የትዮጵያን ሰራዊት ከመበተን ለማዳን የተደረገ አስቸኳይ ጥሪ
ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰራዊት ከሰላም ፈላጊና ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለመቀጠል ከሚደክሙ
⦁ የኢትዮጵያ ጦር ሊረዳ የሚገባው አንድ ነገር ካለ ኢትዮጵያ የለችም ማለት የኢትዮጵያ ጦር የሚባል ነገርም የለም ማለት ነው።
⦁ ስለዚህ ሰራዊቱ ማንንም ሳይጠብቅ በግሉ ኢትዮጵያን የማዳን ትግሉ ውስጥ መግባት አለበት። የሚታገለውም እኛን ለማዳን ሳይሆን እራሱና ልጆቹ ለማኝ ከመሆን ለማዳን መሆኑን መረዳት
⦁ በወገንህ ላይ ተኩስ ሲሉት ጠመንጃውን ወደ ወገንህን አጥፋ ብለው በሚያሳስቱት አዛዦቹ ላይ ማዞር አለበት።
⦁ በህዝብ ላይ ጥቃት ፈጽሙ ሲባል መረጃውን ማውጣት፣ አዛዦቹን እያሰረ የራስን አመራር መፍጠር አለበት።
⦁ ኦነግ ሸኔና የሽመልስ አብዲሳን እና የአብይን የኦፒዲኦ/ብልጽግና ዘረኛና አገር አፍራሽ ታጣቂን እየተፋለመ ለፍርድ ማቅረብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊቱ ኃላፊነት መሆኑን ማወቅ አለበት።
⦁ መከላከያው በአገር ሥም ተደራጅቶ ሳለ ለጎጣቸው ቅድሚያ በመስጠት በሕዝባቸው ላይ ጥቃት የሚያስተባብሩ ጄኔራሎችን ትዕዛዝ መቃወም ግዴታው መሆኑን ማወቅ አለበት።
⦁ አብይ አህመድ ከሁሉ በላይ የተደራጀው ሠራዊት በወገኔ ላይ አልተኩስም ካለ፤ ሕዝብ ለክፉ የኦህዴድ/ብልጽግና አልታዘዝም ማለት ከጀመረ መንግሥት ይፈርሳል ብሎ በመሥገቱ ከባድ መሳሪያን ወደ ወለጋ በማሸሽ ላይ ነው። ሕዝቡና መከላከያው ይሄንን ማስቆም አለበት። ካልተቻለም ትጥቅን ይዞ በያሉበት በመፋለም ዜጎችን ከእልቂት፣ አገርን ከመፍረስ ማዳን ግዴታው ነው።
በአገራችን በተግባር የታዘብናቸው እውነታዎች
በቀድሞ የኢትዮጵያ ወታደር ማለት በቁመናው ቀጥ ያለ፣ ሙሉ የአካል ብቃት ያለው፣ በትምህርት ቤት አንደኛ የወጣና ተወዳድሮ ተመርጦ ወታደር የሆነ ማለት ነበር። በማሰብ ችሎታቸውና በአካዳሚ እውቀታቸው ከፍ ያሉ ወጣቶች ነበሩ ካዴት፣ አየር ሀይል፣ ባህር ሀይል ይገቡ የነበሩት።
እነዚህ ወታደሮች ለሀገር መኩሪያ ነበሩ። ለኛም ኩራት ነበሩ። የሚያሳዝነው እነዚህ ማሰብ ይገባቸው የነበሩ መኮንኖች በመንግስት ካድሬዎች ተተብትበው በራሳቸው እንዳያስቡ ተደርገው ለሽንፈት፣ ለስደት፣ ለአጠቃላይ ውርደት ተጋለጡ። እነዚህ መኮንኖች ተባረው ቆሽሸው ገርጥተው ከሰው እጅ ጠባቂ ሲሆኑ በዓይናችን አይተናል’ በአባቶቻቸው ይኮሩ የነበሩ ወጣቶች ልመናና ሸክም ስራ ሲሰሩም አይተን ልባችን ደምቷል። በኤርትራ በረሀ ለ30 ዓመት፣ በኦጋዴን፣ በሱዳን ድንበር መከራ ሲቀበሉ ኖረውና የእኛን ሕልውና አስቀጥለው እነርሱ ተጣሉ።
በዚያን ጊዜ በደርግ ላይ በነበረው ምሬት የራስን ነፃነት በሌላ እጅ የማስጠበቅ የባርነት ስነ ልቦና ነውና “የባሰ አይመጣም” በሚል እነሱ ተሸወዱ፣ የአሁኑ ጦር ግን ከተሸወደ ማንም አያዝንለትም። ለዚህ ነው ራሱንም ቤተሰቡን ከለማኝነት ለማዳን መታገል ያለበት። ለዚህ ነው አባቶቹ በደምና በአጥንት ጠብቀው ያስረከቡተን አገር ከተደራጁና የአገሪቷን የፖለቲካ ሥልጣን ተቆጣጥረው በሕዝብ ፍጅት፣ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በዘረኝነት፣ በሀብት ዘረፋ የታወሩ የመንግሥት ካድሬዎችን መስማትና የጥፋቸው መሣሪያ መሆን የሌለበት።
አእምሮ ያለው የሠራዊት አባል ይህን አይስተዉም ብለን እናምናለን። ይህን ከሳተና ለዚህ መንግሥት በጭፍን እየታዘዘ በወገኑ ላይ መተኮሱን ከቀጠለ ከቀድሞው ሠራዊት የከፋ ውድቀት ያጋጥመዋል። የሚያዝነለት አይኖርም። ለምኖ መጽዋት አያገኝም። እንደ ናዚ ወታደር በዘር ፍጅት ይከሰሳል፣ ዜጎች ይጸየፉታል። ራሱን ከዚህ የሚያድነው ውትድራነ አገርን ለመጠበቅ እንጂ በሕገ መንግሥት ስም የወሮበሎችን መንግሥት ለመከላከልና ለማጽደቅ ዜጎችን መፍጀት ሊሆን አይችልምና ቆም ብሎ ያስብ እንላለን።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ውለታና ውርደት
የኢትዮጵያ ሰራዊት ላለፉት 88 አመታት ሀገሩን ያገለገለና በሚሊዮን የሚቆጠር ህይወት የገበረ ቢሆንም ውለታው በየግዜው እየተረሳ በብሄር በተደራጀው ወያኔ በተነው። ዛሬም በድጋሜ ህወሀትና በኦፒዲዮ ተስማምተው ሊበትኑት ዝግጅቱ ተጠናቋል ግልጽ መረጃዎች አሉ። ከባድ መሳሪያው ወደ ወለጋ እየተጓዘ ነው። ትንሽ ቆይቶ መሳሪያህን ጥለህ ውጣ ይከተላል። ይህ ሁሉ ከባድ መሳሪያ ለምን ወደ ወለጋ ይወሰዳል ብሎ የሚጠይቅ መኮንን እንዴት ይጠፋል።
ባለፈውና ባሁኑ ያለው ልዩነት
“እያባበልክ ወስደህ ወደ ገደል ገፍትረው” ዶ/ር አብይ አህመድ በእርካብና መንበር መጽሀፍ ላይ አስቀድሞ የተነገረ የሠየራ አሠራርን የተከተለ ነው።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ህወሀትን በመጨረሻ የተዋጋው በጎንደርና በወሎ ክፍለሀገር ነበር። ከጎንደር ቦኃላ ጎጃምን ወያኔ በሶምሶማ ነው የተሻገረው። ወለጋን ደሞ አንድ ጥይት ሳይተኮስበት በጭነት መኪናው ላይ ተንጠላጥለው፣ ተደራርበው፣ ችቦ መስሎ ነው አዲስ አበባ የገባው።
በእርግጥ አንቦ ላይ ሰራዊት ሳይሆን የተቆጣ ህዝብ ወያኔን እስከነ ኮተቱ ከከተማ አባሮት ነበር። ይህ የወያኔን አቅም ደካማነት እንጂ የህዝቡን ወታደራዊ አቅም አያሳይም። ይህ ክስተት ግን አንድ “የይሆናል” ግምት እንድናነሳ ያስገድዳል።
ይህም የኢትዮጵያ ሰራዊት በሀምሳ አለቃና በመቶ አለቃ ተደራጅቶ ወያኔን በየቦታው ቢገጥሙት ኖሮ ወያኔ ይዞት የመጣውን 60 ሺ ጦር ይዞ ማምለጫም እንኳ አያገኝም ነበር። ነገር ግን ሁሉም ባበሪያ ስነ ልቦና እንዲሁም ወገን በወገን አንደዚህ አይጨክንም በሚል ግምት አገሩን በዘር ከፋፍሎ አሁን ለምንገኝበት አጠቃላይ መተላለቅና የአገር ውድመት ለሚያጋልጥ ተከታታይ ሥርዓት አጋልጧት ይገኛል። አሁንም አሁን ያለው መከላከያ ሠራዊት ይህን ስህተት ከመድገም መቆጠብ አለበት።
ያኔ የተከሰተው ሽንፈት ወታደራዊ ሳይሆን የስነልቦና ሽንፈት ስለነበረ። ይህንን ያሰበ ወታደራዊ መኮንንም የአስር አለቃም አልነበረም። ለ17 አመት የመንግስት ካድሬዎች ይነግሩት የነበረው መታዘ እንጂ ማሰብ የሱ የስራ ምድብ እንዳልሆነ ነበር። ጓድ ሊቀመንበር መንግስቱ ሁሉን ያውቃሉ እኛ ደግሞ ለምን ስንል የአንዮታዊ መሪያችንን ትእዛዝ መፈጸም ነበር የስራ ምድባቸው።
አንባገነኖች ማሰብን ይፈራሉ ምክንያቱም ማሰብ ጥያቄ ይጭራል ጥያቄ ደግሞ ውስጥ ተቀብሮ አይቀመጥም። በሆነ መንገድ ይገለጻል። ያ ደግሞ በካድሬዎች ጥርጣሬ ውስጥ ይጥላል። ስለዚህ “ከነገሩ ጦም ይደሩ” ሆነና ወታደሩ ለሀገሩ ቀርቶ ለራሱ፣ ለልጁ እና ለሚስቱ ማሰቡን ለኮ/መንግስቱ እርግፍ አድርጎ እንዲተው ተደረገ።
አሁንም ይህ አዚም ተመልሶ መጥቶ ስናይ ይህ የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለማሰብ፣ ባለ መጠየቅ፣ ባለመናገር በድጋሚ ሊፈረስና ለማኝ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ገብተናል። የሚፈርሰው ደግሞ የራሱን ሕዝብ ወግቶና የካድሬዎች መጠቀሚያ ሆኖ፣ ተጠልቶና ጽዬፍ ሆኖ መሆኑ እጅግ ሰዝናል።
ትናንት ተዘጋጅተህ ትጠብቅ በነበረው ድንበር ላይ አጥብቀህ ራስህን ጠብቅ ከማለት ይልቅ፣ አንበጣ አባር፣ አጨዳ ዋል እየተባለ ከወታደራዊ ተግባር እንዲገለልና እና ደክሞት እንዲተኛ ተደርጎ ሰራዊቱ በተኛበት ታረደ። ወታደር ሲያስብ የታዘዘውን ብቻ መፈጸም ብቻ ሳይሆን የሚመጣውንም ይገምታል ይዘጋጃል።
ስለዚህ በተኛበት ታረደ። እንቅልፍ ያልወሰደው ፈጽሞ የተነሳው፣ ትጥቁን መጋዘን ያላስገባው እየተታኮሰ ኤርትራ ገብቶ ህይወቱን አዳነ። ያልቻለው 11ሺ ወታደር ተማርኮ ጫማውን አውልቆ እንደ ጠላት ጦር በሰልፍ እየተደረገ ቪዲዬ ተቀዳ። በአስፋልት ላይ ተሰልፎ በከባድ መኪና ተዳመጠ፣ ሴት ወታደሮች ማሕጸን ውስጥ ሳንጃ ተሸቀሸቀ፣ ወንድ ተደፈረ። ይህ ሁሉ ራስወዳድ ካድሬዎችን ከአገር አስበልጦ በባርነት የመኖር ስነልቡና ነው።
ህወሓት ተደራድሮ የተማረኩበትንና የታሰሩትን ወታደሮቹን አስፈታ የኢትዮጵያ መንግስት ግን የተማረኩበትን ወዴት አደረሳችሁ ብሎ አልጠየቀም። የተረሸኑ 3500 ወታደሪቹን የጅምላ መቃብር እንኳን ክፍቶ ማሳጣት አይፈልግም። ለዚህ ወታደሮቹን አንደ ውዳቂ እቃ የሚጠቀምና የሚጥል መንግሥት ዘላለም ከሚኖረው የአገር ትውልድ ጋር ተጣልቶና አገር አጥፍቶ መጥፋት አንደማይገባ ማሰብ መጀመር አለብህ።
ለብሄረተኞች የኢትዮጵያ ጦር ዋጋ ከገለባም የቀለለ ነውና።
ያለ ማሰብ መዘዙ
የወታደር ዋነኛው ትምህርት አርቆ ማሰብና በዚህ ብሄድ በዛ ቢመጣብኝ እንዴት ይህቺን ቦታ አስለቅቃለሁ ያንን ነጥብ እቆጣጠራለሁ ነበር።
ይሁን እንጂ በኮለኔል መንግስቱ ግዜ የነበረው ጦር ኮለኔሉ ቢሞቱ፣ ቢሰደዱ፣ ቢታሰሩ ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር። ባለሥልጣንን ማክበርና መታዘዝ የወታደር መገለጫው ቢሆንም፣ ከአጠቃላይ አገራዊ ሕልውና ሕዝብ ደኅነነት ጋር የተጋጨ ትዕዛዝን መቃወም መማርና መሠልጠን ሳይሆን ሰው መሆን ብቻ ይበቃል። እንኳንስ አገሩና ሕዝቡን ሊጠብቅ ቃል ገብቶና ነፍሱን ለሕዝቡ ሰጥቶ ወታደር የሆነ ሰው ቀርቶ እንስሳት እንኳ በሕልውናቸውና በሞሪያቸው አይደራደሩም።
ስለዚህ ኮለኔል መንግስቱ አይሮፕላን ተሳፍረው ሄዱ የተባለ እለት እናቱ እንደጠፋችበት ህጻን ግራ ገብቶት ተንገላወደ። ይህ ነገር ሊመጣ ይችል? ኮለኔሉ ሊሞቱ፣ ሊሸሹ፣ በቃኝ ሊሉ ይችሉ ይሆን የሚል ጥያቄ በሰራዊቱ ጭንቅላት ውስጥ እንዳይገባ በደንብ ተሰርቶ ነበር።
ሰራዊቱ ይህንን አስቦ ቢሆን ኖሮ መፍትሄው ይታየው ነበር። ሀሳቡን በመንግስቱ ሀይለማርያም ካድሬዎች ላይ በመጣሉ እነሱም ግራ ገብቷቸው ተሰልፈው፣ ወረፋ ጠብቀው መሳሪያቸውን ሲያስረክቡ ሰራዊቱም ተከተሎ እንዲሁ አደረገ።
ዘራፍ ቀበቶዬን አልፈታም ያለ ጠፋ።
የሚያሳዝነው ደግሞ አብዛኛው ህይወቱን፣ ልጆቹንና ሀገሩን እንዲጠብቅበት የተሰጠውን መሳሪያ ሸጦ ልብሱን ቀይሮ ተበተነ።
ህወሓት አዲስ አበባ ሲገባ 65% የሚሆነው ኢትዮጵያ ምድር ነጻ ነበር። ከአዲስ አበባ ተነስቶ እስከ ጋምቤላ፣ ሞያሌ፣ ኢሊባቡር፣ቶጎጫሌ፣ ጅቡቲባ ኦጋዴን ጠረፍ ድረስ ነጻ ምድር ነበር።
ይሁንና ሰራዊቱ ጠመንጃውን እንደያዘ ቢበተን እንኳን ህወሓት አሯሩጦ ለመያዝ የሚበቃ ቁጥር አልነበረውም። ግን ሰራዊቱ በስነ ልቦና ጨዋታ ተሽወደ።
የተማረኩ መኮንኖች “የአብዮታዊ መኮንኖች” በሬዲዮ የሚባል ተሰጥቷቸው ሲለፈልፉ ሰራዊቱ መሳሪያዬን ባስረክብ ተሐድሶ ገብቼ ስወጣ ስራዬ እመለሳለሁ ብሎ እንዲያስብ ተገደደ። ይህ ግን ዶ ር አብይ እንደጻፈው “እያባበልክ ገደል ወስደህ ገፍትረው” የሚለውን ስልት የተከተለ ነው ተንኮሉ።
ሰራዊቱ ያኔም አሁንም ያልገባው ሚስጥር የብሄር ፓለቲካና የሀገር መከላከያ ውሀና ዘይት መሆናቸውን ነው።
ሰራዊቱ ስለ ብሄር ፓለቲካ ገብቶት ቢሆን ኖሮ አይታለልም ነበር። የብሄር ፓለቲካና የሀገር መከላከያ ውሀና ዘይት ናቸው። አይቀላቀሉም አይስማሙም።
የብሄር ፓለቲካና የሀገር መከላከያ ሰራዊትና አላማቸውም ግባቸውም የተለያየ ነው። አንደኛው ለሰው ልጅ ደኅንነት፣ ለአገር ሕልውናና ሰላም የሚቆም ነው። የብሔር ፖለቲካ ሰውን አዋርዶ በቡድን መብት ሥር ተደብቆ እንደ ናዚ የዘር ማጥፋትና በታላቅ አገር ውስጥ በዜጎች እልቂትና ደም ላይ የሚመሠረቱ ትናንሽ ገራትን ለመፍጠር የሚያልም የትንንሽ አእምሮዎች ውጤት ነው።
ቀላሉ ጥያቄ ኢትዮጵያ ከሌለች እንዴት የኢትዮጵያ ጦር ይኖራል? ሀገር ለመካፈል የተቋቋመ የብሄር ድርጅቶች የሀገር መከላከያን ይፈልገዋል? አይፈልገውም። በቅርቡ በየሰፈሩ በመሠረታቸውና በዘረኝነትና በጥላቻ በሠለጠኑ ልዩ ኃይሎች ይተካል። ይንን የኦሮሚያ ምንገሥትና ብልጽግና እየፈጸሙት ነው።
የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚኖረው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ስትኖር ብቻ ነው። ይህቺን ሀገር ለማፍረስ መጀመሪያ የኢትዮጵያን ሰራዊት ማፍረስ ግድ ይላል። ማፍረስ ብቻ በቂ አይደለም። በውትድርና የሠለጠነ ሰው እንዳይኖር በተለያዩ መንገዶች ማስወገድም ይከተላል። አሁን ሕዝቡ ላይ ከተኮሳችሁና አገራችሁን ካፈረሳችሁ በኃላ ላይ የቆሰለው ሕዝብ ልጆቻችን፣ ጠባቂዎቻችን መከታዎቻችን ማለቱን ይተወዋል። ከካድሬ ጋር ሆኖ አብሮ ያጠፋችኋል። አይደብቃችሁም። አይራራላችሁም።
የህወሀትና ኦፒዲኦ ፍቅር
ሰራዊቱን ያረደው ህወሀት እና ሊያርድ የተዘጋጀው ኦፒዲኦ ግንባር ፈጥረዋል። ሁለቱም በዘረኝነት ያበዱ ናቸው። ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ተቋማትን በተሌ ሠራዊቱን እንዴት እንደሚጠቀሙበትና ጊዜው ሲደርስ አንደሚያጠፉት የሚያልሙ ባልንጀራዎች ናቸው። ሕወሐት ይህን ሠራዊቱን ከጀርባ ወግቶና አዋርዶ አሳይቷል። ኦፒዲኦ/ብልጽግናም ዝግጅቱን ጨርሷል። ሠራዊቱን የሚፈልገው የአማራንና ሌሎች ኢትዮጵያውያኖችን አቅም ለማዳከም ብቻ ነው። ኦፒዲኦ አባቶቻቸው ለታረዱባቸው የኢትዮጵያ ሰራዊት ልጆች የትምህርት ቤት ዩኒፎርም ሳይገዛ፣ አባቶቻቸውን ላረዱት ለእነ ጄ/ል ታደሰ ወረደንና ጌታቸው ረዳ አብይ አህመድ ሰንጋ አርዶ፣ ውስኪ በሄሌኮፕተር ጭኖ እየጋበዘና እያግባባ ነው።ኒሻቢያ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ 3500 የታረዱና የተረሸኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች በትግራይ እንዳገኘ መስክሯል። በየቦታው ተረሽኖ የተቀበረው ቤት ይቁጠረው። አብይና ሽመልስ 3500 ሰው በተኛበት የታረደባቸው ሳይሆን የፍየል ግልገላቸውን ቀበሮ የበላበት አይመስልም። ለምን ካልክ የኢትዮጵያ ሰራዊት ሲቸግረው ተጠቅሞ የሚጥለው ጠላቱ ነው።
የኢትዮጵያ ሰራዊት አራጆች ጋር ገበታ ቀርቦ ቁርጥ በሉ፣ ውስኪ ጠጡ። ቁርጡ የበሉበት በበሬው ሀሞት ሳይሆን በታረዱ ወታደሮች ደም እንደሆነ አልተሰማቸውም።
ለምን ካልን የሀገር መከላከያ ለህወሀትም ለኦፒዲኦም ጠላቱ ነውና። የሁለቱም ምኞት እንቅፋት የኢትዮጵያ ሰራዊት ነውና። ሠራዊቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያሰጋቸዋል። ሊፈጥሯቸው ለፈለጓቸው የተከፋፈለች አገር እንቅፋት አንደሚሆን ያውቃሉ። ለዚህ ነው ስለ አገርና ስለ ዙጎች ክብር ሳይሆን ስለ ሕገ ምንግሥተትብቻ ደጋግመው የሚናገሩት። ስለ ዜጋ ክብርና ደኅንነት፣ ስለ አገር ሉዓላዊነት አይተነፍሱም። መዝሙራቸው ብሔር፣ ቋንቋ፣ ቡድን፣ የጥላቻ ትርክትና ዌኔና ኦነግ ያዘጋጁት ዘረኛ ሕገ መንግሥት ብቻ የሚሆነው።
እነ ታደሰ ወርደ ሰፈራችን በሻቢያ ተወረረ፣ ባድሜ ተያዘ ያሉ ቀን እሪ ብለው 70 ሺ ሰራዊት ማገዱ። ከዛ ሰላም ነው ብሎ በተኛበት ያለ ርህራሄ 3500 አረዱት። ይሄንን የሻቢያ ወታደር ቀድሞ ሲገባ የቆጠረው የታረደ ብቻ ነው።
አብይም ስልጣኑ አደጋ ላይ ሲወድቅ ደግሞ በጋሸና ምሽግ ማገደው። ሰራዊቱ ወደ ድል ሲቀረብ ደግሞ አስቁሞ ትግራይን ለቀህ ውጣ አለው።
ለአብይም ለታደሰ ወረደ የኢትዮጵያ ጦር የሚማግዱት እንጂ እንደ ሰው የሚቆጥሩት የሚያከብሩት አይደለም።
ሰራዊቱ እንደ የሽንት ቤት ወረቀት የሚጠቀሙበትና የሚጥሉት ነው። ይህ ደግሞ ሲታረቁ እንኳን የሰራዊቱ ስሜት ይጎዳ ይሆን ብለው አይጠየቁም ወይንም አላወያዩም። ሰራዊቱ ለነሱ ግኡዝ እቃ ነው።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ሆይ
በመንግስቱ ግዜ ሰራዊቱ በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተሸወደ። አሁንስ?
የኦፒዲኦና የኦነግ ሸኔ አመራር ሀገር ሲገነጥሉ የኢትዮጵያውያን ሰራዊት ደሞዝ እየከፈለ ካምፕ አስቀምጦ የሚቀልቡ ይመስላችሀል?
የአየር ሀይሉ በላያቸው ላይ ጀትና ድሮንስ እንዲያበር የሚፈቅድ ይመስላችሀል?
ታንክና መድፍ አጠገብ እንዲደርስ ይፈቅድለታል?
እነ ሽመልስና የኢትዮጵያ ጦር ክላሽ ቀርቶ ዱላ እንዲይዝ አይፈቅዱለትም።
የመጀመሪያ ተግባራቸው ክላሹን፣ ታንኩን አስፈትተው ቀበቶውንና ጫማውን አስወልቀው የሽንኩርት ቢላዋ እንኳን እንዳይዝ ነው የሚያደርጉት።
እኛም የብሄር ነጻ አውጪ ብንሆን የኢትዮጵያ ጦር ሴንጢ እንድትየዙ አልፈቅድም። ሽመልስ ይህ ይጠፋዋል? ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ውስጥ እንዴት ኢትዮጵያ ስሜት ያላቸው እስላሞችንና ኦርቶዶክሶችን አጽድቶ እንዳስፈጀ እናውቃለን። በኦሮሚያ የፖሊስ ሥርዓት ውስጥ አንድም ኢትጵያዎ እስላምና ኢትጵያዊ ኦርቶዶክስ እንዳይኖር አድርጎ አጽድቶታል።
ህወሀትም የዛሬ ሁለት አመት ከአምስት ወር በፊት ሰራዊቱን በተኛበት ያረደው የብሄር ፓለቲካና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአንድ ሀገር መኖር ስለማይችሉ ነው። ብሄርና የሀገር መከላከያ ዘይትና ውሀ በመሆናቸው በተግባር ታይቷል።
ታድያ ለምን ያሰለጠኑትን፣ያሳደጉትን፣ የነሱን ድንበር ሲጠብቅ፣ የነሱን ሰብል ሲያጭድ የቆየውን ሰራዊት እነ ጻድቃንና ታደሰ ወረደ አረዱት?
መልሱ ቀላል ነው። የሀገር መከላከያና የብሄር ፓለቲከኞች ጠላት እንጂ አንድ ሆነው አያውቁም። ሊሆኑም አይችሉም። ለጊዜው ግን መጠቀሚያ ናቸው።
ይህ አሁን በኦፒዲኦም እየተደገመ ነው። በአፍ እየደለሉ፣ ልክ እንደ ህወሓት የኦሮሞን ልዩ ሀይል ሜካናይዝና ኮማንዶ እያሰለጠኑ ያሉት የኢትዮጵያን ጦር ለማገዝ ሳይሆን ለመተካት ነው።
ስለዚህ ይህ አልገባ ያለው ለኦፒዲኦ ታዛዥ ሆኖ መቀጠል የሚፈልግ ልጆቹንና መአረጉን አንጥፎ መለመን ምርጫው ነው።
ለራሱ ሞያ፣ለሀገሩ ኩራት፣ለሚስቱና ለልጁ ክብር ያለው ግን ልጆቹ ለማኝ ሆነው ከሚኖሩ ሞቱ ክብሩ ነው። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ጦር ለሀገሩም ለኛም አይደለም መነሳት ያለበት ለራሱ ክብርና ለልጆቹ ብሎ ነው። ልጆቹ በቤተ ክርስቲያንና በመስጊድ ለማኝ ሆኖ ከማየት እስከነ ክብሩ የሞተ ለልጆቹ መኩሪያ ይሆናል።
መፍትሄው
ወታደር ማለት የማያስብ እንጂ ጃስ ሲሉት የሚጮህ ውሻ አይደለም። የሀገር መከላከያ ማሰብ የሚችል፣ ለራሱ፣ ለልጁ፣ ለሀገሩ፣ ለክብሩ የሚሞት ማሰብያ የተገጠመለት የእግዚአብሔር ፍጡር ነው። በፓለቲካ አይገባም ማለት ማሰብያ ጭንቅላት የለውም፣ ውሀና እሳትን አይለይም ማለት አይደለም። የሚያስብ የሚወስን ጥቅሙንና የሀገርን ክብር በጽኑ የተረዳ ማለት ነው።
ስለዚህ
፩: በወገንህ ላይ ተኩስ ሲሉት ጠመንጃውን ወደ አዛዦቹ አዙር
፪: ጥቃት ፈጽም ስትባል መረጃውን ማውጣት፣ አዛዦቹን እያሰርክ የራስን አመራር መፍጠር።
፫: ኦነግ ሸኔና የሽመልስ ታጣቂን እየተፋለመምክ ለፍርድ በማቅረብ አገርና ሕዝብን ከማፍያ የኦፒዲ/ብልጽግናና ከሕወሐት ያልተቀደሰ ሕብረት እድን
፬: ከሁሉ በላይ ተደራጅቶ እንቢ ማለት። መንግስት ይፈርሳል ብሎ የሰጋው አብይ መሳሪያውን ወደ ወለጋ በማሸሽ ላይ ነውና ይሄንን ማስቆም። ካልተቻለም ትጥቅን ይዞ በያሉበት መፋለም መጀመር ይኖርብሀል። በዘገየህ መጠን ፈተናው ይከብዳል።