የብልጽግና ወንጌል ተከታዬችንንና ከብልጽግንል ፓርቲ አባላት፣  ከዲያብሎስ አምልኮ እራሳችሁን አግልሉ

ሰይፈ ስላሴ
ክፍል አንድ
ብዙ መጽሐፍ ቅዱስንና ቁራንን ያጠኑ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ አሉ። ይሁንና እነዚህ ሰዎች አለማዊውን የአዲሱ ዘመን የስነልቦና መጽሀፍትን አላነበቡም። ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖች እስላሞች ሀይማኖታቸውን ቀይረው የአብይና የሱ ዲያብሎስን እምነት ተከታዬች ሆነዋል። አብይ 14 ሚሊዮን ተከታዬች እንዳሉት ባለፈው ሳምንት ነግሮናል።
በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ የስነልቦናውን (The New Age Movement) እና አለማዊውን መጽሀፍ ያነበበቡ ብዙ ኢትዮዊያን አሉ ይሁንና እነሱ መጽሐፍ ቅዱሱንና ቁራኑን አያውቁም። ስለዚህ ሁለቱን የማዛመድና የመመርመር አቅም የላቸውም። ይህ ጽሁፍ አላማ የዲያብሎስ እምነት እንዴት የበግ ለምድ ለብሶ ክርስቲያኑንና እስላሙን ሀይማኖቱን እንዳስቀየረው ለማሳየት ነው። አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በሰይጣን አምልኮ ንዋይ ተታለው_14 ሚሊዮን ሰዎች ሀይማኖታቸውን ቀይረው የዲያብሎስ ተከታዬች ሆነዋል ኮለኔል አብይ ነግሮናል። እኔ አለማዊውንም መንፈሳዊውንም አነባለሁ። ይሄንንም የጻፍኩት የፕሮቴስታንትም የኦርቶዶክስ የእምነት አባቶች ገና ስለ ስለ ብልጽግና ወንጌል ምንጭና ግብ አላነበቡም። ምን እንደሆነም ገና አላወቁም። ብዙዎች አብይን እንደ ክርስቶስ አስተምህሮ ቆጥረው ከሱ ጋር ህብረት ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያሉ። አብይ እራሱ እንዳለው ብርሀንና ጨለማን ለማስታረቅ ጳጳሳቱና ወንጌላውያን እየሞከሩ ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች፣ ፕሮቴስታንቶችና እስላም የብልጽግና ሀይማኖት ተከታዮች በጽሞና አንብቡ። ምክንያቱም እናንተ ሀይማኖት ቀየራችሁ እንጂ የፓለቲካ ፓርቲ አባል አልሆናችሁም። ዛሬ በዝርዝር የምጽፈው ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችና ለፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ነው። የብልጽግና ወንጌል አስተምህሮ በ1950ዎቹ የተፈጠረ ሀይማኖት ቢሆንም ዛሬ በአሜሪካ ትልቁ ተከታይ ያለው ሀይማኖት ለመሆን በቅቷል።

የብልጽግና ወንጌልን ማንጻፈው?
የብልጽግና ወንጌል የተጻፈው መጀመሪያ በስነ ልቦና አነቃቂዎች ነው። እነ ናፖሊዮን ሂል “Think and Grow Rich”  እነ ኖርማን አንስት  “The Power of Positive Thinking”, The Secret, by Byrne የተጻፏት መጽሀፍት ናቸው። እነዚህ መጽሀፍት በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ እየተሸጡ ነው። እነዚህ በራሳቸው እንደ ስነልቦና ማነቃቂያ ችግር የላቸውም። ይሁንና እነዚህን “የብልጽግና ወንጌክ ብሎ ማምለክ ግን ክርስትና አይሆንም። አሁን በአሜሪካ ያሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እያጠፋ ያለው የብልጽና ወንጌል ነው። ይሄንን ትችት ፕሮቴስታንቶቹ ጽፈዋል።
“The Word of Faith Movement, often termed “the prosperity gospel.”  This group has been infiltrating evangelicalism for decades and is now the fastest growing segment of Christianity in the world.  Some have estimated that up to 90 percent of those claiming to be Christians in Africa are of the prosperity gospel variety” ይሄንን በቀላሉ ለሰባኪዌች ሀብት ማፍሪያ ያደረጉት ሰባኪዎች እንል Kenneth Hagin, Kenneth Copeland, Robert Tilton, Paul Yonggi Cho, Benny Hinn, Marilyn Hickey, Frederick Price, John Avanzini, Charles Capps, Jerry Savelle, Morris Cerullo, Joyce Meyer and Paul and Jan Crouch. አብይ አህመድ በድህነት ይደገ ልጅ ነው። ሁላችንም የደሀና የገበሬ ልጆች ነን ይሁንና ብር ለማግኘት ሀይማኖታችንን ግን አልቀየርንም። አብይ ኦርቶዶክስ፣ሙስሊምም ነበር። መጨረሻ ሀብትና ጉልበት የሚሰጠው ከየብልጽግና ወንጌል ሆኖ ስላገኘው ክርስትናውንም እስልምናውንም ትቶ የብልጽግና ሀይማኖት ተከታይ ሆነ። አሁን እሱ የዚህ እምነት ሰባኪ፣ አጥማቂና ጳጳስ ሆንዋል። አላማውም እስላሙንም ክርስቲያንም ወደ የብልጽግና ቤተ አምልኮ ማስገባት ነው። የዚህም ቤተ አምልኮ አላማ በጥቅም የብልጽግና ፓርቲ/ቤተ እምነት ተከታይ ማድረግ ነው። ይህን የስነ ልቦና አስተምህሮ ወስደው ወደ ክርስትና እምነት የቀየሩት ደግሞ  Joel Osteen, በአሜሪካ የትልቁ ቤተ እምነት Lakewood Church ባለቤት እና መስራች ነው። ሁለተኛው ደግሞ Oral Roberts, a pioneering televangelist ነው። ሁለቱም ብዙ መጽሀፍ ጽፈውል ፈልጋችሁ አንብቡት። የብልጽግናን ወንጌል ክርስቲያኖችን የሚያስክድ ነው ብለው ብዙ ሰዎች ጽፈዋል። እነዚህን አንብቡ
https://tottministries.org/joel-osteen-and-the-prosperity-gospel/-
አስተምህሮውም ሀብታም እንድትሆኑ መጀመሪያ ለፓስተራችሁ ለዘር የሚሆን ብር (seed money) ስጡንና በሱ ላይ ጸልየን ወደ ሚሊዮን ይባዛላችሀል እያሉ ይዘርፋሉ። ድሮ ብር ስጠኝ ብሎ ሰው ጠንቋይና ቃልቻ ቤት ነበር የሚሄደው ዛሬ ደግሞ እስራኤል ዳንሳ፣ አዩ ጩፋ እና ዮናታን አክሊሉ እንግዳ ማረፍያ ነው የሚሄደው። ይህ ነው የአብይ አህመድ ክርስትና የሚለው። የብልጽግና እና የጤና መጽሀፍ ቅዱስ የሚባለው በእንግሊዘኛ (The prosperity gospel, also known as the health and wealth gospel or name it and claim it, is a teaching within Protestant Christianity”. ነው ብለው እንዲያምኑ ስለተደረጉ ብዙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ለአብይ ሰይጣን አብይ ሺ አመት ንገስ ብለው በአደባባይ ጸለዩለት. የአብይ የሚከተለው እምነት ከነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጋ አንድ  እንዳልሆነ አይልውቁም። ይህ የብልጽግና ወንጌላውያን ማታለል በአደባባይ እየታየ ነው። 
አሁን በሞባዬላችሁ ከንግድ ባንክ ሚሊዮን ብር እንዲገባ ያላችሁን ሁሉ ለኔ ስጡና  ልጸልይላችሁ የሚሉት እስራኤል ድልንሳ የአብይ አስተምህሮ አንድ ነው። የብልጽግና እምነት የዲያብሎስ አምልኮ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች። አብይ የዲያብሎስ እምነት ተከታይ እንጂ የክስቶስ ተከታይ አይደለም የምለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። በመጀመሪያ  ክርስቲያን ማለት የክርስቶስን ቃል የሚቀበል ማለት ነው። ቃሉን ሳይቀበሉ ክርስቲያን መሆን አይቻልም። አለማወቅ ችግር የለውም ይሁንና አውቀን አለመቀበል ግን ክርስቲያን አያደርገንም።

የብልጽግንና ፍቅረ ንዋይ የክርስቶስ አስተምህሮ አይደለም 
በማቲዎስ ወንጌል ም4 ቁ 1-11 ይሄንን ይላል ። “ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተም ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። አርባ ቀን አርባ ሌሊት ከጦመ በኋላ ተራበ።ፈተኙም ቀርቦ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆን በል አለው።  እርሱም መልሶ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል አለው። ……ከዛም ዲያቢሎስ እጅግ ረዥም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፣ የዓለምን መንግስታት ሁሉ ከክብራቸው  አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ  እሰጥካለሁ አለው። ያን ግዜ ኢየሱስ ሒድ አንተ ሰይጣን ከፊቴ ለአምላክህ ስገድ እሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፏልልና አለው።” 
ይህ ቃል የተጻፈው ዲያቢሎስ እንዴት የሰው ልጅን በጥቅምና በዝና እንደሚፈትሸውና የሰው ልጅም ለሀብትና ጥቅም ብሎ ለሰይጣን መስገድ እንደማይገባው ለማስተማ ነበር። ይሁንና በ20ኛው ክፍለዘመን ብዙ የአነቃቂ ንግግር ጸሀፊዎች የሰው ልጅ እንዴት ሀብታም ይሆናል የሚለውን መጻፍ ጀመሩ። ይህም  የአዲሱ ዘመን ንቅናቄን ፈጠረ (The New Age Movement) ተወለደ። ይህ ስነ ልቦና መሆኑ ቀርቶ ሀይማኖት/እምነት ሆነ አሁን አብይ ክርስቲያንም እስላሙንም የዚህ እምነት ተከታይ አድርጎ ብዙውን ሀይማኖቱን አስቀይሮታል። 
የብልጽግና ወንጌል የፍቅረ ንዋይ በክርስቶስ የተወገዘ ነው።
በሉቃስ ወንጌል ደግሞ ም6: 20-26. ይህንን ይላል “እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።  እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ።  ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።”
የብልጽና ወንጌል ከላይ የተጠቀሱትን የክርስቶስ ቃል አይቀበልም። ሳትሰራ፣ ሳትጥር፣ ሳትደክም ሀብት በሞባዬልህ ይገባል። ለድሆች አታስብ፣ በመንገድ ላይ ወንበዴዎች ደብድበው የጣሉትን አትመልከት፣  ለሚሞቱት ለሚሰቃዩት አታስብ። አንተ ደግ ደጉንና  ሀብታና ንብረት ብቻ ተመኝ። እሱን ታገኛለህ።  መስረቅ፣ መዋሸት፣ ጉቦ መብላት ፣ ድሆችን ለማየት መጠየፍ፣ ቤታቸውን ማፍረስ የብልጽግና ወንጌል መገለጫ ነው። ዛሬ እነ ሽመልስናብወንድሙ በቢሊዮን ብር በጉቦና በሲሚንቶ ንግድ ከብረዋል። እነ አዳነች አቤቤ ሰርቀው ልጆቻቸውን በዶላር ያስተምራሉ፣ ግን ማታ ተሰብስበው ተንበርክከው ለአባታቸው ይጸልያሉ።  ይህ አባታቸው የሌብነት፣ የጥላቻ፣ የግድያ አባት ክርስቶስ አይደለም። አፋቸው እንጂ ተግባራቸው የሀብት የዲያብሎስ ነው። በማቲዎስ ወንጌል ም4:8-11 ላይ እኮ ዲያቢሎስ በምድር ላይ ሀብትና ንብረት መስጠት እንደሚችል ተጽፏል። 
ስለዚህ የብልጽግና ፓርቲ ተከታይ በተለይ የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ንቁ። የኦርቶዶክሱና የእስላም የአብይ ቤተ እምንነት አባላት አብይ ክርስቲያን እንዳልሆነ ይልውቃሉ። እነሱ ሌብነትና ጥቅም ፈልገው ነው የመረጡት።
ብዙዎቹ ግብ የተቀላቀላችሁት እምነት እንጂ የምድራዊ ፓለቲካ ፓርቲ እንዳልሆነ አይልውቁም። ከላይ እብዳያችሁት አርማውብን ተመልከቱ ከአሜሪካ የብልጽግንና ወንጌል አርማ የተቀዳ ነው። እንዴት ይሄንን አርማ የመምረጥና የማጽደቅ መብት የላችሁም? የማብ ብልጽግና ብላችሁ እንኳን አትጠይቁም? የኢትዮጵያ ብልጽግና ወይስ የሰይጣን ተከታዮች ብልጽግንና?

ዘጠና ዘጠኝ 99% የሚሆነው የብልጽግና አባል መንግስት ተጠግቶ ለመዝረፍና ለመክበር ነው። ይህ የንዋይ ፍቅር ግን ወደ ገሀነም እያሳሳቀ እየወሰደው መሆኑን አያውቅም ብልጽግናዎች  እበላለሁ ብላችሁ በዘላለማዊ እሳት እንዳትበሉ። የማቲዎስ ወንጌል 6:24 “ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው አገልጋይ የለም፣ አንዱን ይወዳል ሁለተኛውንም ይጠላል፣ ወይንም አንዱን ይታዘዛል፣ ለሁለተኛውም አይታዘዝም፣ እንግዲህ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም” ይላል። 
ብዙዎች የብልጽግና አባላት ክርስቲያን፣ እስልምና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ናቸው። ከዘማሪ ዶ/ር ደረጄ ከበደ ውጪ ይሄንን የክህደት የዲያቢሎስ መንገድ የተረዳ የለም።
ሙስሊሞችም የተቀላቀላችሁት የብልጽግና ”መጽሐፍብ ቅዱስ”  እንጂ አለማዊ ፓርቲ አይደልም። እራሳችሁን በረመዳን ጦም አታታትሉ። አናውቅም ነበር እንዳትሉ ይሄው ተነግሯችሀል። አብይ Charismatic የሆነና ብዙ ተከታዮችን ማሳሳት የሚያስችል የክፏ መንፈስ ጸጋ ያለው ሰው ነው። 14 ሚሊዮን ሰው አስክዶ ዛሬ የሰይጣን ግብር የሚትልረዱ ህጻናትን እንዳያወግዙ አፋቸውን ለጉምዋል። በመጨረሻው ስታረድ፣ ስገደል፣ ምን አላችሁ ተብለን ሁላችንም እንጠይቃለን። መቼ አየንህና ማለት ያጠፋል።
የዛሬ አምስት አመት የአብን ጨቅላዌች የፈረንጄቹን ፍሪ ሜሴኖች እምነት ሁለት ጭንቅላት ያለውን አርማ ይዘው ሲነጡ። ይህ ከኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና እምነት ጋር ይጋጫል የሰይጣን እምነት 32 ዲግሪ አርማ ነው ተዉ ብንላቸው በድንቁርነታቸው ትፕኩርልርተው እንቢ አሉ። መጀመሪያ አጫፍሮ በመጨረሻ ያጠፋችሀል አልሰማ አሉ። አሁን በየ እስር ቤቱ እየተቀጠቀጡ ጠፏ።

የኦርቶዶክስና የብልጽግና ወንጌል ግጭት
አብይ ከልጅነቱ ጀምሮ ሀብት ንብረት ዝናን ለማግኘት እንደተጋ ነግሮናል። በማቲዎስ ወንጌል 4:8-11 እንደተጻፈው ዲያቢሎስ ከሰገዱለት በምድር ላይ ስልጣንና ሀብትም ይሰጣል። እናቱም ነግራዋለች። ነብይ አይደለችም ስለዚህ ጥንቆላ ነው። ስለዚህ በድህነት ሰቀቀን ስነ ልቦና ለሚሰቃይ ሀብት ስጠኝ እንጂ እሰግድልሀለሁ ይላል። የብልጽግና ወንጌል ልክ እነ መንግስቱ ለማርክስ ኤንግልስና ሌኒን ብታምኑ በምድር ገነት ትገባላችሁ ብለው ብዙ ደሀና በድህነት ያደገ ምሁር አሳምነዋል። እግዚአብሔር የለንም አሳምነውታል ነበር። ይህ ከድህነት ሽሽት ዛሬ ደግሞ 14 ሚሊዮን በድህነት ሰቀቀን ያደገ ክርስቲያንን ሙስሊምና ፕሮቴስታንት ግልብጥ ብሎ ሰርቆ ቅቅቱን ለማራገፍ የብልጽግና ቤተ እምነቱን ተቀላቅሎ ክርስቶስን ጥሎ አብን አምላኪ ሆንዋል።  ብልጭልጭ ህንጻ ውስጥ እንኖራለን፣ ገነት ማለት የአበቦች ቦታ ናት ብለው ብዙ ክርስቲያንና ብዙ የእስልምና ተከታዮችን ወደ ገሀነም አስከትለው እየሄዱ ነው። 
ዲያቢሎስ ደግሞ ግብር ይጠይቃል። ይህም ሀጥያትን መስራት ነው። ይሄም ሀጥያት ነፍስ ማጥፋት ነው፣ የንጹሀንን ደም ማፍሰስ ነው። ወይን መጠጣት ሀጥያት ነው የሚሉት የብልጽግና አማኞች የሰው ደም ማፍሰስ ግን ሀጥያት መስሎ አይታያቸውም ብዙ ናቸው። በየ ሬስትራንቱ እና ሰዎች ፊት ቅዱስ መስለው ለመታየት ወይን ቢራ ባፋችን አይገባም የሚሉት ፕሮቴታንቶች ብለው ጻድቅ መስለው የሚታዩት በጭለማ ደግሞ አብይና የሱ እምነት ተከታዬች ህጻናትን ሲያሳርዱ፣ እናቶችን ሲያስገድሉ፣ በሰራዊታቸው ሴቶችን ይደፍራሉ፣ ዘር ለማጥፋት ይተጋሉ። ደሆችንን ሲሳድዳሉ ዝም በማለት ልክ እንደ ቃዬል እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን በማለት ፈጣሪን ሊሸውዱ ያስባሉ። ግን ፈተናውን እየወደቁ ነው። ማቲዎስ 2:16-18 ላይ ሄሮድ ከሁለት አመት በታች ከሆኑት ውስጥ እብድ አድጎ ስልጣንን ይቀማኛል ብሎ ስለፈራ ሁሉንም አስገደለ።
“ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተዘባበቱበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣና ጭፍራዎቹን ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸውን፥ ከዚያም የሚያንሱትን፥ በቤተ ልሔምና በአውራጃዎችዋ ሁሉ የነበሩትን ሕፃናት አስገደለ።”
እአሁኑስ ልጅ ተወልዶ አድጎ አማራ ይሆናል ተብሎ ከናት ሆድ ተቀዶ ወጥቶ ሲገደል የትኛው የፕሮቴስታንት ወይን አልጠጣም ጻድቅ ነኝ ባይ ወጥቶ ይሄንን ሀጥያት አቁሙ ያለውም የትኛው ሼክና ጳጳስ ነው ያወገዘው። ለግል ሀብትና ክብር የተሰባሰበው ጳጳድ፣ ሼኮችና ወንጌላውያን የሚሉ ግብዞች ወድቀው ታዩ። እኛን በቃልና በልብስ ሸፍነው ሊያታልሉን ቻሉ። ፈጣሪያቸውን ግን ይችላሉ።
ዲያብሎስ ለክርስቶስ እንዳለው ጉልበትና ሀይል ይሰጣቸዋል። ይሄንን ሀይል ለማግኘት ግንድ ክርስቲያኑን እስላሙን፣ መኑኩሴን፣ ሼኩን፣ አባ ገዳውን ህጻናትን ማረድ ግን ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ ለዲያቢሎስ ቃብድ የሚሰጡት በመጀነሪያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞችን በማረድ ነው።
 ሰይጣን ክርስቶስን ሲፈትነው የአለምን ሀብት ሁሉ አሳይቶ ለኔ ብትሰግድልኝ ይሄንን ሁሉ እሰጥሀለሁ እንዳለው ለአብይና ለሽመልስም ሀብት ለማግኘት የማያደርጉት ነገር  ያለም። 
አብይ ላይ የተዳበለውም የክርስቲያንን ደም የሚጠጣው ዲያብሎስ ኑና ለሰይጣን እንስገድ ሀብትና ብልጽግና ይሰጠናል ሲባሉ እሺ ብለው የሚከተሉት ክርስቲያንና እስላም ነን የሚሉ ብዙ ናቸው።
ክርስቶስ ለደቀ መዝሙሮች ማስጠንቀቂያ ደግሞ  በመንገድልችሀ ላይ ወርቅና ብር አትያዙ ነበር ። 
ክርስቶስ  በማቲዎስ ወንጌል 10:7-10 “ሄዳችሁም። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትን አውጡ፣ በከንቱ የተቀበላችሁ፣ በከንቱ ስጡ። ወርቅ ወይንም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፣ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይንም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ”
ይህ ቃል ሁሉ በሁሉም ወንጌሎች ውስጥ ተደጋግሟል። ይሁንና የብልጽግና የዲያቢሎስ ወንጌል ደግሞ ሀብትን፣ ሞገስን እሹ፣ ወርቅና ዶላርን አጋብሱ ነው የሚላቸው። ዲያቢሎስ ለኔ ስገዱ ብልጽግናን እሰጣችሀለሁ ነው።   ይሄንን ባለማውገዛቸውና ባለ መለየታቸው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ፈተናውን ወድቀው ለሀብት ስገዱ ለሚለው እየጸለዩ ነው። ሎጂክ ስንማር A ከ B ጋር እኩል ከሆነና B ደግሞ ከ C ጋር እኩል ከሆነ A ደግሞ ከ C ጋር እኩል ይሆናል። 
አሁን ያለው ፍቅረ ንዋይ ወዳጅና በንጹሀን ደም የሚታጠበውን አለማውገዝ ከተጠያቂነት አያድንም። መደገፍ ደግሞ እጅን በደም ማነካካት ነው። ይህ ደግሞ የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ጳጳሳትንና የሙስሊሞችም የሀይማኖት አባቶች ያካትታል።
ለጥያትን አውግዙ። ስውን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ ተብሏል። ሁላችንም ለፍርድ ስንቀርብ እንጠየቅበታን ።
በክፍል ሁለት የ ሁለት ሺ ዘመኑን የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ፈተና እናያን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *