ነጋሪተ ፋኖ

የፋኖ ህዝባዊ ጥሪ

ቀለብ ስዩም. 03/10/2016 ዓ/ም

በአማራ ግዛት የፋኖ የትጥቅ ትግል ከተጀመረ እነሆ ውሎ አደረ። የትጥቅ ትግል ማድረግ ያስፈለገው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት አይደለም፤ ዲሞክራሲ ለአማራ ህዝብ “ቅንጦት” የሆነበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። ምክንያቱም የፋኖ የትጥቅ ትግል መሰረታዊ አላማው፦የአማራ ህዝብ በህይዎት መኖርና አለመኖር የህልውና ጥያቄ ሆኖ በመገኘቱ ይሆናል።ከ1983ዓም ጀምሮ የኢትዮጵያን ህዝብ በኀይል እየገዙ ያሉት የወያኔ ኢህአዴግ መንግስታት ለአማራ ህዝብ ያስቀመጡት ሁለት አማራጮችን ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ።አንደኛው ምርጫ፦ አማራ የሞራል ትጥቁን ፈትቶ ተዋርዶ እና ዝቅ ብሎ መኖር ሲሆን፦ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ በህይዎት እንዳይኖር ማድረግ ነበር። ከ50 አመታት በላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውም ይኼው ነው። አብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና መንግስትም አጀንዳው ከኢህአዴግ አፈሙዝ የተረፈውን የአማራ ህዝብ በየተራ እየለቀመ ማስወገድና የኦርቶዶክስ ሐይማኖትን የማጥፋት ዘመቻን ማስፈፀም መሆኑ ከመላው አማራ ህዝብ የተሰወረ አይደለም።

ይሁን እንጂ ከአማራ ህዝብ ከፊሉ ገብቶትም ይሁን ሳይገባው የጠላቶቹ መሳሪያ ይሆናል። ጥቂት ፍርፋሪ እንዲጣልለት በመፈለግ ሲያጎበድድ ይታያል። እርስ-በእርስ ተከፋፍሎ በመወዛገብ የፋኖን የትጥቅ ትግል ባያቆመውም የአማራን ህዝብ መከራንና እንግልት ግን ያራዝመዋል። እናም፦ ከፋኖ የተጋድሎ መስመር ላይ እየተገኙ እንቅፋት ለመሆን መሞከር ውድ ዋጋ ያስከፍላል። የትጥቅ ትግሉ የሰደድ እሳት ሆኖ በባንዳነት ከጠላት ጎን የተሰለፉትን ሁሉ ይበላቸዋል። አመድ ትቢያ ያደርጋቸዋል።

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኘው የአማራ ማህበረሰብ ሴት-ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ ሳይል ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ እውቀት ያለው በእውቀቱ፣ ጉልበት ያለውም በጉልበቱ የትግል መዋጮ ማድረግ የግዴታ የሆነበት ሰአት ላይ መድረሱን በመግለፅ ፋኖ ህዝባዊ ጥሪ ያደርጋል። እያንዳንዳችን የአማራ ማህበረሰብ አባላት ተራ-በተራ እየተለቀምን የጥቃት ኢላማ ከመሆናችን በፊት በምንችለው ሁሉ የትግል ተሳትፎ እናድርግ። በሕይወት የምታኖረን ፀሐይ ሳትጠልቅ፣ ድቅድቅ ጨለማ ሳይውጠን ሊያጠፋን የተነሳውን ኃይል ማጥፋት በሕይወት እንድንቆይ ያደርገናል። ይህ ደግሞ የሚሆነው የአማራው ኢሊት ከአድርባይነት፣ ከኢጎ፣ ከቡድንተኝነት፣ ከስውር የስልጣን ጥመኝነት፣ ከተላላኪነት፣ ከከፋፋይነትና ከሴረኝነት መጥፎ በሽታዎች ወጥተን ከአንጀትና ከልብ መሬት ላይ ፊት ለፊት ፋሽሽታዊ ኀይሉን እየተፋለመ ያለውን ከአርበኛ ፋኖዎቻችን ጎን ስንቆም ብቻ ነው። ውድ ወገኖቼ!! ሁሉም አማራ ፋኖ እንደሆነ ልንረዳ ይገባል። ምክንያቱም ሊውጠን የቋመጠው ዘንዶ የጠላት ኃይል አማራ ስለሆን ሊያጠፋን ዘመተብን እንጅ ፋኖ ስላልሆንን የሚምሩን አይደለምና ነው። የኦህዴድ መንግስት የአማራንና የኦርቶዶክስ ሐይማኖትን እንዲሁም ነባር የሙስሊም ሐይማኖትን ማጥፋት የተሰጠው የፖለቲካ ሴራ እንደሆነ ልንገነዘብና ልንሰጋ ያስፈልጋል። ዝቋላ ገዳም ድረስ ወጥቶ መነኮሳቱን ያረደ ኃይል ለማንም ሊያዝን አይችልም።

በቅርቡ ከአዲስ አበባ ሰማይ ስር የተፈፀመውን ታላቅ ገድል ሁላችሁም እናውቃለን። በፋኖ ናሁሰናይ የሚመራው ጓድ ከጎንደር-ሸዋ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ የአብይን መንግስት አርበደበደው። ሶስት አርበኛ ፋኖዎች ያንን ሁሉ ሰራዊት ለሶስት ሰአታት ያህል ገትሮ አቆመው። በመጨረሻም ተተኳሽ ጥይት በመጨረሳቸው ብቻ ሳልሳዊ ቴዎድሮስነታቸውን በሕይወት ብዕራቸው ፅፈው አለፉ። ሁሉም አማራ ይህን መሰል የተጋድሎ ወኔ አለው። ይህን የመሰለ ወኔና ተግባር በድጋሜ እናየዋለን።

የአማራ የለየለት ጠላት የሆነው አብይ አህመድ፦ በደርግ ጊዜ ያልተፈፀመን ፀያፍ ድርጊት ፈፅሟል። “የልጇን የናሁሰናይን አስከሬን ስጡኝና የጀግና ሐይማኖታዊ አቀባበር ላድርግለት” በማለት የጠየቁትን ወላጅ እናቱን በማሰር አሰቃይቷቸዋል። ለአንዲት አቅመ-ደካማ የጀግና እናት የማይራራ የኦህዴድ መንግስት የባህሪ ለውጥ ያመጣል ብላችሁ ከጠበቃችሁ ታሪካዊ ስህተት ተሳስታችኋል።

ውድ ወገኖቼ!! የአማራ ፋኖ በተጋድሎ ድል አድርጎ ነፃነቱን እንደሚቀዳጅ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም። በመጀመሪያ ደረጃ ፋኖ ወደ ትጥቅ ትግል የገባው ለ50 አመታት ሲታሰር፣ ሲሰደድና ሲገደል ታግሶ ከቆየ በኃላ ነው፤ ሁለተኛ፦ የማይነጥፍና የማይታጠፍ የትግል ወኔ አለው፤ ሶስተኛ፦ አልሞ የማይስት፣ ሮጦ የማይደክም ብርቱ አርበኛ ነው። ስለዚህም በስሜት ብቻ ሳይሆን በምክኒያት ፋኖን መደገፍ ያስፈልጋል። በገንዘባችሁ፣ በእውቀታችሁና በጉልበታችሁ ፋኖን መደገፍ የሁላችንም ህልውና መሰረት ነው። የሐይማኖት አባቶች፦ የኦህዴድ መንግስት ሐይማኖታችንን ሊያጠፉ የተነሳ ኃይል እንደሆነ ተገንዝበን የአቡነ ጴጥሮስን የሰማዕትነት ሚናን እንወጣ። ለሐይማኖታችን በፅናት ቁመን ቤተክርስቲያንን እናድን። በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ አውግዙ።
ፋኖ ያሸንፋል!!
ድል ለጭቁኑ አማራ ህዝብ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *