የኢትዮጵያ ሕዝብን ነጻ ማውጣት የሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ የሚወጣው ከማነው? ከባርነት ውስጥ ነውን? ማንስ ነጻ ያወጣዋል? እንዴት ባርያ ሆነ? እንዴት ነጻ ይውጣ? የሚሉ ጥያቄዎች ማንሳትና በማያጠራጥር መንገድ መመለስ ቅድሚያ ያለው የአመክንዮአዊ ተጠየቅ ሂደት ነው።
ትርጓሜ፦
ኢትዮጵያ፦
ኢትዮጵያ ፭ ሺ ዘመናት ታሪክ ያላት አፍሪካዊት ብሔር ስትሆን በተለያዩ ዘመናት የቆዳ ስፋቷ በሰሜን ግብጽን፥ በደበቡብ ሕንድ ውቂያኖስን፥ በምሥራቅ የመንና ህንድን፥ በምዕራብ ሱዳንን እያዋሳነች ስሰተፋና ስትጠብብ የኖረች አገር ናት። በአሁኑ ግዜ ኢትዮጵያ በአውሮፓ ወረራና ቅኝ ግዛት ጣልቃ ገብነት ምክንያት ከቀይ ባሕርና ሕንድ ውቂያኖስ ጅቡቲን፥ ኤርትራንና ሶማልያን በመፍጠርና በመቆነጣጠር ደረቅ ወደብ አልባ አገር ያደረጓት፥ ሕዝቧ በቅኝ ገዥዎችና በአረቦች ወረራና ጣልቃ ገብነት ከአንድ አገርነት በትንሹ ወደ አምስፍ አገራት ተለይተው እንዲኖሩ ሆነዋል። ቤተሰብ ጎረቤት ለመሆን ተገድዷል። ብዙ ሰዎች ትልቋንና አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ እንዳናይይዝና እንዳንተቅ ይፈልጋሉ። ሮም ትልቅ ሀገር ነበረች አሁን ደግሞ ሮም ትንሽ ናት። ትንሽ መሆንዋ ሮማዊነታቸውን አያስቀረውም። የቀደመ ታሪካቸውን ማስብንም አይከለክላቸውም።
ሕዝብ፦
የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ የሚኖር የዜጎች ስብስብ ብቻ ሳይሆን በውጪም ተበትኖ ታሪካዊ፥ ሃይማኖታዊ፥ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትሥሥር ያለውና በሀገርም ውስጥም መንግሥት መሥርቶ የሚኖር ማኅበረሰብ ማለት ነው። ኢትዮጵያዊነት ደም ቆጠራ ሳይሆን እምነት፥ ታሪክና ምርጫም ነው። አንድ ጃማይካዊ ላቲን አሜሪካ ወይንም ሰሜን አሜሪካ ቢወለድም በታሪክ፥ በእምነት፥ በባህል ዝንባሌ ኢትዮጵያዊ መሆን ከፈለገ ኢትዮጵያዊ ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ተብሎ ይቆጠራል። በተቃራኒው በኢትዮጵያ ተወልዶ በሐሰት ትርክትና በቡድን ፖለቲካ መንጋነት የአእምሮ አጠባ የጨለመ አንድ ሰው ተነስቶ እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ማለት ይችላል፥ እያለም ይገኛል፥ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያኖችን ነባር አንድነት፥ ርስት እና ማኅበራዊ ትሥሥር በማፈራረስና በመበጣጠስ ወደ ጦርነት፥ ሞትና ስደት መለወጥ ወንጀል፥ ኃጢአት፥ ኢሰብአዊነትና ኢፍትሐዊነት ስለሚሆን “ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ አይደለሁም” ከአለ ሕዝቡንና አገሩን ሳይጎዳ መኖር የሚችለው ሀሳቡን በልቡ ይዞ ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርስ፥ ዑአገር ሕግ ሳይጥስ፥ ግዴታዉን እየተወጣ ከሆነ ሀሳብ ነውና ይችላል። ከዚህ ካለፈ አገሩን ለቀቅቆ በመሰደድ ማንም ላይ ጉዳት ያለማድረስ ግዴታ ይወድቅበታል።
ነጻነት፦
በአርአያና እምሳለ ስላሴ የተፈጠረው ክቡር የሰው ሁሉ በተፈጠረበት ባለርስትነት፥ ሙሉ ሰብአዊ ክብር፥ የማሰብና የማድረግ፥ የመዘዋወር፥ የማምለክ፥ ሀብት የማካባት፥ አካባቢው የመጠበቅና አዳዲስ ነገሮችን እግዚአብሔር ከፈጠረው ቁሳቁስ በምርምር መልሶ መፍጠር የሚከለክለው ከሌለ ያ ሰው ነጻ ሰው ይባላል።
በዘመናዊው የዛሬዋ ዓለም ነጻ ማለት አንድ ሰው ያለማንም ተጽዕኖ፣ የማሰብ፣ ሀሳቡን የመግለጽ፣ ይስማማኛል የሚለውን ስርዓት እና ህግ የማውጣት፣ የሚመራውን የመምረጥና መመ’ረጥ እኩል መብት ያለው ማለት ነው። ይህ እኩልነትና ነጻነቱ በቋንቋ ጎሣው፥ በአኗኗር ዘይቤውማ አሠፋፈሩ፥ በትውልድ ቦታው፣ በጾታው፣ በቀለም፣ በትምህርት ሆነ በአካላዊ ጉድለቱ መብቱ ከማንም ከፍም ዝቅም የማይል ሰው ማለት ነው።
ጥንት በግዕዙ አንድ ነጻ ህዝብ አምሓራ ይባላል። ይህም አም ማለት ህዝብ ሲሆን ሓራ፣ ሓርነት ደግሞ ነጻ ማለት ነው። ስለዚህ ነጻ ዜጋና ህዝብ አምሓራ ይባል ነበር። በአማርኛው ነጻ ህዝብ ማለት ነው። ነጻ ህዝብ በግሉ፥ በማኅበረሰብ ውስጥ፥ በአገር ዜግነት፥ በእምነትና ባህል ተሳትፎ፥ እምነቱና ባህሉ በሚፈቅደው ድንበር ውስጥ ምርጫ የማድረግ መብት፣ የመኖር፥ የእምነት፥ የስነ ልቦናና አስተዳደር ዘይቤ ነው። የሌሎችን መብትና ነጻነት እና በጋራ ያጸደቁት መብቶችና ግዴታዎች ሳይጥስ በህግ ፊት እኩል የሚታይ ዜጋ ነው ።
ባርነት፦
ባርነት አንድ ሰው በአርያ ስላሴ ነጻ ሆኖ ተፈጥሮ ከፈጣሪው በተሰጠው መጠን የራሱ ጌታ መሆን አትችልም የሚል ከልካይ ሌላ ወገን ሲኖርበት ነው።
ባርነት የተፈጥሮ ጸጋን፥ ማኅበራዊ፥ ሃይማኖታዊ፥ ስነ ልቦናዊ፥ ርስታዊ፥ የትውልድ ትይይዝ ተስፋን በተወሰኑ ሰዎች የበላይነትና ሥልጣን በሚደነገጉ ሕጎች፥ በሚዘረጉ የአስተዳደር መዋቅራትና ዘይቤ የሰውነት መብቱን ሲነጠቅንና በጉልበት ነጻ ዜጋ አይደለህም ተብሎ ገደብ፣ የመኖሪያ ክልል መአቀብ፣ የንግግርና የመዘዋወር ልኬት ተበይኖ ሲሠጠው ነው።
በህይወት የመኖር መብቱን ከፍትህ ውጪ ሲነጠቅ፣ በሰላም ወጥቶ የመግባት መብት ተገድቦ ያለ ፍርድ ሲታሰር፣ ሰቆቃ ሲፈጸምበት፣ ንብረቱ ሲወድም፣ ሰርቶ የማፍራት መብቱ ሲገፈፍ ወይንም የላቡን ውጤት የሚቀማው ሲመጣ አንድ ሰው ባርያ ሆነ ይባላል። ባርያ ማለት ፓለቲካዊ፣ መኅበራዊ ወይንም ኢኮኖሚያዊ መብት የሌለው ፍጡር ማለት ነው።
ነጻነትነፋጊ/ባሪያገዥ፦
የአንድን ሰው ወይንም ቡድን የአንድን በአርያ ስላሴ ነጻ ሆኖ የተፈጠረውን ዜጋ፣ በህይወት የመኖር፣ የመንቀሳቀስ፣ የላቡን ውጤት ባለቤት አይደለህም ብሎ በጉልበት የሚቀማና በዜጎች ህይወትና ሞት፣ ሀብትና ድህነት፥ ማኅበራዊ ቱሳትፎና መገለል፣ የማመን መብቶችን ሲገድብ ወይንም የሚገድብ ሕግና ስርዓት ያቆመ የባሪያ አሳዳሪ ይባላል። በገዢውና በተገዢው መሀከል በሰውነት ብቻ እኩል የሚያደርጉትን ሰብአዊ መብቶች በጉልበት የቀማ ማለት ነው።
የአንድን ማኅበረሰብ ወይንም የአገር ሕዝብ በማስገደድ ከአገር መሠረታዊ እምነት፥ እሤት፥ ሁለንተናዊ አስተመህሮ እና ባህል፥ ነባር ማንነት፣ ስነ መንግሥት፥ አስተዳደር፥ ማኅበራዊ እና ቤተሰባዊ መዋቅርና ሥርዓት ሥልጣን ላይ በወጡ ሰዎች ፍላጎትና ዕሳቤ ልክና አይነት እንዲቀየር የሚያስገደድ የባሪያ አሳዳሪ ስርዓት መገለጫ ነው።
ነጻአውጭ፦
ነጻ አውጭ ግለሰብ፥ ቡደን፥ የአንድ ሥርዓተ ፖለቲካ ተቋም በራሱ በሚተረጉመው መሠረት ሶስት አካላትን ለይቶ በመበየን ይጀምራል፦ አንደኛ ነጻነት ያጡ፥
ሁለተኛ ነጻነት ያሳጡ
ሶስተኛ ነጻ የሚያወጡ ናቸው
በዚህ መሠረት “ነጻ አውጭው እኔ ነኝ” የሚለው ክፍል ራሱን አደራጅቶ ነጻ ወጭዎችና ነጻ አውጭዎችን በትይይቴ በማቆምና ነጻ መውጣት አለባቸው የሚላቸውን ክፍሎች እንደ ራሱ እጅ ሥራና ፍጡር አድርጎ በፕሮፓጋንዳ አእምሮውን በመቆጣጠር ጠላት ወይንም ነጻነት ነፋጊ ባለው ላይ ያዝምታል።
ነጻ አውጭው ወገን ራሱን ነጻነት ላጡት ጠበቃ፥ ነጻነት ላሳጡት ጠላት አድርጎ በመበየን የሚፈጠርን የፖለቲካ ወይንም የውትድርና ንቅናቄ “ነጻ አውጭ” ብሎ ይሰያማል፥ ልዩ ስም ያወጣለታል፥ ከዚያም ራሱን ለዓለም ያስተዋውቃል።
ነጻ አውጭዎች ከምን ነጻ እንደሚያወጡ በግልጽ አይናገሩም። የሚጠቀሙባቸው መልእክቶች አደናጋሪና ጠቅለል ያሉ ናቸው። ከነጻነት በፊትና ከነጻነት በኋላ “ነጻ ወጣ” የሚባለው ሕዝብ በሃይኣኖት፥ በማኅበራዊ፥ በኢኮነሚ፥ በባለ ርስትነት፥ በአጠቃላይ ቀጠናዊ ደኅንነት፥ በትውልድ የአገር ባለቤትነት ተስፋ፥ በማኅበራዊ ሰላማዊ ትሥሥር አንጻር ምን የተሻለ ውጤት እንደሚገኝ ገልጾ በተጠያቂነት ራሱን በማቅረብ ቃል ኪዳን አይገባም። “ነጻነት” የሚለው አጓጊ ቃል በተዐማሪ መብት፥ ክብር በተባሉ ቃላት ድጋፍ የበለጠ የሚያጓጓና ተከታዩን ሲደርስበት ብቻ የሚያውቀው እጅግ ተፈላጊና አሁን እጁ ላይ የሉለ፥ ጠላት በተባሉ አካላት የተወሰዱበት የምድር ላይ ገነት ሆኖ በአእምሮው ይቀረጻል። ነጻ አውጨዎቹ እነዚህ ያልተዘረዘረ፥ መሥፈርትና መለኪያ ያልተቀመጠላቸው ቃላትን በማሳየት ነባርና አሁናዊ ማሥበራዊ፥ መንግሥታዊ፥ እምነትና ባህላዊ ነገሮቸ እሁሉ እንጸየፉ ይደረጋሉ። ነጻ አውጭዎች በዚህ መንገድ ነጻ በሚወጣውና የነጻነት ጠላት በተደረገው ወገን መካከል ሕዝብን በመከፋፈልና አንዱን በአንዱ ላይ በማዝመት ጦርነትን፥ ግጭትና ጥፋት እእየመሩ እንረሱ በድሎትና በገዥነት ይቀጥላሉ።
ነጻነት ለሁሉም በአርያ ስላሴ እኩል የሚሰጥ እንጂ አንዱን ወገን በቡድን ፈርጆ ይህን የበላይ ያኛውን የበታች፣ አንዱን ጌታ ሌላውን ባርያ የሚያደርግ ትግል ነጻ አውጪነት መባል አልነበረበትም። የዚህ አይነት አሠራር ትክክለኛ መገለጫው የጨቋኝነት ተረኝነትና ይገባኛል ኢፍትሐዊነትና ኢሰብአዊነት ንቅናቄ ነበር። በአገራችን የ፶ ዓመታት ታሪክ የኤርትራ፥ የትግራይ፥ የአሮሞ፥ የሲዳማ፥ ወዘተ ነጻ አውጭዎች ከላይ የተዘረዘረውን የነጻ አውጭነት ሚና የተጫወቱ ናቸው።
ትክክለኛው ነጻ አውጭነት፦ አንድን አገር፥ መንግሥት፥ ባህል፥ ታሪክ፥ እምነት፥ ሥርዓተ ማኅበር ያለውን ሕዝብ ከሌላ አህጉር ወይንም አገር በመነሳት እና ድንበር በመሻገር ሁሉንም ቀዳሚ ሀብታትና ሰብአዊ ክብር የሚያሳጣ ባዕድ አካል መልሶ በመዋጋት ማሸነፍና ወደ ቀደመ ክብር መመለስ ነው። በሌላ በኩል አገር ውስጥ በንግሥናም ይሁን “በምርጫ” ወይንም በአብዮት (አመጽ) ተደራጅተው የአገርን የመንግሥት ሥልጣን ወይንም የአንድን አካባቢ ማኅበረሰብ ባህላዊ ነባር መዋቅር በመቆጣጠር የሕዝቡን የተዘረዘሩ ጸጋዎች “በሕገ ወጥ ሕጎች” (ነባር ባህላዊ፥ እምነታዊ፥ ታሪካዊ የሕዝብ እሤቶችን የሚቃረኑ ሕጎች በመደንገግ) አስገዳጅነት ማንነት የሚያስለውጡ “ነጻ አውጭ” ነን ባዮችና አምባገነን መንግሥትን በመዋጋት አሸንፎ ለሕዘቡ በነባር ማንነቱ ላይ ቆሞ የፈቀደውን አንዲያስቀጥል ወይንም እንዲያሻሽል እድል መፍጥር እውነተኛ ነጻ አውጭ ያሰኛል። በዚህ ሚዛን በኢትዮጵያ እውነተኛ ነጻ አውጭ ማኅበረሰብ የማይከፋፍል፥ ነባር እሤቶችን የማያጠፋ፥ ሕገ-ወጥ ሕጎች ለማንበር፥ አገር ለመገንጠል፥ ራሱን ለማንገሥ የማይዋጋ እንደ አማራ ፋኖ ያለ ሊሆን ይችላል። አገር የሚገነጥሉ፥ ለ፭ ዓመታት ሕዝብን የሚከፋፍሉ፥ ለስደት፥ ለርስት አልባነት፥ ከእምነት ለውታት፥ ለእልቂት ጠሚዳርጉ “ነጻ አውጭዎችና መንግሥታት” በግብራቸው ሲጠሩ ወራሪዎችና ባርያ አሳዳሪዎች ተብለው ይበየናሉ።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ባርያ? እንዴት?
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት ባርያ ነውን? መልሱ አዎ ነው ባርያ ነው። ለምን? ከተባለ በባርያ እሳደሪ ዓሥርዓት ውስጥ አንድ ሰው በዕድሜ፥ በዕውቀት፥ በሀብት፥ በማኅበራዊ ክብር ባለው ደረጃ ትንሽ ሊሆን ይችላል፤ ሰውዬው በፖለቲካ መንግሥታዊ ሥልጣኑ ዋና ወይንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሁን የህዝብ ተወካይ በህግ የተጠበቀ እና የሚመካባቸው አንድም ህጋዊ መብት መብት አይኖረውም ።
ለሀምሳ ዓመታት ውስጥ መብት ያለው የአንድ ሰው ብቻ ነው። ሀሳብና ፍላጎት መግለጽ የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው። አንድ ሰው ማለትም አንድ የባሪያ አሳዳሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር የፈለገውን የሚያስርበት፣ የሚገድልበት፣ ሰቆቃ የሚፈጽምበት የባርያ አሳዳሪ ስርዓት ነው። ለምሳሌ ለኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እነ ኮ/ል አጥናፏ አባተ፣ ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ወይንም ጄኔራል አማን እምዶም ሙሉ መብት ያላቸው ሰዎች አልነበሩም። ለአቶ መለስ ዜናዊ አቶ ስዬ አብርሀ፣ ታምራት ላይኔ እኩል ሰዎች ሳይሆኑ እንደ ትል የሚጨፈለቁ ነፍሳት ነበሩ። ለአቶ አብይ አህመድም ለማ መገርሳ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ታዬ ደንደአ እኩል ፍጡር አይደሉም። አገልጋይ ባሮችና የባርያ አሳዳሪው ሲበሳጭ ወስዶ የሚገርፋቸው ምንም መብት የሌላቸው ባሮች ናቸው። ነገ እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን፣ ብርሀኑ ጁላን፣ ሽመልስ አብዲሳን ይዘህ አምጥተህ አጋድመህ አርባ ግረፍልኝ ቢሉ አትችልም የሚል ተቋምም ህግም የለም። የባርያ አሳዳሪ ስርዓት በአንባገነን ሰው መልካም ፈቃድ እንጂ በህግ የተደነገገ ህግና ተቋም አይኖርም። በማኅበረሰብ ደረጃ የአማራ ሕዝብ፥ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ምንም መብት የለዉም፥ ነባር ባህል፥ ነባር እስልምና የሚከተል ዜጋ ምንም መብት የለዉም። ሁሉም በገልጽና በመደበኛ መከላከያ፥ የፖለቲስና የደኅንነት መዋቅር ይታሠራል፥ ይሰደዳል፥ ይጨፈጨፋል። ባርያ አሳዳሪው ያሰበውን ሁሉ በተግባር ለማዋል ማንንም ያጠፋል። በዚህ ሥርዓት ውስጥ፦
፩) ባሪያ አሳዳሪው በተዋረድ ማንም ባለ ስልጣን ከሱ በታች ያሉ ዜጎችን የመግደል፣ የማሰር፣ የማሰቃየት ሙሉ መብት አለው። አቶ መለስ በጥሩ ቋንቋ እንደገለጹት አንድን ሰው “የዓይንህ ቀለም አላማረኝም” ብሎ የማጥፋት፣ የማባረር መብት የሚሰጥ ሥልጣን አላቸው። የባርያ አሳዳሪ በባሮቹ ላይ ደስ ያለውን እርምጃ የመውሰድ መብት አለው። ያስራል፣ ይገርፋል፣ ይቀማል። የኢትዮጵያ እንባገነኖችም ከምክትላቸው ጋር እኩል አደሉም። ፓርላማ ይታዘዛል እንጂ አያዛቸውም። ህዝብ ይታዘዛል ይቀ’ጣል እንጂ የመረጠውን ማውረድ አችልም። ባርያ ጌታውን አይመርጥም።
፪) ባርያ መናገር አይችልም፣ አይፈቀድለትም። ታሪኩን መተረክ እንዳይችል የተደራጁ የፖለቲካ ታዛዥ ልሂቃን ካድሬዎች ህዝብን ሳይጠይቁ የሚፈልገውን፣ የሚጠላውን፣ የሚያወድመውን የሚበቀለውን ያውቁለታል፥ ይተርኩለታልም፥ በመጽሐፍት እየጻፉ ያሳትሙለታል፥ ሙዚየምና ሐውልት የገነቡለታል፥ መዝሙርና ዘፈን ይርሱለታል። እነሱ ልብና ኩላሊትን የመመርመር መለኮታዊ ሥልጣን አለን ይላሉ እንጂ ባርያ የተደረገው ሕዝብ የራሱን ትርክት አያውቅም ተብሎ ይፈረጃል።
፫) ኢትዮጵያኖች ባሮች ተደርገዋል ስንል “እኔ ሰው ነኝ” ማለት አይፈቀድላቸውም። እነሱ ጭቁን ወይ በዝባዥ፣ ወዛደር፣ ቡርዥዋ፣ አብዮተኛ ወይንም ጸረ አብዮተኛ፣ አማራ ወይንም ትግሬ፣ ሲዳማ ወይንም ወላይታ፣ አፋር ወይንም ሱማሌ ነቸው እንጂ በአርያ ስላሴ የተፈጡሩና ከሁሉም ጋር የተዛመዱ አዳማዊ ሰዎች መሆን አይፈቀድላቸውም። ኦሮሞ ከሆነ አማራ ዘመዱ መሆን አይችልም ጠላቱ እንጂ። ራሳቸውን ማንነት ለመተርጎም በተደራጁ የጎሣ ልሂቃን ታግተው በሐሰት ትርክትና በባዕዳን የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ላይ የተመሠረተ አዳዲስ ትርጉም ያላቸው ንዑስ ማንነቶችን ከሚያውቁት ነባር ማንነታቸው በሚቃረን መንገድ እንዲቀበሉ ተገድደዋል። ባርያ ማለት የራሱ ያልሆነና ሰዎች ሞግዚት ሆነው እንድን ማኅበረሰብ ወይን የአገር ሕዝብ ወይንም ግለሰብ ሳይቀር በእርሱ ፍላጎትና ማንነት ላይ ሳይጠይቁት የሚወስኑበት ማለት ነው።
፬) ባርያ “ሰው” አይደለም። መገልገያ ነው። የራሱ ምርጫና ፍላጎት የለውም። ባርያ የግል ማንነት እና ፍላጎት የለውም። ባርያ ለባሮች ምን እንደሚያስፈልጋቸው ራሳቸውን ነጻ አውጭና መንግሥት ያደረጉ ጌቶች ወይንም የእንዚያ ተቋማት ዋና መሪ ጌታቸው ሆኖ ያውቅላቸዋል። ኢትዮጵያን “ሰው” ከመሆን ነጻነታቸው ተዋርደው የፖለቲካ ልሂቃን በሚበይኑላቸው የማንነት አዲስ ትርጉም ውስጥ ቡድን ብቻ ሆነዋል። ይህ አዲስ ማንነታቸው ጥቅምና መብት የሚሰጣቸው ወይንም የሚነሳቸው በተለዩ የአገሪቱ ቦታዎችና በተወሰኑ ቋንቋ በመናገር ብቻ ሲሆን ሙሉና ነጻ ሰው ሆነው ለመኖር ከሞከሩ የሚያጋጥማቸው የስደት፥ የመገደል፥ የመደኸይትና ሙሉ በሙሉ ፍትሕን ማጣት ብቻ ነው። ወይንም አሁን አብይ አህመድ እንደሚያደርገው በጅምላ መጨፍጨፍ፥ በእቅድ መደኸየት፥ ከአገር መሰደድ፥ መኖርያ መንደርና ከተማ ማጣት ብቻ ነው እድላለቸው።
፭) ባርያ የመንቀሳቀስ መብት የለውም። የባርያ ቦታው በባርያ አሳዳሪው ፈቃድ የተበየነለት መንደር ወይንም ክልል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ዜጋ በአገሩ ውስጥ በሚፈቅድበት ቦታ ተዘዋውሮ ያለ ሥጋት፥ መብቱና ነጻነቱ ተከብሮ መኖር፥ ሀብት ማፍራት፥ እምነቱንና ባህሉን በነጻነት ማካሄድ አይችልም።
ከዚህ ወደዚህ እንዴትመጣን?
ከዚያም ወደዚህ ከዚህ ወደዚህ እንዴትመጣን?
ከዚያም ወደዚህ
፮) ባሪያ የአለቃውን ስህተት የመተቸት መብት የለውም። ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን መንግሥት በአገልጋይነት የመመዘንና የማረም መብትና ነጻነት የላቸውም። የተሰባሰቡ የፖለቲካ ልሂቃን የአገሪቱን ሀብትና የጸጥታ መዋቅር፥ የብዝኃን መገናኛና የፍትሕ መዋቅራቱን በመቆጣጠር የሕዝቡን ፍላጎት፥ እሤት፥ ነባር እምነትና የአስተዳደር ሥርዓት በማፈራረስ ያለ ማቋረጥ ላለፉት ፶ ዓመታት ያፈናቅሉታል፥ ያሳድዱታል፥ ይገድሉታል፥ የጋጩታል፥ መደበኛና መነደበኛ ባልሆኑ ታጣቂዎች ይጨፈጭፉታል፥ በቡድን ከፍለው ያዋጉታል፥ ፍትሕ ይነፍጉታል፥ የት መኖር እንደማይችል እና እንደማይችል ይወስኑለታል፥ በመቶ ሺዎች ያሥሩታል። በበረሃ የማጎርያ ካምፕ ያሰቃዩታል፥ ያስርቡታል፥ በበሽታ አስለክፈው ይፈጁታል።
፯) ባሮች የባህል፥ የይማኖት፥ የስነ መንግሥት፥ የስነ ማኅበረሰብ፥ የስነ ብዕል ትርክት የመምረጥ መብት የላቸውም። የጌታቸው ባህል ሀይማኖትና ትርክት የነሱ ይሆናል። ኢትዮጵያ ሕዝብ በሺዎች ዘመናት ሂደት፥ በብዝኃ እምነትና ባህሉ፥ በብዝኃ አሠፋፈሩና በአየር ንብረት ልዩነት፥ በመቀላቀልና ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው በመጓጓዝና በመሥፍር ያፈራቸው ማኅበራዊ፥ ልማታዊ፥ የሕክምና፥ የኪነ ጥበብና የሥርዓተ መንግሥትና ማኅበረሰብ ዕውቀቶቹ፥ እሤቶቹና መዋቅራቱ ሙሉ በሙሉ ተፍቀዋል። ነባር ጸጋዎቹን የተደራጁ ዘመናውያን የባዕዳን እስተሳሰብ አገልጋዮች በጠላትነት ፈርጀው “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ወይንም ታላቋ የእገሌ አገር በሚል የሚጠሩ የጎሣ አገራትን ለመፍጠር ነባርነት ላይ ጦርነት ተከፍቷል። ዜጎች ለልብሳቸው፥ ለመኖሪያ ቤታቸወ እግንባታ፥ ለጤናቸው መድኃኒት፥ ራሳቸውን ለመከላከል መሣሪያ፥ ለግብርናቸው የሰብልና የእንስሳት ዘርያ፥ ለአፈራቸው መልማት ማዳበርያ ሁሉ በውጭ ባዕዳን ላይ ጥገኛ ሆነዋል። ይህ ሁኔታ ሕዝቡን የገዥዎቹ ባርያ ሲያደርጋቸው፥ ገዥዎችን ደግሞ የባዕዳን ባሪያና የውክልና ቅኝ ገዢዎች አገልጋዮች አድእረጎአቸዋል።
ከእነዚህ ከ፯ቱ የባርነት መገለጫዎች ለመገላገል የሚንቀሳቀስ ዜጋ ሁሉ እርሱ እውነተኛ ነጻ ወጭና አውጭ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ ወጭና አውጭ ሆኖ መነሳት በሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ለዚህ ሌላ ነጻ አውጭ ከመጠበቅ የባሪያ ስነ ልቦና ራሱን ነጻ ማውጣት ይጠበቅበታል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ የሚወጣው ከማነው?
ባርያ ምንም መብት የለውም። ከላይ ከላይ ማስመሰል እንጂ ደመቀ መኮንን፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ አበባው ታደሰ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ ወዘተ የባሪያዎቹ ካቦ ወይንም አለቃ ናቸው እንጂ እነሱም ምንም መብት የሌላቸው። ባርያ አሳዳሪው ደስ ያለው ቀን በጠፍር አስዘርጥጦ ከፊቱ ጥሎ የሚገርፋቸው ከሌሎች ባሮች ምንም ከፍ ያለ መብት የላቸውም።
ስዬ አብረሀ ጦርነት መዋጋት ሳይቀር ጦርነት መፍጠር እንችላለን ብሎ ሲታበይ መብትና ሀይል ያለው ሰው ለብዙ ይመስል ነበር። በባሮች ላይ የሚፎልል የባሮች አለቃ ባርያ መሆኑን ተጠልፎ ተጥሎ እስኪገረፍ ለራሱም አያውቅም ነበር። እሱ የመግረፍ፣ የመዝረፍ፣ የመግደል በባሮች ላይ ሙሉ መብት ነበረው። እሱም ባርያ እንደሆነ የገባው ቃሊቲ ያለ ፍርድ ሲወርድ ነው። እነ አበባው ታደሰም እነ ተመስገን ጥሩነህም፣ እነ አደም ፋራህም መጨረሻቸው ጅራፍ ነው።
ለአንድ ሰው መብት ሰጥቶ ለሌላው መከልከል የትም አለም አይቻልም። የአንድን በአርያ ስላሴ የተፈጠረ ሰውን መብት ስንገፍ፣ የኛንም አብረን ነው የምንገፈው። እኛ ከኛ በታች ያሉትን የመግፈፍ መብት የሰጠን እሱም የኛን መብት የመግፈፍ መብት እንዳለው ስለሚያውቅ ነው።
ታድያ ኢትዮጵያውያን እንዴት ባሮች ይይመስላ
ፈረንጆቹ ይቺ ነገር የመጥረቢያው ቀጭን ጫፍ ነች ይላሉ (the thin end of the wedge)። በቀጭኗ ገብቶ ነው የኢትዮጵያውያንን መሰረት መፈልቀቅ የተቻለው።
ኢትዮጵያዊ ምንም ደሀ ቢሆን አንድ ጉልበተኛና ባለ ጊዜ ቢገፋው “ምነው እኔም እንዳንተ በአርያ ስላሴ አምሳል የተፈጠርኩ ሰው ነኝ” የሚል ሁሉን እኩል የሚያደርግ ፍልስፍናና እምነት ነበረው ህዝብ ነበር። ከፊቱ የሚያየው፣ ደሀ፣ ቁስለኛ ወይንም አካለ ስንኩል ቢሆን ይህ ሰው ሁሉን በፈጠረና በመጨረሻውም በሁሉም ላይ የሚፈርድበትን ፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ እንደሆነ የሚያስገነዝብ እምነትና ፍልስፍና የነበረው ነበር።
ቁሬሽና ሳንቲም የሚለውን እንኳን ለማኝ አይልም ነበር። የኔ ቢጤ የሚል እምነትና ፍልስፍና ያለው ነበር። ሰውን በሀብቱ፣ በመልኩ፣ በዘር ሰይፈርጅ እንደ እሱ እኩል በአርአያ ስላሴ አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጡር እንደሆነ ያስብ ነበር።
ሕዝብ ነጻነቱን የሚያሳጡት የሌሎች የሩቅ ባዕዳን ፍላጎቶችና በባዕዳን አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊ ማያቸውን (ነጽሮተ-ዓለም) ተነጥቀው ለነባርነት ጠላት፥ ለማያውቁት አዲስነት ሁሉ ትጉህ የሆኑ አገር-በቀል ባዕዳን የፖለቲካ ልሂቃን፥ እና እነርሱን ተከልለው ነባርነትን ለማጥፋት የሚሠሩ ጽንፈኛ ሰውር ጂሃዲስቶች፥ የናዚ-ጀርመን ክርስትና ትራፊ ፕሮቴስታንቶች ባርነት ነው።
• የዐባይን ወንዝ ለመቆጣጠር ከሺ ዘመን የዘለለ ህልም ያላት፥ በአፈሪካ ጎረቤት አገራት ቤተሰብነት የማታምን፥ ከገዟት ግማሽ ደርዘን ከሚሞሉ ቅኝ ገዥዎች በወረስችው አሉታዊ ሥርዓተ ንግሥታዊ ባህል ከአፍሪካዊነቷ የበለጠ በገዟት የቀድሞ ጌቶቿ አእምሮ የምታስብ ግብጽ፤
• የአረብን ዘይት ተቆጣጠርኖና በአጭር የቀይ ባህር (ባብል ማዴብ) የባሕር መጓጓዣ ለመምጠጥ የሚሠራው፥ የአፈሪካን ልጆች እያባላ ዘላለም ማዕድናትን በዝረፍ ድኽነትን ማስቀጠል የሚፈልገው የምዕራቡ ዓለም ሁሉ ከአድዋ ድል ማግሥት ጀምሮ የተነሳውን የጥቁርና የቢጫ ሕዝብ የነጻነት ፍላጎት መልሳ የምትቀሰቅብን ኢትዮጵያ በመሆኗ ተዳክማና ተበታትና መየት የሚሹቱ፤
• ጅቡቲን፥ አሰብን፥ መጽዋን፥ ህንድ ውቅቂያኖስን በከበባ ከኢትዮጵያ በመነጠል የቀደሙ ቤተሰቦቿኝ ወደ አገርነት በመለወጥና በጠላትነት በማሰለፍ ዙሪያውን እሣት ያደረጉት ምዕራባውያንና ዓለም ሁሉ ለአላህ እስኪሆን እንቅልፍ የሌለው የአረቡ እምነት [“እምነት ሁሉ ለአላህ እሰኪሆን ተዋጉአቸው (وَقَاتِلُوْهُمْ حَتّٰى لَا تَكُوْنَ فِتْنَةٌ وَّيَكُوْنَ الدِّيْنُ كُلُّهٗ لِلّٰهِۚ فَاِنِ انْتَهَوْا فَاِنَّ اللّٰهَ بِمَا يَعْمَلُوْنَ بَصِيْرٌ ( الأنفال: ٣٩ ) . (አል-አፍና[8] : 39)] ክርስትና መሠረት የሆናትን አገር እጅግ የሚፈታተኑ ስብሰቦችና አገራት፤
በስማቸው ሲጠሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ የሚወጣው ከሚከተሉት አስተሳሰቦችና አስተሳሰቦቹን መሣሪያ በማድረግ ከተጫኑ አካላትና ሁኔታዎች ሁሉ ነው፦
አስተሳሰብ | የአስተሳሰቡ ተሸካሚ አካል | አሁን የተፈጠረው ሁኔታ |
፩) ነባር ጠልነት እና ጭፍን አዲስ ናፋቂነት፥ የባዕዳን አስተሳሰብ ተሸካሚነት፥ ታሪክ በራዥነት፥ ሕዝብን የመግዛትና በዘረፋ የመክበር የልሂቃን ሙስና | ፩) ሕወሃት ፪) ኦነግ ፫) ዉሐብያ ኢስላም ድርጅቶችና መድረሳዎች ፬) የቫቲካን እጅ (የተወሰኑ ካቶሊካውያን) ፭) የናዚ-ጀርመን ትራፊ ዘረኛ ፕሮቴስታንት ፮) አምላክ-የለሽ ባእድ አምላኪ ሴኩላር ልሂቃን፥ የትምህርት ተቋማት | ፩) የአገር በቋንቋና በሐሰተኛ ትርክት በተሠመረ ድንበር ተከፋፍሎ ስደት፥ ፖለቲካ ሠራሽ ወገናዊ ድኽነት፥ መፈናቀልና ስደት፥ ፍጅትና ጦርነት ፪) አጠቃላይ ሙስና (ቁሳዊ፥ ሞራላዊ፥ ፖለቲካዊና ማኅበረሰባዊ) ፫) ጥቂት የየጎሣው ልሂቃን “ሕባችን” የሚሉትን ወገን ነፍስና ሥጋ በመቆጣጠር “ሌላ” በሚሉትና በአገራቸው ላይ በአፍራሽነት ማሰለፍ ፫) የሕዝብ አንድነት መላላት፥ የእምነቶች መርከስና የፖለቲካ አገልጋይ መሆን፥ የእርስ በርስ መጋጨትና የተወሰኒ ዒላማ የተደረጉ ማኅበረሰቦችና እምነቶች ህልውና፥ የአገር ሉዓላዊነትና የግዛት አንድንት አደጋ ላይ መውደቅ — የኢትዮጵያን ሕዝብ በድኅነት፥ በሥጋትና በግጭት ውስጥ በማኖር፥ ጥገኝነትን፥ ስደትና መለያየትን ማጠናከር በማኖር የገዥዎችና የነጻ አውጭ ነን ባይ ልሂቃን ቡድን ወይንም የታጠቂዎች ባርነቱን ማስቀጠል። |
፪) የዐባይ ወንዝን በጠቅላይነት መጠቀም፥ ቀይ ባህርን፥ ጅቡቲንና ሶማሌን መቆጣጠርና ለኢትዮጵያ የማይመች ከባቢ መፍጠር፥ ኢትዮጵያ ካልተዳከመችና በተለያዩ የእምነትና የቋንቋ ዘውግ ካልተከፋፈለችና በመጨረሻም ካልፈረሰች የጥቁሮች ነጻነት አቀጣጣይ እርሾ በመሆኗ ዘለቄታዊ እጅ አዙር ቅኝ ግዛትና ዘረፋ እንዳይቀጥል የማድረግ አቅም አላት፤ | ፩) ግብጽ ፪) የአረብ ኢምሬት፥ ሰውዲ አረብያ፥ ኢራን (?)፥ ቱርክ ፫) አውሮፓ (ፈረንሳይ፥ ኢንግሊዝ፥ ጀርመን፥ ጣሊያን፥ —) ፬) አሜሪካ ፭) ኤርትራ (አሰብን መልሳ እንዳትጠይቅ ማዳከም) | ፩) የአገር ውስጥ የእርስ በርስ ግጭትና ጽንፈኞችን መደገፍና ብጥብጥ ማስቀጠል፤ ሶማልያና ሱዳንን እንደ ውክልና የግጭትና የጫና መሣሪያ መጠቀም ፪) ኦርቶዶክስ ክርስትናን፥ አማራን የሚኣጠቃ መንግሥት፥ ሕወሃትን፥ ኦነግን በመገፍ ሰቆቃና ስደት ማስቀጠል ፫) የተፋለሰ የንግድ ግኑኝነትና የብድር ጫና ሥእ መጣልና ሙስናን ማበረታታት (የሰጡትን ብድር መልእሰው በውጭ ሀብት ሲያፈሩና በባንክ ሲያከማቹ ባለሥልጣናትን አለመቆጣጠር) ፬) ኦነግ፥ ብልጽግና፥ ሕወሃት በሕይወት አንዲቀጥሉ ማስታረቅና መርዳት ፭) እውነተና ለአገር አንድነትና ጥንካሬ የሚሠሩ ንቅናቄዎችን ድጋፍ መንሳት እና አጥፊውን መንግሥት በሥልጣን እንዲቀጥል መደገፍ — የኢትዮጵያን ሕዝብ በድኅነት፥ በሥጋትና በግጭት ውስጥ በማኖር፥ ጥገኝነትን፥ ስደትና መለያየትን ማጠናከር በማኖር የገዥዎችና የነጻ አውጭ ነን ባይ ልሂቃን ቡድን ወይንም የታጠቂዎች ባርነቱን ማስቀጠል። |
፫) አፍሪካን ሙሉ በሙሉ ለማስለም በሊቢያ፥ በናይጀርያ፥ በግብጽ ተገኝቶ የነበረው ጂሃዳዊ መስፋፋት የተገታው በኢትዮጵያ ነው፤ ለወደፊቱም እንቅፋትነቷ እንዳይቀጥል ኦርቶዶክስን ከሚያጠፋ ማንኛውም የአገር ውስጥና የውጭ ጠላት ጋር መተባበር | ፩) ጽንፈኛ ዉሀብያ ኢስላም ግለሰቦች፥ ቡድኖች፥ መስጊዶችና መድረሳዎች ፪) አረብ ኤምሬት ፫) ሰውዲ አረብያ ፬) ቱርክ ፭) ግብጽ | ፩) በጎሣ ታጣቂዎች ውስጥና ስም ተደራጅቶ ክርስቲያኖችን ከመላው የኦሮምያ ክልል ማጽዳት፥ በሌሎች ክልሎችም ፍጅት እንዲፈጸምና የእምንተ ጦርነት እንዲነሳሳ ግጭቶችን ማባባስ፥ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መድልዎችን በተቻለ ቦታ ሁሉ መፈጸም ፪) የብልጽግናና የሕወሃትን የአገር ማፍረስ ተልዕኮ በገንዘብ፥ በፕሮፓጋንዳ፥ በቴክኖሎጂ መደገፍ ፫) ማንኛውንም የውስጥና የጎረቤት አገራት ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎች መደገፍ — የኢትዮጵያን ሕዝብ በድኅነት፥ በሥጋትና በግጭት ውስጥ በማኖር፥ ጥገኝነትን፥ ስደትና መለያየትን ማጠናከር በማኖር የገዥዎችና የነጻ አውጭ ነን ባይ ልሂቃን ቡድን ወይንም የታጠቂዎች ባርነቱን ማስቀጠል። |
፬) ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ ጥገኝነት በማሠር ከድኽነት እንዳትወጣና ለጥቅማቸው እንደትኖር ማድረግ፥ ለዚህ አሻንጉሊትና የሕዝቡን የቀደመ ጥንካሬ ለመስበር የሚሠሩ የሀሳብ ስንኩልነት ያላቸውን መሪዎች ሥልጣን ላይ ማውጣት፥ የእርስ በርስ ግጭቱን ማስቀጠል፥ በተለይ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስትናን ማዳከም | ፩) አሜሪካ፦ የቢልጌት ፋውንዴሽን፥ የዓለም ባንክ፥ የዓለም የገንዘብ ድርጅት፥ የተባበሩት መንግሥታት አካላት፥ ፪) አውሮፓ ፫) የባዕዳንን ፍላጎት ሳይመረምሩ የሚያገለግሉ የኢትዮጵያ መንግሥት መዋቅራት፤ በተለይ ግብርና፥ ጤና፥ ትምህርት፥ ንግድ ሚኒስቴሮችና ፖሊሲዎቻቸው | ፩) የምግብ ሰብል ልማት ሙሉ በሙሉ በመንግሥትና መንግሥትን በአሻንጉሊትነት ባስቀመጡ የውጭ ግብአት እና ቴክኖሎጂ አቀራቢ አገራት ላይ ጥገኛ መሆን፤ ፪) ለውጥ ዘረ መል የሰብልና የእንስሳት ዘርያዎች(genetically modified seeds) በማስፋፋትና አገር በቀልና በገበሬ ባለቤትነት የተያዘውን በማጥፋት ዘላለማዊ ተገዥነትን ማረጋገጥ ፫) አገር በቀል እውቀት፥ የአስተዳደር ሥርዓትና መዋቅር፥ ስነ መንግሥትና በማጥፋት ግራ የገባውና የማይግባባ ትውልድ መፍጠር መቻላቸው ፬) ተስፋ ቢስ ዜጋ በመፍጠር በስደት የአእምሮ ፍልሰትና ርካሽ ጉለበትን ወደ ምዕራብ፥ የሴት ባሪያን ለአረብ ለማቅረብ የተገደደች አገር መፍጠር ማቻላቸው — የኢትዮጵያን ሕዝብ በድኅነት፥ በሥጋትና በግጭት ውስጥ በማኖር፥ ጥገኝነትን፥ ስደትና መለያየትን ማጠናከር በማኖር የገዥዎችና የነጻ አውጭ ነን ባይ ልሂቃን ቡድን ወይንም የታጠቂዎች ባርነቱን ማስቀጠል። |
ሲጠቃለል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ የሚወጣው ነባር እምነቶቹን፥ እሤቶቹን፥ በረዥም ታሪክ ያካባታቸውን ዕውቀቶቹን፥ እምነቱንና ባህሉን ለማጥፋት ከተሰለፉት፥ ወንዞቹን፥ ማድናቱንና የባህር በሮቹን ሁሉ በመቆጣጠር — የኢትዮጵያን ሕዝብ በድኅነት፥ በሥጋትና በግጭት ውስጥ በማኖር፥ ጥገኝነትን፥ ስደትና መለያየትን ማጠናከር በማኖር የገዥዎችና የነጻ አውጭ ነን ባይ ልሂቃን ቡድን ወይንም የታጠቂዎች ባርበቱን ለማስቀጠል ከሚሠሩት የውጭና የውስጥ አካላት ሁሉ ነው። እነዚህም ፦
በአስተሳሰብ
፩) ከነባር ጠልነት እና ጭፍን አዲስ ናፋቂነት፥ የባዕዳን አስተሳሰብ ተሸካሚነት፥ ታሪክ በራዥነት፥ ሕዝብን
፪) የዐባይ ወንዝ ባለቤትነት፥ የቀይ ባህርን ታሪካዊ ባለቤትነትና የወደፊት ተጽእኖዋን ታሳቢ በማድረግ፥ ነባር የጥቁር የነጻነት አርአያነቷን ታሳቢ ያደረገ የውጭ ጫናዎችን ተቀብሎ የሚኖር መንግሥትና የልሂቃን የተገዥነት ስነ ልቦና
፫) ከከፋፋይ የማንነት ፖለቲካና ከጽንፈኞች በማንነት ፖለቲካ ተከልሎ ሀገራዊ አደጋ የመደቀን አውድ
፬) ከሁለንተናዊ አገራዊ ጥገኝነት ውስጥ የሚያኖር የመንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት
የክፉ አስተሳሰቡ ተሸካሚ አካላት ደረጃ ኢትዮጵያ ነጻ መውጣት የሚገባት
፩) ከሕወሃት እና ከኦነግ የ፶ ዓመታት አፍራሽ አስተሳሰብ
፫) ነባር ነባህልና እምነትን ሁሉ በማጥፋትና በመተካት ከሚታወቀው የዉሐብያ ኢስላም ድርጅቶችና መድረሳዎች
፬) ከቫቲካን እጅ (የተወሰኑ ካቶሊካውያን) ማስገቢያ ቀዳዳዎች
፭) ከናዚ-ጀርመን ትራፊ ዘረኛ ፕሮቴስታንት
፮) አምላክ-የለሽ ባእድ አምላኪ ሴኩላር ልሂቃን፥ የትምህርት ተቋማት
፯) ግብጽ፥ የአረብ ኢምሬት፥ ሰውዲ አረብያ፥ ኢራን (?)፥ ቱርክ፥ አውሮፓ (ፈረንሳይ፥ ኢንግሊዝ፥ ጀርመን፥ ጣሊያን፥ —)፥ አሜሪካ ጣልቃ ገብነትና ተጽእኖዎች
የኢትዮጵያ ውስጥ በርነት ውስጥ ነውን?
የኢትዮጵያ በሚከተሉት ለሰው ልጅ ነጻነት መሠረት በሆኑ መሥፈርቶች ሁሉ ሲመዘን በራሱ የማይወስን ሕዝብ በመሆኑ ባርያ ነው፦
፩) መሠረታዊ የምግብ የመድኃኒት፥ የመጠለያ፥ ልብስ፥ የማምረጫ ግብአትና ቴክኖሎጂ፥ በመከላከያ ቴክኖሎጂ ሁሉ በሌሎች የውጭ አካላት ለዚያውም በእምነት የማይመስሉት፥ በታሪክና በአሁኑም ዘመን በጥላቻና አገሪቷን በማዳከም በሚሳተፉ አገሮች ላይ ኖውና ባርነት ውስጥ ነው።
፪) ከቤተሰብ እስከ ኅበረተሰብና አጠቃላይ አገር የሚመራበት ማኅበራዊ፥ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ፍልስፍና፥ መዋቅር፥ ትምህርት እሤቱን፥ ነባር እምነቶቹንና ባህሉን፥ ቀዳሚ ስነ መንግሥትና ማሥበራዊ መዋቅሩን ሁሉ በማፈራረስ በጥቂት የተደረጁ ውጭ-ናፋቂ የፖለቲካ ልሂቃን ቁትጥር ሥር በመሆኑ ማርያ ነው።
፫) በገዛ አገሩ የሚኖርበት ሥፍራ በልሂቃን ፖለቲካ የሚበየንለት፥ ስደትና ሞት ሕይወቱ የሆነ፥ ፍትሕ የሚነፈግ፥ ርስት አልባ ሕዝብ በመሆኑ ባርያ ነው።
፬) የእምነት ነጻነቱ ተገስሶ የጎሣ ጳጳሳትና ሼኪዎች በፖለቲካ ሥርዓት የሚመደብለት፤ መእመናን በተለይ ኦርቶዶክሳውያን የመኖር ዋስትናቸው የተገፈፈበት ሕዝብ በመሆኑ ባርያ ነው።
፭) በረዥም ዘመን የለውጥና የነውጥ ማዕበል ውስጥ በማለፉና ነጻ አውጭ ነን በሚሉ ማፍያ ልሂቃን ግራ ሲጋባ የኖረ በመሆኑ ነጻ አውጭ እና መፍትሔ ሰጭ ሌላ አካላ በመጠበቅ መከራ የሚሸከምነባ የባርያ ስነ ልቦና ያዳበረ ሕዝብ በመሆኑ ባርያ ነው።
እንዴት ባርያ ሆነ?
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአብዛኛው አማኝ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በተለይ ክርስቲያኑ እግዚአብሔር ፈጣሪውን ያምናል ፤ በዚየው አንጻር የመንግሥት ሥልጣን ላይ የወጣውን ቡድን ከእግዚአብሔር የተፈቀደላቸው ነው በሚል ብሂል ሳይገዳደር ይቀበላል። በአውሮፓ፥ በቱርክና በግብጽ ወረራዎች ባያቸው የቴክኖሎጂ ብልጫ፥ በፋብሪካና የቴክኖጂ ውጤቶች በመደመም ዘመናዊ ትምህርት ወደ አገር ሲገባ የራሱን ሁሉ ወደ መናቅና በዚያ ዘመናዊ ትምህርት ውስጥ ያለፈውን ሰው ሁሉ እንደ ታዳጊና የችግር ሁሉ መፍትሔ ሰጭ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አዳብሯል። ይህን የተገነዘቡት ልሂቃን ምንም ፍሬ የሚያፈራ ጠቃሚ ዕወቀት ሳይኖራቸው ነባሩን ዕውቀት፥ የአስተዳደርና ማኅበራዊ ሥሪት በማጥፋት ተጠምደው ሕዝቡን ባዶ አስቀሩት።
ሕዝቡ ግጭት መፍታት፥ ቤተሰብ ማስተዳደር፥ እእረሻ ማልማት፥ በሽታን ማከም፥ አገር ማስተዳደር፥ እውቀትን በምርምር ማዳበርም ሆነ መውረስ ሁሉም ለጥቂት ልሂቃን በመተው ጥገኛ ሆነ። በዚህ ጥገኝነት ውስጥ የሚኣጋጥመውን ችግር ሁሉ የቀድሞ ሥርዓት ያመጣባችሁ በመሆኑና የዚህ ሥርዓት አምጭዎችና ደጋፊዎች ኦርቶዶክስ ክርስትናና አማራ የተባለ ማኅበረሰብ፥ የአማራን ባህል በአዎንታዊነት የሚመለከት ወይንም ተመሳሳይ እምነት፥ ባህልና ሀገራዊ ትርክት ያለው ማኅበረሰብና ማኅበራዊ መዋቅር ሁሉ ጨቋኝ ነውና ነጻ ላውጣችሁ ለሚለው ልሂቅ ባርያ ሆነ።
የራሱን ጥሎ፥ የናፈቀውንም የምዕራባውያ ሥልጣኑ ሳያገኝ የምግብ ለማኝና ውራጅ ለባሽ፥ ስደተኛና ተሳዳጅ፥ ተገዳይና ፍትሕ የተነፈገ ባርያ ሆነ።
ይህን የባርነት መንፈስ አሽቀንጥሮ ለመጣል የጠንቀሳቀሰው ክፍለ ሕዝብ ቢኖር ለግዜው የአማራ ፋኖ ነው። በዚህም ማኅበረሰብ ውስጥ ቢሆን የባርያ ስነ ልቦናና ጥገኝነት የጸናባቸው ብዙዎች በባንዳነት ለሕወሐትና ለኦነግ ኦሮሙማ ቀሳፊ የፖለቲካ ሥርዓት ማገልገልን ገና አልጠገቡትም። የነጻነት ታጋዮችን ለማሰናከል ይፍጨረጨራሉ። ሌላው ማኅበረሰብ ትግሉ የብልጽግናና የአማራ መስሎት ቆሞ ይመለከታል፤ ገና ትግሉ ነጻ ሰው፥ ነጻ ዜጋ ለመሆን በሚፈልጉትና ሰውን በባርነት እየገዙና አምላክን ተክተው፥ ራሳቸው አገርና ሕዝብ ተብለው መኖር በሚፈልጉ የፖለቲካ ተቋማት መካከል ነው።
የኢትዮጵያን ማንስ ነጻ ያወጣዋል?
ባህል፥ ሃይማኖትና ታሪክ አንደሚያሳዩት አገር ሲወረር በመንግሥት አስተባባሪነትና መሪነት አገር ከውጭ ጠላት ነጻ ይወጣ ነበር። አሁን ግን የኢትዮጵያ መንግሥት አገርና ሕዝብን ሳይሆን ጎሣን ሰብስቦ በሌላው ላይ እያዘመተ ሁሉነም የሥጋት ባርያ በማድረግ የሚገዛ በመሆኑ ከመንግሥት ነጻነት አይጠበቅም፥ ነጻነት ነጣቂ ነውና።
መንግሥት የሚገባውን ሕዝብን የመጠበቅ ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒ ሲቆም በአገሪቷ ያሉና ለእግዚአብሔርና ለሕሊናቸው ብቻ የሚኖሩ የሃይማኖትና የባህል መሪዎች መንግሥትን በመገሠጽና ሕዝብን በማስተባበር ከነጻነት ነፋጊው መንግሥትም ሆነ ከውጭ ለሚመጣ ጠላት ሕዝብን መርተው ነጻ ያወጡታል። በዛሬዋ ኢትዮጵያ የሃይማኖትና የባህል መሪዎች የጎሣ ፖለቲካ አገልጋዮች ሆነው በክህደት ውስጥ ድሎትና ምቾት የሚያሳድዱ ገድለው ጳጳስ መሆን የሚፈልጉ፥ በጎሣ መጅልስና ሲኖዶስ የሚመሠርቱ ሙሰኞችና ነጻነት ነፋጊዎች ሆነዋልና ከእነርሱ የነጻ አውጭነት ሚና አይጠበቅም።
ነጻ የሲቪል ድርጅቶች ሕዝብን በማንቃትና በማስተባበር ኃላፊነታቸውን መወጣጥ ባልቻሉ መንግሥታት ምትክ ሌላ የሕዝብ መንግሥት እንዲተካ ሚና ይወስዳሉ። በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከጎሣ ፖለቲካው ነጻ የሆኑና ለሕዝብ የቆሙ ሲቪክ ድርጅቶች የሉም፤ ብዙዎች በጥቃቅን ቁሰዊ ልማት ላይ የሚያተኩሩና በውጭ እርዳታ ሰጭዎች ሳንባ የሚተነፍሱ ናቸው። ራሳቸውም የባዕዳን ባሮች ስለሆኑ ነጻነትን የሚመለከት ሚና አይኖራቸውም።
የአገር መንግሥትና የሃይማኖት መሪዎች ሚናቸውን ተቃርነው ሲገኙ፥ አገርና ሕዝብ አደጋ ላይ ሲወድቅ አሁን በአማራ ፋኖ ተጋድሎ አንደታየው የአካባቢ ባህላዊ አደረጃጀቶችና የጎበዝ አለቆች ሕዝቡን አንቀሳቅሰው አጥፊውን ሥርዓት ይፋለሙታል። ይህ ተስፋ ሰጭ ጅምር ነውና ሌሎችም በተመሳሳይ ለመነሳት ነጻ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ከመጠበቅ የባርያ ስነልቦና መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
ስለዚህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከባርነት የሚያላቅቀው የሚከተሉት ተዋንያን ከማመንታት፥ ተአምራት ከመጠበቅና በሌሎች ሰማዕተነት ራሳቸውን ደብቀው ነጻነት ከመጠበቅ ባህል ወጥተው ሲተባበሩ ነው፡
፩) የአምሓራ ፋኖ
፪) የማንኛውም በሰው ልጅ ነጻነት፥ በኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚያምን፥ ከሕወሃትና ከኦነግ ዘረኛ የፖለቲካ ርእዮትና የሐሰት ትርክት ነጻ የሆነ ሁሉ ለአውነትና ለፍትህ፥ ለሰብአዊነትና ለሕሊና በግልና በወል ሲቆም ነው፤
፫) ከዘረኝነት፥ ከሌብነት፥ ከአድልዎ ነጻ የሆኑ መእመናንና ጥቂት የተረፉ ከተገኙ የሃይማኖት መምህራንና መሪዎች ተባብረው “ፖለቲካ አይመለከተንም” ከሚለው ድንቁርናና መደበቂያ ወጥተው አጥፊውን የፖለቲካ ሥርዓትና ነጻ አውጭዎችን ፊት ለፊት ሲጋፈጡት ነው።
፬) ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ፖለቲካ የሚፈጥራቸውን የዘረኞች መጅልሶችና ሲኖዶሶች፥ የዚህ ጥፋት ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችን ፊት ለፊት ሲቃወማቸውና ከቤተ እምነቱ ሲለያቸው ነጻነት ቅርብ ይሆናል።