የዐመሓራ አሁናዊ ንቅናቄ ከቀደሙት በ50 ዓመታት ከታዩት ንቅናቄዎች በምን ይለያል?

ከብዙ ንቅናቄዎች መካከል የዐመሓራን ጨምሮ 6ቱን በንቅናቄዎቼ በስድሰት መሥፍረቶች፡ (1)መግፍኤ፥ (2) የንቅናቄ መሪዎች (3) ፍልስፍና / ርእዮት ( ግብ/ዓለማ (4) የትግል አካሄድ/ ስነ ምግባር/ ስልት (5) ተግሉ ከተነሳበትና ካስቀመጠው ግብ አንፃር ያመጣው የውጤት ዘለቄታዊነት እና (6) ንቅናቄው በተግባር ለአገር ያመጣው ጥቅም ወይንም እዳ መመዘን በእጃችን ላይ ያለውን የዐመሓራ ንቅናቄ ዘለቄታዊነት ያለው አገራዊ ፋይዳ እንዲኖረው በንፅፅር መመልከቱ ይጠቅማል/።

በእነዚህ ሚዛን ሲሰፈር የዐመሓራ ሕዝብ አሁናዊ ንቅናቄ ተፈጥሮአዊ፥ ሰብአዊ፥ ፍትሐዊ፥ አገራዊና ታሪካዊ መሠረት ያለው የህልወና ሲሆን ሌሎቹ መነሻቸው የጥቂት ልሂቃን የውጭ-ገብ የፖለቲካ ርእዮት ሰለባ መሆንነ ኣለነባርነት ጠላት መሆን፥ የትቂት ልሂቃን የሥልጣን ፍላጎት ለማሳካት

  1. የተማሪ ንቅናቄ እና ደርግ፡
     መግፍዔ፡_ የዘውድ ሥርዓት ጥቂት ፊውዳሎችን በብዙኃን ላይ ጨቋን አድርጓቸዋል
     የትግሉ መሪዎች፦ የአገራቸውን እሴት የናቁ ጥቂት ታመሪዎች /ልሂቃንና ወታደሮች ማርክሲስት/ ሌኒኒስት
     ግቡ/ዓላማ፦ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም፤ የዘውድ መንግሥትን እኩልነት በሚያስገኝ ሥርዓት መቀየር
     ስልት።አካሄድ፦ በሰላማዊ ጀምሮ ወደ ማርክሳዊ ፕሮፓጋንዳ፥ ቀጥሎ በአመፅ፥ ሤራ፥ ቀይና ነጭ ሽብር
     ተግባራዊ ውጤት፦ ወቅታዊ ድል፤ ነገር ግን መግፈዔውንና የታለመውን ግብ የተቃረነ መጨረሻ
     የተረጋጋ መንግሥትና ማኅበረሰብ መጥፋት፥ የሕዝብ የልሂቃን ጢሰኛና ባርያ መሆን
  2. የደርግ ተቃዋሚ (አገር ዐቀፍ ድርጅቶች) አብዮቱ በወታደራዊ ጁንታ ተነጥቋልና በሕዝባዊ መንግሥት ይተካ፤ የማእረክሳዊ ርእዮት ትንታኔ ልዩነት የአገራቸውን እሴት የናቁ ጥቂት ታመሪዎች ማርክሲስት/ ሌኒኒስት ወታደራዊ መንግሥትን በሕዝባዊ መቀየር።
    “ትክክለኛ” ሶሻሊዝም መተግበር ማርክሳዊ ፕሮፓጋንዳ፥ የከተማና የገጠር ውጊያ፥ በአመፅ፥ ሤራ፥ ቀይና ነጭ ሽብር ዘውድን ያሰወገደ አብዮት በሌላ ወታደራዊ አምባገነን መቀየር። የሕዝብ ጭቆና መቀጠል ሰፊው ሕዝብ የመንግሥት ጢሰኛ፥ ባሪያና ተሳዳጅ መሆን
  3. የደርግ ተቃዋሚ (የብሔረሰብ ነፃ አውጭዎች)- ሕወሐት የብሔር ጭቆና አለ ከሚል ትንተና ተነስቶ መፍትሔውን ብሔርን ከሌላው የመለየት በማለት ከትግራይ የጣሊያን ባንዳ ቤተሰቦች የተገኙ ጥቂት ልሂቃን፥ በአንዚህ ልሂቃን አእምሮአቸውን የታጠቡ ጥቂቶች ተባባሪዎች፥ በሻቢአና በውጭ ጠላቶች የሚደገፉ መሪዎች ግልጽ ያልሆነ፥ በቁማርና በሤራ የሚመራ፤ ብዙኃንን ለማታለል ብቻ ማርክሲስት ነኝ የሚል ትግራይን ወደ አፋር፥ ወደ አማሃራና ኤርትራ በማስፋት ከዐመሓራ የጸዳ (በወልቃይት ናሙናውን በዘር ፍጅት አሳይቷል) ከኢትኦጵያ ገንጥሎ የትግራይ ሪፐብሊክ መመሥረት የሐሰት ትርክትና ፕሮፓጋንዳ በመጠቀም፥ ሕዝብን በሌላው ላይ ጥላቻ አንዲያሳድር ማድረግ፤ ሤራ፥ ዓለም አቀፍ የአገር ጠላቶች ጋር መተባበር፤ አፈናና ተቃዋሚ ማጥፋት።

በዝርፊያ የሚዘረጉ መሠረተ ልማቶችና የጥቂቶች ብልጽግና፤ በዘረፋና በበድል የተሰበሰበ ሀብት ለማዝለቅ መልሶ በጦርነት ሕዝብን ማስጨረስ ነፃ ይወጣሉ የተባለው የትግራይ ሕዝብ የነፃ አውጨው መሪ ቡድን ባርያ፥ ወጣቱ ወደ ጦር መሣሪያነት የተለወጡበት፥ የልሂቃን ዝርፊያና መበልጸግ፥ የህዝብ ሰቆቃ፥፥ኢትዮጵያን የባህር በር ማሳጣት፥ በአማራና ኦርቶዶክስ ላይ እልቂት መፍጠር

  1. የደርግ ተቃዋሚ (የብሔረሰብ ነፃ አውጭዎች)- ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ቅኝ በመገዛቱ ነፃ መውጣት አለበት የሚል የሐሰት ትርክት ላይ የተመሠረተ መነሻ ጥቂት በውጭ አካላት በእምነት ቤቶች፥ በውጭ አገር የሰለጠኑ ተማሪዎች/ልሂቃን ግልጽ ያልሆነ፥ በቁማርና በሤራ የሚመራ፤ ብዙኃንን ለማታለል ብቻ ማርክሲስት ነኝ የሚል ታላቅ ኦሮሚያ የምትባል፥ ከዐመሓራና ከኦርቶዶክስ የፀዳች አገር ከኢትዮጵያ ቆርሶ መፍጠር (በመላው ኦሮሚያ ባደረገው ፍጅት አሳይቷል) የሐሰት ትርክትና ፕሮፓጋንዳ በመጠቀም ሕዝብን በሌላው ላይ ጥላቻ አንዲያሳድር ማድረግ፤ ሤራ፥ ዓለም አቀፍ የአገር ጠላቶች ጋር መተባበር፤ አፈናና ተቃዋሚ ማጥፋት። የዐመሓራ፥ የኦርቶዶክስ አማኞችን እና ሌሎች ብሔረሰቦችን ማሰደድ፥ ፍጅት፥ ዘረፋ፥ መዋቅራዊ ሤራ፥ ሐሰትን አምርቶ ማሰራጨት፥ ግጨትና ጦርነት መፈናቀል፥ ጦርነት፥ ስደት፥ ቀጣይነት ያለው ደም መፋሰስ
  2. የደርግ ተቃዋሚ (የብሔረሰብ ነፃ አውጭዎች)- ሻዕቢአ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተይዛለች፥ ነፃነቷን መጎናጸፍ አለባት የሚል ክእራባዊያንና አረቦች ፍላጎት ጋር የሚሄድ ጠማማ ትርክት ላይ በመመሥረት በመሻው የመካከለኛውና የግብፅ ድጋፍ ያላቸው የጠቂት ሙስሊም ንቅናቄ፥ ቀጥሎ ማርክሳዊ ዝንባሌ ያላቸውና በምእራባዊያንና በአረቦች የሚደገፉ ጥቂት ልሂቃን ግልጽ ያልሆነ፥ በቁማርና በሤራ የሚመራ፤ ብዙኃንን ለማታለል ነፃነት የሚባል ብሩህ ተስፋን መናኘት፥ ኢትዮጵያን በተለይ ዐመሓራን ማስጠላት፥ ኦነግና ሕወሐትን፥ ሌሎች ግጭቶችን መደገፍ ኤርትራ የምትባል ራሷን የቻለች ነፃ አገር መፍጠር ፕሮፓጋንዳ፥ የሐሰት ትርክት፥ ጦርነት፥ አገርን እርስ በርስ የሚኣጋጩ ንቅናቄዎችን መደገፍና አዳዲስ እንዲፈጠሩ ማድረግ የኤርትራ መገንጥል (ነፃነት)፥ ስደት፥ በአፈና ሥር መኖር፥ ከኢትኦጵያ መባረር፥ መልሶ ከኢትዮጵያ ጋር መዋጋትና እልቂት፥
    ኢትዮጵያን የባህር በር ማሳጣትና ማደኸየት
  3. የዐመሓራ ሕዝባዊ ንቅናቄ (ፋኖ) ነፃ አውጭዎችና የብሔር ፖለቲከኞች በሕገ መንግሠት፥ በመዋቅርና ፍልስፍና በመመራት የዐመሓራን ሕዝብ ህልውና ለማጥፋት መንቀሳቀስ፥ አገር አልባ ማድረግና የተራዘመ የ35 ዓመታት ሁለገብ ዘር የማጥፋት ሂደትን የማስቆም ተፈጥሮአዊ ንቅናቄ ነው፤ መሠረቱም በነባር የማኝበረሰቡ ባህል ላይ የተመሠረተ የወጣቶችና የገበሬዎች፥ የልሂቃን ውህደት ያለው ሕዝባዊ ንቅናቄ ሰብአዊነት፥ ፍትሕ፥ አገራዊነት፥ እውነትን መከላከል፤

ግቡ፦ የሕዝብን ህልውና ማረጋገጥ፥ አገርን ከስሑት ሤረኞች ጥፋት መታደግ፥ የህዝብን እኩልነት፥ መተማመንና አንድነት ማስመለስ በእውነት ሐሰትን መርታት፥ በጦር መሣሪያ ከጠላት መከላከል፥ ሰብአዊነትንና መልካምነትን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በማክበር አርአያ መሆን

ተጠባቂ ውጤት፦

✔️በእውነት፥ በፍትሕ፥ በሰብአዊነት፥ በሕዝቦች አንድነት፥ በእኩል የአገር ባለቤት በመሆን፥ በሕዝብ አመራር የሚካሄድ ተጋድሎ መጨረሻ የሕዝብና የሁሉም ስለሚሆን ዘለቄታዊ መሆኑ ተፈጥሮአዊ ነው (ከውጭ ጠላት መከላከል፥ ሕዝቡ የተሠራበትን ሤራ ማስገንዘብ ከተቻል እኩልነት ላይ የተመሠረተ የአገር ባለቤትነት ዋስትና ማረጋገጥ፤

✔️ተለይቶ ህልውናው የሚጠፋ ክፍለ-ሕዝብ እንዲኖር የሚያደርግ የፖለቲካ ርእዮት መወገድና የሕዝብ መተማመን፥ መዋሀድ፥ የአገርና የህዝብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ

  1. ኢትዮጵያን ዒላማ ያደረጉ የውጭ ወረራዎች፦ የግብጽ፥ የቱርክ፥ የአውሮፓ፥ ወዘተ ተሸንፎአል። በድህረ ሽንፈት ትንተና ኢትዮጵያን ለመስበር “ዐመሓራን፥ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን፥ የንጉሥ ሥርዓትና ረዥም የአገሪቱን ታሪክና ትርክት፥ የሕዝቡን ከእምነትና ባህል ተሻግሮ መጋመድ” መቆራረጥ የሚል ነው። ይህን ብያኔ የዘውድ ሥርዓትን፥ ኦርቶዶክስንና ዐመሓራን ቅድሚያ ሰጥቶ ማጥፋት የሚል ነው።
  1. ሕወሐትና ኦነግ የዚህ ብያኔ የኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ጠላቶችን ቀመር ፕሮጄክት አስፈጻሚዎች ሆነው ለ50 ዓመታት ያለመታከት ሠርተውበታል፤ የድካማቸውንም ፍሬ መጀመሪያ ዘረኝነትን ሕገ ምንግሥታዊ የሚያደርግ የኦነግና የሕወሐትን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ማስገባት፥ ሁሌተኛው የአአውምሮ ልጅ የሆነውን ለብልጽግና መንግሥት ፕሮጄክቱን እንዲያጠናቅቅ ለመንግሥታዊ ሥልጣን በማብቃት ከጎኑ ቆመው ዐመሐራንና ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው።
  2. በኢትዮጵያ ምስቅልቅል የፖለቲካና ማኅበራዊ ውጣውረድ ውስጥ ዋና መንስዔው ከላይ የተገለጠውን ፕሮጄክሕት ለማስፈጸም አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ ውጭ-ገብ ስሑት ርእዮት ምሁር ያሰኛቸው የጎሣ ልሂቃንን የአገሪቷን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ሕይወት አንዲቆጣጠሩ ማስቻል።
  3. እነዚህ የፖለቲካውን ሁለንተናዊ ዘርፍ የተቆጣጠሩ ልሂቃን ራሳቸውን ቸግር ፈች፥ ነፃነት ሰጭ፥ መፍትሔ አማጭ አድርገው በመሰየም በጭፍን የሚከተላቸው የመንጋ ኃይል ለማፍራት የሚሰጡት ተስፋ፥ የሚያግቱት የሐሰት ትርክት፥ በትርክቶቹ ስካር ምከኒያት የሚፈጠረው የማንነት አረዳድ ኪሣራና የስነ ልቦና ቀውስ በመታገዝ “ሕዝባችን” በሚሉት የቋንቋ ዘውግ ላይ ነግሦ ለመኖር ባላቸው ከፍተኛ የሥልጣን ፍተወትና የቁስ ሰቀቀን፥ እንዲሁም በተሳሳተ መረጃና አስተሳሰብ የመጣ የስነ ልቦና ውድቀትን ለማከም በሚደረግ የተሳሳተ የትግል መሥመር አገርንና “ሌሎች” ብለው በሚፈርጇቸው ማሥበረሰቦች ላይ የህልውና አደጋ ምንስዔና ፈጻሚ ሆነው ተገኝተዋል።
  4. አሁን እጃችን ላይ ያለው አንገብጋቢ የዘር ማጥፋት ፕሮጄክት በዐመሓራ ማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ማንነቱ ላይ ታውጆ የሚካሄደው ዘር የማጥፋት ዘመቻም የዚህ የስሑት ርእዮትና ሐሰተኛ ትርክት ውጤት በመሆኑ ዐመሓራን ከህልውና አደጋ መታደግ አድን ክፍለ ሕዝብ እንደ ማኅበረሰብ በአካል ከምድረ ገጽ እንዳይጠፋ መከላከል ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ፥ ለሌሎች ብሐየረሰቦች ህልውና ዋስትና የሆነውን ሰብአዊነትን፥ ፍትሕን፥ እውነተሓነትን፥ የሰው ልጅ እኩልነት እሴትን እና አገርን የሚያጠፋ አደገኛ የሕወሓትና የኦነግ/ኦሮሙማ መርዝን ከትውልድ ውስጥ የማጽዳት ታላቅ ሰብአዊ ኃላፊነት ነው።
  5. የበዐመሓራ የሰብአዊነት፥ የፍትሓዊነት፥ የእኩልነት፥ የባለርስትነት/አገርነት፥ የአብሮነት እሴቶችን ከጥፋት መከከላከል ከኢትዮጵያ ህልውና አልፎ ለአፍሪካዊ አንድነት አደጋ የሆነውን የጎጠኞና የዘረኞችን የማሥበራዊና ፖለቲካዊ ካንሠር እንዳይሠራጭ መግታት ነው።
  6. የዛሬው የዐመሓራ ተጋድሎ ህልውናውን ለማጥፋት ከተሰለፉት አካላትና አስተሳሰቦቻቸው ጋር ነው። ትግሉም ከሕወሐትና የኦነግ ዘረኞች የተለየ የሚያደርገው እንደ ጣላቶቹ በስሁት ርእዮት፥ በሐሰተኛ ትርክት የሚመራ ሳይሆን በተፈጥሮ ሕግ ላይ የቆመ ሰብአዊ፥ ፍትሐዊ፥ እና አገራዊነት ላይ የቆመ ይግድ መጠናቀቅ ያለበት ጀምረው የማይተዉት የመኖርና ያለመኖር አስገዳጅ ሁኔታ ነው።
  7. የዐመሓራ ላለመጥፋት ተገዶ የተነሳ የተጨነቀ ሕዝብ ተፈጥሮአዊ ንቅናቄ እነጂ እንደ ሕወሐትና ኦነግ በአዳራሽ ውስጥ ጥቂት የየጎሣው ተወካይ ሆነው ራሳቸውን የወከሉ የአእምሮ በሽተነኛ ልሂቃን በአደራሽ ውስጥ በሚፈጥሩት የሐሰት ትርክት፥ ሌላውን አጥፍቶ የሚደረስበት በቅዠታዊ ግቦቻቸው አንፃር በተዘጋጀ የፖለቲካ ማኒፌስቶ ላይ የተመሠረተ አይደለም።
  8. በዘረኛ ልሂቃን አእምሮ ታስቦ የሚፈጠረው የጎሣ የንዑስ ማንነት መነሻው አንዱን ወገን ከሌላው የተለየ ነው፥ እናም የተለየ ጥቅም፥ ሥልጣን፥ መሬት፥ ክብር፥ ሃይማኖት፥ ባህል እና ትልቅነት ይገባዋል በሚል የተዛባ ኢሰብአዊ፥ ኢፍትሐዊ እና ኢዜግነታዊ ዕሳቤ ላይ ይመሠረታል፤ በዚህ ዕሳቤ
  9. እኛ ልዩ ነን፥ ከሌሎች እንበልጣለን እናም የሚገባንን ከፍታ እናረጋግጥ፤ ወይንም እኛ ልዩና ከፍ ያልን ነበርን፥ ነገር ግን በታሪክ ሂደት እነ እገሌ የሚባሉ ሌሎች አሳንሰውን በመቆየታቸው ወደ ክብራችን እንመለስ በሚል ብያኔ የየቡድኑ ጎሣ ልሂቃን አእምሮ የሚፀነስና የፖለቲካ ተቋም ከመሆን እስከ መንግሥትነት ሆኖ የሚያድግ ተቋማዊ ዘረኝነት ነው። ይህ ዘረኝነት ሰውን ከማኅበራዊ፥ ከሃይማኖታዊ፥ ከተፈጥሮአዊ ማንነቱ ለይቶ፥ ዜጋዊ አንደነቱን ነጥቆ ወደ ፖለቲካዊ አናሳ የንዑስ ማንነት ዘረኝነት ያሸጋግራል።
  10. በዚትዮጵያ ታሪክ አንድን ሕዝብ ከሰብአዊነት፥ ከማሕበራዊና ፍጥረታዊ ማንነቱ ልይቶ ወደ አናሳ የንዑስ ማንነት ዘረኝነት ያሸጋገሩ እና የተቋማዊ ዘረኝነትን ሕገ መንግሥታዊና አገራዊ ዕሳቤ በማድረግ ሰውን ወደ ፖለቲካ ፍጡራንነት የቀየሩት ሕወሐት እና ኦነግ ሲሆኑ በእነርሱ እርሻ ላይ የበቀለው የብልጽግና መንግሥት አሁን በዚህ ሰውን ፖለቲካዊ ዘር ባደረገ አውድ ውስጥ እልቂእተ እየፈጸመ የሚገኝ ነው።
  11. ራሳቸው የስሐዑት ዕሳቤያቸው ሰለባ የሆኖ የየጎሣው ልሂቃን ተውልዱን በፕሮፓጋንዳ አደንዝዘው ፖለቲካዊ የሰው ዘር በአገሪቷ ውስጥ መፍጠር ለመቻላቸው ምስክሩ ወገንን በወገን ላይ እያዘመቱ ሚሊዮኖችን ማፋጀት፥ የአገር ሠራዊትን አዝዘው ሕዝብ ማስፈጀት መቻላቸው ሲሆን፥ ከሁሉ በላይ ሃይማኖትንና ባህልን ሳይቀር ለፈጠሩት ፖለቲካው የሰው ዘር በመደልደል መጅልስና ሲኖዶስ መፍጠር መቻላቸው ያሳያል።
  12. ፖለቲካዊ የሰው ዘር በመፍጠር ተፈጥሮአዊ ሰብእናን ያዋረዱ እነዚህ የሕወሐትና የኦነግ ልሂቃን ከ50 ዓመታት በኃላ ዐስተሳሰባቸው ከጥቂት ልሂቃን የአዳራሽ መግባቢኣነት የትውልድ እምነት መስሎ ሚሊዮኖች ወደ ጦር ሜዳ ወርደው የሚጋደሉበት፥ ታጣቂዎች ሕፃናትንና አረጋዊያንን በአዲሱ ዘራቸው አንፃር እየፈረጁ በጅምላ የሚያርዱበት፥ የክልል ታጣቂ ሌላ የተባለውን በመንግሠት መዋቅር እየተመራ የሚያጸዳበት ደረጃ ላይ መድረሱን በሕወሐትና በኦነግ/ኦሮሙማ።ብልጽግና የሚመራው መከላከያና የኦሮሚኣ ልዩ ሓይል፥ የትግራይ መከላከያ ኃይል የተባለው ሠራዊት የፈጸማቸው አሰቃቂና ኢሰብአዊ ድርጊቶች መስክረውልናል።

የዐመሓራ የህልውና ንቅናቄ አሁን ባለበት ደረጃ ከቀጠለ ከፖለቲካዊ ዘር ነፃ የሆነ ብቸኛው ንቅናቄ ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል!
በዚህ ዳራ ውስጥ ዐመሓራ የሕወሐትና የኦነግ/ኦሮሙማ/ብልጽግና የማጥፋት ዒላማ በመደረጉ በተፈጥሮ ሕግ ተገፍቶ ላለመጥፋት የተወለደ ተጋድሎ በመሆመኑ ለራሱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ስሕተት ውስጥ የገቡትን ለሚከተሉ የዋሐን ሁሉ መዳኛ ነው።

ነባር-ጠል አዲስ ናፋቂነት መለያቸው የሆኑ የየጎሣው የዘር ፖለቲካ ልሂቃን በገባቸው ልክ እና የግል ጠባብ ፍተወታቸው በሚመራቸው ደም ነፍሳዊ ፖለቲካ የጎሣ ንዑስ ማንነት ፖለቲካ ቡድን በማደራጀትና ተከታዮቻቸውን እያታለሉ በመጠቀሚያነት ራሳቸውን ማንገሥ መነሻቸውና መድረሻቸው ነው።

የዚህ ስልት ወና ፊት አውራሪ ሕወሐት ሲሆን ኦነግ ተከታዩ ነው፤ ኦነግ በእሳኡ የወለደው ኢፒዲኦና ሁሉም ተዳቅለው ያስገኙት ብልጽግን የተባለ የዛሬው የአብይህ አህመድ የኦነግ/ኦሮሙማ መንግሥት ነው። እነዚህ ነባር-ጠል አዲስ ናፋቂ የልሂቃን የንዑስ ማንነት የዘረⶈች ፖለቲካዊ አደረጃጀት ተከታዮችን ለማፍራትና በዘለቄታዊነት ለማስከት የግድ የልሂቃኑ የአእምሮ ውጤት የሆኑ፦

(፩)ልሂቃን የሚፈጥሩት የብሔረሰብ አዳዲስ ንዑሳን ማንነቶች ከነባርነታቸው እና ሌሎች ከሚባሉት ብሔሮች የሚለዩና የሚቃረኑ፥ የተሻሉ የማንነት ጥራት እንዳላቸው ማሳመን(ለምሳሌ ሕወሐትና የፈጠረው ትግራዋይንት እና የኦነግ የፈጠረው ኦሮሞነት ወይንም ኦሮሙማ ከሌሎች ጠላት ከሚላቸው አንፃር ራሳቸውን ቅዱስ፥ ሌላውን ርኩስ አድርጎ መሳል)፤

(፪) አዲስ በፖለቲካ ልሂቃን ፍላጎት የተፈጠረው የብሔረ ሰብ ንዑስ ማንነት መገለጫዎች እየተጠናከሩ እንዲሄዱና በዘለቄታዊነት ለልሂቃኑ ዕሳቤ፥ ሥልጣን፥ ግብና ርእይ የሚሞቱና የሚገድሉ ትውልዶችን ለመፍጠር የተቻለውን ሁሉ ታሪክን በፈጠራ ሐሰት በመበከል፥ ውጭ-ገብ እና ከነባርነት ጋር የሚጋጩ ስሑት ርእዮቶችን በማስተዋወቅ ትውልዱን ከጋራ መሠረቱ ነቅሎ መለያየት፤

፫) ከአውዳቸው ውጭ በማኅበረሰቡ ላይ ተጣመው በሚጫኑ የጥቂት ልሂቃን ውጭ-ገብና ስሑታን አስተሳሰቦች (የፖለቲካ ርእዮቶች) ከታዮችን እያማለሉ ሌሎችን ጠላትና ወዳጅ ብሎ በቋሚንተ ማስፈረጅና የውድድር፥ የጦርነት ፖለቲካ በመምራት ትብብርና አንድነትን ማነወር።

የእነዚህ የንዑስ ማንነት ፖለቲካዊ ተቋማት ጠላትና የጥፋት ዒላማ የተደረገው የአማራ ሕዝብና ኦርቶዶክስ የሆነ ማንኛውም ዜጋና ክፍል-ሕዝብ የማያቋርጥ ሁለገብ ጥቃት ተከፍቶበት ታሪኩ፥ ማንነቱ፥ የምጣኔ ሀብትና የመኖር መሠረት የሆነው መሬቱ፥ ቅርሱ፥ ቋንቋው፥ ፊደሉ፥ ማኅበራዊ መዋቅራት፥ የእምነት ቀኖናውና ዶግማው ሁሉ እንዲዳከሙና እንዲጠፉ ከፖለቲካዊ እስከ ቀጥተኛ አካላዊ ጥቃት ሥር ወደቀ። ይህ ተጨባጭ ሁኔታ የተራዘመ ጥቃት ያስመረረው፥ ፍትሕ የተነፈገውና በ35 ዓመታት በሚሊዮኖች ቁጥሩ እንዲቀንስ፥ እንዲደኸይ፥ እንዲሰደድ፥ እንዲዋረድ እና በመጨረሻም በብልጽግና መንግሥት የታቀደ በፍጥነት ክፍለ ሕዝቡን የማጽዳት ፍጥነት ተጠቂዎችን ለህልውናቸው በአንድነት አንዲቆሙ አስገደዳቸው።
ጥፋት የታወጀበትን ክፍለ ሕዝብ ንቅናቄ የመጀመሪያ ዒላማው ራሱን ከመጥፋት በመከላከል ዋስትናውን መረጋገጥ ነው።

የዐመሓራ ህልውና ዋስትና ትግሉ ምን ሲያሳካ ነው?

ዋስትናው የሚረጋገጠው አደጋ የጋረጡትን ተዋንያን በቀጥታ ማሸነፍ ወይንም የፖለቲካ ርእዮታቸውንና የዘረኝንተ አደረጃጀታቸውን ሙሉ በሙሉ በማስለወጥ ነው። ይህ ዋስትና የሚረጋገጠው በውይይትና በግግር እንዳይሆን መንገዱን ዘርገቶ የያዘው የዘረኞቹ ድርጅቶች ሐሰተኝነት፥ ቁማርተኝነት፥ ጦረኝነትና ዘር ለማጥፋት ያለቸውን ትጋት በ35 ዓመታት ሁለግ ጥቃታቸው መረጋገጡ መፍትሔው በኃይል አስገድዶ ወደ ጠረጴዛ ውይይት በማምጣት የሰው ልጆችን እኩልነት፥ የዜጎችን ሙሉ መብት የሚቀበል ሥርዓት ማቆም መቻል ነው ብቻ ነው።

የዐመሓራ ንቅናቄ ሕልውናውን በዘለቄታዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ በመላው ኢትዮጵያ ሳይሰፍን ወደ ወደ ኋላ መመለስ አይችልም።

ከዚህ መንገድ መቆም ዐመሓራን ብቻ ሳይሆን የሕወሐትና የኦነግ/ኦሮሙማ ሌሎችን ሕዝቦች ባሪያ የማድረግ፥ ሌላውን የማጥፋትና አዳዲስ አገር የመፍጠር ህልማቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የበለጠ ደም መፋሰስ እንዲስፋፋ በር ይከፍታል።

የዐመሓራ የህልውና ንቅናቄ ተጨማሪ ኃላፊነት በትከሻው ላይ ውድቋል። የተጀመረው የፋኖ ሰብአዊ። ግብረ ገባዊና የጀግንነት ስኬት ፋኖን ለመደገፍ መዘጋጀታቸው ምልክት ያሳያዩ የሌሎች ብሔረሰቦችም ትግሉ በስኬት ካልተጠናቀቀ የዘር አጥፊው ዘረኛ ፖለቲካ ዒላማነታቸውን ያጠናክረዋል። ስለዚህ ትግሉ ወደ ኋላ መመለስ አይችልም!
የዐመሓራ ንቅናቄ ዘረኛ ውይስ ሰውኛ?

አንድ ንቅናቄ ዘረኛ የሚባለው እንደ ናዚ ጀርመን እኔ ልዩ ዘር ነኝ፥ ሌሎች ያንሳሉ፥ እናም መትፋት አለባቸው የሚል ሲሆን ነው። ወይንም እኔ ልዩ ነኝ፥ ስለዚህ ከሌሎች የአገሪቱ ዜጎች ተለይቼ ልዩ ጥቅምና ክብር ይገባኛል፥ ይህንንም ለማሳካት ልደራጅ፥ “ሌሎች” የተሰኙትን ለይቼ በማግለል የእኛ ያልኩትን ልጥቀም የሚል እሳቤ ላይ ሲመሠረት ያ ንቅናቄ ዘረኛ ነው።

ይህን ዘረኛ ንቅናቄ ለመቃወም፥ የህልውና አደጋን ለመከላከል የሚጀመር፥ ነገር ግን የሰው እኩልነትን፥ ፍትሕንና እውነትን መሠረት የሚዑኣደርግ ንቅናቄ ሰውኛ ነው።

በዚህ መሥፈርት መሠረት የኦነግ/አሮሙማ እና የሕወሐት ንቅናቄዎች ላለፉት 50 ዓመታት እንዳስመሰከሩት የዘረኝነትና ሌሎችን የማሳነስ ብሎም የማጥፋት መሆኑን በብልጽግና እና በሕወሐት አሁናዊ ተግባር ታውቆ ተደምድሟል።

ከዚህ አንጻር የዐመሓራ ንቅናቄ የራስን ህልውና ከአደጋ የመላከል፥ ቀጥሎም ታሪካዊት አገርንና እነዚህ ዘረኞች በባርነት ሊይዟቸው ያጩኧቸውን ሌሎች ዜጎች አበረታቶና ደግፎ ራሳቸውን ከትፋት ነፃ እንዲያደርጉ፥ የጋራ አገራቸውን እንዲጠብቁ፥ የዘርኝነት ዕሳቤዎች ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ ርእዮትችንና ድርጅቶችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር አንዲያስወግዱ የበኩሉን መወጣት ነው።

የዐመሓራ የህልውና ንቅናቄ እንደ ሌሎቹ የምናውቃቸውን አሁን ለምንገኝበት አገራዊ ምስቅልቅሎስ ከዳረጉን የብሔር የማንነት ፖለቲካ በምንም አይነት አይመሳሰልም።

ቀደም ያሉት አደረጃጀቶች አፈጣጠራቸው በጎሣ ንዑስ ማንነት አንፃር የተጋረጠባቸውና በአስገዳጅ ሁኔታ ተደራጅተው የሚከላከሉት የህልውና አደጋ ሳይጋረጥባቸው የተፈጠሩ ናቸው።

ብዙዎቹ ከማርክሲሰት ርእዮተ ዓለም በመነሳት የአገራቸው የሆነውን ነባር ነገር ከየዩነቨርሲቲውና ከየአካባቢው በመሳሰብ፥ በውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች በመመከር የተፈጠረ አንዱን ክፍለ ሕዝብ፥ ባህልና እምነት ጠላት በማድረግ፥ ሐሰተኛ ትርክት በመፍጠርና የፖለቲካ ማታገያ የተባለ የልሂቃን የፈጠራ አጀንዳ በመቅረፅ የተፈጠረ አይደለም።

በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለህልውና መጠበቅና ለሰብአዊነት፥ ለፍትሕና ለአገራዊነት በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ የተወለደ፥ የፖለቲካ ርእዮት፥ የሃይማኖት፥ የባህል ወይንማ የደምና የአጥንት መሥመርን ሳይከተል የቆመ ንቅናቄ አልታየም። ዐመሐራ በቀዳሚ ታሪኩ ሁሉ አንደም ጊዜ ሌሎች ዘረኞች እንደሚያደርጉት ፦

ሌሎች የቡደን ንቅናቄዎችና የፖለቲካ አደረጃጀቶች በተለይ ሕወሐትና ኦነግ/ኦሮሙማ ያደረጉትና እያደረጉት የሚገኙት፥ ነገር ግን የዐመሓራ ንቅናቄዎች በምንም መንገድ በታሪኩ አድረጓቸው ያማያውቃቸው ፯ የማኅበረ-ፖለቲካ፥ የታሪክና የአገር ጉዳይን የሚመለከቱ ንጉዳዮች

፩) ነባር አገርን አጥፍቶ አዲስ አገር ለመፍጠር ተንቀሳቅሶ አያውቅም
፪) ነባር እምነት፥ ባህልና ታሪክን ደምስሶ አዲስ እምነት፥ ባህልና ትርክት ለመተካት አልሞከረም
፫) ሕዝብን አፈናቅሎና በጅምላ ፈጅቶ አሠፋፈር መቀየር አቅዶ አልሠራም
፬) ፊደል፥ ቅርሥ፥ ጥበብ፥ ገዳማትና መስጂዶች ደምስሶ አሻራን በማጥፋት አዲስ በልሂቃን አእምሮ የተፈጠረች አገር ለመሥራት እልጣረም
፭) ዜጎችን በወገን ለይቶ ለማደኸየት፥ በሽታ ለማስያዝ፥ አግዞ ለማዋረድ፥ ጦር አዝምቶ መለጨፍጨፍ ሞክሮ አያውቅም፥
፮) በምንም ወቅት ሰዎች ዐመሓራ ጎሣና ቋንቋ፥ እምነትና ባህል ለይቶ ወንድና ሴቶች እንዳይጋቡ፥ ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ፥ እርስበርሳቸው
እንዳይዋሐዱ አስተምሮና አስገድዶ፥ በተግባርም ገልጾ አያውቅም
፯) አንድም ቦታ ላይ በጎሣ ዘውግ ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ማኒፌስቶ፥ የትርክት መጽሐፍ፥ በሳይንስ ስም ሌሎች እንደሚኣደርጉት የሐሰት
ትርክትን ለማጠናከር ምሁራን አሰልፎ የሐሰት ጆርናሎችና መጽሐፍትን፥ የሐሰት ማምረቻ ማሥበራትንና የጥናት ማዕከላትን መኅርቶ
አያውቀም

ዐመሐራ አሁን የጀመረው የህልውና ትግል የመኖር የተፈጥሮ ግዴታ ሆኖ የተወለደ፥ ለሰብአዊነትን፥ ለፍትሕንና ለእውነት ዋጋ የሚሰጥ ማንኛውም የሰው ልጅ፥ በተለይ ሰብእናው የተሟላ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የሚደግፈው ብቻ ሳይሆን አብሮ የመቆም ግዴታ ሰብአዊ፥ ኅሊናዊ፥ መንፈሳዊ፥ ታሪካዊ፥ ሞራላዊ ግዴታ ነው።

የዐመሓራ ንቅናቄ ዘረኛ ውይስ ሰውኛ?
አንድ ንቅናቄ ዘረኛ የሚባለው እንደ ናዚ ጀርመን እኔ ልዩ ዘር ነኝ፥ ሌሎች ያንሳሉ፥ እናም መትፋት አለባቸው የሚል ሲሆን ነው። ወይንም እኔ ልዩ ነኝ፥ ስለዚህ ከሌሎች የአገሪቱ ዜጎች ተለይቼ ልዩ ጥቅምና ክብር ይገባኛል፥ ይህንንም ለማሳካት ልደራጅ፥ “ሌሎች” የተሰኙትን ለይቼ በማግለል የእኛ ያልኩትን ልጥቀም የሚል እሳቤ ላይ ሲመሠረት ያ ንቅናቄ ዘረኛ ነው።

ይህን ዘረኛ ንቅናቄ ለመቃወም፥ የህልውና አደጋን ለመከላከል የሚጀመር፥ ነገር ግን የሰው እኩልነትን፥ ፍትሕንና እውነትን መሠረት የሚዑኣደርግ ንቅናቄ ሰውኛ ነው።

በዚህ መሥፈርት መሠረት የኦነግ/አሮሙማ እና የሕወሐት ንቅናቄዎች ላለፉት 50 ዓመታት እንዳስመሰከሩት የዘረኝነትና ሌሎችን የማሳነስ ብሎም የማጥፋት መሆኑን በብልጽግና እና በሕወሐት አሁናዊ ተግባር ታውቆ ተደምድሟል።

ከዚህ አንጻር የዐመሓራ ንቅናቄ የራስን ህልውና ከአደጋ የመላከል፥ ቀጥሎም ታሪካዊት አገርንና እነዚህ ዘረኞች በባርነት ሊይዟቸው ያጩኧቸውን ሌሎች ዜጎች አበረታቶና ደግፎ ራሳቸውን ከትፋት ነፃ እንዲያደርጉ፥ የጋራ አገራቸውን እንዲጠብቁ፥ የዘርኝነት ዕሳቤዎች ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ ርእዮትችንና ድርጅቶችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር አንዲያስወግዱ የበኩሉን መወጣት ነው።

የዐመሓራ የህልውና ንቅናቄ እንደ ሌሎቹ የምናውቃቸውን አሁን ለምንገኝበት አገራዊ ምስቅልቅሎስ ከዳረጉን የብሔር የማንነት ፖለቲካ በምንም አይነት አይመሳሰልም።

ቀደም ያሉት አደረጃጀቶች አፈጣጠራቸው በጎሣ ንዑስ ማንነት አንፃር የተጋረጠባቸውና በአስገዳጅ ሁኔታ ተደራጅተው የሚከላከሉት የህልውና አደጋ ሳይጋረጥባቸው የተፈጠሩ ናቸው። ብዙዎቹ ከማርክሲሰት ርእዮተ ዓለም በመነሳት የአገራቸው የሆነውን ነባር ነገር ከየዩነቨርሲቲውና ከየአካባቢው በመሳሰብ፥ በውጭ የኢትዮጵያ ጠላቶች በመመከር የተፈጠረ አንዱን ክፍለ ሕዝብ፥ ባህልና እምነት ጠላት በማድረግ፥ ሐሰተኛ ትርክት በመፍጠርና የፖለቲካ ማታገያ የተባለ የልሂቃን የፈጠራ አጀንዳ በመቅረፅ የተፈጠረ አይደለም። በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለህልውና መጠበቅና ለሰብአዊነት፥ ለፍትሕና ለአገራዊነት በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ የተወለደ፥ የፖለቲካ ርእዮት፥ የሃይማኖት፥ የባህል ወይንማ የደምና የአጥንት መሥመርን ሳይከተል የቆመ ንቅናቄ አልታየም። ዐመሐራ በቀዳሚ ታሪኩ ሁሉ አንደም ጊዜ ሌሎች ዘረኞች እንደሚያደርጉት ፦

ሌሎች የቡደን ንቅናቄዎችና የፖለቲካ አደረጃጀቶች በተለይ ሕወሐትና ኦነግ/ኦሮሙማ ያደረጉትና እያደረጉት የሚገኙት፥ ነገር ግን የዐመሓራ ንቅናቄዎች በምንም መንገድ በታሪኩ አድረጓቸው ያማያውቃቸው ፯ የማኅበረ-ፖለቲካ፥ የታሪክና የአገር ጉዳይን የሚመለከቱ ንጉዳዮች ፦

፩) ነባር አገርን አጥፍቶ አዲስ አገር ለመፍጠር ተንቀሳቅሶ አያውቅም
፪) ነባር እምነት፥ ባህልና ታሪክን ደምስሶ አዲስ እምነት፥ ባህልና ትርክት ለመተካት አልሞከረም
፫) ሕዝብን አፈናቅሎና በጅምላ ፈጅቶ አሠፋፈር መቀየር አቅዶ አልሠራም
፬) ፊደል፥ ቅርሥ፥ ጥበብ፥ ገዳማትና መስጂዶች ደምስሶ አሻራን በማጥፋት አዲስ በልሂቃን አእምሮ የተፈጠረች አገር ለመሥራት እልጣረም
፭) ዜጎችን በወገን ለይቶ ለማደኸየት፥ በሽታ ለማስያዝ፥ አግዞ ለማዋረድ፥ ጦር አዝምቶ መለጨፍጨፍ ሞክሮ አያውቅም፥
፮) በምንም ወቅት ሰዎች ዐመሓራ ጎሣና ቋንቋ፥ እምነትና ባህል ለይቶ ወንድና ሴቶች እንዳይጋቡ፥ ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ፥ እርስበርሳቸው እንዳይዋሐዱ አስተምሮና አስገድዶ፥ በተግባርም ገልጾ አያውቅም
፯) አንድም ቦታ ላይ በጎሣ ዘውግ ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ማኒፌስቶ፥ የትርክት መጽሐፍ፥ በሳይንስ ስም ሌሎች እንደሚኣደርጉት የሐሰት ትርክትን ለማጠናከር ምሁራን አሰልፎ የሐሰት ጆርናሎችና መጽሐፍትን፥ የሐሰት ማምረቻ ማሥበራትንና የጥናት ማዕከላትን መኅርቶ አያውቀም

ዐመሐራ አሁን የጀመረው የህልውና ትግል የመኖር የተፈጥሮ ግዴታ ሆኖ የተወለደ፥ ለሰብአዊነትን፥ ለፍትሕንና ለእውነት ዋጋ የሚሰጥ ማንኛውም የሰው ልጅ፥ በተለይ ሰብእናው የተሟላ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የሚደግፈው ብቻ ሳይሆን አብሮ የመቆም ግዴታ ሰብአዊ፥ ኅሊናዊ፥ መንፈሳዊ፥ ታሪካዊ፥ ሞራላዊ ግዴታ ነው።

ወሳኝ የትግልና የግልጸኝነት ጥያቄዎች
፩) ዐመሓራ ለህልውና፤ ለሰብአዊነት፥ ለፍትሕና ለእውነት የጀመረው ተጋድሎ ወደ ፖለቲካዊ ዘረኝነት ሊለወጥ አይችልም?
፪) ፖለቲካዊ ዘረኝነትን የሚዋጋው የዐመሓራ ሕዝባዊ ንቅናቄ ራሱን ከፖለቲካዊ ዘረኝነት ጠብቆ በፍትሐዊነት፥ በተፈጥሮ ሰውነት፥ በአገራዊነት፥ በሰብአዊ ማኅበራዊነት ስነ ምግባሩ እንዲቀጥል ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት?
፫) ዐመሓራ ህልውናው ተረጋግጧል፥ ትግሌም ተቋጭቷል በማለት የትጥቅ ትግሉን የሚገታው ምን ሲሟላ ነው?
፬) የአንድ ማኅበረሰብእ የህልውና ዋስትና በራሱ ብቻ የሚረጋገጥ ሳይሆብ በሌሎች የህልውና ዋስትናና አሰላለፍ ላይጥገኛ ብቻ ሳይሆን ተደጋጋፈነት ያለው በመሆኑ የዐሓራ ሕልውና ዋስትና ለትግራይ፥ ለኦሮሞ፥ ለሶማሌ፥ ለአፋርና ለሌሎች ያለው ምልከታ ምንድነው?
፭) በዐመሓራ ላይ የህልውና አደጋ እንዲጋረጥ ያደረጉ ጉዳዮች ርእዮተ ዓለማዊ፥ ትርክታዊ፥ ጂኦ ፖለተካዊ፥ የተፈጥሮ ሀብትና የአገር ባለቤትነት ጉዳዮችና እነዚህን በማስተዳደር ዐመሓራን ከተሳትፎ የሚያገልል የ50 ዓመታት የጭቆና ትርክትና ሥርዓተ መንግሥት መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ፥ ዐመሓራ ሕልውናውን ለማረጋገጥ ንቅናቄው ከትጥቅ ትግሉ መጠናቀቅ በኋላ በእነዚህ ዘርፎች ሁሉ ላይ ምን ተጽእኖ በማሳደር ወደ ጤናማ ሁሉም እኩል የአገር ባለቤትነት የሆነበት ሥርዓት ለመፍጠር ያስባል?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *