የፋኖ ትግል ውጤት እያመጣ መሆኑን ለመረዳት የአብይን እንቅስቃሴ መመልከት በቂ ነው። ፋኖ እንዳቀደው የአማራ ሕዝብ በህይወት የሚያድነው ነጻ አውጪ መጠበቅን አቁሞ የራሱን ነጻነት ሲያውጅ ነው።
ፋኖ አብይን ሲያሯሩጠው እበላ በሎ የከበበው ጥሎት መሸሹን በአይኑ እያየ ነው። ለሰላሳ ሁለት አመታት አማራን በመስደብ፣ በመግደል፣ በመግረፍ፣ በማፈናቀል በህወሀት እና በብልጽና የሚያሾም ነበር። አማራን የሰደበ፣ የደበደበና የገደለ በፈጣን የስልጣን እርከኑን እየዘለሉ መሾም የተለመደ ነበር። አማራን መስደብና መግደል እንደ ታማኝ አገልጋይ በመለስ ዜናዊም ሆነ በነሽመልስ አብዲሳም የሚይሳሳይ ዋነኛ መመዘኛ ነው።
እነ ታምራት ላይኔ “ጊዜው አሁን ነው አማራን በሉት በማለትና ኤርትራ ሄደው በአማራ ስም እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቅ” እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ደርሰው ነበር። “አማራ ልጋጋም ያለ፣ አማራ ው ዛፍ ስለቆረጠ አባረርኩ ያለ እንደ ሽፈራው ሽጉጤ ያለ፣ አማራን ለመግደል አለሁ የሚል እንደ ጄኔራል አበባውና እንደነ አገኘሁ ተሻገር ያለ በስልጣን ላይ ስልጣን በመሬት ላይ መሬት ይጨመርለታል። ለአማራ የተቆረቆረ ደግሞ ይገደላል ወይንም አዋሽ አርባ ተወስዶ ይሰቃያል።
ከአማራ ውስጥ የወጡ የእድገታቸው መሰላል በአማራ ላይ ባላቸው ጥላቻና ጭካኔ ብቻ ነበር። አሁን ግን ይህቺ ጥጋብና ጥላቻ የምታስሾም ሳይሆን ጥይትን ያለ ውሀ የምታስውጥ ሆናለች። ወደ ፌዴራል ተሾሜ እሄዳለውሁ፣ ቪላ ቤት ይሰጠኛል፣ አጃቢና V8 ይኖረኛል፣ ቅቅቴን አራግፌ በቦስተን ስፓ ወገቤን እየታሸሁ፣ ሼራተን እየዋኘሁ እኖራለሁ የምትለው የደሀ የህልም እንጀራ አማራን በመግደል እንደማትገኝ ግልጽ ሆንዋል። ዛሬ ሁለት ሚሊዮን የሚገመት አማራ ታጥቋል። ልጁን የገደለበትን ወይንም ያስገደለበትን እስከ ዘር ማንዘሩ ለፍርድ የማቅረብ አቅም እንዳለው በስድስት ቀን ውስጥ አሳይቷል።
በሀገርም ይኑሩ በውጪም ይሽሱ ከአማራው ህዝብ ክንድ ማንም ማምለጥ እንደማይችል ግልጽ ሆንዋል። በዚህ ምክንያት ለአብይ የሚሞት ካድሬ ጠፍቷል።
ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም አነሰም በዛም በኮሚኒስት አይዲዎሎጂ ያበዱ ህይወታቸውን ሊሰጡት የተዝውጋጁ ካድሬዎች ነበሩት፣ ለገሰ ዜናዊም ካሰለፋቸው 60 ሺ ታጣቂዎች ውስጥህይወታቸውን ሊሰጡት የሚችሉ በሺዎች ነበሩ። ፋኖ ለአብይ አህመድ ሊሞትለት የሚችለው ሰው ማን ነው ብሎ ውይይት አድርጎ ነበር።
ለአብይ አህመድ ብርሀኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ደመቀ መኮንን፣ሽመልስ አብዲሳ፣ ብርሀኑ ነጋ፣ ሬዲዋን ሁሴን፣ ብለነ ስዮም፣ ታደሰ ጫፎ፣ ብናልፍድ አንዱአለም፣ ተስፋዬ ቤልጂጌ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አብረሀም በላይ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ በለጠ ሞላ ወዘተ እያልን ስም እየዘረዘረ ተወያይተን ነበር። እነዚህ ሁሉ ቶሎ ቶሎ ብለው ሀብት ዘርፈው አሜሪካና ዱባይ ቤት ገዝተው ለመሸሽ የተዘጋጁ ረሀብተኞች እንጂ ለአብይ አህመድ ሊሞቱ የተዘጋጁ ወንድሞቹ እንዳልሆኑ የፋኖ ግምገማ አሳይቶ ነበር።
እንደተተነበየውም ይሄው አሁን አብይ ብቻውን ነው የሚያነበንበው፣ በየቦታው እንዳበደ ውሻ ሲከንፍ የሚታየው።
አብይ ሁሉም እየክዳውና ስለሄደ ልቡ ሲሸበር ባለ ቀይ ኮፍያ ወታደሮቹን እራት እየጋበዘ በመሀላቸው እየዞረ ሲያቅፍ ሲደባብስ ላየ እናንተ ናችሁ የቀራችሁኝና አደራ እናንተም እንዳትጥሉኝ የሚል ይመስላል። በጥዋት ተነስቶ ሄሊኮፕተር አስነስቶ ጅማ ይገባና መደበቂያውን ሲቃኝ ሲያስገነባ ይውላል፤ ከዛ ተመልሶ ህወሀትን በሬዲዋን ሁሴን በኩል ለምን በጌምድርንና ራያን ወራችሁ አትወስዱም ይላል። ከዛ አልፎ የህወሀትም 20ሺ የሳምሪ ጦር በሱዳን ጦርነት ምክያት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቀለብ በማቆሙ ሊበተን ሲል እንዳይበተኑ እኔ ቀለባቸውን እልካለሁ በማለት የሳምሪን ኮማንዶ በዶላር እየቀለበ ነው። ይህ ሁሉ የፋኖን ግስጋሴ ማስቆም ስላልቻለ ነው። አሁን ደግሞ ኤርትራ ፋኖን እየደገፈ ነው ብሎ ስለጠረጠረ፤ የህወሀትንም የበቀል ስሜት እቀሰቅሳለሁ፣ አማራውና ፣ ብሄረኢትዮጵያዊውም ቀይ ባህር ሲባል ልቡ ይከፈላል ብሎ ስለቀይ ባህር ሲያወራ ይውላል። አሁን የተሰጠውን አጀንዳ አንጠልጥሎ የሚባዝነው ብኩን ምሁር እንጂ አብይ ስለ ቀይ ባህር ረስቶ ወደ ሌላ አጀንዳ ነጉዳል።
በመጨረሻ ይህ ሁሉ እንዳልሰራ ስለተረዳ በየጃን ማሮ እግር ላይ ወድቆ ኦነግ አዲስ አበባ ዙሪያ አምጥቶ ምሽግ ይዞ እንዲያልቅለት እየተማጸነ ነበር። ይሁንና የጃን ማሮም ፍላጎት በአብይ ምሽግ ገብቶ ከመሞት በላይ ስለሆነ ድርድሩ ለግዜው አልተሳካም። ይሁንና አብይ ጃን ማሮን አታሎ በሄሊኮፕተር ጭኖ አውጥቶታልና አንዴት እንደሚመለስ ማንም አያውቅም።
አሁን ጃን ማሮ አብይ የሚፈልጋትን ፊርማ ፈርሞ፣ በቴሌቭዥን መግለጫ ሰጥቶ፣ ተስማምቻለሁ እስካላለ ድረስ ከታንዛንያ አይወጣትም። ያለበለዚያም ጃን ማሮ ልወዝወዘው በእግሬ እያንጎራጎረ ደቡብ ሱዳን መግባት አለበት።
የአብይ ይህ መቅበዝበዝ በሜካናይዝድ ጦር እንኳን ድል ማምጣት ባለመቻሉ ነው። አብይ በየቀኑ የፋኖ ቁጥር እየጨመረ የሁለተኛው ዙር ጥቃት እየተቃረበ መሆኑን ስለገባው ደግሞ በድሮንስ ፋኖን አሸንፋለሁ ብሎ ንጹሀንን እየፈጀ ነው። የዚህ ደግሞ መላውን የአማራ ህዝብ እያስሸፍት በር ከፍቷል። ሞትና መታረድ የተፈረደበት አማራ ድሮን ፈርቶ ይገብርና ከዛ ተሰልፎ ይታረዳል የሚል ግምት ትልቅ የቂልነት ነው።