ክፍል ሁለት
ውቃቤ የሚባለው ጊዜ የጣለው ውሻ እኔ የሰማሁት “መንግስት በመንግስት ላይ ይነሳል ሲባል ነበር “ውሻ በውሻ ላይ ይነሳል ሲባል አልሰማሁም ነበር” ይላል። በእርግጥ በሀገራችን ውሻ በውሻ ላይ ለምን ተነሳ ብለን መጠይቅ አለብን?
የአዲስ አበባን በዚህ ፍጥነት መፍረስ ያየ የመንግስትን ብቻ ሳይሆን በመሀበረሰቡ ውስጥ ያለውን ቀውስ ይገባዋል። ብዙ ሰው ፒያሳ በመፍረሱ ደስተኛ አይደለም፣ ይሁንና ብዙ ሰው ደግሞ የሚጣልነትን አጥንት ለመቆርጠም በማፍረስ ተሳታፊ ነው።
ለራሱ መብት መቆም ያልቻለ መሀበረሰብ በሌላው ቤት ማፍረስ ተሳታፊ ለምን ይሆናል?
ለምሳሌ በከንቲባዋና ተከታዮቻቸው ይሄንን ከተማ ለማፍረስ እቅድ ካላቸው “በሉ ይቅናችሁ” ማለት ይችል ነበር። ከንቲባዋና ጭፍሮቻቸውና ዲጂኖዋቸውን ይዘው ወጥተው በአንድ ቀን አንድ ቤት አፍርሰው አይጨርሱም ነበር።ይህ ማለት ፒያሳን ለማፍረስ አስር አመት ይፈጅባቸው ነበር። ይሁንና እነ ሉሉ እንደታዘቡት ብዙ ሰው እራሱ ላይ እስከሚደርስ ክፏ ውሻ ለመሆን ይተጋል።
እግዚአብሔር “ብርሀን ይሁን አለ ብርሀንም ሆነ” በሚመስል ፍጥነት ከንቲባዋ ይፍረስ ሲሉ ከተማው ፈረሰ። ነገም በ24 ሰአት ውስጥ ሙሉ ሀገር ሲፈርስ እንደሚችል ያመላክታል። የዶዘሩ ሹፌር፣ የኤክስካቬተር ሹፌር መንገድ ለመስራት ሲቀጠር ቀስ እያለ እያረፈ ነው የሚሰራው። የአንድ ቀን ስራን ሶስት ቀን አራዝሞ ሊያስከፍል ነው የሚጥረው።
ግን ክፏ ጥሩ ውሻ ለመሆን ግን ቤቱል ለማፍረስ እናት ልጅን ይዛ እስከምትወጣ አይጠብቅም።
ባለ ዲጂኖው፣ ባለ ፋሱ፣ ባለ መዶሻው አሮጌ ቆርቆሮ፣ ብረት ለቃሚው ግንብ ቢባል ሳምንት የሚፈጅበት በአንድ ሰአት ደርምሶ አፍርሶ እራሱን ስራ አይ ለማድረግ ለምን ተጋ ካልን። እነ ጆሴ፣ እነ ሉሉ የን አቶ ጌታቸው አሰፋ ውሾች በነበሩበት ግዜ የሚያሳዩት ትጋት ነው።
ለጌጌቶቻችን ክፏ ጥሩ ውሻ ለመባል ይተጉ እንደነበረው የአዲስ አበባ አፍራሾችም እንዲሁ ሲተጉ ታዩ።
ዶዘና ኤክስካቬተር ነጂው ቆይ ልጄን ላውጣ የምትል እናትን እንኳን ጊዜ የማይሰጥ ጭካኔ ከየት መጣ። የኤክስካቬተሩን መቆፈሪያ በሰው ጣራ ላይ ለመጫንና ለመደምሰስ ምን አተጋው።
ይሄንን ስንረዳ አንባገነት ስርአት ደጋፊዎችና ምሰሶዎች እኛው እንደ ሆንን ይገባናል። ታድያ አንባገነን ስርአት በኛ ላይ ያልነገሰ በማን ላይ ይንገስ?
የአቶ ዳንኤል ክብረት ተሳታፊ ሳይሆኑ ታዛቢ በነበሩበት ዘመን “ውሻ በውሻ ላይ ይሄንን ያህል ከጨከነ፣ ሰው በሰው ላይ ቢጨክን ምን ይገርማል” ብሎ ነበር።
የፒያሳ ክፍለ ከተማ ሊቀመንበር
እስቲ ፒያሳን እንይ። የፒያሳን ቀበሌ ሊቀመንበር ነበረው። የመረጣቸውንና የተሾሙበትን የቀበሌ ህዝብ ነበር። ይህ ሙሉ ቤት ሲፈርስና ሲበተን የፒያሳ ወረዳ ሊቀመንበር፣ የጸጥታ ጉዳይ አላፊ፣ የመሀበራዊ ጉዳይ ሰብሳቢ የሚባሉ ብዙ ነበሩ።ከተማው ሲፈርስ እነሱ የቆሙበት ሰገነት መፍረሱ ያገናዝባሉ ይሁንና ክፏ ውሻ ሆነው ለመታየት የወጡበትን ዛፍ ክፕታች ቁረጡ ይላሉ።
እነ ሉሉም እንደነታዬ ደንደአ፣ እንደነ ንጉሱ ጥላሁን እስከሚጣሉ ድረስ እነ የነ ንካውን አለም አያውቁም ነበር።
አሁን የፒያሳ ክፍለ ከተማ ሊቀመንበር የሱን ቀበሌ ሙሉ በሙሉ አስፈርሶ ነዋሪዎቹን እንደ ጨው ዘር በአዲስ አበባ ዙሪያ በመበተኑ የሚመሩት ቀበሌም የለምን ይሁንና ክፏ ውሻ መሆን ከቀበሌ ሊቀመንበርነት አይበልጥም። ውሻ በውሻ ላይ እንዲህ ነው የሚጨክነው።
አቶ ዳንኤል ክብረት በኮለንበስ በተባለው ውሻ አንደበት ሆነው “Bad Dog is a good Dog” ያሉት ነው።
ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ከእንድ ከቢቢሲ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “እኔ እንኳን ሰው ዝንብ ገድዬ አላውቅም ብለው”፣ አለምን ጉድ አስብለው ነበር። አሁን መለስ ብዬ ሳጤነው እውነታቸው ነው።
በእርግጥ ኮለኔል መንግስቱ ተኩሰው ወይንም ቀጥቅጠው የገደሉት ሰው የለም። ግን ቀጥቅጠው ተኩሰው የሚገሉላቸው ብዙ ተናካሽ አብዮት ጠባቂዎች ነበሩዋቸው። አዎ ሉሉ በመጨረሻው ለጌታህ ክፏ ውሻ ሆነህ በመጨረሻ ለጅብ ትጣላለህ እንዳለው እነዚህ ካድሬዌች ናቸው በቀይ ሽብር የተፈረደባቸው።
ኮለኔል መንግስቱ ባለቀ ሰአት ሶሻሊዝምን ትተው ቅይጥ ኢኮኖሚ ብለው ያውጁና ካድሬዎቻቸውን በምክር ቤቱ ሰብስበው ሶሻሊዝም እንደ ቀረና አሁን የቅይጥ ኢኮኖሚ ዘመን እንደሆነ ያስረዳሉ። ያኔ የሶሻሊስት አርበኛ ተብለው ሲሞካሹ የነበሩት ካድሬዎች ይናደዳሉ። አንዱ ደፋር ካድሬ ይነሳና “ጓድ ሊቀመንበር እኛ ለሶሻሊዝም ብለን ከህዝብ ጋር ደም ተቃብተን እንዴት አሁን ሾሻሊዝምን እንትዋለን” ይላቸዋል።
በድፍረቱ የተናደዱት ኮለኔል መንግስቱ መልሳቸው “እኔ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ደም ተቃባልኝ አልኩህ?” ብለው ያፋጥጡታል። አዎ እንኳን ተቃባልኝ ቀርቶ ስሙንም መልኩንም አያውቁትም። የኮለኔሉ ቁርጥ ያለ መልስ እዛው እራስህን ቻል ነበር።
አሁንም አቶ አብይ ንጉሱ ጥላሁንን የታፈኑት ልጃገረዶች ተገኝተዋል በል ብዬሀለሁ፣ ጄኔራል አበባውን ህዝብ ላይ ተኩስ፣ ሴቶችን ድር ብዬሀለሁ እንደሚለው ጥርጥር የለም።
ካድሬው አዎ ብለውኛል ማለት አይችም ይሁንና እንደነ ሉሉ ካድሬዎቹ ከህዝብ ጋር ደም የተቃቡት የጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ጥሩ ውሻ ለመሆን ነበር። አቶ ዳንኤል ክብረት በሉሉ መንፈስ ሆነው ያመላከቱን “አንድ ውሻ ለጌቶው ጥሩ ውሻ እንዲባል መንከስ፣ ማስደንበርና ክፏ መሆን አለበት።”
ሉሉና ጆሲ ህይወት የተማርነው ለአንባገነኖች የምን ሰጠው ግልጋሎት ሱያልቅ ለጂብ መሰጠት ነው። በጨረሻ አቶ አብይም እንደ ኮለኔል መንግስቱ እኔ “ጳጳሱን ፈትሽልኝ አልኩህ፣ ዘርጥጥልኝ አልኩህ የሚል ነው።
አቶ ዳንኤል ክብረት በሚጣፍጥ አማርኛ በነ ሉሉ፣ በነ ንካው፣ በነ ጆሲ፣ በነ ኮሎንበስ፣ የካዛንቺስ ውሾች ነጻ አውጪ መሪ ሲባ በሚባሉ የውሾች አፍ በኢህአዴግ/ብልጽግና ውስጥ ስለነበሩ ለጌቶቻችቸው ጥሩ ውሻ የሆኑ ሰዎችን ታሪክ ከትበው ለታሪክ አስቀምጠዋል።
የሚገርመው ነገር ግን እናቶች “ወልደው ሳያበቁ፣ በሰው ልጅ አይስቁ የሚሉት” ዞሮ በሳቸው ትንቢቱ ተፈጸመ።
ጵጳስና ዲያቆን
ባለፈው ወደ ቤተመንግስት የተጠሩትን አቡነ ማትያስን ድንገት በቀሚሳቸው ስር ሽጉጥ ወይ ጎራዴ ይዘው ይሆናል ብለው ዲያቄን አቶ ዳንኤል ክብረት በደንብ ፈትሸው አሉ ተብሎ ተነግሯል። በእርግጥ ጳጳሱ ስውር አልሞ ተኳሽ (assassin) ይሆናሉ ብለው የሚጠረጠሩ አይመስለኝም። ይሁንና ያ እሳቸው የጻፏትም የክፏ ውሻ የትንቢት በራሳቸው ላይ እንዲፈጸም እንጂ።
የሞራል ጥያቄ
ፈረንጆቹ The moral of the story የሚሉት አላቸው። የውይይቱ ጭብጥ ማለት ነው። የአዲስ አበባ ውሾች ታሪክ በ2010 እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ሳሞራ፣ ደምመላሽ፣ አባይ ጸሀዬን፣ አብይ አህመድን፣ ደመቀ መኮንን ትክ ብሎ ማየት በሚያስፈራበት ዘመን ነበር። አሁንም እነ ደመላሽን፣ አብይን፣ ሽመልስን፣ አበባውን፣ ተመስገን ጥሩነህን፣ አረጋ ከበደን፣ ደሳለን ጣስው፣ ብርሀኑ ነጋን ትክ ብሎ ማየት የሚያስፈራ ነው። ይሁንና እነዚህም እንደነ ሉሉ፣ ጆሲ፣ ንጉሱ ጥላሁን፣ ታዬ ደንደአ፣ ደመቀ መኮንን ወጥተው ለጂብ ይሰጣሉ። ስለዚህ የዚህ ጽሁፍ አላማ እነ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ዳንኤል ክብረት፣ አረጋ ከበደ፣ ደሳለኝ ጣስው፣ በለጠ ሞላ ቆም ብለው እኔ ለጌቶቼ ጥሩ ውሻ ለመባል፣ ለህዝቤ መንከስ አለብኝ ብለው እንዲጠይቁ ነው?
እነ ብርሀኑ ነጋን፣ አበባው ታደሰ፣ እነ አረጋ ከበደ ብቻ ሳይሆን ከታች በየ ቢሮክራሲው የተሰገሰገ በህዝብ ላይ ክፏ ውሻ በመሆን ለመወደድ ለመሾም ለመዝረፍ እንዳይተጉ ነው።
እስቲ ነገ ጥዋት ወደ ወደ ቀበሌ ቢራችን፣ ገቢዎች ባለ ስልጣን፣ ክፍለ ከተማ ቢሮዋችን ስንገባ እኔ ለህዝብ ክፏ ውሻ እሆን ብሎ ሁሉም እራሱን እንዲጠይቅ ነው።
ክላሽና ዱላ ተሰጥቶን ከፌዴራል ፓሊስ ተብለን ስንሰማራ፣ ከተከበረ የህግ ትምህርት ቤት ተመርቀን የተከበረ የአቃቤ ህግ ተብለን ፋይል ሲሰጠን፣ ከዩኒቨርስቲ ተመርቀን የትላልቆቹ ቴሌቭዥኖችና ጋዜጦች ዘጋቢ አንባቢ ስንሆን፣ እኔ የአቶ ዳንኤል በምናብ የሳሉት ሉሉ በሚባል ውሻ እሆን ብሎ እንዲጠይቅ ነው።
ዳንኤል ክብረት በሉሉ አድሮ እንዳስተማረን እኔ “አሪፍ ውሻ ለመባል ለህዝቤ ክፏ ውሻ እየሆንኩ ይሆን” ብለን እራሳችንን እንጠይቅ አለብን።
እነ ሉሉ በነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ በነ ተጋዳላይ አባይ ጸሀዬ፣ በነ ተመስገን ጥሩነህ፣ በነ ለማ መገርሳ፣ በነ አባ ዱላ፣ በነ አቦይ ስብሀት ሰፈር ሲኖሩ የተፈሩ የተከበሩ ነበሩ። ያስፈራሩ፣ ይናከሱ፣ ያስደነብሩ ነበር። ያኔ ጨካኝ ነበር። ከተባረሩ ቦሀላ ደግሞ “ውሻ በውሻ ላይ ይሄንን ያህል ከጨከነ፣ ሰው በውሻ ላይ ቢጨክን አይገርምም” አሉ። በግዜ ለህዝብ መቆም ነው እንጂ ጅብ ካለፈ ውሻ ቢጮህ ምን ይጠቅማል።
አሁን መሀበረሰባችን በሁለት ተከፍሏል። አንዱ ለጌታው ተናካሽ ውሻ የሆነ የብአዴን፣ የኦፒዲኦ፣ የብልጽግና ተናካሽ ውሻ፣ አድማ በታኝ ቃል አቀባይ፣ አሳሪ ፈቺ፣ ገራፊ የሆኑ። ሌላው ደግሞ ተሳዳጅ፣ ቤቱ በላዩ ላይ የሚነድ፣ ልጁ የሚታፈን፣ ሰብሉ በማሳው የሚነድበት፣ የሚራብነ የሚጠማ ነው።
ምርጫችን ሁለት ነው። ተናካሽ ውሻ ሆኖ ማገልገልና እንደነ ንጉሱ ጥላሁን ታዬ ደንደአ ለጂቦች መሰጠት ያለበለዚያም ከህዝብ ጋር ቆሞ ከተማ አፍራሽ፣ ሰላይ፣ ገራፊ፣ ጉቦ አቀባባይ አለመሆን ነው።
ከሀምሳ የማይበልጡ የኦፒዲኦ መሪዎች ብርሀን ይሁን ሲሉ የምናበራ፣ ከተማ ይቅደም ሲሉ የምናወድም ከሆነ ከፍ ግድም ከጸጸትም አንድንም።
እነ ሉሉ በመጨረሻው የት ነበርኩ አሉ። ገበሬ በበሬው ያርስበትና ሲያረጅበት እርስ ይበላዋል። ክፋትን ዞሮ ዞሮ ተመልሶ ይመጣል። ዳንኤል በውሾቹ አፍ ከሚኒሊክ በፊት የነበሩት የነበሩትን ክፏ ገዢ ያስታውሳል። በመጨረሻው እኚህ ጨካኝ ገዢ የግፍ ቀሚስ አል ሰው አቃጥሏቸው። ይህንን ይህች ገጣሚ ይህንን አለች።
“አንተ ክፏ ነበርክ ክፏ ሰደደብህ
እንደ ገና ዳቦ እሳት ሰደደብህ” አለች።
የብልጽግና ጨካኞች መጨረሻው እንዲህ እንዳይሆን።