ይሁን ድጋፉን እኩል ማግኘት እንዳለበት መናገር አለብህ። አሁን ህዝባዊ ሀይሉን የዳዊት የግንባርና ብሎ ለመክፈል መሞከት የሀገር ክህደት ነው። በዳዊት መንገድ ሌላውም በል እንግዲህ ብር የበላህ ሙት እኛ የለንበትም ካለ በአማራው ላይ የባርነት ቀንበር በማልበሳችሁ እንደ ባንዳዎች ታሪክ ይዘክራችሀል።
፪ኛ፣ ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ የሚሰጥ ድጋፍ ለሁሉም ፋኖና ትግሉ እንጂ ለሻለቃ ዳዊት ወይ ለእስክንድር ነጋ ስልጣን ፍላጎት መግዣ የተሰጠ እንዳልሆነ መረዳትና ይህንንም በአደባባይ ወጥተህ ይህ ገንዘብ እስከተቻለ ድረስ ለሁሉም ፋኖ እንደሚደርስ መናገርና አሁን እየተሰራ ያለው አድልዎና ህይወታቸውን ሊሰጡ ለተዘጋጁ ፋኖዎች በብርና በጥቅም በመግዛት ለግል ጥቅም ለማዋል መሞከር ስህተት እንደ ሆነና በአስቸኳይም እንደሚታረም መግለጽ አለብህ። ህይወቱን ሊሰጥ የተዘጋጀውን ህዝብ የላከለትን ጥይት አለመስጠት ትልቅ ኃጥያትም ወንጀልም ነው።
ይህ አድልኦ ማውገዝ የመሪነትና የሞራል ልዕልና ይሰጥሃል። ይህንን አለማድረግ የሚመጣው የህዝብ ገንዘብ እንዲነጥፍና ከግንባሩ ውጪ በተበታተነ መንገድ በቀጥታ ለፋኖዎች መስጠት እንዲጀመር በር ይከፍታል። አሁንም ተጀምሯል።
ይህም ዛሬ የጎረፈውን ድጋፍ የሚያነጥፍና፣ ያለውም እንዲያልቅ የሚያደርግ ይሆናል። ይህ ደግሞ ትግሉ እንዲዳከምና የ8 ትሪሊዮን ብር በጀት ይዞ ሀገርን የሚያምሰው የኦነግ/ኦፒዲኦ ስርዓት ሁላችሁንም በተናጠል በድሮን እያደነ እንዲጨርሳችሁ ወይንም እየማረከ አዋሽ አርባ ወስዶ እንዲቀጠቅጣችሁና የአማራ ማፈርያ የምትሆኑበርን በር መክፈትና መተባበር ነው ።
በደርግ ለኢህአፓ በማርክሳዊ አደረጃጀት ያደጉ ሰዎች ይህ ነገር አይገባቸውም። ፋኖን ለመቆጣጠርና መሪው ለመሆን የሚያደርግ ከፍቅር በቀር ምንም ነገር የለም።
ለጊዜው በብር የተያዘ ይመስላል ይሁንና ዛሬ የመጣ ብር ዛሬ ይበላል ለነገ ወዳጅነት ማሰሪያ አይሆንም። ከኢትዮጵያዊነት ከሀገር ፍቅር በላይ ብር ሊያስረው የሚችል ኃይል አይኖርም። ብሩ ከሻለቃ ወይንም ካንተ ባንክ የወጣ አይደለም። ብሩ ሲያልቅ ፍቅሩም ያልቃልና ዘለቄታዊ የትግል አንድነት አይኖርም። ይልቁንም ይሄንን ሴራ የሰሩትን ያዳከሙትን፣ በወንድሞቹ ደም የቀለዱበት መሆኑን ሰረዳ ከፋኖ በቀል ማምለጥ ማንም አይችልም።
፫ኛ ክብርን የጥቅም መዘዙ። ብር ከተከበረና ህይወትን መስጠት ከተቃለለ ትግሉ ያከትማል። ብር የጭፍራ መሰብሰቢያ ከሆነና በፋኖ ውስጥ ይህ ስነልቦና እንዲሰርጽ ከተደረገ ከግንባሩ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ባለ 8 ትሪሊዮን በጀት ያለው አብይ አህመድ አለ። ፋኖ ፋኖን ለትርፍ መሸጥ ይጀምራል። ባንክ መዝረፍ ወርቅ መቀማት ህዝብ መዝረፍ ስርአት ይሄናል። ዳዊት በምሳሌ እያስተማረ ያለው ይህንን ውንብድና ነው። (The most corruption influence in the struggle the power of money)
በፋኖ ጭንቅላት ውስጥ ብር ሀይል ሆኖ እንዲታይ ካደረግክ ትልቅ የስነልቦና ቀውስ ይወለዳል ድልም ይርቃል።
በብር ስነልቦና ካዋቀርከው ነገ እነ አብይ በመቶ ሚሊዮን እያወጡ ጦር ከሚልኩ፣ የእስክንድርን ጭንቅላት ቆርጦ ላመጣ 10 ሚሊዮን ወረታውን እሰጣለሁ ቢል ዛሬ በዳዊት የልመና ብር የተገዛ ነገ የእስክንድር አንገት ይቆርጣል።
ዳዊት ለ50 ዓመት ሲሸነፍና ውርደት ቀለቡ የሆነ ሰው ነው። ያ ሁሉ ጄነራል አስጨርሶ ሽጉጡን አልጠጣም ። ውስኪውን እየጠጣ ኑሮውን ቀጥሏል ። አንተም ከጀነራሎቹ በላይ አይደለህም ይጠቀምብህና በሚቀጥለው መጽሀፍ ውስጥ አንድ ምእራፍ ትሆናለህ እንጂ ላንተ ብሎ አይሞትም። ላንተ ብለው ግን ብዙ ወጣቶችና መናንያን ተጨፍጭፈዋል። ስለዚህ ከታች ገፍቶ ወደላይ የሚያወጣህ ህዝብ እንጂ ከላይ ሆኖ ጎትቶ ከራሱ ላይ የሚያስቀምጥህ አይኖርም።
ስለዚህ በልመና ብር የሚገዛ ሽንፈት እንጂ ወንድም አንደማይኖር ተረዳ።
የEric Hoffer, the true believers ካነበብክ የህዝባዊ ንቅናቄ ዋናው ሀይሉ self renunciation ነው። እንደ ገዳማዊ መነኩሴ ሀብትና ጥቅምን renounce ያላደረገ ታጋይ ውጤት አያመጣም። ስለዚህ የዲያስፓራ ብር ተከታይ መግዢያና መከፋፈል ከሆነ ትግሉ ይሞታል።
Eric Hoffer, an American philosopher, once said, “A mass movement attracts and holds a following not because it can satisfy the desire for self-advancement, but because it can satisfy the passion for self-renunciation”
This quote highlights the idea that people are often drawn to movements that require them to renounce their individuality and merge with a larger group. Hoffer believed that this desire to belong to something greater than oneself was a fundamental human
አንድ ታጋይ at the early stage of a movement በትግል ውስጥ ጥቅም እንዲያስገባ ከተደረገ ትግሉ ይሞታል። ታጋይ መስዋዕትነት self renunciation ሳይሆን ጥቅም ካሰበ ከጦርነት በላይ በጭቆና ውስጥም ባጃጅ መንዳት አዋጪ ሃኖ ይታየዋል። ስለዚህ በዳዊት በኩል የሚመጣው ብር ታጋዬች እነ እንትና ስንት አገኙ ለእኔስ ስንት ሊደርሰኝ ነው ብሎ እንዲያስብ ካደረጋችሁ ትግሉን ገደላችሁ።
የፋናን የማቴርያል ፍላጎት የሚያሟላ ምንም አይነት ኃይል በኢትዮጵያም በዲያስፓራም የለም።
ስለዚህ ገንዘብ በፓለቲካ እምነት ውስጥ እንዳይገባ ካልታገልክ ድካምህ ሁሉ ከንቱ ሆኖ በጨካኞች እጅ ትወድቃለህ።
፫ኛ እያቶቻችን ሲመክሩ “የድሮ ወዳጅህን በምን ቀበርከው ቢሉት በሻሽ፣ አዲሱ እንዳይሸሽ” ይላሉ። የፓለቲካ መሪ የሚመዘነው በድሮ ወዳጆቹ ላይ በሚሰነዝረው አስተያየትና ውሳኔ ነው። ለምሳሌ እነ ሻልቃ በነ ዶ/ር ወንደሰን እና በነ መስከረም ላይ እነ ዘመድኩንንና እነ 360 አዝምተው የሀሰት ዘመቻ ጀምረዋል። ይህ አንተንና ዳዊትን እንድናከብር ሳይሆን በፍርሀትና በጥርጣሬ እንድናያችሁ ነው ያደረገን። ያው የደርግ እና የአህአፓ ዘመን ብልግና አሁንም እንዳለ ነው የጠቆመን።
ወንድወሰን ስለ አንተ በጎ እንጂ ክፉ ነገር ተናግሮ አያውቅም። አንድ ቤት ውስጥ ተኝታችሁ፣ በአንድ ትሪ በልታችሁ፣ በሳሎን ውስጥ ቆማችሁ ፀልያችሁ፣ በክብ እስፓርት ሰርታችሁ አብራችሁ የተስፋ ግዜ አሳልፋችኋል። ወይ አንተ ወይ እሱ ልትታሰሩ ትችላላችሁ።
ይሁንና አንተ ብትሆን የታሰርከው ወንድወሰን ሀገሩን ብቻ ሳይሆን ፈጣሪውንም የሚፈራ ስለሆነ እስክንድር ሲዘለፍ የተቀነባበረ ዘመቻ ሲካሄድበት ዝም ብሎ አያይም ነበር። ወንድወሰን ሰው እንጂ ፓለቲከኛ አይደለም። አሁን አንተን ሳይ ግን እነ ዳዊትን እንኳን እባካችሁ ተዉ ስትል አትሰማም። ይህ ህይወቱን ለመስጠት ስራውን ልጆቹን ትቶ በእስር ቤት ለሚማቅቅና እራሱን መከላከል እንኳን በማይችልበት ሁኔታ እያለ በግራ ፓለቲካ ጥርሳቸውን የነቁሉና ንጉስ ጳጳስ አንቀው የገደሉ ዛሬም ለሀገራቸው ፍቅር ወደ ትግሉ የገቡትን ሲያጠፏ ዝም ማለት ማለት ግን አጥያት ነው። ትግሉን መጀመር ሰታሰብ ብየፋኖ መሪዋች ገዳም ገብተው ሱባኤ ገብተው ነበር። በመቨረሻ አንድ የገዳም አባት ለሀገር ለወገን ብላችሁ በእግዚአብሔር ስም ከታገላችሁ ታሸንፋላችሁ ነገር ግን ለራሳችሁ ጥቅም በእግዚአብሔር ስም ብትለምኑ እግዚአብሔር አሳልፎ ይሰጣችሀል ያሉት በሁላችንም አይምሮ ላይ ተቀርጿል። ለኔ ገብር የሚለው ለጊዜው ጥቅም ያመጣ ይመስላል ግን አሳልፎ በጨካኝ እጅ የሚያሰጥ ነው።
፬: ለ 50 ዓመት የኢትዮጵያ ትግል ድል ያላመጣው ገና ድል የታየ ቀን እርስ በእርስ መጠፋፋት ስለሚጀመር ነው። አሁንም ትግል በዚህ መንገድ ከሄደ እንደምንሸነፍ ጥርጥር የለውም። የኢትዮጵያ ፓለቲካ ስልጣኑ ሳይያዝ የስልጣን እንቅፋት ይሆናል ተብሎ የታሰበውን ለማጥፋት ሲሮጥ መንግስት ተጠናክሮ ሁለቱንም ያጠፋል።
ኢህአፓና መኢሶን ደርግ ሳይወድቅ እርስ በእርስ ተፋጅተው መጨረሻ ላይ ብርሃነ መስቀል ረዳና ኃይሌ ፊዳ በአንድ እስር ቤት ታስረው፣ በአንድ ጅራፍ ተገርፈው፣ በአንድ ቀን ተረሽነው በአንድ ጉድጓድ ተቀበሩ።
የቅንጅት ውጤት የመኢአድና የኢዴፓ ድርጅታዊ ጥንካሬ ነበር። ይህንን መዋቅር ለመረከብ በቀስተ ዳመና በሚባል ሱቅ በደርግ ዶ/ር ብርሀኑና አንዳርጋቸው ተወዳጅ የሆነችውን ብርቱካን ሚደቅሳን ከፊት አስቀድመው ሀይሉ ሻውልን ለማጥፋት ሲሄዱ ሁሉም ተያይዞ ጠፋ።
አሁንም አንተን መሪያችን የሚሉህ ለነሱ ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትሆንላቸው እንጂ ላንተ ክብርም መሪነትህንም አይቀበሉትም። ጅል ካልሆንክ አንተ ለእነሱ መሪም የእውቀትም የጥበብ ሰውም ነህ ብለው አያስቡም። አንተ ለእነሱ ፈረስ ነህ።
መሪ መሪ የሚሉህ ሰይጣን በሄዋን ላይ የፈጠረውን ተንኮል ለመድገም ነው። ሄዋን ይሄንን ብትበዪ እንደ ፈጣሪ ትሆናለች ነበር ያላት። ከተሰጣት ጸጋ በላይ የፈጣሪዋን ደጋ ተመኘች። ሰይጣን የሚገባው በኢጎ ነው። ዳዊትም ከጓደኞችህ ለመነጠል ዛሬ መሪያችን ይላል ነገ ግን ጫማውንም እንድታስር አይፈቅድልህም። ታየዋለህ።
መጀመሪያ መሪ ሁን ሲልህ አልሆንም ባልክበት ሰዓት “እሱ አይረባም፣ መሪ አይሆንም፣ ፈሪ ነው ወባ ታሟል” እየተባለ ያበሻቅጥህ ነበር። ወድያው ተስማምተህ እሱ ወኪላችን ነው ስትል መሪያችን እስክንድር ማለት ጀመረ።
ዳዊት የዛሬ ሀምሳ አመትም ይህቺን ተንኮል ተጠቅሞባት በመጽሀፏም ጽፏታል። አራተኛ ክፍለጦር ስንፍናን መንግስቱ መጥቶ አውቅሀለሁ አለኝ እኔ ግን ላስታውሰው አልቻልኩም። ቦሀላ ወደ መሪ ምርጫ ስንገባ አጥናፏን ለመምረጥ ስናስብ አጽናፏ አማራ ስለሆነ የአማራውን ገዢ መደብ ማስቀጠል እንደሆነ, ነረዳን። ከዛ ተፈሪን ስንሞክር ኦሮሞ ሁሉ “ያ ተፈሪ” እያለ ሲጨፍር ይሄም ትልቅ ድጋፍ (power base) እንዳለው ተረዳን። ስለዚህ በቀላሉ አስወግደው ስልጣኑን ሊቀሙትና የሚችሉት አንድ ያልተማረ፣ አጭር፣ ጥቁር ወታደር ሻለቃ መንግስቱ ሆኖ አዩ። ስለዚህ የህዝብ ድጋፍ ሊኖራቸው ይችላል ያሉዋቸውን አጽናፏ አባተንና ተፈሪ በንቲን ገለው መንግስቱን አነገሱ። መንግስቱ እንደ ገመቱት ጠቋራ፣ ኩሩሩ፣ መሀይም ሳይሆን ማፍያ ነበር። ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ አደረሰን ብሎ ሁሉንም ጨረሳቸው። ዳዊትም ቁጭ ብሎ የሰቀለውን ቆሞ ማውረድ ስላልቻለ እግር አውጪኝ አለ።
እነዚህ በስታሊን ጽንሰ ሀሳብ ያደጉ the end justifies the means ብለው የሚያምኑት ጊዜው ሲደርስ ታሪክህን ሰርዘው ነው የሚቀብሩህ። ስለዚህ አንተን በጭራሽ መሪ አያደርጉህም። ልክ በነ ወንድወሰን ላይ ዛሬ የማጥላላት ዘመቻ የሚያደርጉት አንተንም በመንጋው ለማስመታት አንድ ቀን አይወስድባቸውም። ስለዚህ ከወጣቱ፣ ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀው፣ ጋሼ ከሚልህ እንጂ ከላይ በሚጠቀሙብህ ሰዎች ላይ አትንጠላጠል።
አንተንም አዋርደው ያጠፉሃል። የገደሉህ ቀን ይህ መቃንርህ ላይ ይህ ይነበባል። ለንዋይና ለስልጣን ብሎ ጓዶቹን ከድቶ ከአራጆቹ ጋር አብሮ ለእርድ እራሱን ሰጠ ይባልልሀል። ስለዚህ ወደ ህሊናህ ተመልሰህ እንደ ሄዋን ለጊዚያዊ ሙገሳ ሳይሆን እውነቱን ለሚነግሩህ ድክመትና ጥንካሬህን ለሚያሳዩህ ወጣታች ጆሮህን ስጥ። እውነትና ታማኝነት ለውጤት ያበቃሀል። የገዳም አባት እንዳስጠነቀቁት ለፈጣሪና ለሀገር ብላችሁ ከሰራችሁ እግዚአብሔር ይባርክላችሀል በእግዚአብሔር ስም ግን የግላችሁን ጥቅም ካስቀደማችሁ አሳልፎ ይሰጣችሀል ያሉት ባንተ ላይ እንዳይፈጸም። ሙገሳው እንደሚያደልቡት በግ ጨው እንደ ማላስ ነው። ለውድቀት ነው።
ለማንኛውም መሪ መሆን ከፈለክ መሪ እንጂ ለሌሎች መገልገያ አትሁን። በመጨረሻው ታሪክህንም አንተንም ያጠፉኃልና። በእነ ወንድወሰን ላይ የተከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ባንተ ትዕዛዝ እንዳልሆነና ያንተም እጅ እንደሌለበት ለማሳየት እጅህን እንደ ጲላጦስ ታጠብ።
ሰውን መፍራት አያስፈልግም እግዚአብሔርን አለመፍራት ግን ካንተ አይጠበቅም። እግዚአብሔር እስከዛሬ ጠብቆሀል እንዳቆየህ አውጥቶ እንዳይጥልህ።
ትግሉንም በወንድማማችነትና በሀገር ፍቅር እንጂ በብር ለመግዛት አትሞክር ምክንያቱም ሌሎቹ ዝም ማለት አቁመው መናገር ሲጀምሩ የብሩም ምንጭ ይደርቃል የተሰበሰበውም ያልቃል። ያኔ ደጋፊም ጠባቂም ዳዊትም አይኖርም። መንጋው እነወንደሰን ባደራጁት ስነ ልቦና ላይ ቆሞ ድል በመታየቱ ነው ብሩ የመጣው። ከዛ በፊት ምን ያህል ልመና እየተደረገ ሬዲዮ እንኳን ገዝቶ የሰጠ የለም።
አንድ ፋኖም ከትግሉ አዝኖ ከወጣ አንድ ሺ ሰው ትግሉን እንደወጣ አስብ። የደቡብ ጎንደር ጥይት አጥቶ ቢሸነፍ ብር የተሰጠው ሰሜን ይጠቃል። ሰሜን ጥይት ቢጨርስ ደቡቡም ይጨረሳል። ፋኖ እንደ አንድ አካል ሆኖ ካልተንቀሳቀሰ ይሸነፋል። መምሬ ብስራት በ1904 አሳትመው ለምኒሊክ በሰጡት መጽሃፍ እንዳሉት ሀገር እንደ አንድ አካል ካልሰራ አይጸናም ብለው ነበር። ለምሳሌ እጅ እኔ ደክሜ ሰርቼ ለሆድ ለምን እቀልባለሁ ካለ፣ ሆድ ሰራብ እጅም ይዝላል። እግር እኔ ምን በወጣኝ ይሄንን ሁሉ የምሸከመው ብሎ ቢለግም እግር ካልተንቀሳቀሰና ካልሰራ ሁሉም ይደክማል። አይልም ጆሮም ሁሉም አንድ አካል ሆኖ ካልሰራ ጤና አይመጣም። እናንተም በሚኒሊክ የተሾማችሁ ሚኒስትሮች እንደ አንድ አካል እንደ አንድ አምሳል ሆናችሁ ካልሰራችሁ መንግስት አይጸናም ብለው መክረው ነበር። ዛሬም ይህ ምክር ይሰራል።ስ
ዛሬም ፋኖን አንደ አንድ አካል ፋኖን ማቆም ካልቻክ መሪም ድልም አታይም።
በጥቅም ይዘን እመራዋሁ ብሎ ከማሰብ የሁሉም መሪ በተግባር፣ በአላማ ጽናትና ለፋኖ በምናሳየው ፍቅርና ወዳጅነት ተከታይ ሳይሆን ወንድም አደርገዋለሁ ብለህ አስብ። ተከታይ በፈተና ግዜ ይበተናል ወንድም ግን አብሮ ይሞታልና። ስለዚህ ይህ ሻለቃ ዳዊት ከደርግ ተውሶ እየዘራ የጥላቻና የመከፋፈል መንገድ አንተ መሪ ነኝ ካልክ አስቁም። የሱ ጭፍራ ካልሆንክ ደግሞ እራስህን በግዜ አግለህ ከወንድሞችህ ጋር ቁም። ፈጣሪውን የማያውቅ አሳማውን እየበላ የጥቁር ፈረንጅ ልሁን ያለ ወታደር ምኞትህን ብቻ ሳይሆን ገሀነም ይዞይ ይወርዳል።
ስለዚህ ጸልይ፣ ከራስህ ጋር ተነጋገር፣ ከፈጣሪህ ፊት ቆመህ ራስህን ጠይቅና ወስን። እራስህን ህዝብን እኛን መዋሸትና በፓለቲካ ቋንቋ እኛን መሸንገል ትችላለህ ግን ፈጣሪህን መዋሸት አትችልም። የገዳም አባት በእግዚአብሔር ስም የራሳችሁን ጥቅም ካስቀደማችሁ እግዚአብሔር አሳልፎ ይሰጣችሀል ያለው ባንተ እንዳይፈጸም።
ጸልየህ አስበህ ወስነህ ወደ እውነት መንገድ ተመለስ። ወንድሞችህ ከትግል ሜዳ።