የካኪስቶክራሲ አገዛዝና የአማራ ህዝብ አርበኝነት
ሰውነት ይበቃል
በዚህ ክፍል የምናተኩርበት ነጥብ በአብይ አህመድ የሚነዳው የብልጽግና አገዛዝ ምን አይነት ባህርይ እንዳለውና የአብይ አህመድ የስልጣን ግንባታ ጉዞ ምን እንደሚመስል መቃኘት ነው። ይህንን ስርአት በተለይም ከአማራ ህዝብ አንጻር ምን ባህርይ እንዳለው ካላወቅን ለአማራም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የሚበቃ ውጤታማ ትግል ማካሄድ አይቻልም። በፅሁፉ ማሳረጊያ ላይ ለአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ አስፈላጊ የምንላቸውን ጥቂት ነጥቦች እናቀርባለን።
በሃገራችን የተጫነው አገዛዝ መንግስት ተብሎ የሚጠራ አይደለም። መንግስት ህዝብ የሚያስተዳድር ስራት ነው። አሁን ያለው አገዛዝ ግን ህዝብ የሚገድል፣ የሚያፈናቅልና፣ በጅምላ የሚያስር የማፊያ ባህርይ ያለው ስብስብ ነው። ምንም አይነት ህዝብን የማገልገል አላማ የለውም። ስለዚህ ከባህሪው አንጻር መንግስት ብለን ልንጠራው አንችልም። ይሁን እንጅ ሁለት ገጽታወች አሉት። አንደኛው ከአማራ ህዝብ አንጻር ያለው ገጽታ ሲሆን ሁለተኛው አማራን ጨምሮ ለሁሉም ህዝብ ያለው ገጽታ ነው። እነዚህን ሁለት የአገዛዙ የክፋትና የጭቆና ገጽታወች ሳያደበላልቁ ለይቶ መገንዘብ ለአማራ ህዝብ ትግል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የአብይ አህመድ አገዛዝ ከአማራ ህዝብ አንጻርና ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር ሲታይ አንድ አይደለም። ወደዚህ ነጥብ በኋላ እንመለሳለን። በቅድሚያ ግን የስራቱ ብያኔ ላይ እናተኩር።
አማራን ጨምሮ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች የአብይ ስራት ካኪስቶክራሲ kakistocracy (a government by the worest and least qualifed persons) የሚባለው አይነት ነው። ካኪስቶክራቶች የዘቀጠ ሰብአዊነትና የደቀቀ እውቀት ይዘው ህዝቡን ከእነሱ ደረጃ በታች አውርደው ለመርገጥ የሚጣጣሩ ቅዠታሞች ናቸው። ካኪስቶክራቶች መርህ አይከተሉም፤ ብቃት የላቸውም፤ እጅግ ክፉወች ናቸው። አላማቸው ብቸኛ የስልጣን ባለቤት ሆነው ሁሉንም ጨቁነው መግዛት ብቻ አይደለም። የፍላጎታቸው ገደብ፣ የክፋታቸው ልክ፣ የተንኮል ስራቸውና አረመኔነታቸው ገደብ የለውም። የገዢነት ስሜት የሚሰማቸው ለምንም አይነት ህግ ተገዢ አለመሆንቸውን በተግባር በማሳየት ነው። ከሁሉም በላይ በመዋሸት፣ በመዝረፍ፣ በመግደል፣ አስነዋሪ ተግባራትን በመናገርና በመፈጸም፣ ጭካኔነታቸውን በማላመድ ወዘተ ከህግና ከስነምግባርና ገደቦች በላይ መሆናቸውን ማሳየት ይሞክራሉ። ከጥቅምና ፍላጎታቸው ውጭ የደራደሩበት መርህ ስለሌላቸው የሚቀርብላቸውን ጥያቄ
በሰላማዊ ውይይት ማስተናገድ አይችሉም። ማንኛውንም የፖለቲካ ድርድር እንደቁማር ነው የሚያዩት።
ካኪስቶክራቶች የፖለቲካው አለም ሰይጣናት ወይም አጋንንት ናቸው። ለማንም ታማኝ ሳይሆኑ ሁሉም እንዲያምናቸው ይፈልጋሉ። ማታለል ልዩ የፖለቲካ ጥበብ ይመስላቸዋል። በስልጣናቸው ከመጡባቸው ህይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ልጆቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውን፣ ወላጆቻቸውን፣ ሃገራቸውን ሁሉ ሳይቀር ቅርጥፍ አድርገው ሊበሉ ይችላሉ። የቆምንበትን መሬትና የምንተነፍሰውን አየር ሳይቀር የእነሱ ስጦታ ስለሆነ አመስግነን መሬቱን እንድንቆምበትና እጅ ነስተን አየሩን እንድንተነፍስ ይፈልጋሉ። ይህን መሬት የሰጠሁህ እኔ ነኝ፤ ይህን አየር እንድትተነፍስ የፈቀድሁልህ እኔ ነኝ እስከማለት ይደርሳሉ። ደስ ሲላቸው ደግሞ “የምተነፍሰውን አየር ተሻማኽኝ” ብለው ንጹህ ሰው ሊገሉ ይችላሉ። በእነሱ ምክንያት ሰው ሲገደል፣ ሲሰቃይ፣ መድረሻ ሲጠፋው፣ ሲጨንቀው፣ ሲርበው የድል አድራጊነት ስሜት ይሰማቸዋል። በገዢነታቸው የሚረጋጉት ሌሎች ሲሸበሩ ነው። የእነሱ ሰላም የሌሎች በሁከት መኖር ነው። ትልቅነት፣ አሸናፊነት፣ ሃያልነት የሚሰማቸው ሌሎች ሲሰቃዩና ሲማቅቁ ነው። ሰውን ሁሉ ስለሚንቁ ይሉኝታ የሚባል ነገር አያውቃቸውም። በእውቀት፣ በታሪክና በዝና የሚበልጣቸው እንዲኖር አይፈልጉም። አዋቂ መስለው በመቅረብ ሁሉንም ካላስተማርሁ ሞቼ እገኛለሁ ይላሉ። አዋቂ ለመምሰል መጽሃፍ ጻፍሁ ይላሉ፤ ዝናብ አዘነብሁ ይላሉ። የሃያልነት ስሜት የሚሰማቸው የተከበሩ ነገሮችን በማዋረድ፣ የማይደፈሩ ነውሮችን በመድፈርና ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ነው። የሚፈልጉት ሰው እንዲወዳቸው ሳይሆን ሰው እንዲፈራቸው ነው። የራሳቸውን የጥራዝ ነጠቅ ቅዠት እንደእውቀት ሁሉም ሰው እንዲማረው ያስገድዳሉ። የህዝቡን ሃብት ሁሉ በስልጣናቸው ስር አስገብተው በታማኝ ባንዳወች እየታገዙ የስራ፣ የምግብ፣ የህይወት፣ የመብት ሁሉ ሰጭ እና ቀሚ ለመሆን የሚያስችል የስልጣን ሀይል ይገነባሉ። የዚህ ስልጣን አላማ ህዝብን ማስተዳደር ሳይሆን ህዝብን መዝረፍ ነው፤ ህግና ስርዓት ማስከበር ሳይሆን ህገወጥነትንና ስርዓት አልበኝነትን የዝርፊያ መሳሪያ ማድረግ ነው።
አብይ አህመድ በካኪስቶክራሲ ጎዳና ላይ ነው። በህይወት የመኖር መብትን ሰጭ እና ቀሚ፣ በኢትዮጵያውያን ህይወት ላይ ብቸኛ ስልጣን ያለው ግለሰብ፣ አቻ የማይገኝለት ምሁር፣ በሁሉም አይነት ሞያ የተካነ ሊቅ፣ ሌላው ቀርቶ ዘናጭና ሳቂታ በመሆን ሳይቀር መሪ መሆን የሚፈልግ በየትኛውም ህግ የማይገዛ እቡይ ሰው ነው። ታዲያ እንዴት ብሎ አንድ ትናንት ማንም የማያውቀው ሰው ዛሬ የአንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ መሪና የአንድ ሃገር ሃብት ዘራፊ ሊሆን የሚያስችል የስልጣን ማማ ላይ ሊደርስ ቻለ? ይህንን ሁሉ የስልጣ መዋቅር፣ ታዛዢነትና “አንቱታ” አገኘ? አንዳንድ ሰወች አብይ በስልጣን ለመቀጠል የቻለበት ዋና ምክንያት ሆዳም ምሁራንና ባንዳወች በምያደርጉለት ድጋፍ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። በእርግጥ ለአብይ ሰብዕና ተስማሚ የሆነ ሰብዕና ያላቸው ጉዳይ አስፈጻሚ ሆዳም ምሁራን በዙሪያው አሉ። ሆኖም አንድ መንግስት የትኛውንም ያህል ሆዳምና ባንዳ ሰወች
ቢያሰባስብ ያለ በቂ የፖለቲካ ካፒታል አንድ ቀን እንኳን በስልጣን ላይ ማደር አይችልም። አብይ የሃገሪቱን ህዝቦች በመርገጥና ሃብቷን በመሸጥ የካኪስቶክራሲ ስርአቱን ለማስፋፋት የሚጠቀምበት ዋና ጉልበት የሚመነጨው እስከዛሬ በሃገሪቱ ላይ ከተጫነው የፖለቲካ ካፒታል ነው። የፖለቲካ ካፒታል ትርጉም ጠለቅ ያለ ትንታኔ ያስፈልገዋል። በአጭሩ የፖለቲካ ካፒታል የምንለው ባለፉት 30-50 አመታት ውስጥ ወደስልጣን ማስጠበቂያነት የተቀየረውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ነው። አሁን ባለው ትውልድ ላይ የተጫነውና በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ የእውቀት፣ የሀብትና የስልጣን ምንጭ ሆኖ የሚያገለግለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ፀረ-አማራነት ነው። አብይ የካኪክስቶክራሲ ስርዓትን በቀላሉ ለመገንባት የሚችለውም ይህንን በአማራ ጥላቻ ላይ እስካሁን የተፈጠረውን የፖለቲካ አስተሳሰብ እንደ ካፒታል በመጠቀም ነው። ይህንን ካፒታል ለመጠቀም ከሚከተለው ስትራቴጂ አንዱ የአማራን ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ዝቅ ያለና መብት አልባ እንዲሆን በማድረግ ነው።……….ይቀጥላል
itaque aut quos eos ipsam sequi laboriosam quo quidem vitae tempora earum est. molestiae voluptatem sint est rem ad ut sit explicabo ut facilis eaque. nobis harum et aut dolorem non. autem ea quo sit sit magni id voluptas optio recusandae aperiam nisi est possimus sit ut eaque optio. voluptatem inventore qui odit cumque et ut sit nobis nisi ad expedita quos.