ከአራቱ የአማራ ጠቅላይ ግዛት ፋኖዎች የተሠጠ መግለጫ

                 

የአማራ ሕዝብ እያካሄደ የሚገኘው የኅልውና ትግል በዓይነትም በስልተ ትግልም ተለዋዋጭ የሥርዓቱን ፖለቲካዊ ሻጥር በሚያፈራርስ ተክለ ቁመና ላይ ይገኛል።  ትግሉ የሕዝባችንን ኅልውና ማረጋገጥ  በሚቻልበት ሃዲድ እየተጓዘ መሆኑን በርካታ አመላካች ጉዳዮች ቢኖሩም በአራቱም ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ጋርዮሻዊ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከመሥራት እስከ በአንድ ተቋም መታገል የሚያበቁ  ተግባራትን መከወን የዘለቁ ሥራዎችን በማከናወን ላይም ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ፋኖ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና  የደህንነት አዛዦች በተደረገ ቅንጅታዊና የታቀደ ኦፕሬሽን በዛሬው እለት ማለትም በ04/08/2016 ዓ.ም የአሸባሪው  ሥርዓት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ከወሎ ሠፈር  እስከ ቦሌ ፍሬንድሽፕ ባለው አካባቢ የሥርዓቱ  ወንበር ጠባቂ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ላይ አስደናቂ  ኦፕሬሽን ሠርቷል። ከረፋዱ 5:00 _ እስከ 7:00 የቆየው  ይህ ልዩ ኦፕሬሽን የአማራ ፋኖ በጎንደር ቀጠናዊ ዘመቻ  አስተባባሪ፣ የአጼዎቹ ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ አዛዥና  በጃንተከል ብርጌድ ዋና አዛዥ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ የተመራ ሲሆን ከ30 በላይ የሥርዓቱ አገልጋዮች በፋኖ አርበኞች እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል። በዚህ የታቀደ ወታደራዊ ኦፕሬሽን የተሳተፉ የአማራ ፋኖ አርበኞች ተልእኳቸውን በተሳካ ሁኔታ መፈጸማቸው የኅልውና ትግላችንን ከክልላችን በፍጥነት አውጥተን  ወደ 4 ኪሎ ለምናደርገው ግስጋሴ እንደ መቅድም የተጠቀምንበት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። በመሆኑም በዚህ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ውስጥ የኦፕሬሽኑ አርበኞች መሪ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ የተሰጠውን ግዳጅ አከናውኖ አርበኛ ጓዶቹን ሽፋን  እየሰጠ ካስወጣ በኋላ በጠላት ጦር ከበባ ተደርጎበት እጁን ለጠላት ላለመስጠት እንደ አጼ ቴዎድሮስ የያዘውን ሽጉጥ ጨልጦ በጀግንነት ተሰውቷል። የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የግብር ልጅ የሆነው አርበኛ  ናሁሰናይ አንዳርጌ ከ2008 ዓም ጀምሮ መሪር ትግል ሲያደርግ የነበረ፣ ዛሬ በጀግንነት እስከተሰዋበት እለትድረስም በአማራ ፋኖ በጎንደር አጼዎቹ ክ/ጦር እንዲሁምጃንተከል ብርጌድ ውስጥ ሲታገልና ሲያታግል የቆየየአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን በአርበኝነት ያስመሰከረ ጀግና ተዋጊ ነው። በአርበኛችን መሰዋት የገጠመን መሪር ሃዘን ቢሆንም ፋኖነት በነጻ ፈቃድ ለፍትህ፣ ለሐቅና ለሕዝብ ኅልውና ዘብ በመቆም የሚከፈል መስዋዕትነት መሆኑን ለሰከንድም ሳንዘነጋ መሪሩን ሃዘናችንን ወደ መራር ትግል መቀየር የትናንት፣ የዛሬና የነገም የትግል መርሃችን መሆኑን እንገነዘባለን። ስለሆነም በአራቱም የአማራ ጠቅላይ ግዛቶች ለምትገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች 

1ኛ. ከነገ 05/08/2016 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ዘመቻ አርበኛ ናሁሰናይ አንዳርጌ በማካሄድ የአሸባሪው ሥርዓት ዙፋን ጠባቂ ጦር ላይ የማያዳግም እርምጃ እንድንወስድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

2ኛ. በጀግንነት የተሰጠውን ግዳጅ ፈጽሞ  የተሰዋውን የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የግብር ልጅ አርበኛ  ናሁሰናይ አንዳርጌን አስከሬን በክብር እንዳያርፍ ጸያፍ  የሽብር ተግባሩን የሚከውነው መንግሥታዊው የሽብር  ቡድን በእያንዳንዷ ተግባሩ ልክ አጸፋውን የሚቀበልበትን  ቀጠናዊ፣ የተናበበና የታቀደ ሁሉንአቀፍ ደመላሻዊ  የአርበኝነት ተግባር እንድንፈጽም ጓዳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

3ኛ. ፋኖ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የዲፕሎማቲክ  መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ  ቀጣይነት ያለውና ደረጃውም ከፍ ያለ ኦፕሬሽን  በተከታታይ የሚያከናውን መሆኑን እየገለጽን የተለያዩ አገሮች ቆንስላ ጽ/ቤት ሠራተኞች ይህንን ተረድተው ከሥርዓቱ የጻእር ሞትና  ሽብርተኛ ተግባር  የራሳቸውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጀምሮ የሥርዓቱን መፈራረስና መውደቅ በሐቅ እንዲገልጹ እንጠይቃለን።

4ኛ. በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ተወላጆችና የአማራ ሕዝብን የኅልውና ትግልን በሃሳብም በግብርም የምትደገፉ ኢትዮጵያውያን የአማራ ፋኖ ትግል አድማሱን እያሰፋ ሥርአቱን መቅበር ወደሚችልበት ምዕራፍ  መሸጋገሩን ተገንዝባችሁ ጠንካራና የታቀደ የዲፕሎማሲ ሥራ በመሥራት ትግላችንን ከፍ እንድታደርጉት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

5ኛ. ለአካላዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ኢኮኖሚያዊ ሰለባ  እንዲሁም መኖሪያ ቤትህ ሳይቀር በላይህ ላይ እየፈረሰ ለስደት፣ ለረሃብና ለማኅበራዊ ቀውስ የተዳረግኸው የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጭ ብሎ ነጻ  አውጭ ከመጠበቅ ደካማ እሳቤ ወጥተህ በመዲናችን አዲስ አበባ በጀግንነት ደሙ የፈሰሰውን አርበኛ  ወንድምህ የተሰዋለትን የትግል ዓላማ በግብር በመደገፍ መንግሥታዊዉን ሽብርተኛ ሥርዓት በተለያዩ መንገዶች እንድትታገለው አርበኛ ወንድሞችህ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን።

6ኛ. በመላው ዓለም የምትገኙ የሚዲያ አካላት ከነገ ጀምሮ  በመላው አማራ የሚካሄደውን ዘመቻ አርበኛ ናሁሰናይ  አንዳርጌን በልዩ ሁኔታ እየተከታተላችሁ ለሕዝብ  እንድታደርሱና  የሥርዓቱን ሠራዊት መፈራረስም ለዓለም ሕዝብ እንድታጋልጡ እንጠይቃለን። በአጠቃላይ ፋኖ ይህንን የታቀደና ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን የፈጸመው በሥርዓቱ ዙፋን ጠባቂ የፌደራል  ፖሊስ፣ የመንግሥት ደኅንነትና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ብቻ ያነጣጠረና ግቡንም ሙሉ በሙሉ  ያሳካ እንደነበር መግለጽ እንወዳለን። ከዚህ ውጭ አሸባሪው  መንግሥታዊ ሥርዓት ይህንን ታላሚ ኦፕሬሽን ተከትሎ በከተማዋ ንጹሐን ላይ ተከታታይነት ያለው ማዋከብና ጅምላ እስር አለፍ ሲልም ወጣቶችን እስከመረሸን የተሻገረ እኩይ ተግባር ሊፈጽም ስለሚችል የከተማዋ ነዋሪ እራሱን ከመጠበቅ እስከ መሪር ትግል ማድረግ መሸጋገር ይኖርበታል። ከዚህ በተጨማሪም  አሸባሪው የብልጽግና መንግሥት ከከተማው ንጹሃን  ጭፍጨፋ በተጨማሪ የውጭ ዜጎች ላይ ጭምር ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም ፋኖ ፈጸመው በማለት በአሸባሪነት በመፈርጅ ለመጋጋጥ እቅድ መያዙንም የፋኖ የደኅንነት ምንጮች ስላረጋገጡ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ የአገሪቱም ሆነ የውጭ ዜጎች ብርቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን። ከምንም በላይ የአማራ ፋኖ የዛሬም ሆነ የቀጣይ ተከታታይ በመዲናዋ ላይ የሚወስዳቸው ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች  የሥርአቱ ዙፋን ጠባቂዎችና ዘራፊና ገዳይ ባለሥልጣናት ላይ ብቻ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

      ፈጣሪ የአርበኛችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያሳርፍ!

            ” ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!”

     የአማራ ፋኖ በጎንደር

      የአማራ ፋኖ በጎጃም

       የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ

       የምሥራቅ አማራ ፋኖ

አማራ፣ ኢትዮጵያ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *